🔥 0 day streak
📖 Long surah — split into smaller parts to help you focus (118 አንቀጽ)
📚 All Surahs
30%
🎤 Tap the microphone icon 🎙️ next to any verse to record yourself reciting it, then listen back and compare with the reciter.
0/118
23:1 🔁 0/5
قَدۡ أَفۡلَحَ ٱلۡمُؤۡمِنُونَ  ۝١
Qad aflahal mu`minoon
ምእምናን ፍላጎታቸውን ሁሉ በእርግጥ አገኙ (ዳኑ)፡፡
🎤 Your recording:
23:2 🔁 0/5
ٱلَّذِينَ هُمۡ فِي صَلَاتِهِمۡ خَٰشِعُونَ  ۝٢
Allazeena hum fee Salaatihim khaashi`oon
እነዚያ እነርሱ በስግደታቸው ውስጥ (አላህን) ፈሪዎች፡፡
🎤 Your recording:
23:3 🔁 0/5
وَٱلَّذِينَ هُمۡ عَنِ ٱللَّغۡوِ مُعۡرِضُونَ  ۝٣
Wallazeena hum `anillaghwimu`ridoon
እነዚያም እነርሱ ከውድቅ ንግግር ራቂዎች፡፡
🎤 Your recording:
23:4 🔁 0/5
وَٱلَّذِينَ هُمۡ لِلزَّكَوٰةِ فَٰعِلُونَ  ۝٤
Wallazeena hum liz Zakaati faa`iloon
እነዚያም እነርሱ ዘካን ሰጭዎች፡፡
🎤 Your recording:
23:5 🔁 0/5
وَٱلَّذِينَ هُمۡ لِفُرُوجِهِمۡ حَٰفِظُونَ  ۝٥
Wallazeena hum lifuroo jihim haafizoon
እነዚያም እነርሱ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች የሆኑት (አገኙ)፡፡
🎤 Your recording:
23:6 🔁 0/5
إِلَّا عَلَىٰٓ أَزۡوَٰجِهِمۡ أَوۡ مَا مَلَكَتۡ أَيۡمَٰنُهُمۡ فَإِنَّهُمۡ غَيۡرُ مَلُومِينَ  ۝٦
Illaa `alaaa azwaajihim aw maa malakat aimaanuhum fa innahum ghairu maloomeen
በሚስቶቻቸው ወይም እጆቻቸው በያዟቸው (ባሪያዎች) ላይ ሲቀር፡፡ እነርሱ (በነዚህ) የማይወቀሱ ናቸውና፡፡
🎤 Your recording:
23:7 🔁 0/5
فَمَنِ ٱبۡتَغَىٰ وَرَآءَ ذَٰلِكَ فَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡعَادُونَ  ۝٧
Famanib taghaa waraaa`a zaalika fa ulaaa`ika humul `aadoon
ከዚህም ወዲያ የፈለጉ ሰዎች እነዚያ እነርሱ ወሰን አላፊዎች ናቸው፡፡
🎤 Your recording:
23:8 🔁 0/5
وَٱلَّذِينَ هُمۡ لِأَمَٰنَٰتِهِمۡ وَعَهۡدِهِمۡ رَٰعُونَ  ۝٨
Wallazeena hum li amaanaatihim wa `ahdihim raa`oon
እነዚያም እነርሱ ለአደራዎቻቸውና ለቃል ኪዳናቸው ጠባቂዎች፡፡
🎤 Your recording:
23:9 🔁 0/5
وَٱلَّذِينَ هُمۡ عَلَىٰ صَلَوَٰتِهِمۡ يُحَافِظُونَ  ۝٩
Wallazeena hum `alaa Salawaatihim yuhaafizoon
እነዚያም እነሱ በስግደቶቻቸው ላይ የሚጠባበቁ የኸኑት (አገኙ)፡፡
🎤 Your recording:
23:10 🔁 0/5
أُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡوَٰرِثُونَ  ۝١٠
Ulaaa`ika humul waarisoon
እነዚያ ወራሾቹ እነርሱ ናቸው፡፡
🎤 Your recording:
23:11 🔁 0/5
ٱلَّذِينَ يَرِثُونَ ٱلۡفِرۡدَوۡسَ هُمۡ فِيهَا خَٰلِدُونَ  ۝١١
Allazeena yarisoonal Firdawsa hum feehaa khaalidoon
እነዚያ ፊርደውስን (ላዕላይ ገነትን)፤ የሚወርሱ ናቸው፡፡ እነርሱ በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡
🎤 Your recording:
23:12 🔁 0/5
وَلَقَدۡ خَلَقۡنَا ٱلۡإِنسَٰنَ مِن سُلَٰلَةٍ مِّن طِينٍ  ۝١٢
Wa laqad khalaqnal insaana min sulaalatim minteen
በእርግጥም ሰውን ከነጠረ ጭቃ ፈጠርነው፡፡
🎤 Your recording:
23:13 🔁 0/5
ثُمَّ جَعَلۡنَٰهُ نُطۡفَةً فِي قَرَارٍ مَّكِينٍ  ۝١٣
Summa ja`alnaahu nutfatan fee qaraarim makeen
ከዚያም በተጠበቀ መርጊያ ውስጥ የፍትወት ጠብታ አደረግነው፡፡
🎤 Your recording:
23:14 🔁 0/5
ثُمَّ خَلَقۡنَا ٱلنُّطۡفَةَ عَلَقَةً فَخَلَقۡنَا ٱلۡعَلَقَةَ مُضۡغَةً فَخَلَقۡنَا ٱلۡمُضۡغَةَ عِظَٰمًا فَكَسَوۡنَا ٱلۡعِظَٰمَ لَحۡمًا ثُمَّ أَنشَأۡنَٰهُ خَلۡقًا ءَاخَرَۚ فَتَبَارَكَ ٱللَّهُ أَحۡسَنُ ٱلۡخَٰلِقِينَ  ۝١٤
Summa khalaqnan nutfata `alaqatan fakhalaqnal `alaqata mudghatan fakhalaq nal mudghata `izaaman fakasawnal `izaama lahman summa anshaanaahu khalqan aakhar; fatabaarakal laahu ahsanul khaaliqeen
ከዚያም ጠብታዋን (በአርባ ቀን) የረጋ ደም አድርገን ፈጠርን፡፡ የረጋውንም ደም ቁራጭ ሥጋ አድርገን ፈጠርን፡፡ ቁራጯንም ሥጋ አጥንቶች አድርገን ፈጠርን፡፡ አጥንቶቹንም ሥጋን አለበስናቸው፡፡ ከዚያም (ነፍስን በመዝራት) ሌላ ፍጥረትን አድርገን አስገኘነው፡፡ ከሰዓሊዎችም ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ላቀ፡፡
🎤 Your recording:
23:15 🔁 0/5
ثُمَّ إِنَّكُم بَعۡدَ ذَٰلِكَ لَمَيِّتُونَ  ۝١٥
Summa innakum ba`da zaalika la maaiyitoon
ከዚያም እናንተ ከዚህ በኋላ በእርግጥ ሟቾች ናችሁ፡፡
🎤 Your recording:
23:16 🔁 0/5
ثُمَّ إِنَّكُمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ تُبۡعَثُونَ  ۝١٦
Summa innakum Yawmal Qiyaamati tub`asoon
ከዚያም እናንተ በትንሣኤ ቀን ትቀሰቀሳላችሁ፡፡
🎤 Your recording:
23:17 🔁 0/5
وَلَقَدۡ خَلَقۡنَا فَوۡقَكُمۡ سَبۡعَ طَرَآئِقَ وَمَا كُنَّا عَنِ ٱلۡخَلۡقِ غَٰفِلِينَ  ۝١٧
Wa laqad khalaqnaa fawqakum sab`a taraaa`iqa wa maa kunnaa `anil khalqi ghaafileen
በእርግጥም ከበላያችሁ ሰባትን ሰማያት ፈጠርን፡፡ ከፍጥረቶቹም ዘንጊዎች አይደለንም፡፡
🎤 Your recording:
23:18 🔁 0/5
وَأَنزَلۡنَا مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءَۢ بِقَدَرٍ فَأَسۡكَنَّٰهُ فِي ٱلۡأَرۡضِۖ وَإِنَّا عَلَىٰ ذَهَابِۭ بِهِۦ لَقَٰدِرُونَ  ۝١٨
Wa anzalnaa minas samaaa`i maaa`am biqadarin fa-askannaahu fil ardi wa innaa `alaa zahaabim bihee laqaa diroon
ከሰማይም ውሃን በልክ አወረድን፡፡ በምድርም ውስጥ አስቀመጥነው፡፡ እኛም እርሱን በማስወገድ ላይ በእርግጥ ቻዮች ነን፡፡
🎤 Your recording:
23:19 🔁 0/5
فَأَنشَأۡنَا لَكُم بِهِۦ جَنَّٰتٍ مِّن نَّخِيلٍ وَأَعۡنَٰبٍ لَّكُمۡ فِيهَا فَوَٰكِهُ كَثِيرَةٌ وَمِنۡهَا تَأۡكُلُونَ  ۝١٩
Fa anshaanaa lakum bihee Jannaatim min nakheelinw wa a`naab; lakum feehaa fawaakihu kaseeratunw wa minhaa taakuloon
በእርሱም ከዘምባባዎችና ከወይኖች የኾኑን አትክልቶች ለእናንተ አስገኘንላችሁ፡፡ በውስጧ ለእናንተ ብዙ ፍራፍሬዎች አሏችሁ፡፡ ከእርሷም ትበላላችሁ፡፡
🎤 Your recording:
23:20 🔁 0/5
وَشَجَرَةً تَخۡرُجُ مِن طُورِ سَيۡنَآءَ تَنۢبُتُ بِٱلدُّهۡنِ وَصِبۡغٍ لِّلۡأٓكِلِينَ  ۝٢٠
Wa shajaratan takhruju min Toori Sainaaa`a tambutu bidduhni wa sibghil lil aakileen
ከሲና ተራራም የምትወጣን ዛፍ በቅባትና ለበይዎችም መባያ በሚኾን (ዘይት) ተቀላቅላ የምትበቅልን (አስገኘንላችሁ)፡፡
🎤 Your recording:
23:21 🔁 0/5
وَإِنَّ لَكُمۡ فِي ٱلۡأَنۡعَٰمِ لَعِبۡرَةًۖ نُّسۡقِيكُم مِّمَّا فِي بُطُونِهَا وَلَكُمۡ فِيهَا مَنَٰفِعُ كَثِيرَةٌ وَمِنۡهَا تَأۡكُلُونَ  ۝٢١
Wa inna lakum fil an`aami la`ibrah; nusqeekum mimmaa fee butoonihaa wa lakum feehaa manaafi`u kaseeratunw wa minhaa taakuloon
ለእናንተም በግመል፣ በከብት፣ በፍየልና በበግ መገምገሚያ አልላችሁ፡፡ በሆዶችዋ ውስጥ ካለው (ወተት) እናጠጣችኋለን፡፡ ለእናንተም በእርሷ ብዙ ጥቅሞች አሏችሁ፡፡ ከእርሷም ትበላላችሁ፡፡
🎤 Your recording:
23:22 🔁 0/5
وَعَلَيۡهَا وَعَلَى ٱلۡفُلۡكِ تُحۡمَلُونَ  ۝٢٢
Wa `alaihaa wa`alal fulki tuhmaloon
በእርሷም ላይ በመርከብም ላይ ትጫናላችሁ፡፡
🎤 Your recording:
23:23 🔁 0/5
وَلَقَدۡ أَرۡسَلۡنَا نُوحًا إِلَىٰ قَوۡمِهِۦ فَقَالَ يَٰقَوۡمِ ٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ مَا لَكُم مِّنۡ إِلَٰهٍ غَيۡرُهُۥٓۚ أَفَلَا تَتَّقُونَ  ۝٢٣
Wa laqad arsalnaa Noohan ilaa qawmihee faqaala yaa qawmi`budul laaha maa lakum min ilahin ghairuhoo afalaa tattaqoon
ኑሕንም ወደ ሕዝቦቹ በእርግጥ ላክነው፡፡ ወዲያውም «ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም፡፡ አትጠነቀቁምን» አላቸው፡፡
🎤 Your recording:
23:24 🔁 0/5
فَقَالَ ٱلۡمَلَؤُاْ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ مِن قَوۡمِهِۦ مَا هَٰذَآ إِلَّا بَشَرٌ مِّثۡلُكُمۡ يُرِيدُ أَن يَتَفَضَّلَ عَلَيۡكُمۡ وَلَوۡ شَآءَ ٱللَّهُ لَأَنزَلَ مَلَٰٓئِكَةً مَّا سَمِعۡنَا بِهَٰذَا فِيٓ ءَابَآئِنَا ٱلۡأَوَّلِينَ  ۝٢٤
Faqaalal mala`ul lazeena kafaroo min qawmihee maa haazaaa illaa basharum mislukum yureedu ai yatafaddala `alaikum wa law shaaa`al laahu la anzala malaaa`ikatam maa sami`naa bihaazaa feee aabaaa`inal awwaleen
ከሕዝቦቹም እነዚያ ታላላቆቹ ሰዎች አሉ «ይህ ብጤያችሁ ሰው እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ በእናንተ ላይ መብለጥን ይፈልጋል፡፡ አላህም በሻ ኖሮ መላእክትን ባወረደ ነበር፡፡ ይህንንም (የሚለውን) በመጀመሪያዎቹ አባቶቻችን አልሰማንም፡፡
🎤 Your recording:
23:25 🔁 0/5
إِنۡ هُوَ إِلَّا رَجُلُۢ بِهِۦ جِنَّةٌ فَتَرَبَّصُواْ بِهِۦ حَتَّىٰ حِينٍ  ۝٢٥
In huwa illaa rajulum bihee jinnatun fatarabbasoo bihee hattan heen
«እርሱ በእርሱ ዕብደት ያለበት ሰው እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ በእርሱም እስከ ጊዜ (ሞቱ) ድረስ ተጠባበቁ» (አሉ)፡፡
🎤 Your recording:
23:26 🔁 0/5
قَالَ رَبِّ ٱنصُرۡنِي بِمَا كَذَّبُونِ  ۝٢٦
Qaala Rabbin surnee bimaa kazzaboon
(ኑሕም) «ጌታዬ ሆይ! ባስተባበሉኝ ምክንያት እርዳኝ» አለ፡፡
🎤 Your recording:
23:27 🔁 0/5
فَأَوۡحَيۡنَآ إِلَيۡهِ أَنِ ٱصۡنَعِ ٱلۡفُلۡكَ بِأَعۡيُنِنَا وَوَحۡيِنَا فَإِذَا جَآءَ أَمۡرُنَا وَفَارَ ٱلتَّنُّورُ فَٱسۡلُكۡ فِيهَا مِن كُلٍّ زَوۡجَيۡنِ ٱثۡنَيۡنِ وَأَهۡلَكَ إِلَّا مَن سَبَقَ عَلَيۡهِ ٱلۡقَوۡلُ مِنۡهُمۡۖ وَلَا تُخَٰطِبۡنِي فِي ٱلَّذِينَ ظَلَمُوٓاْ إِنَّهُم مُّغۡرَقُونَ  ۝٢٧
Fa awhainaaa ilaihi anis na`il fulka bi a`yuninaa wa wahyinaa fa izaa jaaa`a amrunaa wa faarat tannooru fasluk feehaa min kullin zawjainis naini wa ahlaka illaa man sabaqa `alaihil qawlu minhum wa laa tukhaat ibnee fil lazeena zalamooo innaahum mughraqoon
ወደርሱም (እንዲህ ስንል) ላክን «በተመልካችነታችንና በትእዛዛችንም ታንኳን ሥራ በመጣና እቶኑ በፈለቀ ጊዜ በውስጧ ከሁሉም ሁለት ዓይነቶችን ቤተሰቦችህንም ከነሱ (ጠፊ በመኾን) ቃል ያለፈበት ብቻ ሲቀር፤ አግባ፡፡ በእነዚያም በበደሉት ሰዎች ነገር አታነጋግረኝ፡፡ እነሱ ተሰጣሚዎች ነቸውና፡፡
🎤 Your recording:
23:28 🔁 0/5
فَإِذَا ٱسۡتَوَيۡتَ أَنتَ وَمَن مَّعَكَ عَلَى ٱلۡفُلۡكِ فَقُلِ ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ ٱلَّذِي نَجَّىٰنَا مِنَ ٱلۡقَوۡمِ ٱلظَّٰلِمِينَ  ۝٢٨
Fa izas tawaita ata wa mam ma`aka `alal fulki faqulil hamdu lillaahil lazee najjaanaa minal qawmiz zalimeen
አንተም አብረውህ ካሉት ጋር በታንኳይቱ ላይ በተደላደልክ ጊዜ «ምስጋና ለዚያ ከበደለኞች ሕዝቦች ላዳነን አላህ ይገባው» በል፡፡
🎤 Your recording:
23:29 🔁 0/5
وَقُل رَّبِّ أَنزِلۡنِي مُنزَلًا مُّبَارَكًا وَأَنتَ خَيۡرُ ٱلۡمُنزِلِينَ  ۝٢٩
Wa qur Rabbi anzilnee munzalam mubaarakanw wa Anta khairul munzileen
በልም «ጌታዬ ሆይ! ብሩክ የኾነን ማውረድ አውርደኝ፡፡ አንተም ከአውራጆች ሁሉ በላጭ ነህ፡፡»
🎤 Your recording:
23:30 🔁 0/5
إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٍ وَإِن كُنَّا لَمُبۡتَلِينَ  ۝٣٠
Inna fee zaalika la Aayaatinw wa in kunnaa lamubtaleen
በዚህ ውስጥ (ለከሃሊነታችን) ምልከቶች አልሉበት፡፡ እነሆ! (የኑሕን ሰዎች) በእርግጥም ፈትታኞች ነበርን፡፡
🎤 Your recording:
23:31 🔁 0/5
ثُمَّ أَنشَأۡنَا مِنۢ بَعۡدِهِمۡ قَرۡنًا ءَاخَرِينَ  ۝٣١
Summaa anshaana mim ba`dihim qarnan aakhareen
ከዚያም ከኋላቸው ሌሎችን የክፍለ ዘመን ሕዝቦች አስገኘን፡፡
🎤 Your recording:
23:32 🔁 0/5
فَأَرۡسَلۡنَا فِيهِمۡ رَسُولًا مِّنۡهُمۡ أَنِ ٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ مَا لَكُم مِّنۡ إِلَٰهٍ غَيۡرُهُۥٓۚ أَفَلَا تَتَّقُونَ  ۝٣٢
Fa arsalnaa feehim Rasoolam minhum ani`budul laaha maa lakum min ilaahin ghairuhoo afalaa tattaqoon
በውስጣቸውም ከእነሱ የኾነን መልክተኛ አላህን ተገዙ ከእርሱ ሌላ አምላክ የላችሁም አትጠነቀቁምን በማለት ላክን፡፡
🎤 Your recording:
23:33 🔁 0/5
وَقَالَ ٱلۡمَلَأُ مِن قَوۡمِهِ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ وَكَذَّبُواْ بِلِقَآءِ ٱلۡأٓخِرَةِ وَأَتۡرَفۡنَٰهُمۡ فِي ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا مَا هَٰذَآ إِلَّا بَشَرٌ مِّثۡلُكُمۡ يَأۡكُلُ مِمَّا تَأۡكُلُونَ مِنۡهُ وَيَشۡرَبُ مِمَّا تَشۡرَبُونَ  ۝٣٣
Wa qaalal mala-u min qawmihil lazeena kafaroo wa kazzaboo bi liqaaa`il Aakhirati wa atrafnaahum fil hayaatid dunyaa maa haazaaa illaa basharum mislukum yaakulu mimmaa taakuloona minhu wa yashrabu mimmaa tashraboon
ከሕዝቦቹም እነዚያ የካዱት በመጨረሻይቱም ቀን መገናኘት ያስተባበሉት በቅርቢቱም ሕይወት ያቀማጠልናቸው ታላላቅ ሰዎች «ይህ ብጤያችሁ ሰው እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ ከርሱ ከምትበሉት ምግብ ይበላል፡፡ ከምትጠጡትም ውሃ ይጠጣል» አሉ፡፡
🎤 Your recording:
23:34 🔁 0/5
وَلَئِنۡ أَطَعۡتُم بَشَرًا مِّثۡلَكُمۡ إِنَّكُمۡ إِذًا لَّخَٰسِرُونَ  ۝٣٤
Wa la`in at`atum basharam mislakum innakum izal lakhaasiroon
«ብጤያችሁም የኾነን ሰው ብትታዘዙ እናንተ ያን ጊዜ በእርግጥ የተሞኛችሁ ናቸሁ» (አሉ)፡፡
🎤 Your recording:
23:35 🔁 0/5
أَيَعِدُكُمۡ أَنَّكُمۡ إِذَا مِتُّمۡ وَكُنتُمۡ تُرَابًا وَعِظَٰمًا أَنَّكُم مُّخۡرَجُونَ  ۝٣٥
A-Ya`idukum annakum izaa mittum wa kuntum turaabanw wa izaaman annakum mukhrajoon
«እናንተ በሞታችሁና ዐፈርና አጥንቶችም በኾናችሁ ጊዜ እናንተ (ከመቃብር) ትወጣላችሁ በማለት ያስፈራራችኋልን
🎤 Your recording:
23:36 🔁 0/5
۞ هَيۡهَاتَ هَيۡهَاتَ لِمَا تُوعَدُونَ  ۝٣٦
Haihaata haihaata limaa too`adoon
«ያ የምትስፈራሩበት ነገር ራቀ፤ በጣም ራቀ፡፡
🎤 Your recording:
23:37 🔁 0/5
إِنۡ هِيَ إِلَّا حَيَاتُنَا ٱلدُّنۡيَا نَمُوتُ وَنَحۡيَا وَمَا نَحۡنُ بِمَبۡعُوثِينَ  ۝٣٧
In hiya illaa hayaatunad dunyaa namootu wa nahyaa wa maa nahnu bimab`ooseen
«እርሷ (ሕይወት) ቅርቢቱ ሕይወታችን እንጂ ሌላ አይደለችም፡፡ እንሞታለን፤ (ልጆቻችን ስለሚተኩ) ሕያውም እንኾናለን፡፡ እኛም ተቀስቃሾች አይደለንም፡፡
🎤 Your recording:
23:38 🔁 0/5
إِنۡ هُوَ إِلَّا رَجُلٌ ٱفۡتَرَىٰ عَلَى ٱللَّهِ كَذِبًا وَمَا نَحۡنُ لَهُۥ بِمُؤۡمِنِينَ  ۝٣٨
In huwa illaa rajulunif taraa `alal laahi kazibanw wa maa nahnuu lahoo bimu`mineen
«እርሱ በአላህ ላይ ውሸትን የቀጠፈ ሰው እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ እኛም ለእርሱ አማኞች አይደለንም» (አሉ)፡፡
🎤 Your recording:
23:39 🔁 0/5
قَالَ رَبِّ ٱنصُرۡنِي بِمَا كَذَّبُونِ  ۝٣٩
Qaala Rabbin surnee bimaa kazzaboon
(መልክተኛውም) «ጌታዬ ሆይ! ስላስተባበሉኝ እርዳኝ» አለ፡፡
🎤 Your recording:
23:40 🔁 0/5
قَالَ عَمَّا قَلِيلٍ لَّيُصۡبِحُنَّ نَٰدِمِينَ  ۝٤٠
Qaala `ammaa qaleelil la yusbihunna naadimeen
(አላህም) «ከጥቂት ጊዜ በኋላ (በጥፋታቸው) በእርግጥ ተጸጻቾች ይኾናሉ» አለው፡፡
🎤 Your recording:
23:41 🔁 0/5
فَأَخَذَتۡهُمُ ٱلصَّيۡحَةُ بِٱلۡحَقِّ فَجَعَلۡنَٰهُمۡ غُثَآءًۚ فَبُعۡدًا لِّلۡقَوۡمِ ٱلظَّٰلِمِينَ  ۝٤١
Fa akhazat humus saihatu bilhaqqi faja`alnaahum ghusaaa`aa; fabu;dal lilqaw miz zaalimeen
ወዲያውም (የጥፋት) ጩኸቲቱ በእውነት ያዘቻቸው፡፡ እንደ ጎርፍ ግብስባሽም አደረግናቸው፡፡ ለበደለኞች ሕዝቦችም (ከእዝነት) መራቅ ተገባቸው፡፡
🎤 Your recording:
23:42 🔁 0/5
ثُمَّ أَنشَأۡنَا مِنۢ بَعۡدِهِمۡ قُرُونًا ءَاخَرِينَ  ۝٤٢
Summa anshaanaa mim ba`dihim quroonan aakhareen
ከዚያም ከእነሱ በኋላ ሌሎችን የክፍለ ዘመናት ሕዝቦች አስገኘን፡፡
🎤 Your recording:
23:43 🔁 0/5
مَا تَسۡبِقُ مِنۡ أُمَّةٍ أَجَلَهَا وَمَا يَسۡتَـٔۡخِرُونَ  ۝٤٣
Maa tasbiqu min ummatin ajalahaa wa maa yastaakhiroon
ማንኛይቱም ሕዝብ ጊዜያዋን አትቀድምም፤ አይቅቆዩምም፡፡
🎤 Your recording:
23:44 🔁 0/5
ثُمَّ أَرۡسَلۡنَا رُسُلَنَا تَتۡرَاۖ كُلَّ مَا جَآءَ أُمَّةً رَّسُولُهَا كَذَّبُوهُۖ فَأَتۡبَعۡنَا بَعۡضَهُم بَعۡضًا وَجَعَلۡنَٰهُمۡ أَحَادِيثَۚ فَبُعۡدًا لِّقَوۡمٍ لَّا يُؤۡمِنُونَ  ۝٤٤
Summa arsalnaa Rusulanaa tatraa kulla maa jaaa`a ummatar Rasooluhaa kazzabooh; fa atba`naa ba`dahum ba`danw wa ja`alnaahum ahaadees; fabu`dal liqawmil laa yu`minoon
ከዚያም መልክተኞቻችንን የሚከታተሉ ኾነው ላክን፡፡ ማንኛይቱንም ሕዝብ መልክተኛዋ በመጣላት ቁጥር አስተባበሉት፡፡ ከፊላቸውንም በከፊሉ (በጥፋት) አስከታተለን፡፡ ወሬዎችም አደረግናቸው፡፡ ለማያምኑም ሕዝቦች (ከእዝነታችን) መራቅ ተገባቸው፡፡
🎤 Your recording:
23:45 🔁 0/5
ثُمَّ أَرۡسَلۡنَا مُوسَىٰ وَأَخَاهُ هَٰرُونَ بِـَٔايَٰتِنَا وَسُلۡطَٰنٍ مُّبِينٍ  ۝٤٥
Summa arsalnaa Moosaa wa akhaahu Haaroona bi Aayaatinaa wa sultaanim mubeen
ከዚያም ሙሳንና ወንድሙን ሃሩንን በተዓምራታችንና በግልጽ አስረጅ ላክን፡፡
🎤 Your recording:
23:46 🔁 0/5
إِلَىٰ فِرۡعَوۡنَ وَمَلَإِيْهِۦ فَٱسۡتَكۡبَرُواْ وَكَانُواْ قَوۡمًا عَالِينَ  ۝٤٦
Ilaa Fir`awna wa mala`ihee fastakbaroo wa kaanoo qawman `aaleem
ወደ ፈርዖንና ወደ ጭፍሮቹ (ላክናቸው)፡፡ ኮሩም፡፡ የተንበጣረሩ ሕዝቦችም ነበሩ፡፡
🎤 Your recording:
23:47 🔁 0/5
فَقَالُوٓاْ أَنُؤۡمِنُ لِبَشَرَيۡنِ مِثۡلِنَا وَقَوۡمُهُمَا لَنَا عَٰبِدُونَ  ۝٤٧
Faqaaloo annu`minu libasharaini mislinaa wa qawmuhumaa lanaa `aabidoon
«ብጤያችንም ለኾኑ ሁለት ሰዎች ሕዝቦቻቸው ለእኛ ተገዢዎች ኾነው ሳሉ እናምናለን» አሉ፡፡
🎤 Your recording:
23:48 🔁 0/5
فَكَذَّبُوهُمَا فَكَانُواْ مِنَ ٱلۡمُهۡلَكِينَ  ۝٤٨
Fakazzaboohumaa fakaanoo minal mmuhlakeen
አስተባበሉዋቸውም፡፡ ከጠፊዎቹም ኾኑ፡፡
🎤 Your recording:
23:49 🔁 0/5
وَلَقَدۡ ءَاتَيۡنَا مُوسَى ٱلۡكِتَٰبَ لَعَلَّهُمۡ يَهۡتَدُونَ  ۝٤٩
Wa laqad aatainaa Moosal Kitaaba la`allahum yahtadoon
ሙሳንም (ነገዶቹ) ይምመሩ ዘንድ መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው፡፡
🎤 Your recording:
23:50 🔁 0/5
وَجَعَلۡنَا ٱبۡنَ مَرۡيَمَ وَأُمَّهُۥٓ ءَايَةً وَءَاوَيۡنَٰهُمَآ إِلَىٰ رَبۡوَةٍ ذَاتِ قَرَارٍ وَمَعِينٍ  ۝٥٠
Wa ja`alnab na Maryama wa ummahooo aayatannw wa aawainaahumaaa ilaa rabwatin zaati qaraarinw wa ma`een
የመርየምን ልጅና እናቱንም ተዓምር አደረግናቸው፡፡ የመደላደልና የምንጭ ባለቤት ወደ ኾነች ከፍተኛ ስፍራም አስጠጋናቸው፡፡
🎤 Your recording:
23:51 🔁 0/5
يَٰٓأَيُّهَا ٱلرُّسُلُ كُلُواْ مِنَ ٱلطَّيِّبَٰتِ وَٱعۡمَلُواْ صَٰلِحًاۖ إِنِّي بِمَا تَعۡمَلُونَ عَلِيمٌ  ۝٥١
Yaaa aiyuhar Rusulu kuloo minat taiyibaati wa`maloo saalihan innee bimaa ta`maloona `Aleem
እናንተ መልክተኞች ሆይ! ከተፈቀዱት ምግቦች ብሉ፡፡ በጎ ሥራንም ሥሩ፡፡ እኔ የምተሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነኝ፡፡
🎤 Your recording:
23:52 🔁 0/5
وَإِنَّ هَٰذِهِۦٓ أُمَّتُكُمۡ أُمَّةً وَٰحِدَةً وَأَنَا۠ رَبُّكُمۡ فَٱتَّقُونِ  ۝٥٢
Wa inna haaziheee ummatukum ummatanw waahidatanw wa Ana Rabbukum fattaqoon
ይህችም (በአንድ አምላክ የማመን ሕግጋት) አንድ መንገድ ስትኾን ሃይማኖታችሁ ናት፡፡ እኔም ጌታችሁ ነኝና ፍሩኝ፡፡
🎤 Your recording:
23:53 🔁 0/5
فَتَقَطَّعُوٓاْ أَمۡرَهُم بَيۡنَهُمۡ زُبُرًاۖ كُلُّ حِزۡبِۭ بِمَا لَدَيۡهِمۡ فَرِحُونَ  ۝٥٣
Fataqatta`ooo amrahum bainahum zuburaa; kullu hizbim bimaa ladaihim farihoon
(ከዚያ ተከታዮቻቸው) የሃይማኖት ነገራቸውንም በመካከላቸው ክፍልፍሎች አድርገው ቆራረጡ፡፡ ሕዝብ ሁሉ እነርሱ ዘንድ ባለው ሃይማኖት ተደሳቾች ናቸው፡፡
🎤 Your recording:
23:54 🔁 0/5
فَذَرۡهُمۡ فِي غَمۡرَتِهِمۡ حَتَّىٰ حِينٍ  ۝٥٤
Fazarhum fee ghamratihim hattaa heen
እስከ ጊዜያቸውም ድረስ በጥምመታቸው ውስጥ ተዋቸው፡፡
🎤 Your recording:
23:55 🔁 0/5
أَيَحۡسَبُونَ أَنَّمَا نُمِدُّهُم بِهِۦ مِن مَّالٍ وَبَنِينَ  ۝٥٥
A-yahsaboona annnamaa numiduhum bihee mimmaalinw wa baneen
ከገንዘብና ከልጆች በእርሱ የምንጨምርላቸውን ያስባሉን
🎤 Your recording:
23:56 🔁 0/5
نُسَارِعُ لَهُمۡ فِي ٱلۡخَيۡرَٰتِۚ بَل لَّا يَشۡعُرُونَ  ۝٥٦
Nusaari`u lahum fil khairaat; bal laa yash`uroon
በበጎ ነገሮች የምንቻኮልላቸው መኾንን (ያስባሉን) አይደለም፤ (ለማዘንጋት መኾኑን) አያውቁም፡፡
🎤 Your recording:
23:57 🔁 0/5
إِنَّ ٱلَّذِينَ هُم مِّنۡ خَشۡيَةِ رَبِّهِم مُّشۡفِقُونَ  ۝٥٧
Innal lazeena hum min khashyati Rabbihim mushfiqoon
እነዚያ እነርሱ ጌታቸውን ከመፍራት የተነሳ ተጨናቂዎች የኾኑት፡፡
🎤 Your recording:
23:58 🔁 0/5
وَٱلَّذِينَ هُم بِـَٔايَٰتِ رَبِّهِمۡ يُؤۡمِنُونَ  ۝٥٨
Wallazeena hum bi Aayaati Rabbihim yu`minoon
እነዚያም እነርሱ በጌታቸው ተዓምራቶች ከሚያምኑት፡፡
🎤 Your recording:
23:59 🔁 0/5
وَٱلَّذِينَ هُم بِرَبِّهِمۡ لَا يُشۡرِكُونَ  ۝٥٩
Wallazeena hum bi Rabbihim laa yushrikoon
እነዚያም እነርሱ በጌታቸው (ጣዖትን) የማያጋሩት፡፡
🎤 Your recording:
23:60 🔁 0/5
وَٱلَّذِينَ يُؤۡتُونَ مَآ ءَاتَواْ وَّقُلُوبُهُمۡ وَجِلَةٌ أَنَّهُمۡ إِلَىٰ رَبِّهِمۡ رَٰجِعُونَ  ۝٦٠
Wallazeena yu`toona maaa aataw wa quloobuhum wajilatun annahum ilaa Rabbihim raaji`oon
እነዚያም የሚሰጡትን ነገር እነርሱ ወደ ጌታቸው ተመላሾች መኾናቸውን ልቦቻቸው የሚፈሩ ኾነው የሚሰጡት፡፡
🎤 Your recording:
23:61 🔁 0/5
أُوْلَٰٓئِكَ يُسَٰرِعُونَ فِي ٱلۡخَيۡرَٰتِ وَهُمۡ لَهَا سَٰبِقُونَ  ۝٦١
Ulaaa`ika yusaari`oona fil khairaati wa hum lahaa saabiqoon
እነዚያ በመልካም ሥራዎች ይጣደፋሉ፡፡ እነሱም ለርሷ ቀዳሚዎች ናቸው፡፡
🎤 Your recording:
23:62 🔁 0/5
وَلَا نُكَلِّفُ نَفۡسًا إِلَّا وُسۡعَهَاۚ وَلَدَيۡنَا كِتَٰبٌ يَنطِقُ بِٱلۡحَقِّ وَهُمۡ لَا يُظۡلَمُونَ  ۝٦٢
Wa laa nukallifu nafsan illaa wus`ahaa wa ladainaa kitaabuny yantiqu bilhaqqi w ahum la yuzlamoon
ማንኛይቱንም ነፍስ ችሎታዋን እንጂ አናስገድዳትም፡፡ እኛም ዘንድ በእውነት የሚናገር መጽሐፍ አልለ፡፡ እነርሱም አይበደሉም፡፡
🎤 Your recording:
23:63 🔁 0/5
بَلۡ قُلُوبُهُمۡ فِي غَمۡرَةٍ مِّنۡ هَٰذَا وَلَهُمۡ أَعۡمَٰلٌ مِّن دُونِ ذَٰلِكَ هُمۡ لَهَا عَٰمِلُونَ  ۝٦٣
Bal quloobuhum fee ghamratim min haazaa wa lahum a`maalum min dooni zaalika hum lahaa `aamiloon
በእውነቱ (ከሓዲዎች) ልቦቻቸው ከዚያ (መጽሐፍ) በዝንጋቴ ውስጥ ናቸው፡፡ ለእነሱም ከዚህ ሌላ እነሱ ለርሷ ሠሪዎችዋ የኾኑ (መጥፎ) ሥራዎች አሏቸው፡፡
🎤 Your recording:
23:64 🔁 0/5
حَتَّىٰٓ إِذَآ أَخَذۡنَا مُتۡرَفِيهِم بِٱلۡعَذَابِ إِذَا هُمۡ يَجۡـَٔرُونَ  ۝٦٤
Hattaaa izaaa akhznaa mutrafeehim bil`azaabi izaa hum yaj`aroon
ቅምጥሎቻቸውንም በቅጣት በያዝናቸው ጊዜ ወዲያውኑ እነርሱ ይወተውታሉ፡፡
🎤 Your recording:
23:65 🔁 0/5
لَا تَجۡـَٔرُواْ ٱلۡيَوۡمَۖ إِنَّكُم مِّنَّا لَا تُنصَرُونَ  ۝٦٥
Laa taj`arul yawma innakum minnaa laa tunsaroon
ዛሬ አትወትውቱ፤ እናንተ ከእኛ ዘንድ አትረዱም፡፡
🎤 Your recording:
23:66 🔁 0/5
قَدۡ كَانَتۡ ءَايَٰتِي تُتۡلَىٰ عَلَيۡكُمۡ فَكُنتُمۡ عَلَىٰٓ أَعۡقَٰبِكُمۡ تَنكِصُونَ  ۝٦٦
Qad kaanat Aayaatee tutlaa `alaikum fakuntum `alaaa a`qaabikum tankisoon
አንቀጾቹ በእናንተ ላይ በእርግጥ ይነበቡላችሁ ነበር፡፡ በተረከዞቻችሁም ላይ ወደ ኋላችሁ ትመለሱ ነበራችሁ፡፡
🎤 Your recording:
23:67 🔁 0/5
مُسۡتَكۡبِرِينَ بِهِۦ سَٰمِرًا تَهۡجُرُونَ  ۝٦٧
Mustakbireena bihee saamiran tahjuroon
በእርሱ (በክልሉ ቤት) ኩሩዎች ሌሊት ተጫዋቾች (ቁርኣንንም) የምትተው ኾናችሁ (ትመለሱ ነበራችሁ ይባላሉ)፡፡
🎤 Your recording:
23:68 🔁 0/5
أَفَلَمۡ يَدَّبَّرُواْ ٱلۡقَوۡلَ أَمۡ جَآءَهُم مَّا لَمۡ يَأۡتِ ءَابَآءَهُمُ ٱلۡأَوَّلِينَ  ۝٦٨
Afalam yaddabbarrul qawla am jaaa`ahum maa lam yaati aabaaa`ahumul awwaleen
(የቁርኣንን) ንግግሩንም አያስተነትኑምን ወይስ ለመጀመሪያዎቹ አባቶቻቸው ያልመጣ ነገር መጣባቸውን
🎤 Your recording:
23:69 🔁 0/5
أَمۡ لَمۡ يَعۡرِفُواْ رَسُولَهُمۡ فَهُمۡ لَهُۥ مُنكِرُونَ  ۝٦٩
Am lam ya`rifoo Rasoolahum fahum lahoo munkiroon
ወይስ መልክተኛቸውን አላወቁምን ስለዚህ እነርሱ ለእርሱ ከሓዲዎች ናቸውን
🎤 Your recording:
23:70 🔁 0/5
أَمۡ يَقُولُونَ بِهِۦ جِنَّةُۢۚ بَلۡ جَآءَهُم بِٱلۡحَقِّ وَأَكۡثَرُهُمۡ لِلۡحَقِّ كَٰرِهُونَ  ۝٧٠
Am yaqooloona bihee jinnnah; bal jaaa`ahum bilhaqqi wa aksaruhum lil haqqi kaarihoon
ወይስ በእርሱ ዕብደት አለበት ይላሉን አይደለም፡፡ እውነትን ይዞ መጣላቸው፡፡ አብዛኞቻቸውም እውነትን ጠይዎች ናቸው፡፡
🎤 Your recording:
23:71 🔁 0/5
وَلَوِ ٱتَّبَعَ ٱلۡحَقُّ أَهۡوَآءَهُمۡ لَفَسَدَتِ ٱلسَّمَٰوَٰتُ وَٱلۡأَرۡضُ وَمَن فِيهِنَّۚ بَلۡ أَتَيۡنَٰهُم بِذِكۡرِهِمۡ فَهُمۡ عَن ذِكۡرِهِم مُّعۡرِضُونَ  ۝٧١
Wa lawit taba`al haqqu ahwaaa`ahum lafasadatis samaawaatu wal ardu wa man feehinnn; bal atainaahum bizikrihim fahum `an zikrihim mu`ridon
አላህም ዝንባሌዎቻቸውን በተከተለ ኖሮ ሰማያትና ምድር በውስጣቸውም ያለው ሁሉ በእርግጥ በተበላሸ ነበር፡፡ ይልቁንም ክብራቸው ያለበትን ቁርኣን አመጣንላቸው፡፡ እነርሱም ከክብራቸው ዘንጊዎች ናቸው፡፡
🎤 Your recording:
23:72 🔁 0/5
أَمۡ تَسۡـَٔلُهُمۡ خَرۡجًا فَخَرَاجُ رَبِّكَ خَيۡرٌۖ وَهُوَ خَيۡرُ ٱلرَّٰزِقِينَ  ۝٧٢
Am tas`aluhum kharjan fakharaaju Rabbika khairunw wa Huwa khairur raaziqeen
ወይስ ግብርን ትጠይቃቸዋለህን የጌታህም ችሮታ በላጭ ነው፡፡ እርሱም ከሰጪዎች ሁሉ በላጭ ነው፡፡
🎤 Your recording:
23:73 🔁 0/5
وَإِنَّكَ لَتَدۡعُوهُمۡ إِلَىٰ صِرَٰطٍ مُّسۡتَقِيمٍ  ۝٧٣
Wa innaka latad`oohum ilaa Siraatim Mustaqeem
አንተም ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ትጠራቸዋለህ፡፡
🎤 Your recording:
23:74 🔁 0/5
وَإِنَّ ٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ بِٱلۡأٓخِرَةِ عَنِ ٱلصِّرَٰطِ لَنَٰكِبُونَ  ۝٧٤
Wa innnal lazeena laa yu`minoona bil Aakhirati `anis siraati lanaakiboon
እነዚያም በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት ከትክክለኛው መንገድ ተዘንባዮች ናቸው፡፡
🎤 Your recording:
23:75 🔁 0/5
۞ وَلَوۡ رَحِمۡنَٰهُمۡ وَكَشَفۡنَا مَا بِهِم مِّن ضُرٍّ لَّلَجُّواْ فِي طُغۡيَٰنِهِمۡ يَعۡمَهُونَ  ۝٧٥
Wa law rahimnaahum wa kashafnaa maa bihim min durril lalajjoo fee tughyaanihim ya`mahoon
ባዘንንላቸውና ከጉዳትም በእነርሱ ያለውን ባነሳንላቸው ኖሮ በጥመታቸው ውስጥ የሚዋልሉ ኾነው ይዘወትሩ ነበር፡፡
🎤 Your recording:
23:76 🔁 0/5
وَلَقَدۡ أَخَذۡنَٰهُم بِٱلۡعَذَابِ فَمَا ٱسۡتَكَانُواْ لِرَبِّهِمۡ وَمَا يَتَضَرَّعُونَ  ۝٧٦
Wa laqad akhaznaahum bil`azaabi famastakaanoo li Rabbihim wa maa yatadarra`oon
በእርግጥም በቅጣት ያዝናቸው፡፡ ታዲያ ለጌታቸው አልተናነሱም፡፡ አይዋደቁምም፡፡
🎤 Your recording:
23:77 🔁 0/5
حَتَّىٰٓ إِذَا فَتَحۡنَا عَلَيۡهِم بَابًا ذَا عَذَابٍ شَدِيدٍ إِذَا هُمۡ فِيهِ مُبۡلِسُونَ  ۝٧٧
Hattaaa izaa fatahnaa `alaihim baaban zaa `azaabin shadeedin izaa hum feehi mublisoon
በእነሱም ላይ የብርቱ ቅጣት ባለቤት የኾነ ደጃፍን በከፈትንባቸው ጊዜ እነርሱ ያን ጊዜ በእርሱ ተስፋ ቆራጮች ናቸው፡፡
🎤 Your recording:
23:78 🔁 0/5
وَهُوَ ٱلَّذِيٓ أَنشَأَ لَكُمُ ٱلسَّمۡعَ وَٱلۡأَبۡصَٰرَ وَٱلۡأَفۡـِٔدَةَۚ قَلِيلًا مَّا تَشۡكُرُونَ  ۝٧٨
Wa Huwal lazeee ansha a-lakumus sam`a wal absaara wal af`idah; qaleelam maa tashkuroon
እርሱም ያ መስሚያዎችንና ማያዎችን ልቦችንም ለእናንተ የፈጠረላችሁ ነው፡፡ ጥቂትን እንጅ አታመሰግኑም፡፡
🎤 Your recording:
23:79 🔁 0/5
وَهُوَ ٱلَّذِي ذَرَأَكُمۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَإِلَيۡهِ تُحۡشَرُونَ  ۝٧٩
Wa Huwal lazee zara akum fil ardi wa ilaihi tuhsharoon
እርሱም ያ በምድር ውስጥ የበተናችሁ ነው፡፡ ወደርሱም ትሰበሰባላችሁ፡፡
🎤 Your recording:
23:80 🔁 0/5
وَهُوَ ٱلَّذِي يُحۡيِۦ وَيُمِيتُ وَلَهُ ٱخۡتِلَٰفُ ٱلَّيۡلِ وَٱلنَّهَارِۚ أَفَلَا تَعۡقِلُونَ  ۝٨٠
Wa Huwal lazee yuhyee wa yumeetu wa lahukh tilaaful laili wannahaar; afalaa ta`qiloon
እርሱም ያ ሕያው የሚያደርግ የሚገድልም ነው፡፡ የሌሊትና የቀን መተካካትም የእርሱ ነው፡፡ አታውቁምን
🎤 Your recording:
23:81 🔁 0/5
بَلۡ قَالُواْ مِثۡلَ مَا قَالَ ٱلۡأَوَّلُونَ  ۝٨١
Bal qaaloo misla maa qaalal awwaloon
ይልቁንም (የመካ ከሓዲዎች) የፊተኞቹ ሕዝቦች እንዳሉት ብጤ አሉ፡፡
🎤 Your recording:
23:82 🔁 0/5
قَالُوٓاْ أَءِذَا مِتۡنَا وَكُنَّا تُرَابًا وَعِظَٰمًا أَءِنَّا لَمَبۡعُوثُونَ  ۝٨٢
Qaalooo `a-izaa mitnaa wa kunnaa turaabanw wa `izaaman `a-innaa lamab `oosoon
«በሞትንና ዐፈርና አጥንቶች በኾን ጊዜ እኛ ተቀስቃሾች ነን» አሉ፡፡
🎤 Your recording:
23:83 🔁 0/5
لَقَدۡ وُعِدۡنَا نَحۡنُ وَءَابَآؤُنَا هَٰذَا مِن قَبۡلُ إِنۡ هَٰذَآ إِلَّآ أَسَٰطِيرُ ٱلۡأَوَّلِينَ  ۝٨٣
Laqad wu`idnaa nahnu wa aabaaa`unaa haazaa min qablu in haazaaa illaaa asaateerul awwaleen
«ይህንን እኛም ከእኛ በፊትም የነበሩት አባቶቻችን በእርግጥ ተቀጥረናል፡፡ ይህ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች እንጂ ሌላ አይደለም» (አሉ)፡፡
🎤 Your recording:
23:84 🔁 0/5
قُل لِّمَنِ ٱلۡأَرۡضُ وَمَن فِيهَآ إِن كُنتُمۡ تَعۡلَمُونَ  ۝٨٤
Qul limanil ardu wa man feehaaa in kuntum ta`lamoon
«ምድርና በውስጥዋ ያለው ሁሉ የማን ነው የምታውቁ ብትኾኑ (ንገሩኝ)» በላቸው፡፡
🎤 Your recording:
23:85 🔁 0/5
سَيَقُولُونَ لِلَّهِۚ قُلۡ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ  ۝٨٥
Sa-yaqooloona lillaah; qul afalaa tazakkkaroon
«በእርግጥ የአላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ታዲያ አትገሰጹምን» በላቸው፡፡
🎤 Your recording:
23:86 🔁 0/5
قُلۡ مَن رَّبُّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ ٱلسَّبۡعِ وَرَبُّ ٱلۡعَرۡشِ ٱلۡعَظِيمِ  ۝٨٦
Qul mar Rabbus samaawaatis sab`i wa Rabbul `Arshil `Azeem
«የሰባቱ ሰማያት ጌታና የታላቁ ዐርሽ ጌታ ማን ነው» በላቸው፡፡
🎤 Your recording:
23:87 🔁 0/5
سَيَقُولُونَ لِلَّهِۚ قُلۡ أَفَلَا تَتَّقُونَ  ۝٨٧
Sa yaqooloona lillaah; qul afalaa tattaqoon
«በእርግጥ አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «እንግዲያ አትፈሩትምን» በላቸው፡፡
🎤 Your recording:
23:88 🔁 0/5
قُلۡ مَنۢ بِيَدِهِۦ مَلَكُوتُ كُلِّ شَيۡءٍ وَهُوَ يُجِيرُ وَلَا يُجَارُ عَلَيۡهِ إِن كُنتُمۡ تَعۡلَمُونَ  ۝٨٨
Qul mam bi yadihee malakootu kulli shai`inw wa Huwa yujeeru wa laa yujaaru `alaihi in kuntum ta`lamoon
«የነገሩ ሁሉ ግዛት በእጁ የኾነ እርሱ የሚጠብቅ በእርሱ ላይ የማይጠበቅ ማን ነው የምታውቁ እንደኾናችሁ (መልሱልኝ)» በላቸው፡፡
🎤 Your recording:
23:89 🔁 0/5
سَيَقُولُونَ لِلَّهِۚ قُلۡ فَأَنَّىٰ تُسۡحَرُونَ  ۝٨٩
Sa yaqooloona lillaah; qul fa annaa tus haroon
«በእርግጥ አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ታዲያ እንዴት ትታለላላችሁ» በላቸው፡፡
🎤 Your recording:
23:90 🔁 0/5
بَلۡ أَتَيۡنَٰهُم بِٱلۡحَقِّ وَإِنَّهُمۡ لَكَٰذِبُونَ  ۝٩٠
Bal atainaahum bil haqqi wa innahum lakaaziboon
ይልቁንም እውነትን አመጣንላቸው፡፡ እነርሱም (በመካዳቸው) ውሸታሞች ናቸው፡፡
🎤 Your recording:
23:91 🔁 0/5
مَا ٱتَّخَذَ ٱللَّهُ مِن وَلَدٍ وَمَا كَانَ مَعَهُۥ مِنۡ إِلَٰهٍۚ إِذًا لَّذَهَبَ كُلُّ إِلَٰهِۭ بِمَا خَلَقَ وَلَعَلَا بَعۡضُهُمۡ عَلَىٰ بَعۡضٍۚ سُبۡحَٰنَ ٱللَّهِ عَمَّا يَصِفُونَ  ۝٩١
Mat takhazal laahu minw waladinw wa maa kaana ma`ahoo min ilaah; izal lazahaba kullu ilaahim bimaa khalaqa wa la`alaa ba`duhum `alaa ba`d; Subhaannal laahi `ammaa yasifoon
አላህ ምንም ልጅን አልያዘም (አልወለደም)፡፡ ከእርሱም ጋር አንድም አምላክ የለም፡፡ ያን ጊዜ (ሌላ አምላክ በነበረ) አምላክ ሁሉ በፈጠረው ነገር በተለየ ነበር፡፡ ከፊላቸውም በከፊሉ ለይ በላቀ ነበር፡፡ አላህ ከሚመጥኑት ሁሉ ጠራ፡፡
🎤 Your recording:
23:92 🔁 0/5
عَٰلِمِ ٱلۡغَيۡبِ وَٱلشَّهَٰدَةِ فَتَعَٰلَىٰ عَمَّا يُشۡرِكُونَ  ۝٩٢
Aalimil Ghaibi wash shahhaadati fata`aalaa `ammaa yushrikoon
ሩቁንና ቅርቡንም ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ (በእርሱ) ከሚያጋሩትም ሁሉ ከፍ አለ፡፡
🎤 Your recording:
23:93 🔁 0/5
قُل رَّبِّ إِمَّا تُرِيَنِّي مَا يُوعَدُونَ  ۝٩٣
Qur Rabbi immmaa turiyannee maa yoo`adoon
(ሙሐመድ ሆይ!) በል «ጌታዬ ሆይ! የሚያስፈራሩበትን (ቅጣት) ብታሳየኝ፡፡
🎤 Your recording:
23:94 🔁 0/5
رَبِّ فَلَا تَجۡعَلۡنِي فِي ٱلۡقَوۡمِ ٱلظَّٰلِمِينَ  ۝٩٤
Rabbi falaa taj`alnee fil qawmiz zaalimeen
«ጌታዬ ሆይ! በበደለኞች ሕዝቦች ውስጥ አታድርገኝ፡፡»
🎤 Your recording:
23:95 🔁 0/5
وَإِنَّا عَلَىٰٓ أَن نُّرِيَكَ مَا نَعِدُهُمۡ لَقَٰدِرُونَ  ۝٩٥
Wa innaa `alaaa an nuriyaka maa na`iduhum laqaadiroon
እኛም የምናስፈራራቸውን ነገር ልናሳይህ በእርግጥ ቻዮች ነን፡፡
🎤 Your recording:
23:96 🔁 0/5
ٱدۡفَعۡ بِٱلَّتِي هِيَ أَحۡسَنُ ٱلسَّيِّئَةَۚ نَحۡنُ أَعۡلَمُ بِمَا يَصِفُونَ  ۝٩٦
Idfa` billate hiya ahsanus saiyi`ah; nahnu a`lamu bimaa yasifoon
በዚያች እርስዋ መልካም በኾነችው (ጠባይ) መጥፎይቱን ነገር ገፍትር፡፡ እኛ የሚሉትን ሁሉ ዐዋቂዎች ነን፡፡
🎤 Your recording:
23:97 🔁 0/5
وَقُل رَّبِّ أَعُوذُ بِكَ مِنۡ هَمَزَٰتِ ٱلشَّيَٰطِينِ  ۝٩٧
Wa qur Rabbi a`oozu bika min hamazaatish Shayaateen
በልም «ጌታዬ ሆ! ከሰይጣናት ጉትተጎታዎች በአንተ እጠበቃለሁ፡፡
🎤 Your recording:
23:98 🔁 0/5
وَأَعُوذُ بِكَ رَبِّ أَن يَحۡضُرُونِ  ۝٩٨
Wa a`oozu bika Rabbi ai-yahduroon
«ባንተም ጌታዬ ሆይ! (በነገሮቼ) ወደእኔ ከመጣዳቸው እጠበቃለሁ፡፡»
🎤 Your recording:
23:99 🔁 0/5
حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءَ أَحَدَهُمُ ٱلۡمَوۡتُ قَالَ رَبِّ ٱرۡجِعُونِ  ۝٩٩
Hattaaa izaa jaaa`a ahada humul mawtu qaala Rabbir ji`oon
አንዳቸውንም ሞት በመጣበት ጊዜ እንዲህ ይላል «ጌታዬ ሆይ! (ወደ ምድረ ዓለም) መልሱኝ፡፡
🎤 Your recording:
23:100 🔁 0/5
لَعَلِّيٓ أَعۡمَلُ صَٰلِحًا فِيمَا تَرَكۡتُۚ كـَلَّآۚ إِنَّهَا كَلِمَةٌ هُوَ قَآئِلُهَاۖ وَمِن وَرَآئِهِم بَرۡزَخٌ إِلَىٰ يَوۡمِ يُبۡعَثُونَ  ۝١٠٠
La`alleee a`malu saalihan feemaa taraktu kallaa; innahaa kalimatun huwa qaaa`iluhaa wa minw waraaa`him barzakhun ilaa Yawmi yub`asoon
«በተውኩት ነገር በጎን ሥራ ልሠራ እከጅላለሁና፡፡» (ይህን ከማለት) ይከልከል፡፡ እርስዋ እርሱ ተናጋሪዋ የኾነች ከንቱ ቃል ናት፡፡ ከስተፊታቸውም እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ ግርዶ አልለ፡፡
🎤 Your recording:
23:101 🔁 0/5
فَإِذَا نُفِخَ فِي ٱلصُّورِ فَلَآ أَنسَابَ بَيۡنَهُمۡ يَوۡمَئِذٍ وَلَا يَتَسَآءَلُونَ  ۝١٠١
Fa izaa nufikha fis Soori falaaa ansaaba bainahum yawma`izinw wa laa yatasaaa`aloon
በቀንዱም በተነፋ ጊዜ በዚያ ቀን በመካከላቸው ዝምድና የለም፡፡ አይጠያየቁምም፡፡
🎤 Your recording:
23:102 🔁 0/5
فَمَن ثَقُلَتۡ مَوَٰزِينُهُۥ فَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡمُفۡلِحُونَ  ۝١٠٢
Faman saqulat mawaazee nuhoo fa ulaaa`ika humul muflihoon
ሚዛኖቹም የከበዱለት ሰው እነዚያ እነርሱ ፍላጎታቸውን ያገኙ ናቸው፡፡
🎤 Your recording:
23:103 🔁 0/5
وَمَنۡ خَفَّتۡ مَوَٰزِينُهُۥ فَأُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ خَسِرُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ فِي جَهَنَّمَ خَٰلِدُونَ  ۝١٠٣
Wa man khaffat mawaa zeenuhoo fa ulaaa`ikal lazeena khasiroon anfusahum fee Jahannnama khaalidoon
ሚዛኖቹም የቀለሉበት ሰው እነዚያ እነርሱ ነፍሶቻቸውን ያከሰሩ ናቸው፡፡ በገሀነም ውስጥ ዘመውታሪዎች ናቸው፡፡
🎤 Your recording:
23:104 🔁 0/5
تَلۡفَحُ وُجُوهَهُمُ ٱلنَّارُ وَهُمۡ فِيهَا كَٰلِحُونَ  ۝١٠٤
Talfahu wujoohahumun Naaru wa hum feehaa kaalihood
ፊቶቻቸውን እሳት ትገርፉቸዋለች፡፡ እነርሱም በእርሷ ውስጥ ከንፈሮቻቸው የተኮማተሩ ናቸው፡፡
🎤 Your recording:
23:105 🔁 0/5
أَلَمۡ تَكُنۡ ءَايَٰتِي تُتۡلَىٰ عَلَيۡكُمۡ فَكُنتُم بِهَا تُكَذِّبُونَ  ۝١٠٥
Alam takun Aayaatee tutlaa `alaikum fakuntum bihaa tukazziboon
«አንቀጾቼ በእናንተ ላይ የሚነበቡላችሁና በእነርሱ የምታስተባብሉ አልነበራችሁምን» (ይባላሉ)፡፡
🎤 Your recording:
23:106 🔁 0/5
قَالُواْ رَبَّنَا غَلَبَتۡ عَلَيۡنَا شِقۡوَتُنَا وَكُنَّا قَوۡمًا ضَآلِّينَ  ۝١٠٦
Qaaloo Rabbanaa ghalabat `alainaa shiqwatunaa wa kunnaa qawman daaalleen
ይላሉ «ጌታችን ሆይ! በእኛ ላይ መናጢነታችን አሸነፈችን፡፡ ጠማማዎችም ሕዝቦች ነበርን፡፡
🎤 Your recording:
23:107 🔁 0/5
رَبَّنَآ أَخۡرِجۡنَا مِنۡهَا فَإِنۡ عُدۡنَا فَإِنَّا ظَٰلِمُونَ  ۝١٠٧
Rabbanaa akhrijnaa minhaa fa in `udnaa fa innaa zaalimoon
«ጌታችን ሆይ! ከእርሷ አውጣን፡፡ (ወደ ክህደት) ብንመለስም እኛ በደዮች ነን፡፡»
🎤 Your recording:
23:108 🔁 0/5
قَالَ ٱخۡسَـُٔواْ فِيهَا وَلَا تُكَلِّمُونِ  ۝١٠٨
Qaalakh sa`oo feehaa wa laa tukallimoon
(አላህም) «ወራዶች ኾናችሁ በውስጥዋ እርጉ፡፡ አታናግሩኝም» ይላቸዋል፡፡
🎤 Your recording:
23:109 🔁 0/5
إِنَّهُۥ كَانَ فَرِيقٌ مِّنۡ عِبَادِي يَقُولُونَ رَبَّنَآ ءَامَنَّا فَٱغۡفِرۡ لَنَا وَٱرۡحَمۡنَا وَأَنتَ خَيۡرُ ٱلرَّٰحِمِينَ  ۝١٠٩
Innahoo kaana fareequm min `ibaadee yaqooloona Rabbanaaa aamannaa faghfir lanaa warhamnaa wa Anta khairur raahimeen
እነሆ ከባሮቼ «ጌታችን ሆይ! አምነናልና ማረን፡፡ እዘንልንም አንተም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህ» የሚሉ ክፍሎች ነበሩ፡፡
🎤 Your recording:
23:110 🔁 0/5
فَٱتَّخَذۡتُمُوهُمۡ سِخۡرِيًّا حَتَّىٰٓ أَنسَوۡكُمۡ ذِكۡرِي وَكُنتُم مِّنۡهُمۡ تَضۡحَكُونَ  ۝١١٠
Fattakhaztumoohum sikhriyyan hattaaa ansawkum zikree wa kuntum minhum tadhakoon
እኔንም ማውሳትን እስካስረሷችሁ ድረስም ማላገጫ አድርጋችሁ ያዛችኋቸው፡፡ በእነርሱም የምትስቁ ነበራችሁ፡፡
🎤 Your recording:
23:111 🔁 0/5
إِنِّي جَزَيۡتُهُمُ ٱلۡيَوۡمَ بِمَا صَبَرُوٓاْ أَنَّهُمۡ هُمُ ٱلۡفَآئِزُونَ  ۝١١١
Inee jazaituhumul Yawma bimaa sabarooo annahum humul faaa`izoon
እኔ ዛሬ በትዕግስታቸው ምክንያት እነሱ ፍላጎታቸውን የሚያገኙት እነርሱ ብቻ በመኾን መነዳኋቸው፤ (ይላቸዋል)፡፡
🎤 Your recording:
23:112 🔁 0/5
قَٰلَ كَمۡ لَبِثۡتُمۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ عَدَدَ سِنِينَ  ۝١١٢
Qaala kam labistum fil ardi `adada sineen
«በምድር ውስጥ ከዓመታት ቁጥር ስንትን ቆያችሁ» ይላቸዋል፡፡
🎤 Your recording:
23:113 🔁 0/5
قَالُواْ لَبِثۡنَا يَوۡمًا أَوۡ بَعۡضَ يَوۡمٍ فَسۡـَٔلِ ٱلۡعَآدِّينَ  ۝١١٣
Qaaloo labisnaa yawman aw ba`da yawmin fas`alil `aaaddeen
«አንድ ቀንን ወይም ከፊል ቀንን ቆየን፡፡ ቆጣሪዎቹንም ጠይቅ» ይላሉ፡፡
🎤 Your recording:
23:114 🔁 0/5
قَٰلَ إِن لَّبِثۡتُمۡ إِلَّا قَلِيلًاۖ لَّوۡ أَنَّكُمۡ كُنتُمۡ تَعۡلَمُونَ  ۝١١٤
Qaala il labistum illaa qaleelal law annakum kuntum ta`lamoon
«እናንተ (የቆያችሁትን መጠን) የምታውቁ ብትኾኑ ኖሮ (በእሳት ውስጥ በምትቆዩት አንፃር) ጥቂትን ጊዜ እንጂ አልቆያችሁም» ይላቸዋል፡፡
🎤 Your recording:
23:115 🔁 0/5
أَفَحَسِبۡتُمۡ أَنَّمَا خَلَقۡنَٰكُمۡ عَبَثًا وَأَنَّكُمۡ إِلَيۡنَا لَا تُرۡجَعُونَ  ۝١١٥
Afahsibtum annamaa khalaqnaakum `abasanw wa annakum ilainaa laa turja`oon
«የፈጠርናችሁ ለከንቱ መኾኑን እናንተም ወደኛ የማትመለሱ መኾናችሁን ጠረጠራችሁን» (ለከንቱ የፈጠርናችሁ መሰላችሁን)
🎤 Your recording:
23:116 🔁 0/5
فَتَعَٰلَى ٱللَّهُ ٱلۡمَلِكُ ٱلۡحَقُّۖ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ رَبُّ ٱلۡعَرۡشِ ٱلۡكَرِيمِ  ۝١١٦
Fata`aalal laahul Malikul Haqq; laaa ilaaha illaa Huwa Rabbul `Arshil Kareem
የእውነቱም ንጉስ አላህ ከፍተኛነት ተገባው፡፡ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ የሚያምረው ዐርሽ ጌታ ነው፡፡
🎤 Your recording:
23:117 🔁 0/5
وَمَن يَدۡعُ مَعَ ٱللَّهِ إِلَٰهًا ءَاخَرَ لَا بُرۡهَٰنَ لَهُۥ بِهِۦ فَإِنَّمَا حِسَابُهُۥ عِندَ رَبِّهِۦٓۚ إِنَّهُۥ لَا يُفۡلِحُ ٱلۡكَٰفِرُونَ  ۝١١٧
Wa mai yad`u ma`allaahi ilaahan aakhara laa burhaana lahoo bihee fa innnamaa hisaabuhoo `inda Rabbih; innahoo laa yuflihul kaafiroon
ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ ለእርሱ በእርሱ ማስረጃ የሌለውን የሚገዛ ሰው ምርመራው እጌታው ዘንድ ብቻ ነው፡፡ እነሆ ከሓዲዎች አይድኑም፡፡
🎤 Your recording:
23:118 🔁 0/5
وَقُل رَّبِّ ٱغۡفِرۡ وَٱرۡحَمۡ وَأَنتَ خَيۡرُ ٱلرَّٰحِمِينَ  ۝١١٨
Wa qur Rabbigh fir warham wa Anta khairur raahimeen
በልም «ጌታዬ ሆይ ማር፤ እዘንም፡፡ አንተም ከአዛኞች ሁሉ በላጭ ነህ፡፡»
🎤 Your recording:
💡 Tap any hidden word to reveal it temporarily — your progress is saved automatically in this browser.

🎉
🎊 Well Done! Memorization Complete
Mishary Rashid Alafasy
Mahmoud Khalil Al-Husary
Abdurrahman As-Sudais
Mohamed Siddiq Al-Minshawi
Abdul Basit Abdul Samad
Ali Al-Hudhaify
Ahmed ibn Ali al-Ajamy
Abu Bakr Ash-Shaatree
Muhammad Ayyoub
Abdullah Basfar
Abdullah Al-Juhani
Maher Al Muaiqly
0:00
0:00
-

ቅዱስ ቁርኣን


Tuesday, August 18, 2026

Don't forget us in your sincere prayers