🔥 0 day streak
📖 Long surah — split into smaller parts to help you focus (109 አንቀጽ)
0/109
10:1
🔁 0/5
الٓرۚ تِلۡكَ ءَايَٰتُ ٱلۡكِتَٰبِ ٱلۡحَكِيمِ ١
Alif-Laaam-Raa; tilka Aayaatul Kitaabil Hakeem
አ.ለ.ረ (አሊፍ ላም ራ) ይህቺ (ሱራ) ጥበብ ከተመላው መጽሐፍ (ከቁርኣን) አንቀጾች ናት፡፡
🎤 Your recording:
10:2
🔁 0/5
أَكَانَ لِلنَّاسِ عَجَبًا أَنۡ أَوۡحَيۡنَآ إِلَىٰ رَجُلٍ مِّنۡهُمۡ أَنۡ أَنذِرِ ٱلنَّاسَ وَبَشِّرِ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ أَنَّ لَهُمۡ قَدَمَ صِدۡقٍ عِندَ رَبِّهِمۡۗ قَالَ ٱلۡكَٰفِرُونَ إِنَّ هَٰذَا لَسَٰحِرٌ مُّبِينٌ ٢
A kaana linnaasi `aaban an awhainaaa ilaa rajulim minhum an anzirin naasa wa bashshiril lazeena aamanoo anna lahum qadama sidqin `inda Rabbihim; qaalal kaafiroona inna haaza lasaahirum mubeen
«ሰዎችን አስፈራራ፡፡ እነዚያንም ያመኑትን ለእነሱ ከጌታቸው ዘንድ መልካም ምንዳ ያላቸው መኾኑን አብስር» በማለት ከነርሱው ወደ ኾነ አንድ ሰው ራእይን ማውረዳችን ለሰዎች ድንቅ ኾነባቸውን ከሓዲዎቹ፡- «ይህ በእርግጥ ግልጽ ድግምተኛ ነው» አሉ፡፡
🎤 Your recording:
10:3
🔁 0/5
إِنَّ رَبَّكُمُ ٱللَّهُ ٱلَّذِي خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ فِي سِتَّةِ أَيَّامٍ ثُمَّ ٱسۡتَوَىٰ عَلَى ٱلۡعَرۡشِۖ يُدَبِّرُ ٱلۡأَمۡرَۖ مَا مِن شَفِيعٍ إِلَّا مِنۢ بَعۡدِ إِذۡنِهِۦۚ ذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبُّكُمۡ فَٱعۡبُدُوهُۚ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ ٣
Inna Rabbakumul laahul lazee khalaqas samaawaati wal arda fee sittati aiyaamin summas tawaa `alal `Arshi yudabbirul amra maa min shafee`in illaa mim ba`di iznih; zalikumul laahu Rabbukum fa`budooh; afalaa tazakkaroon
ጌታችሁ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ አላህ ነው፡፡ ከዚያም ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብር ሲኾን በዐርሹ ላይ (ስልጣኑ) ተደላደለ፡፡ ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም፡፡ እነሆ! አላህ ጌታችሁ ነውና ተገዙት፤ አትገሰጹምን
🎤 Your recording:
10:4
🔁 0/5
إِلَيۡهِ مَرۡجِعُكُمۡ جَمِيعًاۖ وَعۡدَ ٱللَّهِ حَقًّاۚ إِنَّهُۥ يَبۡدَؤُاْ ٱلۡخَلۡقَ ثُمَّ يُعِيدُهُۥ لِيَجۡزِيَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ بِٱلۡقِسۡطِۚ وَٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لَهُمۡ شَرَابٌ مِّنۡ حَمِيمٍ وَعَذَابٌ أَلِيمُۢ بِمَا كَانُواْ يَكۡفُرُونَ ٤
Ilaihi marji`ukum jamee `anw wa`dal laahi haqqaa; innahoo yabda`ul khalqa summa yu`eeduhoo liyajziyal lazeena aamanoo wa `amilus saalihaati bilqist; wallazeena kafaroo lahum sharaabum min hamee minw wa `azaabun aleemum bimaa kaanoo yakfuroon
ሁላችሁም ኾናችሁ መመለሻችሁ ወደ እርሱ ነው፡፡ (ይህም) የተረጋገጠ የአላህ ቃል ኪዳን ነው፤ እርሱ መፍጠርን ይጀምራል፡፡ ከዚያም እነዚያን ያመኑትንና መልካም የሠሩትን በትክክል ይመነዳ ዘንድ ይመልሰዋል፡፡ እነዚያ የካዱትም ይክዱት በነበሩት ነገር ለነርሱ ከፈላ ውሃ የኾነ መጠጥና አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡
🎤 Your recording:
10:5
🔁 0/5
هُوَ ٱلَّذِي جَعَلَ ٱلشَّمۡسَ ضِيَآءً وَٱلۡقَمَرَ نُورًا وَقَدَّرَهُۥ مَنَازِلَ لِتَعۡلَمُواْ عَدَدَ ٱلسِّنِينَ وَٱلۡحِسَابَۚ مَا خَلَقَ ٱللَّهُ ذَٰلِكَ إِلَّا بِٱلۡحَقِّۚ يُفَصِّلُ ٱلۡأٓيَٰتِ لِقَوۡمٍ يَعۡلَمُونَ ٥
Huwal lazee ja`alash shamsa diyaaa`anw walqamara nooranw wa qaddarahoo manaaz zila lita`lamoo `adadas sineena walhisaab; maa khalaqal laahu zaalika illa bilhaqq; yufassilul aayaati liqawminw ya`lamoon
እርሱ ያ ፀሐይን አንጻባራቂ ጨረቃንም አብሪ ያደረገ ነው፡፡ የዓመታትን ቁጥርና ሒሳብን ታውቁ ዘንድም ለእርሱ መስፈሪያዎችን የለካ ነው፡፡ አላህ ይህንን በእውነት እንጂ (በከንቱ) አልፈጠረውም፡፡ ለሚያውቁ ሕዝቦች አንቀጾችን ያብራራል፡፡
🎤 Your recording:
10:6
🔁 0/5
إِنَّ فِي ٱخۡتِلَٰفِ ٱلَّيۡلِ وَٱلنَّهَارِ وَمَا خَلَقَ ٱللَّهُ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ لَأٓيَٰتٍ لِّقَوۡمٍ يَتَّقُونَ ٦
Inna fikh tilaafil laili wannahaari wa maa khalaqal laahu fis samaawaati wal ardi la Aayaatil liqawminy yattaqoon
ሌሊትና ቀን በመተካካታቸው አላህም በሰማያትና በምድር ውስጥ በፈጠረው ሁሉ ለሚጠነቀቁ ሕዝቦች ምልክቶች አሉ፡፡
🎤 Your recording:
10:7
🔁 0/5
إِنَّ ٱلَّذِينَ لَا يَرۡجُونَ لِقَآءَنَا وَرَضُواْ بِٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا وَٱطۡمَأَنُّواْ بِهَا وَٱلَّذِينَ هُمۡ عَنۡ ءَايَٰتِنَا غَٰفِلُونَ ٧
Innal lazeena laa yarjoona liqaaa`anaa wa radoo bilhayaatid dunyaa watma annoo bihaa wallazeena hum `an Aayaatinaa ghaafiloon
እነዚያ መገናኘታችንን የማይፈሩ ቅርቢቱንም ሕይወት የወደዱ በእሷም የረኩ እነዚያም እነሱ ከአንቀጾቻችን ዘንጊዎች የኾኑ፡፡
🎤 Your recording:
10:8
🔁 0/5
أُوْلَٰٓئِكَ مَأۡوَىٰهُمُ ٱلنَّارُ بِمَا كَانُواْ يَكۡسِبُونَ ٨
Ulaaa`ika maawaahumun Naaru bimaa kaanoo yaksiboon
እነዚያ ይሠሩት በነበሩት ምክንያት መኖሪያቸው በእሳት ውስጥ ነው፡፡
🎤 Your recording:
10:9
🔁 0/5
إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ يَهۡدِيهِمۡ رَبُّهُم بِإِيمَٰنِهِمۡۖ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهِمُ ٱلۡأَنۡهَٰرُ فِي جَنَّٰتِ ٱلنَّعِيمِ ٩
Innal lazeena aamanoo wa `amilus saalihaati yahdeehim Rabbuhum bi eemaanihim tajree min tahtihimul anhaaru fee jannaatin Na`eem
እነዚያ ያመኑና መልካም ሥራዎችን የሠሩ ጌታቸው በእምነታቸው ምክንያት (የገነትን መንገድ) ይመራቸዋል፡፡ ከሥራቸው ወንዞች ይፈስሳሉ፡፡ በመጠቀሚያ ገነቶች ውስጥ ይኖራሉ፡፡
🎤 Your recording:
10:10
🔁 0/5
دَعۡوَىٰهُمۡ فِيهَا سُبۡحَٰنَكَ ٱللَّهُمَّ وَتَحِيَّتُهُمۡ فِيهَا سَلَٰمٌۚ وَءَاخِرُ دَعۡوَىٰهُمۡ أَنِ ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ ١٠
Da`waahum feehaa Subbaanakal laahumma wa tahiyyatuhum feehaa salaam; wa aakhiru da`waahum anil hamdu lillaahi Rabbil `aalameen
በእርሷም ውስጥ ጸሎታቸው ጌታችን ሆይ! ጥራት ይገባህ (ማለት) ነው፡፡ በእርሷ ውስጥ መከባበሪያቸውም ሰላም መባባል ነው፤ የመጨረሻ ጸሎታቸውም ምስጋና ለዓለማት ጌታ ይሁን (ማለት) ነው፡፡
🎤 Your recording:
10:11
🔁 0/5
۞ وَلَوۡ يُعَجِّلُ ٱللَّهُ لِلنَّاسِ ٱلشَّرَّ ٱسۡتِعۡجَالَهُم بِٱلۡخَيۡرِ لَقُضِيَ إِلَيۡهِمۡ أَجَلُهُمۡۖ فَنَذَرُ ٱلَّذِينَ لَا يَرۡجُونَ لِقَآءَنَا فِي طُغۡيَٰنِهِمۡ يَعۡمَهُونَ ١١
Wa law yu`aijilul laahu linnaasish sharras ti`jaalahum bilkhairi laqudiya ilaihim ajaluhum fanazarul lazeena laa yarjoona liqaaa`anna fee tughyaanihim ya`mahoon
አላህ ለሰዎች ደግን ነገር ለማግኘት እንደ መቻኮላቸው (አጥፋን ሲሉት) ክፉን ነገር ቢያስቸኩል ኖሮ ጊዜያቸው ወደነሱ በተፈጸመ ነበር፡፡ እነዚያንም መገናኘታችንን የማይፈሩትን በጥመታቸው ውስጥ የሚዋልሉ ሲኾኑ እንተዋቸዋለን፡፡
🎤 Your recording:
10:12
🔁 0/5
وَإِذَا مَسَّ ٱلۡإِنسَٰنَ ٱلضُّرُّ دَعَانَا لِجَنۢبِهِۦٓ أَوۡ قَاعِدًا أَوۡ قَآئِمًا فَلَمَّا كَشَفۡنَا عَنۡهُ ضُرَّهُۥ مَرَّ كَأَن لَّمۡ يَدۡعُنَآ إِلَىٰ ضُرٍّ مَّسَّهُۥۚ كَذَٰلِكَ زُيِّنَ لِلۡمُسۡرِفِينَ مَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ ١٢
Wa izaa massal insaanad durru da`aanaa lijambiheee aw qaa`idan aw qaaa`iman falammaa kashafnaa `anhu durrahoo marra ka al lam yad`unaaa ilaa durrim massah; kazaalika zuyyina lilmusrifeena maa kaanoo ya`maloon
ሰውንም ጉዳት ባገኘው ጊዜ በጎኑ ላይ ተጋድሞ ወይም ተቀምጦ ወይም ቆሞ ይለምነናል፡፡ ጉዳቱንም ከእሱ ላይ በገለጥንለት ጊዜ ወደ አገኘው ጉዳት እንዳልጠራን ሆኖ ያልፋል፡፡ እንደዚሁ ለድንበር አላፊዎች ይሠሩት የነበሩት ሥራ ተሸለመላቸው፡፡
🎤 Your recording:
10:13
🔁 0/5
وَلَقَدۡ أَهۡلَكۡنَا ٱلۡقُرُونَ مِن قَبۡلِكُمۡ لَمَّا ظَلَمُواْ وَجَآءَتۡهُمۡ رُسُلُهُم بِٱلۡبَيِّنَٰتِ وَمَا كَانُواْ لِيُؤۡمِنُواْۚ كَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلۡقَوۡمَ ٱلۡمُجۡرِمِينَ ١٣
Wa laqad ahlaknal quroona min qablikum lammaa zalamoo wa jaaa`at hum Rusuluhum bil baiyinaati wa maa kaanoo liyu`minoo; kazaalika najzil qawmal mujrimeen
ከእናንተ በፊት የነበሩትንም የክፍለ ዘመናት ሰዎች መልክተኞቻቸው በማስረጃዎች የመጧቸው ሲኾኑ በበደሉና የማያምኑም በኾኑ ጊዜ በእርግጥ አጠፋናቸው፡፡ እንደዚሁ ተንኮለኞችን ሕዝቦች እንቀጣለን፡፡
🎤 Your recording:
10:14
🔁 0/5
ثُمَّ جَعَلۡنَٰكُمۡ خَلَٰٓئِفَ فِي ٱلۡأَرۡضِ مِنۢ بَعۡدِهِمۡ لِنَنظُرَ كَيۡفَ تَعۡمَلُونَ ١٤
Summa ja`alnaakum khalaaa`ifa fil ardi mim ba`dihim linanzura kaifa ta`maloon
ከዚያም እንዴት እንደምትሠሩ ልንመለከት ከእነሱ በኋላ በምድር ላይ ምትኮች አደረግናችሁ፡፡
🎤 Your recording:
10:15
🔁 0/5
وَإِذَا تُتۡلَىٰ عَلَيۡهِمۡ ءَايَاتُنَا بَيِّنَٰتٍ قَالَ ٱلَّذِينَ لَا يَرۡجُونَ لِقَآءَنَا ٱئۡتِ بِقُرۡءَانٍ غَيۡرِ هَٰذَآ أَوۡ بَدِّلۡهُۚ قُلۡ مَا يَكُونُ لِيٓ أَنۡ أُبَدِّلَهُۥ مِن تِلۡقَآيِٕ نَفۡسِيٓۖ إِنۡ أَتَّبِعُ إِلَّا مَا يُوحَىٰٓ إِلَيَّۖ إِنِّيٓ أَخَافُ إِنۡ عَصَيۡتُ رَبِّي عَذَابَ يَوۡمٍ عَظِيمٍ ١٥
Wa izaa tutlaa `alaihim aayaatunaa baiyinaatin qaalal lazeena laa yarjoona liqaaa`ana`ti bi Quraanin ghairi haazaaa aw baddilh; qul maa yakoonu leee an ubaddilahoo min tilqaaa`i nafsee in attabi`u illaa maa yoohaaa ilaiya inneee akhaafu in `asaytu Rabbee `azaaba Yawmin `Azeeem
አንቀጾቻችንም ግልጽ ኾነው በእነርሱ ላይ በተነበቡላቸው ጊዜ እነዚያ መገናኘታችንን የማይፈሩት ከዚህ ሌላ የሆነን ቁርኣን አምጣልን ወይም ለውጠው ይላሉ፡፡ እኔ ከራሴ በኩል ልለውጠው አይገባኝም፡፡ ወደእኔ የሚወርደውን እንጂ አልከተልም፡፡ እኔ ከጌታዬ ባምጽ የታላቁን ቀን ቅጣት እፈራለሁ በላቸው፡፡
🎤 Your recording:
10:16
🔁 0/5
قُل لَّوۡ شَآءَ ٱللَّهُ مَا تَلَوۡتُهُۥ عَلَيۡكُمۡ وَلَآ أَدۡرَىٰكُم بِهِۦۖ فَقَدۡ لَبِثۡتُ فِيكُمۡ عُمُرًا مِّن قَبۡلِهِۦٓۚ أَفَلَا تَعۡقِلُونَ ١٦
Qul law shaaa`al laahu maa talawtuhoo `alaikum wa laaa adraakum bihee faqad labistu feekum `umuram min qablih; afalaa ta`qiloon
አላህ በሻ ኖሮ በእናንተ ላይ ባለነበብኩትም (አላህ) እርሱን ባላሳወቃችሁም ነበር፡፡ በእናንተም ውስጥ ከእርሱ በፊት (ምንም ሳልል) ብዙን ዕድሜ በእርግጥ ኖሬአለሁ፤ አታውቁምን
🎤 Your recording:
10:17
🔁 0/5
فَمَنۡ أَظۡلَمُ مِمَّنِ ٱفۡتَرَىٰ عَلَى ٱللَّهِ كَذِبًا أَوۡ كَذَّبَ بِـَٔايَٰتِهِۦٓۚ إِنَّهُۥ لَا يُفۡلِحُ ٱلۡمُجۡرِمُونَ ١٧
Faman azlamu mimmanif taraa `alal laahi kaziban aw kazzaba bi Aayaatih; innahoo laa yuflihul mujrimoon
በአላህም ላይ እብለትን ከቀጣጠፈ ወይም በአንቀጾቹ ከአስተባበለ ይበልጥ በዳይ ማን ነው እነሆ አመጸኞች አይድኑም፡፡
🎤 Your recording:
10:18
🔁 0/5
وَيَعۡبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَا لَا يَضُرُّهُمۡ وَلَا يَنفَعُهُمۡ وَيَقُولُونَ هَٰٓؤُلَآءِ شُفَعَٰٓؤُنَا عِندَ ٱللَّهِۚ قُلۡ أَتُنَبِّـُٔونَ ٱللَّهَ بِمَا لَا يَعۡلَمُ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَلَا فِي ٱلۡأَرۡضِۚ سُبۡحَٰنَهُۥ وَتَعَٰلَىٰ عَمَّا يُشۡرِكُونَ ١٨
Wa ya`budoona min doonil laahi maa laa yadurruhum wa laa yanfa`uhum wa yaqooloona haaa`ulaaa`i shufa`aaa `unaa `indal laah; qul atunabbi `oonal laaha bima laa ya`lamu fis samaawaati wa laa fil ard; subhaanahoo wa Ta`aalaa `ammaa yushrikoon
ከአላህም ሌላ የማይጎዳቸውን የማይጠቅማቸውንም ይግገዛሉ፡፡ «እነዚህም አላህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው» ይላሉ፡፡ «አላህን በሰማያትና በምድር ውስጥ የማያውቀው ነገር ኖሮ ትነግሩታላችሁን» በላቸው፡፡ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ፤ ላቀም፡፡
🎤 Your recording:
10:19
🔁 0/5
وَمَا كَانَ ٱلنَّاسُ إِلَّآ أُمَّةً وَٰحِدَةً فَٱخۡتَلَفُواْۚ وَلَوۡلَا كَلِمَةٌ سَبَقَتۡ مِن رَّبِّكَ لَقُضِيَ بَيۡنَهُمۡ فِيمَا فِيهِ يَخۡتَلِفُونَ ١٩
Wa maa kaanan naasu illaaa ummmatanw waahidatan fakh talafoo; wa law laa kalimatun sabaqat mir Rabbika laqudiya bainahum fee maa feehi yakhtalifoon
ሰዎችም አንድ ሕዝብ እንጂ ሌላ አልነበሩም፡፡ ተለያዩም፡፡ ከጌታህ ያለፈች ቃልም ባልነበረች ኖሮ በእርሱ በሚለያዩበት ነገር በመካከላቸው በእርግጥ (በቶሎ) በተፈረደ ነበር፡፡
🎤 Your recording:
10:20
🔁 0/5
وَيَقُولُونَ لَوۡلَآ أُنزِلَ عَلَيۡهِ ءَايَةٌ مِّن رَّبِّهِۦۖ فَقُلۡ إِنَّمَا ٱلۡغَيۡبُ لِلَّهِ فَٱنتَظِرُوٓاْ إِنِّي مَعَكُم مِّنَ ٱلۡمُنتَظِرِينَ ٢٠
W yaqooloona law laaa unzila `alaihi aayatum mir Rabbihee faqul innamal ghaibu lillaahi fantaziroo innee ma`akum minal muntazireen
በእርሱ ላይም ከጌታው የሆነች ተዓምር ለምን አትወረድለትም ይላሉ፡፡ «ሩቅ ነገርም ሁሉ የአላህ ብቻ ነው፡፡ ተጠባበቁም፤ እኔ ከናንተ ጋር ከሚጠባበቁት ነኝና» በላቸው፡፡
🎤 Your recording:
10:21
🔁 0/5
وَإِذَآ أَذَقۡنَا ٱلنَّاسَ رَحۡمَةً مِّنۢ بَعۡدِ ضَرَّآءَ مَسَّتۡهُمۡ إِذَا لَهُم مَّكۡرٌ فِيٓ ءَايَاتِنَاۚ قُلِ ٱللَّهُ أَسۡرَعُ مَكۡرًاۚ إِنَّ رُسُلَنَا يَكۡتُبُونَ مَا تَمۡكُرُونَ ٢١
Wa izaaa azaqnan naasa rahmatam mim ba`di darraaa`a massat hum izaa lahum makrun feee aayaatinaa; qulil laahu asra`u makraa; inna rusulanaa yaktuboona maa tamkuroon
ሰዎችንም ካገኛቸው ጉዳት በኋላ እዝነትን (ዝናብና ምቾትን) ባቀመስናቸው ጊዜ ወዲያውኑ ለእነሱ በተዓምራቶቻችን (በማላገጥ) ተንኮል ይኖራቸዋል፡፡ አላህ ቅጣተ ፈጣን ነው፡፡ «መልክተኞቻችን የምትመክሩትን ነገር በእርግጥ ይጽፋሉ» በላቸው፡፡
🎤 Your recording:
10:22
🔁 0/5
هُوَ ٱلَّذِي يُسَيِّرُكُمۡ فِي ٱلۡبَرِّ وَٱلۡبَحۡرِۖ حَتَّىٰٓ إِذَا كُنتُمۡ فِي ٱلۡفُلۡكِ وَجَرَيۡنَ بِهِم بِرِيحٍ طَيِّبَةٍ وَفَرِحُواْ بِهَا جَآءَتۡهَا رِيحٌ عَاصِفٌ وَجَآءَهُمُ ٱلۡمَوۡجُ مِن كُلِّ مَكَانٍ وَظَنُّوٓاْ أَنَّهُمۡ أُحِيطَ بِهِمۡ دَعَوُاْ ٱللَّهَ مُخۡلِصِينَ لَهُ ٱلدِّينَ لَئِنۡ أَنجَيۡتَنَا مِنۡ هَٰذِهِۦ لَنَكُونَنَّ مِنَ ٱلشَّٰكِرِينَ ٢٢
Huwal lazee yusaiyirukum fil barri walbahri hattaaa izaa kuntum fil fulki wa jaraina bihim bireeh in taiyibatinw wa farihoo bihaa jaaa`at haa reehun `aasifunw wa jaaa`ahumul mawju min kulli makaaninw wa zannooo annahum uheeta bihim da`awul laaha mukhliseena lahud deena la`in anjaitanaa min haazihee lanakoonannna minash shaakireen
እርሱ (አላህ) ያ በየብስና በባሕር የሚያስኬዳችሁ ነው፡፡ በመርከቦችም ውስጥ በሆናችሁና በእነርሱም በመልካም ነፋስ በርሷ የተደሰቱ ኾነው (መርከቦቹ) በተንሻለሉ ጊዜ ኀይለኛ ነፋስ ትመጣባታለች፡፡ ከየስፍራውም ማዕበል ይመጣባቸዋል፡፡ እነሱም (ለጥፋት) የተከበቡ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ፡፡ (ያን ጊዜ) አላህን ከዚህች (ጭንቀት) ብታድነን በእርግጥ ከአመስጋኞቹ እንሆናለን ሲሉ ሃይማኖትን ለርሱ ብቻ ያጠሩ ሆነው ይለምኑታል፡፡
🎤 Your recording:
10:23
🔁 0/5
فَلَمَّآ أَنجَىٰهُمۡ إِذَا هُمۡ يَبۡغُونَ فِي ٱلۡأَرۡضِ بِغَيۡرِ ٱلۡحَقِّۗ يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ إِنَّمَا بَغۡيُكُمۡ عَلَىٰٓ أَنفُسِكُمۖ مَّتَٰعَ ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَاۖ ثُمَّ إِلَيۡنَا مَرۡجِعُكُمۡ فَنُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ ٢٣
Falammaaa anjaahum izaa hum yabghoona fil ardi bighairil haqq; yaaa aiyuhannaasu innamaa bagh yukum `alaaa anfusikum mataa`al hayaatid dunyaa summa ilainaa marji`ukum fanunabbi `ukum bimaa kuntum ta`maloon
በአዳናቸውም ጊዜ እነሱ ወዲያውኑ ያለ አግባብ በምድር ላይ ወሰን ያልፋሉ፡፡ እናንተ ሰዎች ሆይ! ወሰን ማለፋችሁ (ጥፋቱ) በነፍሶቻችሁ ላይ ብቻ ነው፡፡ (እርሱም) የቅርቢቱ ሕይወት መጠቀሚያ ነው፡፡ ከዚያም መመለሻችሁ ወደኛ ነው፡፡ ትሠሩት የነበራችሁትንም ሁሉ እንነግራችኋለን፡፡
🎤 Your recording:
10:24
🔁 0/5
إِنَّمَا مَثَلُ ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا كَمَآءٍ أَنزَلۡنَٰهُ مِنَ ٱلسَّمَآءِ فَٱخۡتَلَطَ بِهِۦ نَبَاتُ ٱلۡأَرۡضِ مِمَّا يَأۡكُلُ ٱلنَّاسُ وَٱلۡأَنۡعَٰمُ حَتَّىٰٓ إِذَآ أَخَذَتِ ٱلۡأَرۡضُ زُخۡرُفَهَا وَٱزَّيَّنَتۡ وَظَنَّ أَهۡلُهَآ أَنَّهُمۡ قَٰدِرُونَ عَلَيۡهَآ أَتَىٰهَآ أَمۡرُنَا لَيۡلًا أَوۡ نَهَارًا فَجَعَلۡنَٰهَا حَصِيدًا كَأَن لَّمۡ تَغۡنَ بِٱلۡأَمۡسِۚ كَذَٰلِكَ نُفَصِّلُ ٱلۡأٓيَٰتِ لِقَوۡمٍ يَتَفَكَّرُونَ ٢٤
Innamaa masalul hayaatid dunyaa kammaaa`in anzalnaahu minas sammaaa`i fakhtalata bihee nabaatul ardi mimmaa yaakulun naasu wal an`aam; hattaaa izaaa akhazatil ardu zukhrufahaa wazziyanat wa zanna ahluhaaa annahum qaadiroona `alaihaaa ataahaaa amrunaa lailan aw nahaaran faja`alnaahaa haseedan ka allam taghna bil-ams; kazaalika nufassilul aayaati liqawminy yatafakkaroon
የቅርቢቱ ሕይወት ምሳሌ ከሰማይ እንዳወረድነው ውሃ፣ በእርሱም ሰውና እንስሳዎች ከሚበሉት የምድር በቃይ ተቀላቅሎበት (እንደ ፋፋ) ምድርም ውበትዋን በያዘችና ባጌጠች ጊዜ ባለቤቶችዋም በርሷ ላይ እነርሱ ቻዮች መኾናቸውን ባሰቡ ጊዜ ትእዛዛችን ሌሊት ወይም ቀን መጥቶባት ትላንት እንዳልነበረች የታጨደች እንዳደረግናት ብጤ ነው፡፡ እንደዚሁም ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች አንቀጾችን እናብራራለን፡፡
🎤 Your recording:
10:25
🔁 0/5
وَٱللَّهُ يَدۡعُوٓاْ إِلَىٰ دَارِ ٱلسَّلَٰمِ وَيَهۡدِي مَن يَشَآءُ إِلَىٰ صِرَٰطٍ مُّسۡتَقِيمٍ ٢٥
Wallaahu yad`ooo ilaa daaris salaami wa yahdee mai yashaaa`u ilaa Siraatim Mustaqeem
አላህም ወደ ሰላም አገር ይጠራል፡፡ የሚሻውንም ሰው ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይመራል፡፡
🎤 Your recording:
10:26
🔁 0/5
۞ لِّلَّذِينَ أَحۡسَنُواْ ٱلۡحُسۡنَىٰ وَزِيَادَةٌۖ وَلَا يَرۡهَقُ وُجُوهَهُمۡ قَتَرٌ وَلَا ذِلَّةٌۚ أُوْلَٰٓئِكَ أَصۡحَٰبُ ٱلۡجَنَّةِۖ هُمۡ فِيهَا خَٰلِدُونَ ٢٦
Lillazeena ahsanul husnaa wa ziyaadahtunw wa laa yarhaqu wujoohahum qatarunw wa laa zillah; ulaaa`ika ashaabul jannnati hum feehaa khaalidoon
ለእነዚያ መልካም ለሠሩት መልካም ነገርና ጭማሪም አላቸው፡፡ ፊቶቻቸውንም ጥቁረትና ውርደት አይሸፍናቸውም፡፡ እነዚያ የገነት ሰዎች ናቸው፡፡ እነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡
🎤 Your recording:
10:27
🔁 0/5
وَٱلَّذِينَ كَسَبُواْ ٱلسَّيِّـَٔاتِ جَزَآءُ سَيِّئَةِۭ بِمِثۡلِهَا وَتَرۡهَقُهُمۡ ذِلَّةٌۖ مَّا لَهُم مِّنَ ٱللَّهِ مِنۡ عَاصِمٍۖ كَأَنَّمَآ أُغۡشِيَتۡ وُجُوهُهُمۡ قِطَعًا مِّنَ ٱلَّيۡلِ مُظۡلِمًاۚ أُوْلَٰٓئِكَ أَصۡحَٰبُ ٱلنَّارِۖ هُمۡ فِيهَا خَٰلِدُونَ ٢٧
Wallazeena kasabus saiyi aati jazaaa`u saiyi`atim bimislihaa wa tarhaquhum zillah; maa lahum minal laahi min `aasimin ka annamaaa ughshiyat wujoohuhum qita `am minal laili muzlimaa; ulaaa`ika Ashaabun Naari hum feeha khaalidoon
ለእነዚያም ኃጢአቶችን ለሠሩት የኃጢኣቲቱ ቅጣት በብጤዋ አለቻቸው፡፡ ውርደትም ትሸፍናቸዋለች፡፡ ለእነሱ ከአላህ (ቅጣት) ጠባቂ የላቸውም፡፡ ፊቶቻቸው ከጨለመ ሌሊት ቁራጮች እንደ ተሸፈኑ ይኾናሉ፡፡ እነዚያ የእሳት ሰዎች ናቸው፡፡ እነርሱ በውስጧ ዘለዓለም ነዋሪዎች ናቸው፡፡
🎤 Your recording:
10:28
🔁 0/5
وَيَوۡمَ نَحۡشُرُهُمۡ جَمِيعًا ثُمَّ نَقُولُ لِلَّذِينَ أَشۡرَكُواْ مَكَانَكُمۡ أَنتُمۡ وَشُرَكَآؤُكُمۡۚ فَزَيَّلۡنَا بَيۡنَهُمۡۖ وَقَالَ شُرَكَآؤُهُم مَّا كُنتُمۡ إِيَّانَا تَعۡبُدُونَ ٢٨
Wa yawma nahshuruhum jamee`an summa naqoolu lillazeena ashrakoo makaanakum antum wa shurakaaa`ukum; fazaiyalnaa bainahum wa qaala shurakaaa`uhum maa kuntum iyyaanaa ta`budoon
ሁሉንም የምንሰበስባቸውን ከዚያም ለእነዚያ ለአጋሩት እናንተም ተጋሪዎችሁም ስፍራችሁን ያዙ የምንልበትን ተጋሪዎቻቸውም እኛን ትገዙ አልነበራችሁም የሚሉዋቸው ሲኾኑ በመካከላቸው የምንለይበትን ቀን (አስታውስ)፡፡
🎤 Your recording:
10:29
🔁 0/5
فَكَفَىٰ بِٱللَّهِ شَهِيدَۢا بَيۡنَنَا وَبَيۡنَكُمۡ إِن كُنَّا عَنۡ عِبَادَتِكُمۡ لَغَٰفِلِينَ ٢٩
Fakafaa billaahi shaheedam bainanaa wa bainakum in kunnaa `an `ibaadatikum laghaafileen
«(ጣዖታቶቹ ለእኛ) ከመገዛታችሁ በእርግጥ ዘንጊዎች ለመኾናችንም በእኛና በእናንተ መካከል የአላህ መስካሪነት በቃ» (ይሏቸዋል)፡፡
🎤 Your recording:
10:30
🔁 0/5
هُنَالِكَ تَبۡلُواْ كُلُّ نَفۡسٍ مَّآ أَسۡلَفَتۡۚ وَرُدُّوٓاْ إِلَى ٱللَّهِ مَوۡلَىٰهُمُ ٱلۡحَقِّۖ وَضَلَّ عَنۡهُم مَّا كَانُواْ يَفۡتَرُونَ ٣٠
Hunaalika tabloo kullu nafsim maaa aslafat; wa ruddoo ilal laahi mawlaahu mul haqqi wa dalla `anhum maa kaanoo yaftaroon
በዚያ ቀን ነፍስ ሁሉ ያሳለፈችውን ሥራ ታውቃለች፡፡ (አጋሪዎች) ወደ አላህም እውነተኛ ወደ ሆነው ጌታቸው ይመለሳሉ፡፡ ከእነሱም ይቀጣጥፉት የነበሩት ነገር ይጠፋቸዋል፡፡
🎤 Your recording:
10:31
🔁 0/5
قُلۡ مَن يَرۡزُقُكُم مِّنَ ٱلسَّمَآءِ وَٱلۡأَرۡضِ أَمَّن يَمۡلِكُ ٱلسَّمۡعَ وَٱلۡأَبۡصَٰرَ وَمَن يُخۡرِجُ ٱلۡحَيَّ مِنَ ٱلۡمَيِّتِ وَيُخۡرِجُ ٱلۡمَيِّتَ مِنَ ٱلۡحَيِّ وَمَن يُدَبِّرُ ٱلۡأَمۡرَۚ فَسَيَقُولُونَ ٱللَّهُۚ فَقُلۡ أَفَلَا تَتَّقُونَ ٣١
Qul mai yarzuqukum minas samaaa`i wal ardi ammany yamlikus sam`a wal absaara wa mai yukhrijul haiya minal maiyiti wa yikhrijul maiyita minal haiyi wa mai yudabbirul amr; fasa yaqooloonal laah; faqul afalaa tattaqoon
«ከሰማይና ከምድር ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማን ነው መስሚያዎችንና ማያዎችንስ የፈጠረ ማን ነው ከሙትም ሕያውን የሚያወጣ ከሕያውም ሙትን የሚያወጣስ ማን ነው ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብርስ ማን ነው» በላቸው፡፡ «በእርግጥም አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ታዲያ (ለምን ታጋራላችሁ) አትፈሩትምን» በላቸው፡፡
🎤 Your recording:
10:32
🔁 0/5
فَذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبُّكُمُ ٱلۡحَقُّۖ فَمَاذَا بَعۡدَ ٱلۡحَقِّ إِلَّا ٱلضَّلَٰلُۖ فَأَنَّىٰ تُصۡرَفُونَ ٣٢
Fazaalikumul laahu Rabbukumul haqq; famaazaa ba`dal haqqi illad dalaalu fa annnaa tusrafoon
እርሱ እውነተኛ ጌታችሁ አላህ ነው፡፡ ከእውነትም በኋላ ጥመት እንጂ ሌላ ምን አለ (ከውነት) እንዴት ትዞራላችሁ
🎤 Your recording:
10:33
🔁 0/5
كَذَٰلِكَ حَقَّتۡ كَلِمَتُ رَبِّكَ عَلَى ٱلَّذِينَ فَسَقُوٓاْ أَنَّهُمۡ لَا يُؤۡمِنُونَ ٣٣
Kazaalika haqqat Kalimatu Rabbika `alal lazeena fasaqooo annahum laa yu`minoon
እንደዚሁ የጌታህ ቃል በእነዚያ ባመጹት ላይ እነርሱ የማያምኑ መሆናቸው ተረጋገጠች፡፡
🎤 Your recording:
10:34
🔁 0/5
قُلۡ هَلۡ مِن شُرَكَآئِكُم مَّن يَبۡدَؤُاْ ٱلۡخَلۡقَ ثُمَّ يُعِيدُهُۥۚ قُلِ ٱللَّهُ يَبۡدَؤُاْ ٱلۡخَلۡقَ ثُمَّ يُعِيدُهُۥۖ فَأَنَّىٰ تُؤۡفَكُونَ ٣٤
Qul hal min shurakaaa `ikum mai yabda`ul khalqa suma yu`eeduh; qulil laahu yabda`ul khalqa summa yu`eeduhoo fa annaa tu`fakoon
«ከምታጋሩዋቸው (ጣዖታት) ውስጥ መፍጠርን የሚጀምር ከዚም የሚመልሰው አለን» በላቸው፡፡ «አላህ መፍጠርን ይጀምራል፤ ከዚያም ይመልሰዋል፡፡ ታዲያ (ከእምነት) እንዴት ትዞራላችሁ» በላቸው፡፡
🎤 Your recording:
10:35
🔁 0/5
قُلۡ هَلۡ مِن شُرَكَآئِكُم مَّن يَهۡدِيٓ إِلَى ٱلۡحَقِّۚ قُلِ ٱللَّهُ يَهۡدِي لِلۡحَقِّۗ أَفَمَن يَهۡدِيٓ إِلَى ٱلۡحَقِّ أَحَقُّ أَن يُتَّبَعَ أَمَّن لَّا يَهِدِّيٓ إِلَّآ أَن يُهۡدَىٰۖ فَمَا لَكُمۡ كَيۡفَ تَحۡكُمُونَ ٣٥
Qul hal min shurakaaa `ikum mai yahdeee ilal haqq; qulil laahu yahdee lilhaqq; afamai yahdeee ilal haqqi ahaqqu ai yuttaba`a ammal laa yahiddeee illaaa ai yuhdaa famaa lakum kaifa tahkumoon
«ከምታጋሩዋቸው፤ ወደ እውነት የሚመራ አለን» በላቸው፡፡ «አላህ ወደ እውነቱ ይመራል፡፡ ወደ እውነት የሚመራው ሊከተሉት የተገባው ነውን ወይስ ካልተመራ በስተቀር የማይመራው ለእናንተም ምን (አስረጅ) አላችሁ እንዴት (በውሸት) ትፈርዳላችሁ» በላቸው፡፡
🎤 Your recording:
10:36
🔁 0/5
وَمَا يَتَّبِعُ أَكۡثَرُهُمۡ إِلَّا ظَنًّاۚ إِنَّ ٱلظَّنَّ لَا يُغۡنِي مِنَ ٱلۡحَقِّ شَيۡـًٔاۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلِيمُۢ بِمَا يَفۡعَلُونَ ٣٦
Wa maa yattabi`u aksaruhum illaa zannaa; innaz zanna laa yughnee minal haqqi shai`aa; innal laaha `Aleemum bimaa yaf`aloon
አብዛኞቻቸውም ጥርጣሬን እንጂ አይከተሉም፡፡ ጥርጣሬ ከእውነት ምንም አያብቃቃም፡፡ አላህ የሚሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡
🎤 Your recording:
10:37
🔁 0/5
وَمَا كَانَ هَٰذَا ٱلۡقُرۡءَانُ أَن يُفۡتَرَىٰ مِن دُونِ ٱللَّهِ وَلَٰكِن تَصۡدِيقَ ٱلَّذِي بَيۡنَ يَدَيۡهِ وَتَفۡصِيلَ ٱلۡكِتَٰبِ لَا رَيۡبَ فِيهِ مِن رَّبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ ٣٧
Wa maa kaana haazal Quraanu ai yuftaraa min doonil laahi wa laakin tasdeeqal lazee baina yadaihi wa tafseelal Kitaabi laa raiba fee mir Rabbil `aalameen
ይህም ቁርኣን ከአላህ ሌላ (ከሆነ ፍጡር) የተቀጠፈ ሊሆን አይገባውም፡፡ ግን ያንን ከእርሱ በፊት ያለውን (መጽሐፍ) የሚያረጋግጥና በመጽሐፉ ውስጥ ያለውን የሚዘረዝር በእርሱ ጥርጣሬ የሌለበት ሲሆን ከዓለማት ጌታ (የተወረደ) ነው፡፡
🎤 Your recording:
10:38
🔁 0/5
أَمۡ يَقُولُونَ ٱفۡتَرَىٰهُۖ قُلۡ فَأۡتُواْ بِسُورَةٍ مِّثۡلِهِۦ وَٱدۡعُواْ مَنِ ٱسۡتَطَعۡتُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ ٣٨
Am yaqooloonaf taraahu qul faatoo bisooratim mislihee wad`oo manis tata`tum min doonil laahi in kuntum saadiqeen
በእውነትም «(ሙሐመድ) ቀጣጠፈው» ይላሉን «ይህ ከሆነ መሰሉን (አንዲት) ሱራ አምጡ፡፡ ከአላህም ሌላ የቻላችሁትን ሁሉ (ረዳት) ጥሩ፡፡ እውነተኞች እንደሆናችሁ (ተጋግዛችሁ አምጡ)» በላቸው፡፡
🎤 Your recording:
10:39
🔁 0/5
بَلۡ كَذَّبُواْ بِمَا لَمۡ يُحِيطُواْ بِعِلۡمِهِۦ وَلَمَّا يَأۡتِهِمۡ تَأۡوِيلُهُۥۚ كَذَٰلِكَ كَذَّبَ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡۖ فَٱنظُرۡ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلظَّٰلِمِينَ ٣٩
Bal kazzaboo bimaa lam yuheetoo bi`ilmihee wa lammaa yaatihim taaweeluh; kazaalika kazzabal lazeena min qablihim fanzur kaifa kaana `aaqibatuz zaalimeen
ይልቁንም (ከቁርኣን) እውቀቱን ባላደረሱት ፍቹም ገና ባልመጣቸው ነገር አስተባበሉ፡፡ እንደዚሁ እነዚያ ከእነሱ በፊት የነበሩት አስተባብለዋል፡፡ የበዳዮችም መጨረሻ እንዴት እንደ ነበረ ተመልከት፡፡
🎤 Your recording:
10:40
🔁 0/5
وَمِنۡهُم مَّن يُؤۡمِنُ بِهِۦ وَمِنۡهُم مَّن لَّا يُؤۡمِنُ بِهِۦۚ وَرَبُّكَ أَعۡلَمُ بِٱلۡمُفۡسِدِينَ ٤٠
Wa minhum mai yu `minu bihee wa minhum mal laa yu`minu bih; wa Rabbuka a`lamu bilmufsideen
ከእነርሱም ውስጥ (ወደፊት) በርሱ የሚያምኑ አልሉ፡፡ ከእነርሱም በእርሱ የማያምኑ አልሉ፡፡ ጌታህም አጥፊዎቹን በጣም ዐዋቂ ነው፡፡
🎤 Your recording:
10:41
🔁 0/5
وَإِن كَذَّبُوكَ فَقُل لِّي عَمَلِي وَلَكُمۡ عَمَلُكُمۡۖ أَنتُم بَرِيٓـُٔونَ مِمَّآ أَعۡمَلُ وَأَنَا۠ بَرِيٓءٌ مِّمَّا تَعۡمَلُونَ ٤١
Wa in kazzabooka faqul lee `amalee wa lakum `amalukum antum bareee`oona mimmaaa a`malu wa ana bareee`um mimmaa ta`maloon
«ቢያስተባብሉህም ለእኔ ሥራዬ አለኝ፡፡ ለእናንተም ሠራችሁ አላችሁ፡፡ እናንተ ከምሠራው ነገር ንጹሕ ናችሁ፡፡ እኔም ከምትሠሩት ነገር ንጹሕ ነኝ» በላቸው፡፡
🎤 Your recording:
10:42
🔁 0/5
وَمِنۡهُم مَّن يَسۡتَمِعُونَ إِلَيۡكَۚ أَفَأَنتَ تُسۡمِعُ ٱلصُّمَّ وَلَوۡ كَانُواْ لَا يَعۡقِلُونَ ٤٢
Wa minhum mai yastami`oona iliak; afa anta tusmi`us summa wa law kaanoo la ya`qiloon
ከእነሱም ወደ አንተ የሚያዳምጡ (እና የማያምኑ) አልሉ፡፡ አንተ ደንቆሮዎችን የማያውቁ ቢኾኑም ታሰማለህን
🎤 Your recording:
10:43
🔁 0/5
وَمِنۡهُم مَّن يَنظُرُ إِلَيۡكَۚ أَفَأَنتَ تَهۡدِي ٱلۡعُمۡيَ وَلَوۡ كَانُواْ لَا يُبۡصِرُونَ ٤٣
Wa minhum mai yanzuru ilaik; afa anta tahdil `umya wa law kaanoo laa yubsiroon
ከእነሱም ወደ አንተ የሚመለከቱ አልሉ፡፡ አንተ (ልበ) ዕውራንን የማያዩ ቢኾኑም ትመራለህን
🎤 Your recording:
10:44
🔁 0/5
إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَظۡلِمُ ٱلنَّاسَ شَيۡـًٔا وَلَٰكِنَّ ٱلنَّاسَ أَنفُسَهُمۡ يَظۡلِمُونَ ٤٤
Innal laaha laa yazlimun naasa shai`anw wa laakin nannaasa anfusahum yazlimoon
አላህ ሰዎችን ምንም አይበድልም፡፡ ግን ሰዎች ነፍሶቻቸውን ይበድላሉ፡፡
🎤 Your recording:
10:45
🔁 0/5
وَيَوۡمَ يَحۡشُرُهُمۡ كَأَن لَّمۡ يَلۡبَثُوٓاْ إِلَّا سَاعَةً مِّنَ ٱلنَّهَارِ يَتَعَارَفُونَ بَيۡنَهُمۡۚ قَدۡ خَسِرَ ٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ بِلِقَآءِ ٱللَّهِ وَمَا كَانُواْ مُهۡتَدِينَ ٤٥
Wa Yawma yahshuruhum ka al lam yalbasooo illaa saa`atam minan nahaari yata`aarafoona bainahum; qad khasiral lazeena kazzaboo biliqaaa`il laahi wa maa kaanoo muhtadeen
(ከሓዲዎችን) ከቀን አንዲትን ሰዓት እንጂ እንዳልቆዩ መስለው በመካከላቸው የሚተዋወቁ ሲሆኑ በምንሰበስባቸው ቀን (አስታውስ)፡፡ እነዚያ በአላህ መገናኘት ያስተባበሉት በእርግጥ ከሰሩ የተመሩም አልነበሩም፡፡
🎤 Your recording:
10:46
🔁 0/5
وَإِمَّا نُرِيَنَّكَ بَعۡضَ ٱلَّذِي نَعِدُهُمۡ أَوۡ نَتَوَفَّيَنَّكَ فَإِلَيۡنَا مَرۡجِعُهُمۡ ثُمَّ ٱللَّهُ شَهِيدٌ عَلَىٰ مَا يَفۡعَلُونَ ٤٦
Wa imma nuriyannaka ba`dal lazee na`iduhum aw natawaffayannaka fa ilainaa marji`uhum summal laahu shaheedun `alaa maa yaf`aloon
የዚያንም የምናስፈራራቸውን ከፊሉን (በሕይወትህ) ብናሳይህ (መልካም ነው)፡፡ ወይም (ሳናሳይህ) ብንገድልህ መመለሻቸው ወደ እኛ ነው፡፡ ከዚያም አላህ በሚሠሩት ስራ ላይ ዐዋቂ ነው፡፡
🎤 Your recording:
10:47
🔁 0/5
وَلِكُلِّ أُمَّةٍ رَّسُولٌۖ فَإِذَا جَآءَ رَسُولُهُمۡ قُضِيَ بَيۡنَهُم بِٱلۡقِسۡطِ وَهُمۡ لَا يُظۡلَمُونَ ٤٧
Wa likulli ummatir Rasoolun fa izaa jaaa`a Rasooluhum qudiya bainahum bilqisti wa hum laa yuzlamoon
ለሕዝቦችም ሁሉ መልክተኛ አላቸው፡፡ መልክተኛውም በመጣ ጊዜ (ሲያስተባብሉ) በመካከላቸው በትክክል ይፈረዳል፡፡ እነርሱም አይበደሉም፡፡
🎤 Your recording:
10:48
🔁 0/5
وَيَقُولُونَ مَتَىٰ هَٰذَا ٱلۡوَعۡدُ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ ٤٨
Wa yaqooloona mataa haazal wa`du in kuntum saadiqeen
«እውነተኞችም ከሆናችሁ ይህ (የቅጣቱ) ቀጠሮ መቼ ነው» ይላሉ፡፡
🎤 Your recording:
10:49
🔁 0/5
قُل لَّآ أَمۡلِكُ لِنَفۡسِي ضَرًّا وَلَا نَفۡعًا إِلَّا مَا شَآءَ ٱللَّهُۗ لِكُلِّ أُمَّةٍ أَجَلٌۚ إِذَا جَآءَ أَجَلُهُمۡ فَلَا يَسۡتَـٔۡخِرُونَ سَاعَةً وَلَا يَسۡتَقۡدِمُونَ ٤٩
Qul laaa amliku linafsee darranw wa laa naf`an illaa maa shaaa`al laah; likulli ummatin ajalun izaa jaaa`a ajaluhum falaaa yastaakhiroona saa`a tanw wa laa yastaqdimoon
«ለራሴ ጉዳትንም ጥቅምንም አላህ ከሻው በስተቀር አልችልም፡፡ ለሕዝቦች ሁሉ የተወሰነ ጊዜ አልላቸው፡፡ ጊዜያቸው በመጣ ወቅት አንዲትን ሰዓት አይቆዩም፤ አይቀደሙምም» በላቸው፡፡
🎤 Your recording:
10:50
🔁 0/5
قُلۡ أَرَءَيۡتُمۡ إِنۡ أَتَىٰكُمۡ عَذَابُهُۥ بَيَٰتًا أَوۡ نَهَارًا مَّاذَا يَسۡتَعۡجِلُ مِنۡهُ ٱلۡمُجۡرِمُونَ ٥٠
Qul ara`aitum in ataakum `azaabuhoo bayaatan aw nahaaram maazaa yasta`jilu minhul mujrimoon
«ቅጣቱ በሌሊት ወይም በቀን ቢመጣባችሁ፤ አጋሪዎቹ ከርሱ የሚቻኮሉበት ነገር ምንድን ነው ንገሩኝ» በላቸው፡፡
🎤 Your recording:
10:51
🔁 0/5
أَثُمَّ إِذَا مَا وَقَعَ ءَامَنتُم بِهِۦٓۚ ءَآلۡـَٰٔنَ وَقَدۡ كُنتُم بِهِۦ تَسۡتَعۡجِلُونَ ٥١
Asumma izaa maa waqa`a aamantum bih; aaal`aana wa qad kuntum bihee tasta`jiloon
«ከዚያም (ቅጣቱ) በወደቀ ጊዜ በእርሱ አመናችሁበትን በእርግጥ በእርሱ የምትቻኮሉ የነበራችሁ ስትሆኑ አሁን» (ይባላሉ)፡፡
🎤 Your recording:
10:52
🔁 0/5
ثُمَّ قِيلَ لِلَّذِينَ ظَلَمُواْ ذُوقُواْ عَذَابَ ٱلۡخُلۡدِ هَلۡ تُجۡزَوۡنَ إِلَّا بِمَا كُنتُمۡ تَكۡسِبُونَ ٥٢
Summa qeela lillazeena zalamoo zooqoo `azaabal khuld hal tujzawna illaa bimaa kuntum taksiboon
ከዚያም ለእነዚያ ለበደሉት፡- «ዘውታሪን ቅጣት ቅመሱ ትሠሩት የነበረችሁትን ዋጋ እንጂ አትመነዱም» ይባላሉ፡፡
🎤 Your recording:
10:53
🔁 0/5
۞ وَيَسۡتَنۢبِـُٔونَكَ أَحَقٌّ هُوَۖ قُلۡ إِي وَرَبِّيٓ إِنَّهُۥ لَحَقٌّۖ وَمَآ أَنتُم بِمُعۡجِزِينَ ٥٣
Wa yastambi`oonaka ahaqqun huwa qul ee wa Rabbeee innahoo lahaqq; wa maaa antum bimu`jizeen
እርሱም «እውነት ነውን» (ሲሉ) ይጠይቁሃል፡፡ «አዎን፤ በጌታዬ እምላለሁ፤ እርሱ እውነት ነው፡፡ እናንተም አምላጮች አይደላችሁም፤» በላቸው፡፡
🎤 Your recording:
10:54
🔁 0/5
وَلَوۡ أَنَّ لِكُلِّ نَفۡسٍ ظَلَمَتۡ مَا فِي ٱلۡأَرۡضِ لَٱفۡتَدَتۡ بِهِۦۗ وَأَسَرُّواْ ٱلنَّدَامَةَ لَمَّا رَأَوُاْ ٱلۡعَذَابَۖ وَقُضِيَ بَيۡنَهُم بِٱلۡقِسۡطِ وَهُمۡ لَا يُظۡلَمُونَ ٥٤
Wa law anna likulli nafsin zalamat maa fil ardi laftadat bih; wa asarrun nadaamata lammaa ra awul `azaab, wa qudiya bainahum bilqist; wa hum laa yuzlamoon
ለበደለችም ነፍስ ሁሉ በምድር ላይ ያለው ሁሉ ቢኖራት ኖሮ በእርግጥ በተበዠችበት ነበር፡፡ ቅጣቱንም ባዩ ጊዜ ጸጸትን ይገልጻሉ፡፡ በመካከላቸውም በትክክል ይፈረዳል፡፡ እነርሱም አይበደሉም፡፡
🎤 Your recording:
10:55
🔁 0/5
أَلَآ إِنَّ لِلَّهِ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۗ أَلَآ إِنَّ وَعۡدَ ٱللَّهِ حَقٌّ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَهُمۡ لَا يَعۡلَمُونَ ٥٥
Alaaa inna lillaahi maa fis samaawaati wal ard; alaaa inna wa`dal laahi haqqunw wa laakinna aksarahum laa ya`lamoon
ንቁ! በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነው፡፡ ንቁ! የአላህ ተስፋ ቃል እርግጥ ነው፡፡ ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡
🎤 Your recording:
10:56
🔁 0/5
هُوَ يُحۡيِۦ وَيُمِيتُ وَإِلَيۡهِ تُرۡجَعُونَ ٥٦
Huwa yuhyee wa yumeetu wailaihi turja`oon
እርሱ ሕያው ያደርጋል፤ ይገድላልም ወደ እርሱም ትመለሳላችሁ፡፡
🎤 Your recording:
10:57
🔁 0/5
يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ قَدۡ جَآءَتۡكُم مَّوۡعِظَةٌ مِّن رَّبِّكُمۡ وَشِفَآءٌ لِّمَا فِي ٱلصُّدُورِ وَهُدًى وَرَحۡمَةٌ لِّلۡمُؤۡمِنِينَ ٥٧
Yaaa aiyuhan naasu qad jaaa`atkum maw `izatum mir Rabbikum wa shifaaa`ul limaa fis sudoori wa hudanw wa rahmatul lilmu`mineen
እናንተ ሰዎች ሆይ! ከጌታችሁ ግሳጼ በደረቶች ውስጥም ላለው (የመጠራጠር በሽታ) መድኃኒት ለምእምናንም ብርሃንና እዝነት በእርግጥ መጣችላችሁ፡፡
🎤 Your recording:
10:58
🔁 0/5
قُلۡ بِفَضۡلِ ٱللَّهِ وَبِرَحۡمَتِهِۦ فَبِذَٰلِكَ فَلۡيَفۡرَحُواْ هُوَ خَيۡرٌ مِّمَّا يَجۡمَعُونَ ٥٨
Qul bifadlil laahi wa birahmatihii fabizaalika falyaf rahoo huwa khairum mimmaa yajma`oon
«በአላህ ችሮታና በእዝነቱ (ይደሰቱ)፡፡ በዚህም ምክንያት ይደሰቱ፡፡ እርሱ ከሚሰበስቡት ሀብት በላጭ ነው» በላቸው፡፡
🎤 Your recording:
10:59
🔁 0/5
قُلۡ أَرَءَيۡتُم مَّآ أَنزَلَ ٱللَّهُ لَكُم مِّن رِّزۡقٍ فَجَعَلۡتُم مِّنۡهُ حَرَامًا وَحَلَٰلًا قُلۡ ءَآللَّهُ أَذِنَ لَكُمۡۖ أَمۡ عَلَى ٱللَّهِ تَفۡتَرُونَ ٥٩
Qul ara`aitum maaa anzalal laahu lakum mir rizqin faja`altum minhu haraamanw wa halaalan qul aaallaahu azina lakum am `alal laahi taftaroon
«አላህ ከሲሳይ ለእናንተ ያወረደውን ከእርሱም እርምና የተፈቀደ ያደረጋችሁትን አያችሁን» በላቸው፡፡ «አላህ (ይህንን) ለእናንተ ፈቀደላችሁን ወይስ በአላህ ላይ ትቀጣጥፋላችሁ» በላቸው፡፡
🎤 Your recording:
10:60
🔁 0/5
وَمَا ظَنُّ ٱلَّذِينَ يَفۡتَرُونَ عَلَى ٱللَّهِ ٱلۡكَذِبَ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِۗ إِنَّ ٱللَّهَ لَذُو فَضۡلٍ عَلَى ٱلنَّاسِ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَهُمۡ لَا يَشۡكُرُونَ ٦٠
Wa maa zannul lazeena yaftaroona `alal laahil kaziba Yawmal Qiyaamah; innal laaha lazoo fadlin `alan naasi wa laakinna aksarahum laa yashkuroon
የእነዚያም በአላህ ላይ ውሸትን የሚቀጣጥፉ (ሰዎች) በትንሣኤ ቀን (በአላህ) ጥርጣሬያቸው ምንድን ነው (አይቀጡም ይመስላቸዋልን) አላህ በሰዎች ላይ (ቅጣትን ባለማቻኮል) የልግስና ባለቤት ነው፡፡ ግን አብዛኛዎቹ አያመሰግኑም፡፡
🎤 Your recording:
10:61
🔁 0/5
وَمَا تَكُونُ فِي شَأۡنٍ وَمَا تَتۡلُواْ مِنۡهُ مِن قُرۡءَانٍ وَلَا تَعۡمَلُونَ مِنۡ عَمَلٍ إِلَّا كُنَّا عَلَيۡكُمۡ شُهُودًا إِذۡ تُفِيضُونَ فِيهِۚ وَمَا يَعۡزُبُ عَن رَّبِّكَ مِن مِّثۡقَالِ ذَرَّةٍ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَلَا فِي ٱلسَّمَآءِ وَلَآ أَصۡغَرَ مِن ذَٰلِكَ وَلَآ أَكۡبَرَ إِلَّا فِي كِتَٰبٍ مُّبِينٍ ٦١
Wa maa takoonu fee shaaninw wa maa tatloo minhu min quraaninw wa laa ta`maloona min `amalin illaa kunnaa `alaikum shuhoodan iz tufeedoona feeh; wa maa ya`zubu `ar Rabbika mim mis qaali zarratin fil ardi wa laa fis samaaa`i wa laaa asghara min zaalika wa laaa akbara illaa fee Kitaabim Mubeen
(ሙሐመድ ሆይ!) በማንኛውም ነገር ላይ አትሆንም፣ ከርሱም ከቁርኣን አታነብም፣ ማንኛውንም ሥራ (አንተም ሰዎቹም) አትሠሩም በገባችሁበት ጊዜ በናንተ ላይ ተጠባባቂዎች ብንሆን እንጂ፡፡ በምድርም ሆነ በሰማይ የብናኝ ክብደት ያክል ከጌታህ (ዕውቀት) አይርቅም፡፡ ከዚያም ያነሰ የተለቀም የለም፤ በግልጹ መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈ ቢሆን እንጂ፡፡
🎤 Your recording:
10:62
🔁 0/5
أَلَآ إِنَّ أَوۡلِيَآءَ ٱللَّهِ لَا خَوۡفٌ عَلَيۡهِمۡ وَلَا هُمۡ يَحۡزَنُونَ ٦٢
Alaa innaa awliyaaa`al laahi laa khawfun `alaihim wa laa hum yahzanoon
ንቁ! የአላህ ወዳጆች በእነሱ ላይ ፍርሃት የለባቸውም፤ እነሱም አያዝኑም፡፡
🎤 Your recording:
10:63
🔁 0/5
ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَكَانُواْ يَتَّقُونَ ٦٣
Allazeena aamanoo wa kaanoo yattaqoon
(እነሱም) እነዚያ ያመኑትና ይፈሩት የነበሩ ናቸው፡፡
🎤 Your recording:
10:64
🔁 0/5
لَهُمُ ٱلۡبُشۡرَىٰ فِي ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا وَفِي ٱلۡأٓخِرَةِۚ لَا تَبۡدِيلَ لِكَلِمَٰتِ ٱللَّهِۚ ذَٰلِكَ هُوَ ٱلۡفَوۡزُ ٱلۡعَظِيمُ ٦٤
Lahumul bushraa filha yaatid dunyaa wa fil Aakhirah; laa tabdeela likalimaatil laah; zaalika huwal fawzul `azeem
ለእነሱ በቅርቢቱ ሕይወትም በመጨረሻይቱም ብስራት አላቸው፤ የአላህ ቃላት መለወጥ የላትም፤ ይህ እርሱ ታላቅ ዕድል ነው፡፡
🎤 Your recording:
10:65
🔁 0/5
وَلَا يَحۡزُنكَ قَوۡلُهُمۡۘ إِنَّ ٱلۡعِزَّةَ لِلَّهِ جَمِيعًاۚ هُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡعَلِيمُ ٦٥
Wa laa yahzunka qawluhum; innal `izzata lillaahi jamee`aa; Huwas Samee`ul `Aleem
ንግግራቸውም አያሳዝንህ፡፡ ኀይል ሁሉ በሙሉ የአላህ ብቻ ነውና፡፡ እርሱ ሰሚው ዐዋቂው ነው፡፡
🎤 Your recording:
10:66
🔁 0/5
أَلَآ إِنَّ لِلَّهِ مَن فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَن فِي ٱلۡأَرۡضِۗ وَمَا يَتَّبِعُ ٱلَّذِينَ يَدۡعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ شُرَكَآءَۚ إِن يَتَّبِعُونَ إِلَّا ٱلظَّنَّ وَإِنۡ هُمۡ إِلَّا يَخۡرُصُونَ ٦٦
Alaaa inna lillaahi man fis samaawaati wa man fil ard; wa maa yattabi`ul lazeena yad`oona min doonil laahi shurakaaa`; iny yattabi`oona illaz zannna wa in hum illaa yakhrusoon
ንቁ! በሰማያት ያሉትና በምድርም ያሉት ሁሉ በእርግጥ የአላህ ናቸው፤ እነዚያ ከአላህ ሌላ ተጋሪዎችን የሚጠሩ ምንን ይከተላሉ ጥርጣሬን እንጂ ሌላ አይከተሉም፡፡ እነርሱም የሚዋሹ እንጂ አይደሉም፡፡
🎤 Your recording:
10:67
🔁 0/5
هُوَ ٱلَّذِي جَعَلَ لَكُمُ ٱلَّيۡلَ لِتَسۡكُنُواْ فِيهِ وَٱلنَّهَارَ مُبۡصِرًاۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٍ لِّقَوۡمٍ يَسۡمَعُونَ ٦٧
Huwal lazee ja`ala lakumul laila litaskunoo feehi wannahaara mubsiraa; inna fee zaalika la Aayaatil liqawmai yasma`oon
እርሱ ያ ሌሊትን በውስጡ ልታርፉበት (ጨለማ)፤ ቀንንም (ልትሠሩበት) ብርሃን ያደረገላችሁ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚሰሙ ሕዝቦች በእርግጥ ታምራቶች አሉ፡፡
🎤 Your recording:
10:68
🔁 0/5
قَالُواْ ٱتَّخَذَ ٱللَّهُ وَلَدًاۗ سُبۡحَٰنَهُۥۖ هُوَ ٱلۡغَنِيُّۖ لَهُۥ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِۚ إِنۡ عِندَكُم مِّن سُلۡطَٰنِۭ بِهَٰذَآۚ أَتَقُولُونَ عَلَى ٱللَّهِ مَا لَا تَعۡلَمُونَ ٦٨
Qaalut takhazal laahu waladan Subhaanahoo Huwal Ghaniyyu lahoo maa fis samaawaati wa maa fil ard; in `indakum min sultaanim bihaazaaa; ataqooloona `alal laahi maa laa ta`lamoon
«አላህ ልጅን ያዘ (ወለደ)» አሉ፡፡ (ከሚሉት) ጥራት ተገባው፡፡ እርሱ ተብቃቂ ነው፡፡ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የርሱ ነው፡፡ እናንተ ዘንድ በዚህ (በምትሉት) ምንም አስረጅ የላችሁም፡፡ በአላህ ላይ የማታውቁትን ትናገራላችሁን
🎤 Your recording:
10:69
🔁 0/5
قُلۡ إِنَّ ٱلَّذِينَ يَفۡتَرُونَ عَلَى ٱللَّهِ ٱلۡكَذِبَ لَا يُفۡلِحُونَ ٦٩
Qul innal lazeena yaftaroona `alal laahil kaziba laa yuflihoon
«እነዚያ በአላህ ላይ ውሸትን የሚቀጣጥፉ ፈጽሞ አይድኑም፤» በላቸው፡፡
🎤 Your recording:
10:70
🔁 0/5
مَتَٰعٌ فِي ٱلدُّنۡيَا ثُمَّ إِلَيۡنَا مَرۡجِعُهُمۡ ثُمَّ نُذِيقُهُمُ ٱلۡعَذَابَ ٱلشَّدِيدَ بِمَا كَانُواْ يَكۡفُرُونَ ٧٠
Mataa`un fiddunyaa summa ilainaa marji`uhum summa nuzeequhumul `azaabash shadeeda bimaa kaanoo yakkfuroon
(እነሱ) በቅርቢቱ ዓለም መጠቀም አላቸው፡፡ ከዚያም መመለሻቸው ወደእኛ ነው፡፡ ከዚያም ይክዱ በነበሩት ምክንያት ብርቱን ቅጣት እናቀምሳቸዋለን፡፡
🎤 Your recording:
10:71
🔁 0/5
۞ وَٱتۡلُ عَلَيۡهِمۡ نَبَأَ نُوحٍ إِذۡ قَالَ لِقَوۡمِهِۦ يَٰقَوۡمِ إِن كَانَ كَبُرَ عَلَيۡكُم مَّقَامِي وَتَذۡكِيرِي بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ فَعَلَى ٱللَّهِ تَوَكَّلۡتُ فَأَجۡمِعُوٓاْ أَمۡرَكُمۡ وَشُرَكَآءَكُمۡ ثُمَّ لَا يَكُنۡ أَمۡرُكُمۡ عَلَيۡكُمۡ غُمَّةً ثُمَّ ٱقۡضُوٓاْ إِلَيَّ وَلَا تُنظِرُونِ ٧١
Watlu `alaihim naba-a-Noohin iz qaala liqawmihee yaa qawmi in kaana kabura `alaikum maqaamee wa tazkeeree bi Aayaatil laahi fa`alal laahi tawakkaltu fa ajmi`ooo amrakum wa shurakaaa`akum summa laa yakun amrukum `alaikum ghummatan summmaq dooo ilaiya wa laa tunziroon
የኑሕንም ወሬ በእነሱ ላይ አንብብላቸው፡፡ ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ «ሕዝቦቼ ሆይ! በእናንተ ውስጥ ብዙ ጊዜ መቆየቴ በአላህም ተዓምራት ማስታወሴ በእናንተ ላይ የከበደ ቢሆን፤ በአላህ ላይ ተጠግቻለሁ፡፡ ነገራችሁንም ከምታጋሩዋቸው (ጣዖታት) ጋር ሆናችሁ ቁረጡ፡፡ ከዚያም ነገራችሁ በእናንተ ላይ ድብቅ አይሁን (ግለጹት)፡፡ ከዚያም (የሻችሁትን) ወደእኔ አድርሱ፡፡ ጊዜም አትስጡኝ (ከምንም አልቆጥራችሁም)፡፡»
🎤 Your recording:
10:72
🔁 0/5
فَإِن تَوَلَّيۡتُمۡ فَمَا سَأَلۡتُكُم مِّنۡ أَجۡرٍۖ إِنۡ أَجۡرِيَ إِلَّا عَلَى ٱللَّهِۖ وَأُمِرۡتُ أَنۡ أَكُونَ مِنَ ٱلۡمُسۡلِمِينَ ٧٢
Fa in tawallaitum famaa sa altukum min ajrin in ajriya illaa `alal laahi wa umirtu an akoona minal muslimeen
«ብትሸሹም (አትጎዱኝም)፡፡ ከምንዳ ምንንም አልለምናችሁምና፡፡ ምንዳዬ በአላህ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይደለም፡፡ ከሙስሊሞች እንድሆንም ታዝዣለሁ፡፡»
🎤 Your recording:
10:73
🔁 0/5
فَكَذَّبُوهُ فَنَجَّيۡنَٰهُ وَمَن مَّعَهُۥ فِي ٱلۡفُلۡكِ وَجَعَلۡنَٰهُمۡ خَلَٰٓئِفَ وَأَغۡرَقۡنَا ٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَاۖ فَٱنظُرۡ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلۡمُنذَرِينَ ٧٣
Fakazzaboohu fanajjainaahu wa mamm`ahoo fil fulki wa ja`alnaahum khalaaa`ifa wa aghraqnal lazeena kazzaboo bi aayaatinaa fanzur kaifa kaana `aaqibatul munzareen
አስተባበሉትም፡፡ እርሱንና ከእርሱ ጋር የነበሩትንም በታንኳይቱ ውስጥ አዳንናቸው፡፡ (ለጠፉት) ምትኮችም አደረግናቸው፡፡ እነዚያንም በአንቀጾቻችን ያስተባበሉትን አሰጠምን፡፡ የተስፈራሩትም ሕዝቦች መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከት፡፡
🎤 Your recording:
10:74
🔁 0/5
ثُمَّ بَعَثۡنَا مِنۢ بَعۡدِهِۦ رُسُلًا إِلَىٰ قَوۡمِهِمۡ فَجَآءُوهُم بِٱلۡبَيِّنَٰتِ فَمَا كَانُواْ لِيُؤۡمِنُواْ بِمَا كَذَّبُواْ بِهِۦ مِن قَبۡلُۚ كَذَٰلِكَ نَطۡبَعُ عَلَىٰ قُلُوبِ ٱلۡمُعۡتَدِينَ ٧٤
Summma ba`asnaa mim ba`dihee Rusulan ilaa qawmihim fajaaa`oohum bilbaiyinaati famaa kaanoo liyu`minoo bimaa kazzaboo bihee min qabl; kazaalika natba`u `alaa quloobil mu`tadeen
ከዚያም ከእርሱ በኋላ መልክተኞችን ወደየሕዝቦቻቸው ላክን፡፡ በግልጽ ማስረጃዎችም መጧቸው፡፡ (ከመላካቸው) በፊት በእርሱ ባስተባበሉበትም ነገር፤ የሚያምኑ አልሆኑም፡፡ እንደዚሁ በወሰን አላፊዎች ልቦች ላይ እናትማለን፡፡
🎤 Your recording:
10:75
🔁 0/5
ثُمَّ بَعَثۡنَا مِنۢ بَعۡدِهِم مُّوسَىٰ وَهَٰرُونَ إِلَىٰ فِرۡعَوۡنَ وَمَلَإِيْهِۦ بِـَٔايَٰتِنَا فَٱسۡتَكۡبَرُواْ وَكَانُواْ قَوۡمًا مُّجۡرِمِينَ ٧٥
Summa ba`asnaa mim ba`dihim Moosaa Wa Haaroona ilaa Fir`awna wa mala`ihee bi aayaatinaa fastakbaroo wa kaanoo qawmam mujrimeen
ከዚያም ከእነሱ ኋላ ሙሳንና ሃሩንን ወደ ፈርዖንና ወደ መማክርቱ በተዓምራታችን ላክን፡፡ ኮሩም ትዕቢተኞች ሕዝቦችም ነበሩ፡፡
🎤 Your recording:
10:76
🔁 0/5
فَلَمَّا جَآءَهُمُ ٱلۡحَقُّ مِنۡ عِندِنَا قَالُوٓاْ إِنَّ هَٰذَا لَسِحۡرٌ مُّبِينٌ ٧٦
Falammaa jaaa`ahumul haqqu min `indinaa qaalooo inna haazaa lasihrum mubeen
ከእኛም ዘንድ እውነቱ በመጣላቸው ጊዜ «ይህ በእርግጥ ግልጽ ድግምት ነው» አሉ፡፡
🎤 Your recording:
10:77
🔁 0/5
قَالَ مُوسَىٰٓ أَتَقُولُونَ لِلۡحَقِّ لَمَّا جَآءَكُمۡۖ أَسِحۡرٌ هَٰذَا وَلَا يُفۡلِحُ ٱلسَّٰحِرُونَ ٧٧
Qaalaa Moosaaa ataqooloona lilhaqqi lammmaa jaaa`a kum asihrun haazaa wa laa yuflihus saabiroon
ሙሳ አለ፡- «እውነቱን በመጣላችሁ ጊዜ ድግምተኞች የማይድኑ ሲኾኑ (እርሱ ድግምት ነው) ትላላችሁን ይህ ድግምት ነውን»
🎤 Your recording:
10:78
🔁 0/5
قَالُوٓاْ أَجِئۡتَنَا لِتَلۡفِتَنَا عَمَّا وَجَدۡنَا عَلَيۡهِ ءَابَآءَنَا وَتَكُونَ لَكُمَا ٱلۡكِبۡرِيَآءُ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَمَا نَحۡنُ لَكُمَا بِمُؤۡمِنِينَ ٧٨
Qaaloo aji`tanaa litalfitanaa `ammaa wajadnaa `alaihi aabaaa`anaa wa takoona lakumal kibriyaaa`u fil ardi wa maa nahnu lakumaa bimu` mineen
(እነርሱም) አሉ፡- «አባቶቻችንን በእርሱ ላይ ካገኘንበት ሃይማኖት ልታዞረን ለእናንተም በምድር ውስጥ ኩራት (ሹመት) ልትኖራችሁ መጣህብን እኛም ለእናንተ አማኞች አይደለንም፡፡»
🎤 Your recording:
10:79
🔁 0/5
وَقَالَ فِرۡعَوۡنُ ٱئۡتُونِي بِكُلِّ سَٰحِرٍ عَلِيمٍ ٧٩
Wa qaala Fir`awnu` toonee bikulli saahirin `aleem
ፈርዖንም፡- «ዐዋቂ ድግምተኛን ሁሉ አምጡልኝ» አለ፡፡
🎤 Your recording:
10:80
🔁 0/5
فَلَمَّا جَآءَ ٱلسَّحَرَةُ قَالَ لَهُم مُّوسَىٰٓ أَلۡقُواْ مَآ أَنتُم مُّلۡقُونَ ٨٠
Falammaa jaaa`assa haratu qaala lahum Moosaaa alqoo maaa antum mulqoon
ድግምተኞቹም በመጡ ጊዜ ሙሳ ለእነርሱ፡- «እናንተ የምትጥሉትን ነገር ጣሉ» አላቸው፡፡
🎤 Your recording:
10:81
🔁 0/5
فَلَمَّآ أَلۡقَوۡاْ قَالَ مُوسَىٰ مَا جِئۡتُم بِهِ ٱلسِّحۡرُۖ إِنَّ ٱللَّهَ سَيُبۡطِلُهُۥٓ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُصۡلِحُ عَمَلَ ٱلۡمُفۡسِدِينَ ٨١
Falammaaa alqaw qaala Moosaa maa ji`tum bihis sihru innal laaha sa yubtiluhoo innal laaha laa yuslihu `amalal mufsideen
(ገመዶቻቸውን) በጣሉም ጊዜ ሙሳ አለ፡- «ያ በርሱ የመጣችሁበት ነገር ድግምት ነው፡፡ አላህ በእርግጥ ያፈርሰዋል፡፡ አላህ የአጥፊዎችን ሥራ ፈጽሞ አያበጅምና፡፡»
🎤 Your recording:
10:82
🔁 0/5
وَيُحِقُّ ٱللَّهُ ٱلۡحَقَّ بِكَلِمَٰتِهِۦ وَلَوۡ كَرِهَ ٱلۡمُجۡرِمُونَ ٨٢
Wa yuhiqqul laahul haqqa bi Kalimaatihee wa law karihal mujrimoon
አላህም ከሓዲዎች ቢጠሉም እውነትን በቃላቱ ያረጋግጣል፡፡
🎤 Your recording:
10:83
🔁 0/5
فَمَآ ءَامَنَ لِمُوسَىٰٓ إِلَّا ذُرِّيَّةٌ مِّن قَوۡمِهِۦ عَلَىٰ خَوۡفٍ مِّن فِرۡعَوۡنَ وَمَلَإِيْهِمۡ أَن يَفۡتِنَهُمۡۚ وَإِنَّ فِرۡعَوۡنَ لَعَالٍ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَإِنَّهُۥ لَمِنَ ٱلۡمُسۡرِفِينَ ٨٣
Famaaa aamana li-Moosaaa illaa zurriyyatum min qawmihee `alaa khawfim min Fir`awna wa mala`ihim ai yaftinahum; wa inna Fir`awna la`aalin fil ardi wa innahoo laminal musrifeen
ለሙሳም ከፈርዖንና ከሹማምንቶቻቸው ማሰቃየትን ከመፍራት ጋር ከወገኖቹ የኾኑ ጥቂቶች ትውልዶች እንጂ አላመኑለትም፡፡ ፈርዖንም በምድር ላይ በእርግጥ የኮራ ነበር፡፡ እርሱም በእርግጥ ወሰን ካለፉት ነበር፡፡
🎤 Your recording:
10:84
🔁 0/5
وَقَالَ مُوسَىٰ يَٰقَوۡمِ إِن كُنتُمۡ ءَامَنتُم بِٱللَّهِ فَعَلَيۡهِ تَوَكَّلُوٓاْ إِن كُنتُم مُّسۡلِمِينَ ٨٤
Wa qaala Moosaa yaa qawmi in kuntum aamantum billaahi fa`alaihi tawakkalooo in kuntum muslimeen
ሙሳም አለ፡- «ሕዝቦቼ ሆይ! በአላህ አምናችሁ እንደ ሆነ በርሱ ላይ ተጠጉ፡፡ ታዛዦች እንደ ሆናችሁ (በአላህ ላይ ትመካላችሁ)፡፡»
🎤 Your recording:
10:85
🔁 0/5
فَقَالُواْ عَلَى ٱللَّهِ تَوَكَّلۡنَا رَبَّنَا لَا تَجۡعَلۡنَا فِتۡنَةً لِّلۡقَوۡمِ ٱلظَّٰلِمِينَ ٨٥
Faqaaloo `alal laahi tawakkalnaa Rabbanaa laa taj`alnaa fitnatal lilqawmiz zaalimeen
አሉም፡- «በአላህ ላይ ተጠጋን፡፡ ጌታችን ሆይ! ለበደለኞች ሕዝቦች መፈተኛ አታድርገን፡፡»
🎤 Your recording:
10:86
🔁 0/5
وَنَجِّنَا بِرَحۡمَتِكَ مِنَ ٱلۡقَوۡمِ ٱلۡكَٰفِرِينَ ٨٦
Wa najjinaa birahmatika minal qawmil kaafireen
በእዝነትህም ከከሓዲዎች ሕዝቦች አድነን፡፡
🎤 Your recording:
10:87
🔁 0/5
وَأَوۡحَيۡنَآ إِلَىٰ مُوسَىٰ وَأَخِيهِ أَن تَبَوَّءَا لِقَوۡمِكُمَا بِمِصۡرَ بُيُوتًا وَٱجۡعَلُواْ بُيُوتَكُمۡ قِبۡلَةً وَأَقِيمُواْ ٱلصَّلَوٰةَۗ وَبَشِّرِ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ ٨٧
Wa awhainaaa ilaa Moosaa wa akheehi an tabaw wa aa liqawmikuma bi Misra bu yootanw waj`aloo bu yootakum qiblatanw wa aqeemus Salaah; wa bashshiril mu`mineen
ወደ ሙሳና ወደ ወንድሙ፡- «ለሕዝቦቻችሁ በምስር ቤቶችን ሥሩ፡፡ ቤቶቻችሁንም መስገጃ አድርጉ፡፡ ሶላትንም በደንቡ ስገዱ፡፡ (ለሙሳ) ምእምናኖቹንም አብስር» ስንል ላክን፡፡
🎤 Your recording:
10:88
🔁 0/5
وَقَالَ مُوسَىٰ رَبَّنَآ إِنَّكَ ءَاتَيۡتَ فِرۡعَوۡنَ وَمَلَأَهُۥ زِينَةً وَأَمۡوَٰلًا فِي ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا رَبَّنَا لِيُضِلُّواْ عَن سَبِيلِكَۖ رَبَّنَا ٱطۡمِسۡ عَلَىٰٓ أَمۡوَٰلِهِمۡ وَٱشۡدُدۡ عَلَىٰ قُلُوبِهِمۡ فَلَا يُؤۡمِنُواْ حَتَّىٰ يَرَوُاْ ٱلۡعَذَابَ ٱلۡأَلِيمَ ٨٨
Wa qaala Mosaa Rabbanaaa innaka aataita Fir`awna wa mala ahoo zeenatanw wa amwaalan fil hayaatid dunyaa Rabbanaa liyudillo `ansabeelika Rabbanat mis `alaaa amwaalihim washdud `alaa quloobihim falaa yu`minoo hatta yarawul `azaabal aleem
ሙሳም አለ፡- «ጌታችን ሆይ! አንተ ለፈርዖንና ለሹሞቹ በቅርቢቱ ሕይወት ጌጥን ብዙ ገንዘቦችንም በእርግጥ ሰጠህ፡፡ ጌታችን ሆይ! ከመንገድህ ያሳስቱ ዘንድ (ሰጠሃቸው)፡፡ ጌታችን ሆይ! ገንዘቦቻቸውን አጥፋ፡፡ በልቦቻቸውም ላይ አትም፡፡ አሳማሚን ቅጣት እስከሚያዩ አያምኑምና፡፡»
🎤 Your recording:
10:89
🔁 0/5
قَالَ قَدۡ أُجِيبَت دَّعۡوَتُكُمَا فَٱسۡتَقِيمَا وَلَا تَتَّبِعَآنِّ سَبِيلَ ٱلَّذِينَ لَا يَعۡلَمُونَ ٨٩
Qaala qad ujeebad da`watukumaa fastaqeemaa wa laa tattabi`aaanni sabeelal lazeena laaya`lamoon
(አላህም) «ጸሎታችሁ በእርግጥ ተሰምታለች፡፡ ቀጥም በሉ፡፡ የእነዚያንም የማያውቁትን ሰዎች መንገድ አትከተሉ» አላቸው፡፡
🎤 Your recording:
10:90
🔁 0/5
۞ وَجَٰوَزۡنَا بِبَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ ٱلۡبَحۡرَ فَأَتۡبَعَهُمۡ فِرۡعَوۡنُ وَجُنُودُهُۥ بَغۡيًا وَعَدۡوًاۖ حَتَّىٰٓ إِذَآ أَدۡرَكَهُ ٱلۡغَرَقُ قَالَ ءَامَنتُ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا ٱلَّذِيٓ ءَامَنَتۡ بِهِۦ بَنُوٓاْ إِسۡرَٰٓءِيلَ وَأَنَا۠ مِنَ ٱلۡمُسۡلِمِينَ ٩٠
Wa jaawaznaa bi Baneee Israaa`eelal bahra fa atba`ahum Fir`awnu wa junooduhoo baghyanw wa `adwan hattaaa izaaa adrakahul gharaqu qaala aamantu annnahoo laaa ilaaha illal lazeee aamanat bihee Banooo Israaa`eela wa ana minal muslimeen
የእስራኤልንም ልጆች ባሕሩን አሳለፍናቸው፡፡ ፈርዖንና ሰራዊቱም ወሰን ለማለፍና ለመበደል ተከተሏቸው፡፡ መስጠምም ባገኘው ጊዜ፡- «አመንኩ፡፡ እነሆ ከዚያ የእስራኤል ልጆች በርሱ ከአመኑበት በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ እኔም ከታዛዦቹ ነኝ» አለ፡፡
🎤 Your recording:
10:91
🔁 0/5
ءَآلۡـَٰٔنَ وَقَدۡ عَصَيۡتَ قَبۡلُ وَكُنتَ مِنَ ٱلۡمُفۡسِدِينَ ٩١
Aaal`aana wa qad `asaita qablu wa kunta minal mufsideen
ከአሁን በፊት በእርግጥ ያመጽክ ከአጥፊዎችም የነበርክ ስትሆን አሁን (አመንኩ ትላለህ)
🎤 Your recording:
10:92
🔁 0/5
فَٱلۡيَوۡمَ نُنَجِّيكَ بِبَدَنِكَ لِتَكُونَ لِمَنۡ خَلۡفَكَ ءَايَةًۚ وَإِنَّ كَثِيرًا مِّنَ ٱلنَّاسِ عَنۡ ءَايَٰتِنَا لَغَٰفِلُونَ ٩٢
Falyawma nunajjeeka bibadanika litakoona liman khalfaka Aayah; wa inna kaseeram minan naasi `an aayaatinaa laghaafiloon
ዛሬማ ከኋላህ ላሉት ተዓምር ትሆን ዘንድ በድን ሆነህ (ከባሕሩ) እናወጣሃለን (ተባለ)፡፡ ከሰዎችም ብዙዎቹ ከተዓምራታችን በእርግጥ ዘንጊዎች ናቸው፡፡
🎤 Your recording:
10:93
🔁 0/5
وَلَقَدۡ بَوَّأۡنَا بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ مُبَوَّأَ صِدۡقٍ وَرَزَقۡنَٰهُم مِّنَ ٱلطَّيِّبَٰتِ فَمَا ٱخۡتَلَفُواْ حَتَّىٰ جَآءَهُمُ ٱلۡعِلۡمُۚ إِنَّ رَبَّكَ يَقۡضِي بَيۡنَهُمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ فِيمَا كَانُواْ فِيهِ يَخۡتَلِفُونَ ٩٣
Wa laqad bawwaanaa Baneee Israaa`eela mubawwa-a sidqinw wa razaqnaahum minnat taiyibaati famakh talafoo hattaa jaaa`ahmul `ilm; inna Rabbaka yaqdee bainahum Yawmal Qiyaamati feemaa kaanoo feehi yakhtalifoon
የእስራኤልንም ልጆች ምስጉንን ስፍራ በእርግጥ አሰፈርናቸው፡፡ ከመልካም ሲሳዮችም ሰጠናቸው፡፡ ዕውቀትም (ቁርኣን) እስከመጣቸው ድረስ አልተለያዩም፡፡ ጌታህ በርሱ ይለያዩበት በነበሩት ነገር በትንሣኤ ቀን በመካከላቸው ይፈርዳል፡፡
🎤 Your recording:
10:94
🔁 0/5
فَإِن كُنتَ فِي شَكٍّ مِّمَّآ أَنزَلۡنَآ إِلَيۡكَ فَسۡـَٔلِ ٱلَّذِينَ يَقۡرَءُونَ ٱلۡكِتَٰبَ مِن قَبۡلِكَۚ لَقَدۡ جَآءَكَ ٱلۡحَقُّ مِن رَّبِّكَ فَلَا تَكُونَنَّ مِنَ ٱلۡمُمۡتَرِينَ ٩٤
Fa in kunta fee shakkim mimmaaa anzalnaaa ilaika fas`alil lazeena yaqra`oonal Kitaaba min qablik; laqad jaaa`akal haqqu mir Rabbika falaa takoonanna minal mumtareen
ወደ አንተም ካወረድነው በመጠራጠር ውስጥ ብትሆን እነዚያን ከአንተ በፊት መጽሐፉን የሚያነቡትን ጠይቅ፡፡ እውነቱ ከጌታህ ዘንድ በእርግጥ መጥቶልሃል፡፡ ከተጠራጣሪዎቹም አትሁን፡፡
🎤 Your recording:
10:95
🔁 0/5
وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ ٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ فَتَكُونَ مِنَ ٱلۡخَٰسِرِينَ ٩٥
Wa laa takoonanna minal lazeena kazzaboo bi Aayaatil laahi fatakoona minal khaasireen
ከእነዚያም የአላህን አንቀጾች ከአስተባበሉት አትሁን፡፡ ከከሳሪዎቹ ትሆናለህና፡፡
🎤 Your recording:
10:96
🔁 0/5
إِنَّ ٱلَّذِينَ حَقَّتۡ عَلَيۡهِمۡ كَلِمَتُ رَبِّكَ لَا يُؤۡمِنُونَ ٩٦
Innal lazeena haqqat `alaihim Kalimatu Rabbika laa yu`minoon
እነዚያ በእነርሱ ላይ የጌታህ ቃል የተረጋገጠባቸው አያምኑም፡፡
🎤 Your recording:
10:97
🔁 0/5
وَلَوۡ جَآءَتۡهُمۡ كُلُّ ءَايَةٍ حَتَّىٰ يَرَوُاْ ٱلۡعَذَابَ ٱلۡأَلِيمَ ٩٧
Wa law jaaa`at hum kullu Aayatin hattaa yarawul `azaabal aleem
ተዓምር ሁሉ ብትመጣላቸውም አሳማሚን ቅጣት እስከሚያዩ ድረስ (አያምኑም)፡፡
🎤 Your recording:
10:98
🔁 0/5
فَلَوۡلَا كَانَتۡ قَرۡيَةٌ ءَامَنَتۡ فَنَفَعَهَآ إِيمَٰنُهَآ إِلَّا قَوۡمَ يُونُسَ لَمَّآ ءَامَنُواْ كَشَفۡنَا عَنۡهُمۡ عَذَابَ ٱلۡخِزۡيِ فِي ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا وَمَتَّعۡنَٰهُمۡ إِلَىٰ حِينٍ ٩٨
Falaw laa kaanat qaryatun aamanat fanafa`ahaaa eemaanuhaaa illaa qawma Yoonusa lammaaa aamanoo kashafnaa `anhum `azaabal khizyi fil hayaatid dunyaa wa matta`naahum ilaa heen
(ከዩኑስ በፊት ካለፉት ከተሞች) ያመነችና እምነትዋ የጠቀማት ከተማ ለምን አልኖረችም ግን የዩኑስ ሕዝቦች ባመኑ ጊዜ በቅርቢቱ ሕይወት የውርደትን ቅጣት ከእነሱ ላይ አነሳንላቸው፡፡ እስከ ጊዜም ድረስ አጣቀምናቸው፡፡
🎤 Your recording:
10:99
🔁 0/5
وَلَوۡ شَآءَ رَبُّكَ لَأٓمَنَ مَن فِي ٱلۡأَرۡضِ كُلُّهُمۡ جَمِيعًاۚ أَفَأَنتَ تُكۡرِهُ ٱلنَّاسَ حَتَّىٰ يَكُونُواْ مُؤۡمِنِينَ ٩٩
Wa law shaaa`a Rabbuka la aamana man fil ardi kulluhum jamee`aa; afa anta tukrihun naasa hattaa yakoonoo mu`mineen
ጌታህም በሻ ኖሮ በምድር ያሉት ሰዎች ሁሉም የተሰበሰቡ ሆነው ባመኑ ነበር፡፡ ታዲያ አንተ ሰዎችን አማኞች እንዲኾኑ ታስገድዳለህን
🎤 Your recording:
10:100
🔁 0/5
وَمَا كَانَ لِنَفۡسٍ أَن تُؤۡمِنَ إِلَّا بِإِذۡنِ ٱللَّهِۚ وَيَجۡعَلُ ٱلرِّجۡسَ عَلَى ٱلَّذِينَ لَا يَعۡقِلُونَ ١٠٠
Wa maa kaana linafsin an tu`mina illaa bi iznil laah; wa yaj`alur rijsa `alal lazeena laa ya`qiloon
ለማንኛዋም ነፍስ በአላህ ፈቃድ ቢሆን እንጂ ልታምን (ችሎታ) የላትም፡፡ (አላህ ለከፊሎቹ እምነትን ይሻል)፡፡ በእነዚያም በማያውቁት ላይ ርክሰትን ያደርጋል፡፡
🎤 Your recording:
10:101
🔁 0/5
قُلِ ٱنظُرُواْ مَاذَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ وَمَا تُغۡنِي ٱلۡأٓيَٰتُ وَٱلنُّذُرُ عَن قَوۡمٍ لَّا يُؤۡمِنُونَ ١٠١
Qulin zuroo maazaa fissamaawaati wal ard; wa maa tughnil Aayaatu wannuzuru `an qawmil laa yu`minoon
«በሰማያትና በምድር ያለውን (ተዓምር) ተመልከቱ» በላቸው፡፡ ተዓምራቶችና አስፈራሪዎችም ለማያምኑ ሕዝቦች አይጠቅሙም፡፡
🎤 Your recording:
10:102
🔁 0/5
فَهَلۡ يَنتَظِرُونَ إِلَّا مِثۡلَ أَيَّامِ ٱلَّذِينَ خَلَوۡاْ مِن قَبۡلِهِمۡۚ قُلۡ فَٱنتَظِرُوٓاْ إِنِّي مَعَكُم مِّنَ ٱلۡمُنتَظِرِينَ ١٠٢
Fahal yantaziroona illaa misla ayyaamil lazeena khalaw min qablihim; qul fantazirooo innee ma`akum minal muntazireen
የእነዚያን ከእነሱ በፊት ያለፉትን ሕዝቦች ቀኖች ብጤ እንጂ ሌላን ይጠባበቃሉን «ተጠባበቁ፤ እኔ ከናንተ ጋር ከሚጠባበቁት ነኝ» በላቸው፡፡
🎤 Your recording:
10:103
🔁 0/5
ثُمَّ نُنَجِّي رُسُلَنَا وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْۚ كَذَٰلِكَ حَقًّا عَلَيۡنَا نُنجِ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ ١٠٣
Summma nunajjee Ruslanaa wallazeena aamanoo; kazaalika haqqan `alainaa nunjil mu`mineen
ከዚያም መልክተኞቻችንን እነዚያንም ያመኑትን እናድናለን፡፡ እንደዚሁም ምእምናንን (ከጭንቅ ሁሉ) እናድናለን፡፡ (ይህ) በእኛ ላይ ተረጋገጠ፡፡
🎤 Your recording:
10:104
🔁 0/5
قُلۡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ إِن كُنتُمۡ فِي شَكٍّ مِّن دِينِي فَلَآ أَعۡبُدُ ٱلَّذِينَ تَعۡبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ وَلَٰكِنۡ أَعۡبُدُ ٱللَّهَ ٱلَّذِي يَتَوَفَّىٰكُمۡۖ وَأُمِرۡتُ أَنۡ أَكُونَ مِنَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ ١٠٤
Qul yaaa ayyuhan naasu in kuntum fee shakkkim min deenee falaa a`budul lazeena ta`budoona min doonil laahi wa laakin a`budul laahal lazee yatawaffaakum wa umirtu an akoona minal mu`mineen
«እናንተ ሰዎች ሆይ! ከእኔ ሃይማኖት በመጠራጠር ውስጥ ብትሆኑ እነዚያን ከአላህ ሌላ የምትገዟቸውን አልገዛም፡፡ ግን ያንን የሚገድላችሁን አላህን እገዛለሁ፡፡ ከምእምናን እንድሆንም ታዝዣለሁ» በላቸው፡፡
🎤 Your recording:
10:105
🔁 0/5
وَأَنۡ أَقِمۡ وَجۡهَكَ لِلدِّينِ حَنِيفًا وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ ٱلۡمُشۡرِكِينَ ١٠٥
Wa an aqim wajhaka liddeeni Haneefanw wa laa takoonannna minal mushrikeen
ፊትህንም (ወደ ቀጥታ) ያዘነበልክ ስትሆን ለሃይማኖት ቀጥ አድርግ፡፡ ከአጋሪዎቹም አትሁን፡፡
🎤 Your recording:
10:106
🔁 0/5
وَلَا تَدۡعُ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَا لَا يَنفَعُكَ وَلَا يَضُرُّكَۖ فَإِن فَعَلۡتَ فَإِنَّكَ إِذًا مِّنَ ٱلظَّٰلِمِينَ ١٠٦
Wa laa tad`u min doonil laahi maa laa yanfa`uka wa laa yadurruka fa in fa`alta fa innaka izam minaz zaalimeen
«ከአላህም በቀር የማይጠቅምንና የማይጎዳን አትገዛ፡፡ ብትሠራም አንተ ያንጊዜ ከበደለኞቹ ትሆናለህ» (ተብያለሁ በላቸው)፡፡
🎤 Your recording:
10:107
🔁 0/5
وَإِن يَمۡسَسۡكَ ٱللَّهُ بِضُرٍّ فَلَا كَاشِفَ لَهُۥٓ إِلَّا هُوَۖ وَإِن يُرِدۡكَ بِخَيۡرٍ فَلَا رَآدَّ لِفَضۡلِهِۦۚ يُصِيبُ بِهِۦ مَن يَشَآءُ مِنۡ عِبَادِهِۦۚ وَهُوَ ٱلۡغَفُورُ ٱلرَّحِيمُ ١٠٧
Wa iny yamsaskal laahu bidurrin falaa kaashifa lahoo illaa Huwa wa iny yuridka bikhairin falaa raaadda lifadlih; yuseebu bihee man yashaaa`u min `ibaadih; wa huwal Ghafoorur Raheem
አላህም ጉዳትን ቢያደርስብህ ከእርሱ ሌላ ለእርሱ ገላጭ የለውም፡፡ በጎንም ነገር ቢሻልህ ለችሮታው መላሽ የለም፡፡ ከባሮቹ የሚሻውን በእርሱ ይለይበታል፡፡ እርሱም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡
🎤 Your recording:
10:108
🔁 0/5
قُلۡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ قَدۡ جَآءَكُمُ ٱلۡحَقُّ مِن رَّبِّكُمۡۖ فَمَنِ ٱهۡتَدَىٰ فَإِنَّمَا يَهۡتَدِي لِنَفۡسِهِۦۖ وَمَن ضَلَّ فَإِنَّمَا يَضِلُّ عَلَيۡهَاۖ وَمَآ أَنَا۠ عَلَيۡكُم بِوَكِيلٍ ١٠٨
Qul yaaa aiyuhan naasu qad jaaa`akumul haqqu mir Rabbikum famanih tadaa fa innamaa yahtadee linafsihee wa man dalla fa innamaa yadillu `alaihaa wa maaa ana `alaikum biwakeel
«እናንተ ሰዎች ሆይ! እውነቱ ከጌታችሁ በእርግጥ መጣላችሁ፡፡ (በእርሱ) የተመራም ሰው የሚመራው ለራሱ ነው፡፡ የተሳሳተም ሰው የሚሳሳተው (ጉዳቱ) በራሱ ላይ ነው፡፡ እኔም በእናንተ ላይ ተጠባበቂ አይደለሁም» በላቸው፡፡
🎤 Your recording:
10:109
🔁 0/5
وَٱتَّبِعۡ مَا يُوحَىٰٓ إِلَيۡكَ وَٱصۡبِرۡ حَتَّىٰ يَحۡكُمَ ٱللَّهُۚ وَهُوَ خَيۡرُ ٱلۡحَٰكِمِينَ ١٠٩
Qattabi` maa yoohaaa ilaika wasbir hattaa yahkumal laah; wa Huwa khairul haakimeen
ወዳንተም የሚወረደውን ነገር ተከተል፡፡ አላህም (በነሱ ላይ) እስከሚፈርድ ድረስ ታገስ፡፡ እርሱም ከፈራጆቹ ሁሉ በላጭ ነው፡፡
🎤 Your recording:
💡 Tap any hidden word to reveal it temporarily — your progress is saved automatically in this browser.
العربيةEnglishBahasa IndonesiaTürkçeРусскийفارسیFrançaisاردوবাংলাDeutschEspañol中文हिन्दीPortuguêsItalianoภาษาไทยPolskiNederlandsShqipKiswahiliO'zbekதமிழ்MelayuBosanskiSoomaaliAzərbaycanکوردی한국어日本語SvenskaDanskNorskپښتوമലയാളംසිංහලTamazightHausaአማርኛБългарскиТоҷикӣҚазақшаFilipinoسنڌيYorùbáFulfuldeТатарчаئۇيغۇرچەКыргызчаਪੰਜਾਬੀJawaతెలుగుမြန်မာગુજરાતીOromoमराठीTiếng ViệtMalagasyНохчийнWolofދިވެހިಕನ್ನಡУкраїнськаΕλληνικάქართულიខ្មែរدریQafar afMaranaoनेपाली
ቅዱስ ቁርኣን
Tuesday, August 18, 2026
Don't forget us in your sincere prayers







