Surah Al-Infitar with Amharic
إِذَا السَّمَاءُ انفَطَرَتْ(1) ሰማይ በተሰነጠቀች ጊዜ፤ |
وَإِذَا الْكَوَاكِبُ انتَثَرَتْ(2) ከዋክብትም ተበታትነው በወደቁ ጊዜ፤ |
وَإِذَا الْبِحَارُ فُجِّرَتْ(3) ባሕሮችም በተከፈቱና በተደበላለቁ ጊዜ፤ |
وَإِذَا الْقُبُورُ بُعْثِرَتْ(4) መቃብሮችም በተገለባበጡና (ሙታን) በተነሱ ጊዜ፤ |
عَلِمَتْ نَفْسٌ مَّا قَدَّمَتْ وَأَخَّرَتْ(5) ማንኛይቱም ነፍስ ያስቀደመችውንና ያቆየችውን ታውቃለች፡፡ |
يَا أَيُّهَا الْإِنسَانُ مَا غَرَّكَ بِرَبِّكَ الْكَرِيمِ(6) አንተ ሰው ሆይ! በቸሩ ጌታህ ምን አታለለህ? |
الَّذِي خَلَقَكَ فَسَوَّاكَ فَعَدَلَكَ(7) በዚያ በፈጠረህ አካለ ሙሉም ባደረገህ ባስተካከለህም፡፡ |
فِي أَيِّ صُورَةٍ مَّا شَاءَ رَكَّبَكَ(8) በማንኛውም በሻው ቅርፅ በገጣጠመህ (ጌታህ ምን አታለለህ)፡፡ |
كَلَّا بَلْ تُكَذِّبُونَ بِالدِّينِ(9) ተከልከሉ፤ በእውነቱ በፍርዱ ቀን ታስተባብላላችሁ፡፡ |
وَإِنَّ عَلَيْكُمْ لَحَافِظِينَ(10) በእናንተ ላይ ተጠባባቂዎች ያሉባችሁ፤ ስትኾኑ፤ |
كِرَامًا كَاتِبِينَ(11) የተከበሩ ጸሐፊዎች የኾኑ፤ (ተጠባባቂዎች)፡፡ |
يَعْلَمُونَ مَا تَفْعَلُونَ(12) የምትሠሩትን ሁሉ የሚያውቁ፡፡ |
إِنَّ الْأَبْرَارَ لَفِي نَعِيمٍ(13) እውነተኞቹ ምእምናን በእርግጥ በገነት ውስጥ ናቸው፡፡ |
وَإِنَّ الْفُجَّارَ لَفِي جَحِيمٍ(14) ከሓዲዎቹም በእርግጥ በገሀነም ውስጥ ናቸው፡፡ |
يَصْلَوْنَهَا يَوْمَ الدِّينِ(15) በፍርዱ ቀን ይገቧታል፡፡ |
وَمَا هُمْ عَنْهَا بِغَائِبِينَ(16) እነርሱም ከርሷ ራቂዎች አይደሉም፡፡ |
وَمَا أَدْرَاكَ مَا يَوْمُ الدِّينِ(17) የፍርድ ቀን ምን እንደኾነ ምን አሳወቀህ? |
ثُمَّ مَا أَدْرَاكَ مَا يَوْمُ الدِّينِ(18) ከዚያም የፍርዱ ቀን ምን እንደኾነ ምን አሳወቀህ? |
يَوْمَ لَا تَمْلِكُ نَفْسٌ لِّنَفْسٍ شَيْئًا ۖ وَالْأَمْرُ يَوْمَئِذٍ لِّلَّهِ(19) (እርሱ) ማንኛይቱም ነፍስ ለሌላይቱ ነፍስ ምንም ማድረግን የማትችልበት ቀን ነው፡፡ ነገሩም ሁሉ በዚያ ቀን ለአላህ ብቻ ነው፡፡ |
More surahs in Amharic:
Download surah Al-Infitar with the voice of the most famous Quran reciters :
surah Al-Infitar mp3 : choose the reciter to listen and download the chapter Al-Infitar Complete with high quality
Ahmed Al Ajmy
Bandar Balila
Khalid Al Jalil
Saad Al Ghamdi
Saud Al Shuraim
Abdul Basit
Abdul Rashid Sufi
Abdullah Basfar
Abdullah Al Juhani
Fares Abbad
Maher Al Muaiqly
Al Minshawi
Al Hosary
Mishari Al-afasi
Yasser Al Dosari
لا تنسنا من دعوة صالحة بظهر الغيب