🔥 0 day streak
📖 Long surah — split into smaller parts to help you focus (60 አንቀጽ)
📚 All Surahs
30%
🎤 Tap the microphone icon 🎙️ next to any verse to record yourself reciting it, then listen back and compare with the reciter.
0/60
30:1 🔁 0/5
الٓمٓ  ۝١
Alif-Laaam-Meeem
አ.ለ.መ (አሊፍ ላም ሚም)፡፡
🎤 Your recording:
30:2 🔁 0/5
غُلِبَتِ ٱلرُّومُ  ۝٢
Ghulibatir Room
ሩም ተሸነፈች፡፡
🎤 Your recording:
30:3 🔁 0/5
فِيٓ أَدۡنَى ٱلۡأَرۡضِ وَهُم مِّنۢ بَعۡدِ غَلَبِهِمۡ سَيَغۡلِبُونَ  ۝٣
Feee adnal ardi wa hummim ba`di ghalabihim sa ya ghliboon
በጣም ቅርብ በሆነችው ምድር፡፡ እነርሱም ከመሸነፋቸው በኋላ በእርግጥ ያሸንፋሉ፡፡
🎤 Your recording:
30:4 🔁 0/5
فِي بِضۡعِ سِنِينَۗ لِلَّهِ ٱلۡأَمۡرُ مِن قَبۡلُ وَمِنۢ بَعۡدُۚ وَيَوۡمَئِذٍ يَفۡرَحُ ٱلۡمُؤۡمِنُونَ  ۝٤
Fee bid`i sineen; lillaahil amru min qablu wa mim ba`d; wa yawma`iziny yafrahul mu`minoon
በጥቂት ዓመታት ውስጥ (ያሸንፋሉ)፡፡ ትዕዛዙ በፊትም በኋላም የአላህ ነው፡፡ በዚያ ቀንም ምእመናን ይደሰታሉ፡፡
🎤 Your recording:
30:5 🔁 0/5
بِنَصۡرِ ٱللَّهِۚ يَنصُرُ مَن يَشَآءُۖ وَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلرَّحِيمُ  ۝٥
Binasril laa; yansuru mai yashaaa`u wa Huwal `Azeezur Raheem
በአላህ እርዳታ (ይደሰታሉ)፡፡ የሚሻውን ሰው ይረዳል፤ እርሱም አሸናፊው አዛኙ ነው፡፡
🎤 Your recording:
30:6 🔁 0/5
وَعۡدَ ٱللَّهِۖ لَا يُخۡلِفُ ٱللَّهُ وَعۡدَهُۥ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعۡلَمُونَ  ۝٦
Wa`dal laahi laa yukhliful laahu wa`dahoo wa laakin na aksaran naasi laa ya`lamoon
አላህ እርዳታን ቀጠረ፡፡ አላህ ቀጠሮውን አያፈርስም፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም፡፡
🎤 Your recording:
30:7 🔁 0/5
يَعۡلَمُونَ ظَٰهِرًا مِّنَ ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا وَهُمۡ عَنِ ٱلۡأٓخِرَةِ هُمۡ غَٰفِلُونَ  ۝٧
Ya`lamoona zaahiram minal hayaatid dunya wa hum `anil Aakhirati hum ghaafiloon
ከቅርቢቱ ህይወት ግልጹን ብቻ ያውቃሉ፡፡ እነርሱም ከኋለኛይቱ ዓለም እነርሱ ዘንጊዎች ናቸው፡፡
🎤 Your recording:
30:8 🔁 0/5
أَوَلَمۡ يَتَفَكَّرُواْ فِيٓ أَنفُسِهِمۗ مَّا خَلَقَ ٱللَّهُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ وَمَا بَيۡنَهُمَآ إِلَّا بِٱلۡحَقِّ وَأَجَلٍ مُّسَمًّىۗ وَإِنَّ كَثِيرًا مِّنَ ٱلنَّاسِ بِلِقَآيِٕ رَبِّهِمۡ لَكَٰفِرُونَ  ۝٨
Awalam yatafakkaroo feee anfusihim; maa khalaqal laahus samaawaati wal arda wa maa bainahumaaa illaa bil haqqi wa ajalim musammaa; wa inna kaseeram minan naasi biliqaaa`i Rabbihim lakaafiroon
በነፍሶቻቸው (ሁኔታ) አያስተውሉምን? ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ አላህ በእውነትና በተወሰነ ጊዜ እንጂ አልፈጠራቸውም፡፡ ከሰዎቹም ብዙዎቹ በጌታቸው መገናኘት ከሓዲዎች ናቸው፡፡
🎤 Your recording:
30:9 🔁 0/5
أَوَلَمۡ يَسِيرُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ فَيَنظُرُواْ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡۚ كَانُوٓاْ أَشَدَّ مِنۡهُمۡ قُوَّةً وَأَثَارُواْ ٱلۡأَرۡضَ وَعَمَرُوهَآ أَكۡثَرَ مِمَّا عَمَرُوهَا وَجَآءَتۡهُمۡ رُسُلُهُم بِٱلۡبَيِّنَٰتِۖ فَمَا كَانَ ٱللَّهُ لِيَظۡلِمَهُمۡ وَلَٰكِن كَانُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ يَظۡلِمُونَ  ۝٩
Awalm yaseeroo fil ardi fa-yanzuroo kaifa kaana `aaqibatul lazeena min qablihim; kaanooo ashadda minhhum quwwatanw wa asaarul arda wa `amaroohaaa aksara mimmaa `amaroohaa wa jaaa`athum Rusuluhum bil baiyinaati famaa kaanal laahu liyazli mahum wa laakin kaanooo anfusahum yazlimoon
በምድር ላይ አይኼዱምና የእነዚያን ከበፊታቸው የነበሩትን ሰዎች ፍጻሜ እንዴት እንደነበረ አይመለከቱምን? በኀይል ከእነርሱም ይበልጥ የጠነከሩ ነበሩ፡፡ ምድርንም አረሱ፡፡ (እነዚህ) ከአለሟትም የበዛ አለሟት፡፡ መልዕክተ ኞቻቸውም በተዓምራቶች መጡባቸው፤ (አስተባበሉምና ጠፉ)፡፡ አላህም የሚበድላቸው አልነበረም፤ ግን ነፍሶቻቸውን ይበድሉ ነበሩ፡፡
🎤 Your recording:
30:10 🔁 0/5
ثُمَّ كَانَ عَٰقِبَةَ ٱلَّذِينَ أَسَٰٓـُٔواْ ٱلسُّوٓأَىٰٓ أَن كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ وَكَانُواْ بِهَا يَسۡتَهۡزِءُونَ  ۝١٠
Summa kaana`aaqibatal lazeena asaaa`us sooo aaa an kazzaboo bi aayaatil laahi wa kaanoo bihaa yastahzi`oon
ከዚያም የእነዚያ ያጠፉት ሰዎች መጨረሻ በአላህ አንቀጾች በማስተባበላቸውና በእርሷ የሚሳለቁ በመኾናቸው ምክንያት መጥፎ ቅጣት ሆነች፡፡
🎤 Your recording:
30:11 🔁 0/5
ٱللَّهُ يَبۡدَؤُاْ ٱلۡخَلۡقَ ثُمَّ يُعِيدُهُۥ ثُمَّ إِلَيۡهِ تُرۡجَعُونَ  ۝١١
Allaahu yabda`ul khalqa summa yu`eeduhoo summa ilaihi turja`oon
አላህ መፍጠርን ይጀምራል፡፡ ከዚያም ይመልሰዋል፤ ከዚያም ወደርሱ ትመለሳላችሁ፡፡
🎤 Your recording:
30:12 🔁 0/5
وَيَوۡمَ تَقُومُ ٱلسَّاعَةُ يُبۡلِسُ ٱلۡمُجۡرِمُونَ  ۝١٢
Wa yawma taqoomus Saa`atu yublisul mujrimoon
ሰዓቲቱም በምትቆምበት ቀን አመጸኞች ጭጭ ይላሉ፡፡
🎤 Your recording:
30:13 🔁 0/5
وَلَمۡ يَكُن لَّهُم مِّن شُرَكَآئِهِمۡ شُفَعَٰٓؤُاْ وَكَانُواْ بِشُرَكَآئِهِمۡ كَٰفِرِينَ  ۝١٣
Wa lam yakul lahum min shurakaaa`ihim shufa`aaa`u wa kaanoo bishurakaaa`ihim kaafireen
ለእነርሱም ከሚያጋሩዋቸው (ጣዖታት) አማላጆች አይኖሯቸውም፤ በሚያጋሯቸውም (ጣዖታት) ከሓዲዎች ይኾናሉ፡፡
🎤 Your recording:
30:14 🔁 0/5
وَيَوۡمَ تَقُومُ ٱلسَّاعَةُ يَوۡمَئِذٍ يَتَفَرَّقُونَ  ۝١٤
Wa Yawma taqoomus Saa`atu Yawma`iziny yatafarraqoon
ሰዓቲቱ በምትቆምበት ቀንም በዚያ ቀን ይለያያሉ፡፡
🎤 Your recording:
30:15 🔁 0/5
فَأَمَّا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ فَهُمۡ فِي رَوۡضَةٍ يُحۡبَرُونَ  ۝١٥
Fa ammal lazeena aamanoo wa `amilus saalihaati fahum fee rawdatiny yuhbaroon
እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን ሥራዎች የሠሩትማ እነርሱ በገነት ጨፌ ውስጥ ይደሰታሉ፡፡
🎤 Your recording:
30:16 🔁 0/5
وَأَمَّا ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ وَكَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَا وَلِقَآيِٕ ٱلۡأٓخِرَةِ فَأُوْلَٰٓئِكَ فِي ٱلۡعَذَابِ مُحۡضَرُونَ  ۝١٦
Wa ammal lazeena kafaroo wa kazzaboo bi-Aayaatinaa wa liqaaa`il Aakhirati faulaaa`ika fil`azaabi muhdaroon
እነዚያም የካዱትማ በአንቀጾቻችንና በኋለኛይቱም ዓለም መገናኘት ያስተባበሉት እነዚያ በቅጣቱ ውስጥ የሚጣዱ ናቸው፡፡
🎤 Your recording:
30:17 🔁 0/5
فَسُبۡحَٰنَ ٱللَّهِ حِينَ تُمۡسُونَ وَحِينَ تُصۡبِحُونَ  ۝١٧
Fa Subhaanal laahi heena tumsoona wa heena tusbihoon
አላህንም በምታመሹ ጊዜ በምታነጉም ጊዜ አጥሩት፤ (ስገዱለት)፡፡
🎤 Your recording:
30:18 🔁 0/5
وَلَهُ ٱلۡحَمۡدُ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَعَشِيًّا وَحِينَ تُظۡهِرُونَ  ۝١٨
Wa lahul hamdu fis samaawaati wal ardi wa `ashiyyanw wa heena tuzhiroon
ምስጋናም በሰማያትና በምድር ውስጥ ለርሱ ብቻ (የተገባው) ነው፡፡ በሰርክም፤ በቀትር ውስጥ በምትገቡም ጊዜ፤ (አጥሩት)፡፡
🎤 Your recording:
30:19 🔁 0/5
يُخۡرِجُ ٱلۡحَيَّ مِنَ ٱلۡمَيِّتِ وَيُخۡرِجُ ٱلۡمَيِّتَ مِنَ ٱلۡحَيِّ وَيُحۡيِ ٱلۡأَرۡضَ بَعۡدَ مَوۡتِهَاۚ وَكَذَٰلِكَ تُخۡرَجُونَ  ۝١٩
Yukhrijul haiya minal maiyiti wa yukhrijul maiyita minal haiyi wa yuhyil arda ba`da mawtihaa; wa kazaalika tukhrajoon
ሕያውን ከሙት ያወጣል፡፡ ሙታንም ከሕያው ያወጣል፡፡ ምድርንም ከሞተች በኋላ ህያው ያደርጋታል፡፡ እንደዚሁም (ከመቃብር) ትወጣላችሁ፡፡
🎤 Your recording:
30:20 🔁 0/5
وَمِنۡ ءَايَٰتِهِۦٓ أَنۡ خَلَقَكُم مِّن تُرَابٍ ثُمَّ إِذَآ أَنتُم بَشَرٌ تَنتَشِرُونَ  ۝٢٠
Wa min Aayaatiheee an khalaqakum min turaabin summa izaaa antum basharun tantashiroon
እናንተንም ከዐፈር መፍጠሩ ከዚያም እናንተ ወዲያውኑ የምትበታተኑ ሰዎች መኾናችሁ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፡፡
🎤 Your recording:
30:21 🔁 0/5
وَمِنۡ ءَايَٰتِهِۦٓ أَنۡ خَلَقَ لَكُم مِّنۡ أَنفُسِكُمۡ أَزۡوَٰجًا لِّتَسۡكُنُوٓاْ إِلَيۡهَا وَجَعَلَ بَيۡنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحۡمَةًۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٍ لِّقَوۡمٍ يَتَفَكَّرُونَ  ۝٢١
Wa min Aayaatiheee an khalaqa lakum min anfusikum azwaajal litaskunooo ilaihaa wa ja`ala bainakum mawad datanw wa rahmah; inna fee zaalika la Aayaatil liqawminy yatafakkaroon
ለእናንተም ከነፍሶቻችሁ (ከጎሶቻችሁ) ሚስቶችን ወደእነርሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ፣ በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚያስተውሉ ሕዝቦች ተዓምራቶች አልሉ፡፡
🎤 Your recording:
30:22 🔁 0/5
وَمِنۡ ءَايَٰتِهِۦ خَلۡقُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَٱخۡتِلَٰفُ أَلۡسِنَتِكُمۡ وَأَلۡوَٰنِكُمۡۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٍ لِّلۡعَٰلِمِينَ  ۝٢٢
Wa min Aayaatihee khalqus samaawaati wal aardi wakhtilaafu alsinatikum wa alwaanikum; inna fee zaalika la Aayaatil lil`aalimeen
ሰማያትንና ምድርንም መፍጠሩ፣ የቋንቋዎቻችሁና የመልኮቻችሁም መለያየት፣ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለዐዋቂዎች ተዓምራቶች አልሉበት፡፡
🎤 Your recording:
30:23 🔁 0/5
وَمِنۡ ءَايَٰتِهِۦ مَنَامُكُم بِٱلَّيۡلِ وَٱلنَّهَارِ وَٱبۡتِغَآؤُكُم مِّن فَضۡلِهِۦٓۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٍ لِّقَوۡمٍ يَسۡمَعُونَ  ۝٢٣
Wa min Aayaatihee manaamukum bil laili wannahaari wabtighaaa`ukum min fadlih; inna fee zaalika la Aayaatil liqawminy yasma`oon
በሌሊትና በቀንም መተኛታችሁ፣ ከችሮታውም መፈለጋችሁ ከምልክቶቹ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚሰሙ ሕዝቦች ተዓምራቶች አልሉበት፡፡
🎤 Your recording:
30:24 🔁 0/5
وَمِنۡ ءَايَٰتِهِۦ يُرِيكُمُ ٱلۡبَرۡقَ خَوۡفًا وَطَمَعًا وَيُنَزِّلُ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءً فَيُحۡيِۦ بِهِ ٱلۡأَرۡضَ بَعۡدَ مَوۡتِهَآۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٍ لِّقَوۡمٍ يَعۡقِلُونَ  ۝٢٤
Wa min Aayaatihee yureekumul barqa khawfanw wa tama`anw wa yunazzilu minas samaaa`i maaa`an fa yuhyee bihil arda ba`da mawtihaaa inna fee zaalika la Aayaatil liqawminy ya`qiloon
ብልጭታንም ፈሪዎችና ከጃዮች ስትሆኑ ለእናንተ ማሳየቱ፣ ከሰማይም ውሃን ማውረዱ፣ በእርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ሕያው ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚያስቡ ሕዝቦች ተዓምራቶች አልሉበት፡፡
🎤 Your recording:
30:25 🔁 0/5
وَمِنۡ ءَايَٰتِهِۦٓ أَن تَقُومَ ٱلسَّمَآءُ وَٱلۡأَرۡضُ بِأَمۡرِهِۦۚ ثُمَّ إِذَا دَعَاكُمۡ دَعۡوَةً مِّنَ ٱلۡأَرۡضِ إِذَآ أَنتُمۡ تَخۡرُجُونَ  ۝٢٥
Wa min Aayaatihee an taqoomas samaaa`u wal ardu bi-amrih; summa izaa da`aakum da`watam minal ardi izaaa antum takhrujoon
ሰማይና ምድርም (ያለምሰሶ) በትዕዛዙ መቆማቸው፣ ከዚያም (መልአኩ ለትንሣኤ) ከምድር ጥሪን በጠራችሁ ጊዜ እናንተ ወዲያውኑ የምትወጡ መሆናችሁ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፡፡
🎤 Your recording:
30:26 🔁 0/5
وَلَهُۥ مَن فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۖ كُلٌّ لَّهُۥ قَٰنِتُونَ  ۝٢٦
Wa lahoo man fissamaawaati wal ardi kullul lahoo qaanitoon
በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው፡፡ ሁሉም ለእርሱ ታዛዦች ናቸው፡፡
🎤 Your recording:
30:27 🔁 0/5
وَهُوَ ٱلَّذِي يَبۡدَؤُاْ ٱلۡخَلۡقَ ثُمَّ يُعِيدُهُۥ وَهُوَ أَهۡوَنُ عَلَيۡهِۚ وَلَهُ ٱلۡمَثَلُ ٱلۡأَعۡلَىٰ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ وَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ  ۝٢٧
Wa Huwal lazee yabda`ul khalqa summa yu`eeduhoo wa huwa ahwanu `alaih; wa lahul masalul la`laa fissamaawaati wal-ard; wa Huwal `Azeezul Hakeem
እርሱም ያ መፍጠርን የሚጀምር ከዚያም የሚመልሰው ነው፡፡ እርሱም (መመለሱ) በእርሱ ላይ በጣም ገር ነው፡፡ ለእርሱም በሰማያትም በምድርም ከፍተኛ ባሕርይ (አንድነትና ለእርሱ ብጤ የሌለው መኾን) አልለው፡፡ እርሱም አሸናፊ ጥበበኛ ነው፡፡
🎤 Your recording:
30:28 🔁 0/5
ضَرَبَ لَكُم مَّثَلًا مِّنۡ أَنفُسِكُمۡۖ هَل لَّكُم مِّن مَّا مَلَكَتۡ أَيۡمَٰنُكُم مِّن شُرَكَآءَ فِي مَا رَزَقۡنَٰكُمۡ فَأَنتُمۡ فِيهِ سَوَآءٌ تَخَافُونَهُمۡ كَخِيفَتِكُمۡ أَنفُسَكُمۡۚ كَذَٰلِكَ نُفَصِّلُ ٱلۡأٓيَٰتِ لِقَوۡمٍ يَعۡقِلُونَ  ۝٢٨
Daraba lakum masalam min anfusikum hal lakum mimmaa malakat aymaanukum min shurakaaa`a fee maa razaqnaakum fa antum feehi sawaaa`un takhaafoonahum kakheefa tikum anfusakum; kazaalika nufassilul Aayaati liqawminy ya`qiloon
ለእናንተ ከነፍሶቻችሁ የሆነን ምሳሌ አደረገላችሁ፡፡ (እርሱም) እጆቻችሁ ከያዟቸው (ባሮች) ውስጥ በሰጠናችሁ ጸጋ ለእናንተ ተጋሪዎች አሏችሁን? ታዲያ እናንተና እነርሱ በእርሱ ትክክል ናችሁን? ነፍሶቻችሁን (ብጤዎቻችሁን) እንደምትፈሩ ትፈሯቸዋላችሁን? እንደዚሁ ለሚያስተውሉ ሕዝቦች፤ አንቀጾችን እንገልጻለን፡፡
🎤 Your recording:
30:29 🔁 0/5
بَلِ ٱتَّبَعَ ٱلَّذِينَ ظَلَمُوٓاْ أَهۡوَآءَهُم بِغَيۡرِ عِلۡمٍۖ فَمَن يَهۡدِي مَنۡ أَضَلَّ ٱللَّهُۖ وَمَا لَهُم مِّن نَّٰصِرِينَ  ۝٢٩
Balit taba`al lazeena zalamooo ahwaaa`ahum bighairi `ilmin famai yahdee man adallal laahu wa maa lahum min naasireen
ይልቁንም እነዚያ የበደሉ ሰዎች ያለ ዕውቀት ዝንባሌዎቻቸውን ተከተሉ፡፡ አላህም ያጠመመውን ሰው የሚያቀናው ማነው? ለእነርሱም ከረዳቶች ምንም የላቸውም፡፡
🎤 Your recording:
30:30 🔁 0/5
فَأَقِمۡ وَجۡهَكَ لِلدِّينِ حَنِيفًاۚ فِطۡرَتَ ٱللَّهِ ٱلَّتِي فَطَرَ ٱلنَّاسَ عَلَيۡهَاۚ لَا تَبۡدِيلَ لِخَلۡقِ ٱللَّهِۚ ذَٰلِكَ ٱلدِّينُ ٱلۡقَيِّمُ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعۡلَمُونَ  ۝٣٠
Fa aqim wajhaka liddeeni Haneefaa; fitratal laahil latee fataran naasa `alaihaa; laa taabdeela likhalqil laah; zaalikad deenul qaiyimu wa laakinna aksaran naasi laa ya`lamoon
ወደ እውነት ተዘንባይ ኾነህም ፊትህን ለሃይማኖት ቀጥ አድርግ፡፡ የአላህን ፍጥረት ያችን አላህ ሰዎችን በእርስዋ ላይ የፈጠረባትን (ሃይማኖት ያዟት)፡፡ የአላህን ፍጥረት መለወጥ የለም፡፡ ይህ ቀጥተኛ ሃይማኖት ነው፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም፡፡
🎤 Your recording:
30:31 🔁 0/5
۞ مُنِيبِينَ إِلَيۡهِ وَٱتَّقُوهُ وَأَقِيمُواْ ٱلصَّلَوٰةَ وَلَا تَكُونُواْ مِنَ ٱلۡمُشۡرِكِينَ  ۝٣١
Muneebeena ilaihi wattaqoohu wa aqeemus Salaata wa laa takoonoo minal mushrikeen
ወደእርሱ ተመላሾች ሆናቸሁ (የአላህን ሃይማኖት ያዙ)፡፡ ፍሩትም፡፡ ሶላትንም አስተካክላችሁ ስገዱ፡፡ ከአጋሪዎቹም አትሁኑ፡፡
🎤 Your recording:
30:32 🔁 0/5
مِنَ ٱلَّذِينَ فَرَّقُواْ دِينَهُمۡ وَكَانُواْ شِيَعًاۖ كُلُّ حِزۡبِۭ بِمَا لَدَيۡهِمۡ فَرِحُونَ  ۝٣٢
Minal lazeena farraqoo deenahum wa kaanoo shiya`an kullu hizbim bimaa ladaihim farihoon
ከእነዚያ ሃይማኖታቸውን ከለያዩትና ክፍልፍሎችም ከሆኑት (አትሁኑ)፡፡ ሕዝብ ሁሉ እነሱ ዘንድ ባለው ነገር ተደሳቾች ናቸው፡፡
🎤 Your recording:
30:33 🔁 0/5
وَإِذَا مَسَّ ٱلنَّاسَ ضُرٌّ دَعَوۡاْ رَبَّهُم مُّنِيبِينَ إِلَيۡهِ ثُمَّ إِذَآ أَذَاقَهُم مِّنۡهُ رَحۡمَةً إِذَا فَرِيقٌ مِّنۡهُم بِرَبِّهِمۡ يُشۡرِكُونَ  ۝٣٣
Wa izaa massan naasa durrun da`aw Rabbahum muneebeena ilaihi summa izaaa azaqahum minhu rahmatan izaa fareequm minhum be Rabbihim yushrikoon
ሰዎችንም ችግር ባገኛቸው ጊዜ ጌታቸውን ወደርሱ ተመላሾች ሆነው ይጠሩታል፡፡ ከዚያም ከእርሱ ችሮታን ባቀመሳቸው ጊዜ ከእነርሱ ከፊሎቹ ወዲያውኑ በጌታቸው (ጣዖትን) ያጋራሉ፡፡
🎤 Your recording:
30:34 🔁 0/5
لِيَكۡفُرُواْ بِمَآ ءَاتَيۡنَٰهُمۡۚ فَتَمَتَّعُواْ فَسَوۡفَ تَعۡلَمُونَ  ۝٣٤
Li yakfuroo bimaaa aatainaahum; fatamatta`oo fasawfa ta`lamoon
በሰጠናቸው ጸጋ ሊክዱ (ያጋራሉ)፡፡ ተጣቀሙም፤ በእርግጥም (መጨረሻችሁን) ወደፊት ታውቃላችሁ፡፡
🎤 Your recording:
30:35 🔁 0/5
أَمۡ أَنزَلۡنَا عَلَيۡهِمۡ سُلۡطَٰنًا فَهُوَ يَتَكَلَّمُ بِمَا كَانُواْ بِهِۦ يُشۡرِكُونَ  ۝٣٥
Am anzalnaa `alaihim sultaanan fahuwa yatakallamu bimaa kaanoo bihee yushrikoon
በእነርሱ ላይ አስረጅ አወረድን? ታዲያ እርሱ በዚያ በእርሱ ያጋሩ በነበሩት ነገር ይናገራልን;(የለም)፡፡
🎤 Your recording:
30:36 🔁 0/5
وَإِذَآ أَذَقۡنَا ٱلنَّاسَ رَحۡمَةً فَرِحُواْ بِهَاۖ وَإِن تُصِبۡهُمۡ سَيِّئَةُۢ بِمَا قَدَّمَتۡ أَيۡدِيهِمۡ إِذَا هُمۡ يَقۡنَطُونَ  ۝٣٦
Wa izaaa azaqnan naasa rahmatan farihoo bihaa wa in tusibhum sayyi`atum bimaa qaddamat aydeehim izaa hum yaqnatoon
ሰዎችንም ችሮታን ባቀመስናቸው ገዜ በእርሷ ይደሰታሉ፡፡ እጆቻቸውም ባሳለፉት ምክንያት መከራ ብታገኛቸው ወዲያውኑ እነርሱ ተስፋ ይቆርጣሉ፡፡
🎤 Your recording:
30:37 🔁 0/5
أَوَلَمۡ يَرَوۡاْ أَنَّ ٱللَّهَ يَبۡسُطُ ٱلرِّزۡقَ لِمَن يَشَآءُ وَيَقۡدِرُۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٍ لِّقَوۡمٍ يُؤۡمِنُونَ  ۝٣٧
Awalam yaraw annal laaha yabsutur rizqa limai yashaaa`u wa yaqdir; inna fee zaalika la Aayaatil liqawminy yu`minoon
አላህ ለሚሻው ሰው ሲሳይን የሚያሰፋ የሚያጠብም መሆኑን አያዩምን በዚህ ውስጥ ለሚያምኑ ሕዝቦች አስደናቂ ምልክቶች አልሉበት፡፡
🎤 Your recording:
30:38 🔁 0/5
فَـَٔاتِ ذَا ٱلۡقُرۡبَىٰ حَقَّهُۥ وَٱلۡمِسۡكِينَ وَٱبۡنَ ٱلسَّبِيلِۚ ذَٰلِكَ خَيۡرٌ لِّلَّذِينَ يُرِيدُونَ وَجۡهَ ٱللَّهِۖ وَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡمُفۡلِحُونَ  ۝٣٨
Fa aati zal qurbaa haqqahoo walmiskeena wabnassabeel; zaalika khairul lil lazeena yureedoona Wajhal laahi wa ulaaa`ika humul muflihoon
የዝምድናን ባለቤት ተገቢውን ስጠው፡፡ ለድኻም ለመንገደኛም (እርዳ)፡፡ ይህ ለእነዚያ የአላህን ፊት (ውዴታውን) ለሚሹ መልካም ነው፡፡ እነዚያም እነርሱ የፈለጉትን የሚያገኙ ናቸው፡፡
🎤 Your recording:
30:39 🔁 0/5
وَمَآ ءَاتَيۡتُم مِّن رِّبًا لِّيَرۡبُوَاْ فِيٓ أَمۡوَٰلِ ٱلنَّاسِ فَلَا يَرۡبُواْ عِندَ ٱللَّهِۖ وَمَآ ءَاتَيۡتُم مِّن زَكَوٰةٍ تُرِيدُونَ وَجۡهَ ٱللَّهِ فَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡمُضۡعِفُونَ  ۝٣٩
Wa maaa aataitum mir ribal li yarbuwa feee amwaalin naasi falaa yarboo `indal laahi wa maaa aataitum min zaakaatin tureedoona wajhal laahi fa ulaaa`ika humul mud`ifoon
ከበረከትም በሰዎች ገንዘቦች ውስጥ ይጨመር ዘንድ የምትሰጡት አላህ ዘንድ አይጨምርም፡፡ ከምጽዋትም የአላህን ፊት የምትሹ ሆናችሁ የምትሰጡት እነዚያ (ሰጪዎች) አበርካቾች እነርሱ ናቸው፡፡
🎤 Your recording:
30:40 🔁 0/5
ٱللَّهُ ٱلَّذِي خَلَقَكُمۡ ثُمَّ رَزَقَكُمۡ ثُمَّ يُمِيتُكُمۡ ثُمَّ يُحۡيِيكُمۡۖ هَلۡ مِن شُرَكَآئِكُم مَّن يَفۡعَلُ مِن ذَٰلِكُم مِّن شَيۡءٍۚ سُبۡحَٰنَهُۥ وَتَعَٰلَىٰ عَمَّا يُشۡرِكُونَ  ۝٤٠
Allaahul lazee khalaqa kum summa razaqakm summa yumeetukum summa yuhyeekum hal min shurakaaa`ikum mai yaf`alu min zaalikum min shai`; Sub haanahoo wa Ta`aalaa `ammaa yushrikoon
አላህ ያ የፈጠራችሁ፣ ከዚያም ሲሳይን የሰጣችሁ፣ ከዚያም የሚገድላችሁ ከዚያም ሕያው የሚያደርጋችሁ ነው፡፡ ከምታጋሯቸው (ጣዖታት) ውስጥ ከዚህ ነገር አንዳችን የሚሠራ አለን ለአላህ ጥራት ይገባው፡፡ (በእርሱ) ከሚያጋሩትም ሁሉ ላቀ፡፡
🎤 Your recording:
30:41 🔁 0/5
ظَهَرَ ٱلۡفَسَادُ فِي ٱلۡبَرِّ وَٱلۡبَحۡرِ بِمَا كَسَبَتۡ أَيۡدِي ٱلنَّاسِ لِيُذِيقَهُم بَعۡضَ ٱلَّذِي عَمِلُواْ لَعَلَّهُمۡ يَرۡجِعُونَ  ۝٤١
Zaharal fasaadu fil barri wal bahri bimaa kasabat aydinnaasi li yuzeeqahum ba`dal lazee `amiloo la`allahum yarji`oon
የሰዎች እጆች በሠሩት ኃጢኣት ምክንያት የዚያን የሠሩትን ከፊሉን ያቀምሳቸው ዘንድ መከራው በየብስና በባሕር ተገለጠ፤ (ተሰራጨ)፡፡ እነርሱ ሊመለሱ ይከጀላልና፡፡
🎤 Your recording:
30:42 🔁 0/5
قُلۡ سِيرُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ فَٱنظُرُواْ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلُۚ كَانَ أَكۡثَرُهُم مُّشۡرِكِينَ  ۝٤٢
Qul seeroo fil ardi fanzuroo kaifa kaana `aaqibatul lazeena min qabl; kaana aksaruhum mushrikeen
«በምድር ላይ ኺዱ የእነዚያንም በፊት የነበሩትን ሰዎች መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከቱ» በላቸው፡፡ አብዛኞቻቸው አጋሪዎች ነበሩ፡፡
🎤 Your recording:
30:43 🔁 0/5
فَأَقِمۡ وَجۡهَكَ لِلدِّينِ ٱلۡقَيِّمِ مِن قَبۡلِ أَن يَأۡتِيَ يَوۡمٌ لَّا مَرَدَّ لَهُۥ مِنَ ٱللَّهِۖ يَوۡمَئِذٍ يَصَّدَّعُونَ  ۝٤٣
Fa aqim wajhaka lid deenil qaiyimi min qabli any yaatiya Yawmul laa maradda lahoo minal laahi Yawma`iziny yassadda`oon
ለርሱ መመለስ የሌለው ቀን (የትንሣኤ ቀን) ከአላህ ሳይመጣ በፊት ፊትህን ወደ ቀጥተኛው ሃይማኖት ቀጥ አድርግ፡፡ በዚያ ቀን (ወደ ገነትና ወደ እሳት) ይለያያሉ፡፡
🎤 Your recording:
30:44 🔁 0/5
مَن كَفَرَ فَعَلَيۡهِ كُفۡرُهُۥۖ وَمَنۡ عَمِلَ صَٰلِحًا فَلِأَنفُسِهِمۡ يَمۡهَدُونَ  ۝٤٤
Man kafara fa`alaihi kufruhoo wa man `amila saalihan fali anfusihim yamhadoon
የካደ ሰው ክህደቱ (ጠንቁ) በእርሱው ላይ ነው፡፡ መልካምም የሠሩ ለነፍሶቻቸው (ማረፊያዎችን) ያዘጋጃሉ፡፡
🎤 Your recording:
30:45 🔁 0/5
لِيَجۡزِيَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ مِن فَضۡلِهِۦٓۚ إِنَّهُۥ لَا يُحِبُّ ٱلۡكَٰفِرِينَ  ۝٤٥
Li yajziyal lazeena aamanoo wa `amilus saalihaati min fadlih; innahoo laa yuhibbul kaafireen
እነዚያን ያመኑትንና መልካሞችንም የሠሩትን ከችሮታው ይመነዳ ዘንድ (ይለያያሉ)፡፡ እርሱ ከሓዲዎችን አይወድምና፡፡
🎤 Your recording:
30:46 🔁 0/5
وَمِنۡ ءَايَٰتِهِۦٓ أَن يُرۡسِلَ ٱلرِّيَاحَ مُبَشِّرَٰتٍ وَلِيُذِيقَكُم مِّن رَّحۡمَتِهِۦ وَلِتَجۡرِيَ ٱلۡفُلۡكُ بِأَمۡرِهِۦ وَلِتَبۡتَغُواْ مِن فَضۡلِهِۦ وَلَعَلَّكُمۡ تَشۡكُرُونَ  ۝٤٦
Wa min Aayaatiheee anyyursilar riyaaha mubashshi raatinw wa li yuzeeqakum mir rahmatihee wa litajriyal fulku bi amrihee wa litabtaghoo min fadlihee wa la`allakum tashkuroon
ነፋሶችንም (በዝናብ) ልታበስራችሁ፣ ከችሮታውም (በእርሷ) ሊያቀምሳችሁ፣ መርከቦችም በትዕዛዙ እንዲንሻለሉ፣ ከችሮታውም እንድትፈልጉ፣ ታመሰግኑትም ዘንድ መላኩ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፡፡
🎤 Your recording:
30:47 🔁 0/5
وَلَقَدۡ أَرۡسَلۡنَا مِن قَبۡلِكَ رُسُلًا إِلَىٰ قَوۡمِهِمۡ فَجَآءُوهُم بِٱلۡبَيِّنَٰتِ فَٱنتَقَمۡنَا مِنَ ٱلَّذِينَ أَجۡرَمُواْۖ وَكَانَ حَقًّا عَلَيۡنَا نَصۡرُ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ  ۝٤٧
Wa laqad arsalnaa min qablika Rusulan ilaa qawmihim fajaaa`oohum bil baiyinaati fantaqamnaa minal lazeena ajramoo wa kaana haqqan `alainaa nasrul mu`mineen
ከአንተ በፊትም መልክተኞችን ወደየሕዝቦቻቸው በእርግጥ ላክን፡፡ በግልጽ ማስረጃዎችም መጡባቸው፡፡ ከእነዚያ ካመጹትም ተበቀልን፡፡ ምእመኖቹንም መርዳት በእኛ ላይ ተገቢ ሆነ፡፡
🎤 Your recording:
30:48 🔁 0/5
ٱللَّهُ ٱلَّذِي يُرۡسِلُ ٱلرِّيَٰحَ فَتُثِيرُ سَحَابًا فَيَبۡسُطُهُۥ فِي ٱلسَّمَآءِ كَيۡفَ يَشَآءُ وَيَجۡعَلُهُۥ كِسَفًا فَتَرَى ٱلۡوَدۡقَ يَخۡرُجُ مِنۡ خِلَٰلِهِۦۖ فَإِذَآ أَصَابَ بِهِۦ مَن يَشَآءُ مِنۡ عِبَادِهِۦٓ إِذَا هُمۡ يَسۡتَبۡشِرُونَ  ۝٤٨
Allaahul lazee yursilur riyaaha fatuseeru sahaaban fa yabsutuhoo fis samaaa`i kaifa yashaaa`u wa yaj`aluhoo kisafan fataral wadqa yakhruju min khilaalihee fa izaaa asaaba bihee mai yashaaa`u min `ibaadiheee izaa hum yastabshiroon
አላህ ያ ነፋሶችን የሚልክ ነው፡፡ ደመናንም ይቀሰቅሳሉ፡፡ በሰማይ ላይም እንደሚሻ ይዘረጋዋል፡፡ ቁርጥራጮችም ያደርገዋል፡፡ ዝናቡንም ከደመናው መካከል ሲወጣ ታያለህ፡፡ በእርሱም ከባሮቹ የሚሻውን በለየ ጊዜ ወዲያውኑ እነሱ ይደሰታሉ፡፡
🎤 Your recording:
30:49 🔁 0/5
وَإِن كَانُواْ مِن قَبۡلِ أَن يُنَزَّلَ عَلَيۡهِم مِّن قَبۡلِهِۦ لَمُبۡلِسِينَ  ۝٤٩
Wa in kaanoo min qabli any yunazzala `alaihim min qablihee lamubliseen
በእነርሱም ላይ ከመወረዱ በፊት ከእርሱ በፊት በእርግጥ ተስፋ ቆራጮች ነበሩ፡፡
🎤 Your recording:
30:50 🔁 0/5
فَٱنظُرۡ إِلَىٰٓ ءَاثَٰرِ رَحۡمَتِ ٱللَّهِ كَيۡفَ يُحۡيِ ٱلۡأَرۡضَ بَعۡدَ مَوۡتِهَآۚ إِنَّ ذَٰلِكَ لَمُحۡيِ ٱلۡمَوۡتَىٰۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٍ قَدِيرٌ  ۝٥٠
Fanzur ilaaa aasaari rahmatil laahi kaifa yuhyil arda ba`da mawtihaa; inna zaalika lamuhyil mawtaa wa Huwa `alaa kulli shai`in Qadeer
ምድርንም ከሞተች በኋላ እንዴት ሕያው እንደሚያደርጋት ወደ አላህ ችሮታ ፈለጎች ተመልከት፡፡ ይህ (አድራጊ) ሙታንንም በእርግጥ ሕያው አድራጊ ነው፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡
🎤 Your recording:
30:51 🔁 0/5
وَلَئِنۡ أَرۡسَلۡنَا رِيحًا فَرَأَوۡهُ مُصۡفَرًّا لَّظَلُّواْ مِنۢ بَعۡدِهِۦ يَكۡفُرُونَ  ۝٥١
Wa la`in arsalnaa reehan fara awhu musfarral lazalloo mim ba`dihee yakfuroon
ነፋስንም (በአዝመራዎች ላይ) ብንልክና ገርጥቶ ቢያዩት ከእርሱ በኋላ በእርግጥ (ችሮታውን) የሚክዱ ይሆናሉ፡፡
🎤 Your recording:
30:52 🔁 0/5
فَإِنَّكَ لَا تُسۡمِعُ ٱلۡمَوۡتَىٰ وَلَا تُسۡمِعُ ٱلصُّمَّ ٱلدُّعَآءَ إِذَا وَلَّوۡاْ مُدۡبِرِينَ  ۝٥٢
Fa innaka laa tusmi`ul mawtaa wa laa tusmi`us summad du`aaa`a izaa wallaw mudbireen
አንተም ሙታንን አታሰማም፡፡ ደንቆሮዎችንም ዟሪዎች ሆነው በሸሹ ጊዜ ጥሪን አታሰማም፡፡
🎤 Your recording:
30:53 🔁 0/5
وَمَآ أَنتَ بِهَٰدِ ٱلۡعُمۡيِ عَن ضَلَٰلَتِهِمۡۖ إِن تُسۡمِعُ إِلَّا مَن يُؤۡمِنُ بِـَٔايَٰتِنَا فَهُم مُّسۡلِمُونَ  ۝٥٣
Wa maa anta bihaadil `umyi `an dalaalatihim in tusmi`u illaa mai yuminu bi aayaatinaa fahum muslimoon
አንተ ዕውሮችንም ከጥመታቸው የምታቀና አይደለህም፡፡ በአንቀጾቻችን የሚያምኑትን ሰዎች እንጂ ሌላን አታሰማም፡፡ እነርሱም ታዛዦች ናቸው፡፡
🎤 Your recording:
30:54 🔁 0/5
۞ ٱللَّهُ ٱلَّذِي خَلَقَكُم مِّن ضَعۡفٍ ثُمَّ جَعَلَ مِنۢ بَعۡدِ ضَعۡفٍ قُوَّةً ثُمَّ جَعَلَ مِنۢ بَعۡدِ قُوَّةٍ ضَعۡفًا وَشَيۡبَةًۚ يَخۡلُقُ مَا يَشَآءُۚ وَهُوَ ٱلۡعَلِيمُ ٱلۡقَدِيرُ  ۝٥٤
Allahul lazee khalaqa kum min du`fin summa ja`ala mim ba`di du`fin quwwatan summa ja`ala mim ba`di quwwatin du`fanw wa shaibah; yakhluqu maa yashaaa`u wa Huwal `Aleemul Qadeer
አላህ ያ ከደካማ (ፍትወት ጠብታ) የፈጠራችሁ ነው፡፡ ከዚያም ከደካማነት በኋላ ኀይልን አደረገ፡፡ ከዚያም ከብርቱነት በኋላ ደካማነትንና ሽበትን አደረገ፡፡ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ እርሱም ዐዋቂው ቻዩ ነው፡፡
🎤 Your recording:
30:55 🔁 0/5
وَيَوۡمَ تَقُومُ ٱلسَّاعَةُ يُقۡسِمُ ٱلۡمُجۡرِمُونَ مَا لَبِثُواْ غَيۡرَ سَاعَةٍۚ كَذَٰلِكَ كَانُواْ يُؤۡفَكُونَ  ۝٥٥
Wa Yawma taqoomus Saa`atu yuqsimul mujrimoona maa labisoo ghaira saa`ah; kazaalika kaanoo yu`fakoon
ሰዓቲቱ በምትሆንበት ቀን ከሓዲዎች «ከአንዲት ሰዓት በስተቀር (በመቃብር) አልቆየንም» ብለው ይምላሉ፡፡ እንደዚሁ (ከእውነት) ይመለሱ ነበሩ፡፡
🎤 Your recording:
30:56 🔁 0/5
وَقَالَ ٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡعِلۡمَ وَٱلۡإِيمَٰنَ لَقَدۡ لَبِثۡتُمۡ فِي كِتَٰبِ ٱللَّهِ إِلَىٰ يَوۡمِ ٱلۡبَعۡثِۖ فَهَٰذَا يَوۡمُ ٱلۡبَعۡثِ وَلَٰكِنَّكُمۡ كُنتُمۡ لَا تَعۡلَمُونَ  ۝٥٦
Wa qaalal lazeena ootul `ilma wal eemaana laqad labistum fee kitaabil laahi ilaa yawmil ba`si fahaazaa yawmul ba`si wa laakinnakum kuntum laa ta`lamoon
እነዚያንም ዕውቀትንና እምነትን የተሰጡት «በአላህ መጽሐፍ (ፍርድ) እስከ ትንሣኤ ቀን በእርግጥ ቆያችሁ፡፡ ይህም (የካዳችሁት) የትንሣኤ ቀን ነው፡፡ ግን እናንተ የማታውቁ ነበራችሁ» ይሏቸዋል፡፡
🎤 Your recording:
30:57 🔁 0/5
فَيَوۡمَئِذٍ لَّا يَنفَعُ ٱلَّذِينَ ظَلَمُواْ مَعۡذِرَتُهُمۡ وَلَا هُمۡ يُسۡتَعۡتَبُونَ  ۝٥٧
Fa Yawma`izil laa yanfa`ul lazeena zalamoo ma`ziratu hum wa laa hum yusta`taboon
በዚያም ቀን እነዚያን የበደሉትን ማመካኘታቸው አይጠቅማቸውም፡፡ እነርሱም በወቀሳ አይታለፉም፡፡
🎤 Your recording:
30:58 🔁 0/5
وَلَقَدۡ ضَرَبۡنَا لِلنَّاسِ فِي هَٰذَا ٱلۡقُرۡءَانِ مِن كُلِّ مَثَلٍۚ وَلَئِن جِئۡتَهُم بِـَٔايَةٍ لَّيَقُولَنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ إِنۡ أَنتُمۡ إِلَّا مُبۡطِلُونَ  ۝٥٨
Wa laqad darabnaa linnaasi fee haazal Quraani min kulli masal; wa la`in ji`tahum bi aayatil la yaqoolannal lazeena kafaroo in antum illaa mubtiloon
በዚያም ቁርኣን ውስጥ ከምሳሌ ሁሉ ለሰዎች በእርግጥ ገለጽን፡፡ በተዓምርም ብትመጣባቸው እነዚያ የካዱት ሰዎች «እናንተ አበላሺዎች እንጂ ሌላ አይደላችሁም» ይላሉ፡፡
🎤 Your recording:
30:59 🔁 0/5
كَذَٰلِكَ يَطۡبَعُ ٱللَّهُ عَلَىٰ قُلُوبِ ٱلَّذِينَ لَا يَعۡلَمُونَ  ۝٥٩
Kazaalika yatba`ul laahu `alaa quloobil lazeena laa ya`lamoon
እንደዚሁ አላህ በእነዚያ በማያውቁት ሰዎች ልቦች ላይ ያትማል፡፡
🎤 Your recording:
30:60 🔁 0/5
فَٱصۡبِرۡ إِنَّ وَعۡدَ ٱللَّهِ حَقٌّۖ وَلَا يَسۡتَخِفَّنَّكَ ٱلَّذِينَ لَا يُوقِنُونَ  ۝٦٠
Fasbir inna wa`dal laahi haqqunw wa laa yastakhif fannakal lazeena laa yooqinoon
ስለዚህ ታገስ፡፡ የአላህ ቀጠሮ እውነት ነውና፡፡ እነዚያም በትንሣኤ የሚያረጋግጡት አያቅልሉህ፡፡
🎤 Your recording:
💡 Tap any hidden word to reveal it temporarily — your progress is saved automatically in this browser.

🎉
🎊 Well Done! Memorization Complete
Mishary Rashid Alafasy
Mahmoud Khalil Al-Husary
Abdurrahman As-Sudais
Mohamed Siddiq Al-Minshawi
Abdul Basit Abdul Samad
Ali Al-Hudhaify
Ahmed ibn Ali al-Ajamy
Abu Bakr Ash-Shaatree
Muhammad Ayyoub
Abdullah Basfar
Abdullah Al-Juhani
Maher Al Muaiqly
0:00
0:00
-

ቅዱስ ቁርኣን


Tuesday, August 18, 2026

Don't forget us in your sincere prayers