🔥 0 day streak
📖 Long surah — split into smaller parts to help you focus (83 አንቀጽ)
📚 All Surahs
30%
🎤 Tap the microphone icon 🎙️ next to any verse to record yourself reciting it, then listen back and compare with the reciter.
0/83
36:1 🔁 0/5
يسٓ  ۝١
Yaa-Seeen
የ.ሰ.(ያ ሲን)
🎤 Your recording:
36:2 🔁 0/5
وَٱلۡقُرۡءَانِ ٱلۡحَكِيمِ  ۝٢
Wal-Qur-aanil-Hakeem
ጥበብ በተመላበት ቁርኣን እምላለሁ፡፡
🎤 Your recording:
36:3 🔁 0/5
إِنَّكَ لَمِنَ ٱلۡمُرۡسَلِينَ  ۝٣
Innaka laminal mursaleen
አንተ በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነህ፡፡
🎤 Your recording:
36:4 🔁 0/5
عَلَىٰ صِرَٰطٍ مُّسۡتَقِيمٍ  ۝٤
Alaa Siraatim Mustaqeem
በቀጥታም መንገድ ላይ ነህ፡፡
🎤 Your recording:
36:5 🔁 0/5
تَنزِيلَ ٱلۡعَزِيزِ ٱلرَّحِيمِ  ۝٥
Tanzeelal `Azeezir Raheem
አሸናፊ አዛኝ ከሆነው አምላክ መወረድን ተወረደ፡፡
🎤 Your recording:
36:6 🔁 0/5
لِتُنذِرَ قَوۡمًا مَّآ أُنذِرَ ءَابَآؤُهُمۡ فَهُمۡ غَٰفِلُونَ  ۝٦
Litunzira qawmam maaa unzira aabaaa`uhum fahum ghaafiloon
አባቶቻቸው ያልተስፈራሩትን ሕዝቦች ልታስጠነቅቅበት (ተወረደ)፡፡ እነርሱ ዘንጊዎች ናቸውና፡፡
🎤 Your recording:
36:7 🔁 0/5
لَقَدۡ حَقَّ ٱلۡقَوۡلُ عَلَىٰٓ أَكۡثَرِهِمۡ فَهُمۡ لَا يُؤۡمِنُونَ  ۝٧
Laqad haqqal qawlu `alaaa aksarihim fahum laa yu`minoon
በአብዛኞቻቸው ላይ ቃሉ በእውነት ተረጋገጠ፡፡ ስለዚህ እነርሱ አያምኑም፡፡
🎤 Your recording:
36:8 🔁 0/5
إِنَّا جَعَلۡنَا فِيٓ أَعۡنَٰقِهِمۡ أَغۡلَٰلًا فَهِيَ إِلَى ٱلۡأَذۡقَانِ فَهُم مُّقۡمَحُونَ  ۝٨
Innaa ja`alnaa feee a`naaqihim aghlaalan fahiya ilal azqaani fahum muqmahoon
እኛ በአንገቶቻቸው ላይ እንዛዝላዎችን አደረግን፡፡ እርሷም (እንዛዝላይቱ) ወደ አገጮቻቸው ደራሽ ናት፡፡ እነርሱም ራሶቻቸውን ያንጋጠጡ ናቸው፡፡
🎤 Your recording:
36:9 🔁 0/5
وَجَعَلۡنَا مِنۢ بَيۡنِ أَيۡدِيهِمۡ سَدًّا وَمِنۡ خَلۡفِهِمۡ سَدًّا فَأَغۡشَيۡنَٰهُمۡ فَهُمۡ لَا يُبۡصِرُونَ  ۝٩
Wa ja`alnaa mim baini aydeehim saddanw-wa min khalfihim saddan fa aghshai naahum fahum laa yubsiroon
ከስተፊታቸውም ግርዶን ከስተኋላቸውም ግርዶን አደረግን፡፡ ሸፈንናቸውም፡፡ ስለዚህ እነሱ አያዩም፡፡
🎤 Your recording:
36:10 🔁 0/5
وَسَوَآءٌ عَلَيۡهِمۡ ءَأَنذَرۡتَهُمۡ أَمۡ لَمۡ تُنذِرۡهُمۡ لَا يُؤۡمِنُونَ  ۝١٠
Wa sawaaa`un `alaihim `a-anzartahum am lam tunzirhum laa yu`minoon
ብታሰጠነቅቃቸውም ባታስጠነቅቃቸውም በእነርሱ ላይ እኩል ነው፡፡ አያምኑም፡፡
🎤 Your recording:
36:11 🔁 0/5
إِنَّمَا تُنذِرُ مَنِ ٱتَّبَعَ ٱلذِّكۡرَ وَخَشِيَ ٱلرَّحۡمَٰنَ بِٱلۡغَيۡبِۖ فَبَشِّرۡهُ بِمَغۡفِرَةٍ وَأَجۡرٍ كَرِيمٍ  ۝١١
Innamaa tunziru manit taba `az-Zikra wa khashiyar Rahmaana bilghaib, fabashshirhu bimaghfiratinw-wa ajrin kareem
የምታስጠነቅቀው ግሳጼን የተከተለንና አልረሕማንን በሩቅ የፈራን ሰው ብቻ ነው፡፡ በምሕረትና በመልካም ምንዳም አብስረው፡፡
🎤 Your recording:
36:12 🔁 0/5
إِنَّا نَحۡنُ نُحۡيِ ٱلۡمَوۡتَىٰ وَنَكۡتُبُ مَا قَدَّمُواْ وَءَاثَٰرَهُمۡۚ وَكُلَّ شَيۡءٍ أَحۡصَيۡنَٰهُ فِيٓ إِمَامٍ مُّبِينٍ  ۝١٢
Innaa Nahnu nuhyil mawtaa wa naktubu maa qaddamoo wa aasaarahum; wa kulla shai`in ahsainaahu feee Imaamim Mubeen
እኛ ሙታንን እኛ በእርግጥ ሕያው እናደርጋለን፡፡ ያስቀደሙትንም ሥራ ፈለጎቻቸውንም እንጽፋለን፡፡ ነገሩንም ሁሉ ገላጭ መሪ በኾነ መጽሐፍ ውስጥ አጠቃለልነው፡፡
🎤 Your recording:
36:13 🔁 0/5
وَٱضۡرِبۡ لَهُم مَّثَلًا أَصۡحَٰبَ ٱلۡقَرۡيَةِ إِذۡ جَآءَهَا ٱلۡمُرۡسَلُونَ  ۝١٣
Wadrib lahum masalan Ashaabal Qaryatih; iz jaaa`ahal mursaloon
ለእነርሱም የከተማይቱን (የአንጾኪያን) ሰዎች ምሳሌ መልክተኞቹ በመጧት ጊዜ (የኾነውን) ግለጽላቸው፡፡
🎤 Your recording:
36:14 🔁 0/5
إِذۡ أَرۡسَلۡنَآ إِلَيۡهِمُ ٱثۡنَيۡنِ فَكَذَّبُوهُمَا فَعَزَّزۡنَا بِثَالِثٍ فَقَالُوٓاْ إِنَّآ إِلَيۡكُم مُّرۡسَلُونَ  ۝١٤
Iz arsalnaaa ilaihimusnaini fakazzaboohumaa fa`azzaznaa bisaalisin faqaalooo innaaa ilaikum mursaloon
ወደእነርሱ ሁለትን ሰዎች በላክንና ባስተባበሉዋቸው ጊዜ በሶስተኛም በአበረታንና እኛ ወደ እናንተ መልክተኞች ነን ባሏቸው ጊዜ (የኾነውን ምሳሌ ግለጽላቸው)፡፡
🎤 Your recording:
36:15 🔁 0/5
قَالُواْ مَآ أَنتُمۡ إِلَّا بَشَرٌ مِّثۡلُنَا وَمَآ أَنزَلَ ٱلرَّحۡمَٰنُ مِن شَيۡءٍ إِنۡ أَنتُمۡ إِلَّا تَكۡذِبُونَ  ۝١٥
Qaaloo maaa antum illaa basharum mislunaa wa maaa anzalar Rahmaanu min shai`in in antum illaa takziboon
እናንተ መሰላችን ሰዎች እንጂ ሌላ አይደላችሁም፡፡ አልረሕማንም ምንም ነገር አላወረደም፡፡ እናንተ የምትዋሹ እንጂ ሌላ አይደላችሁም አሉዋቸው፡፡
🎤 Your recording:
36:16 🔁 0/5
قَالُواْ رَبُّنَا يَعۡلَمُ إِنَّآ إِلَيۡكُمۡ لَمُرۡسَلُونَ  ۝١٦
Qaaloo Rabbunaa ya`lamu innaaa ilaikum lamursaloon
(መልክተኞቹም) አሉ «ጌታችን ያውቃል፡፡ እኛ ወደእናንተ በእርግጥ መልክተኞች ነን፡፡
🎤 Your recording:
36:17 🔁 0/5
وَمَا عَلَيۡنَآ إِلَّا ٱلۡبَلَٰغُ ٱلۡمُبِينُ  ۝١٧
Wa maa `alainaaa illal balaaghul mubeen
«በእኛ ላይም ግልጽ የኾነ ማድረስ እንጂ ሌላ የለብንም፡፡»
🎤 Your recording:
36:18 🔁 0/5
قَالُوٓاْ إِنَّا تَطَيَّرۡنَا بِكُمۡۖ لَئِن لَّمۡ تَنتَهُواْ لَنَرۡجُمَنَّكُمۡ وَلَيَمَسَّنَّكُم مِّنَّا عَذَابٌ أَلِيمٌ  ۝١٨
Qaaloo innaa tataiyarnaa bikum la`il-lam tantahoo lanar jumannakum wa la-yamassan nakum minnaa `azaabun aleem
(ሕዝቦቹም) «እኛ በእናንተ ገደ ቢሶች ኾን፡፡ ባትከለከሉ በእርግጥ እንወግራችኋለን፡፡ ከእኛም አሳማሚ ቅጣት በእርግጥ ያገኛችኋል» አሉ፡፡
🎤 Your recording:
36:19 🔁 0/5
قَالُواْ طَٰٓئِرُكُم مَّعَكُمۡ أَئِن ذُكِّرۡتُمۚ بَلۡ أَنتُمۡ قَوۡمٌ مُّسۡرِفُونَ  ۝١٩
Qaaloo taaa`irukum ma`akum; a`in zukkirtum; bal antum qawmum musrifoon
«ገደ ቢስነታችሁ ከእናንተው ጋር ነው፡፡ ብትገሰጹ (ትዝታላችሁን?) በእውነቱ እናንተ ወሰን አላፊዎች ሕዝቦች ናችሁ» አሏቸው፡፡
🎤 Your recording:
36:20 🔁 0/5
وَجَآءَ مِنۡ أَقۡصَا ٱلۡمَدِينَةِ رَجُلٌ يَسۡعَىٰ قَالَ يَٰقَوۡمِ ٱتَّبِعُواْ ٱلۡمُرۡسَلِينَ  ۝٢٠
Wa jaaa`a min aqsal madeenati rajuluny yas`aa qaala yaa qawmit tabi`ul mursaleen
ከከተማይቱም ሩቅ ዳርቻ የሚሮጥ ሰው መጣ፡፡ «ወገኖቼ ሆይ! መልክተኞቹን ተከተሉ» አለ፡፡
🎤 Your recording:
36:21 🔁 0/5
ٱتَّبِعُواْ مَن لَّا يَسۡـَٔلُكُمۡ أَجۡرًا وَهُم مُّهۡتَدُونَ  ۝٢١
Ittabi`oo mal-laa yas`alukum ajranw-wa hum muhtadoon
«እነርሱ ቅኑን መንገድ የተመሩ ሲኾኑ ዋጋን የማየጠይቁዋችሁን ሰዎች ተከተሉ» (አላቸው)፡፡
🎤 Your recording:
36:22 🔁 0/5
وَمَالِيَ لَآ أَعۡبُدُ ٱلَّذِي فَطَرَنِي وَإِلَيۡهِ تُرۡجَعُونَ  ۝٢٢
Wa maa liya laaa a`budul lazee fataranee wa ilaihi turja`oon
«ያንንም የፈጠረኝን፤ ወደርሱም የምትመለሱበትን (ጌታ) የማልገዛ ለእኔ ምን አለኝ?» (አለ)፡፡
🎤 Your recording:
36:23 🔁 0/5
ءَأَتَّخِذُ مِن دُونِهِۦٓ ءَالِهَةً إِن يُرِدۡنِ ٱلرَّحۡمَٰنُ بِضُرٍّ لَّا تُغۡنِ عَنِّي شَفَٰعَتُهُمۡ شَيۡـًٔا وَلَا يُنقِذُونِ  ۝٢٣
A-attakhizu min dooniheee aalihatan iny-yuridnir Rahmaanu bidurril-laa tughni `annee shafaa `atuhum shai `anw-wa laa yunqizoon
«ከእርሱ ሌላ አማልክትን እይዛለሁን? አልረህማን በጉዳት ቢሻኝ ምልጃቸው ከእኔ (ለመመለስ) ምንም አትጠቅመኝም፤ አያድኑኝምም፡፡
🎤 Your recording:
36:24 🔁 0/5
إِنِّيٓ إِذًا لَّفِي ضَلَٰلٍ مُّبِينٍ  ۝٢٤
Inneee izal-lafee dalaa-lim-mubeen
«እኔ ያን ጊዜ በግልጽ ስህተት ውስጥ ነኝ፡፡
🎤 Your recording:
36:25 🔁 0/5
إِنِّيٓ ءَامَنتُ بِرَبِّكُمۡ فَٱسۡمَعُونِ  ۝٢٥
Inneee aamantu bi Rabbikum fasma`oon
«እኔ በጌታችሁ አመንኩ፤ ስሙኝም፤» (አለ)፡፡
🎤 Your recording:
36:26 🔁 0/5
قِيلَ ٱدۡخُلِ ٱلۡجَنَّةَۖ قَالَ يَٰلَيۡتَ قَوۡمِي يَعۡلَمُونَ  ۝٢٦
Qeelad khulil Jannnah; qaala yaa laita qawmee ya`lamoon
«ገነትን ግባ» ተባለ፡፡ (እርሱም) አለ፡- «ወገኖቼ ቢያውቁ እመኛለሁ፡፡
🎤 Your recording:
36:27 🔁 0/5
بِمَا غَفَرَ لِي رَبِّي وَجَعَلَنِي مِنَ ٱلۡمُكۡرَمِينَ  ۝٢٧
Bimaa ghafara lee Rabbee wa ja`alanee minal mukrameen
«ጌታዬ ለእኔ ምሕረት ያደረገልኝና ከተከበሩትም ያደረገኝ መኾኑን፡፡»
🎤 Your recording:
36:28 🔁 0/5
۞ وَمَآ أَنزَلۡنَا عَلَىٰ قَوۡمِهِۦ مِنۢ بَعۡدِهِۦ مِن جُندٍ مِّنَ ٱلسَّمَآءِ وَمَا كُنَّا مُنزِلِينَ  ۝٢٨
Wa maaa anzalnaa `alaa qawmihee mim ba`dihee min jundim minas-samaaa`i wa maa kunnaa munzileen
ከእርሱም በኋላ በሕዝቦቹ ላይ (ልናጠፋቸው) ሰራዊትን ከሰማይ አላወረድንም፡፡ (በማንም ላይ) አወራጆችም አልነበርንም፡፡
🎤 Your recording:
36:29 🔁 0/5
إِن كَانَتۡ إِلَّا صَيۡحَةً وَٰحِدَةً فَإِذَا هُمۡ خَٰمِدُونَ  ۝٢٩
In kaanat illaa saihatanw waahidatan fa-izaa hum khaamidoon
(ቅጣታቸው) አንዲት ጩኸት እንጂ ሌላ አልነበረችም፡፡ ወዲያውኑም እነርሱ ጠፊዎች ኾኑ፡፡
🎤 Your recording:
36:30 🔁 0/5
يَٰحَسۡرَةً عَلَى ٱلۡعِبَادِۚ مَا يَأۡتِيهِم مِّن رَّسُولٍ إِلَّا كَانُواْ بِهِۦ يَسۡتَهۡزِءُونَ  ۝٣٠
Yaa hasratan `alal `ibaad; maa yaateehim mir Rasoolin illaa kaanoo bihee yastahzi `oon
በባሮቹ ላይ ዋ ቁልጭት! ከመልክተኛ አንድም አይመጣቸውም በእርሱ የሚሳለቁበት ቢኾኑ እንጅ፡፡
🎤 Your recording:
36:31 🔁 0/5
أَلَمۡ يَرَوۡاْ كَمۡ أَهۡلَكۡنَا قَبۡلَهُم مِّنَ ٱلۡقُرُونِ أَنَّهُمۡ إِلَيۡهِمۡ لَا يَرۡجِعُونَ  ۝٣١
Alam yaraw kam ahlak naa qablahum minal qurooni annahum ilaihim laa yarji`oon
ከእነርሱ በፊት ከክፍለ ዘመናት ሕዝቦች ብዙዎችን ማጥፋታችንንና እነርሱ ወደነርሱ የማይመለሱ መኾናቸውን አላወቁምን?
🎤 Your recording:
36:32 🔁 0/5
وَإِن كُلٌّ لَّمَّا جَمِيعٌ لَّدَيۡنَا مُحۡضَرُونَ  ۝٣٢
Wa in kullul lammaa jamee`ul-ladainaa muhdaroon
ሁሉም እኛ ዘንድ የሚሰበሰቡ የሚቀረቡ እንጂ ሌላ አይደሉም፡፡
🎤 Your recording:
36:33 🔁 0/5
وَءَايَةٌ لَّهُمُ ٱلۡأَرۡضُ ٱلۡمَيۡتَةُ أَحۡيَيۡنَٰهَا وَأَخۡرَجۡنَا مِنۡهَا حَبًّا فَمِنۡهُ يَأۡكُلُونَ  ۝٣٣
Wa Aayatul lahumul ardul maitatu ahyainaahaa wa akhrajnaa minhaa habban faminhu yaakuloon
የሞተችውም ምድር ለእነርሱ ምልክት ናት! ሕያው አደረግናት፡፡ ከእርሷም ፍሬን አወጣን፤ ከርሱም ይበላሉ፡፡
🎤 Your recording:
36:34 🔁 0/5
وَجَعَلۡنَا فِيهَا جَنَّٰتٍ مِّن نَّخِيلٍ وَأَعۡنَٰبٍ وَفَجَّرۡنَا فِيهَا مِنَ ٱلۡعُيُونِ  ۝٣٤
Wa ja`alnaa feehaa jannaatim min nakheelinw wa a`naabinw wa fajjarnaa feeha minal `uyoon
በእርሷም ውሰጥ ከዘምበባዎችና ከወይኖች የኾኑ አትክልቶችን አደረግን፡፡ በእርሷም ውስጥ ምንጮችን አፈለቅን፡፡
🎤 Your recording:
36:35 🔁 0/5
لِيَأۡكُلُواْ مِن ثَمَرِهِۦ وَمَا عَمِلَتۡهُ أَيۡدِيهِمۡۚ أَفَلَا يَشۡكُرُونَ  ۝٣٥
Liyaakuloo min samarihee wa maa `amilat-hu aideehim; afalaa yashkuroon
ከፍሬውና እጆቻቸው ከሠሩትም ይበሉ ዘንድ (ይህን አደረግን)፤ አያመሰግኑምን?
🎤 Your recording:
36:36 🔁 0/5
سُبۡحَٰنَ ٱلَّذِي خَلَقَ ٱلۡأَزۡوَٰجَ كُلَّهَا مِمَّا تُنۢبِتُ ٱلۡأَرۡضُ وَمِنۡ أَنفُسِهِمۡ وَمِمَّا لَا يَعۡلَمُونَ  ۝٣٦
Subhaanal lazee khalaqal azwaaja kullahaa mimmaa tumbitul ardu wa min anfusihim wa mimmaa laa ya`lamoon
ያ ምድር ከምታበቅለው ከነፍሶቻቸውም ከማያውቁትም ነገር ዓይነቶችን ሁሏንም የፈጠረ (አምላክ) ጥራት ይገባው፡፡
🎤 Your recording:
36:37 🔁 0/5
وَءَايَةٌ لَّهُمُ ٱلَّيۡلُ نَسۡلَخُ مِنۡهُ ٱلنَّهَارَ فَإِذَا هُم مُّظۡلِمُونَ  ۝٣٧
Wa Aayatul lahumul lailu naslakhu minhun nahaara fa-izaa hum muzlimoon
ሌሊቱም ለእነርሱ ምልክት ነው፡፡ ከእርሱ ላይ ቀንን እንገፍፋለን፡፡ ወዲያውኑም እነርሱ በጨለማ ውስጥ ይገባሉ፡፡
🎤 Your recording:
36:38 🔁 0/5
وَٱلشَّمۡسُ تَجۡرِي لِمُسۡتَقَرٍّ لَّهَاۚ ذَٰلِكَ تَقۡدِيرُ ٱلۡعَزِيزِ ٱلۡعَلِيمِ  ۝٣٨
Wash-shamsu tajree limustaqarril lahaa; zaalika taqdeerul `Azeezil Aleem
ፀሐይም ለእርሷ ወደ ሆነው መርጊያ ትሮጣለች፡፡ ይህ የአሸናፊው የዐዋቂው አምላክ ውሳኔ ነው፡፡
🎤 Your recording:
36:39 🔁 0/5
وَٱلۡقَمَرَ قَدَّرۡنَٰهُ مَنَازِلَ حَتَّىٰ عَادَ كَٱلۡعُرۡجُونِ ٱلۡقَدِيمِ  ۝٣٩
Walqamara qaddarnaahu manaazila hattaa `aada kal`ur joonil qadeem
ጨረቃንም የመስፈሪያዎች ባለቤት ሲኾን እንደ ዘንባባ አሮጌ ቀንዘል እስኪኾን ድረስ (መኼዱን) ለካነው፡፡
🎤 Your recording:
36:40 🔁 0/5
لَا ٱلشَّمۡسُ يَنۢبَغِي لَهَآ أَن تُدۡرِكَ ٱلۡقَمَرَ وَلَا ٱلَّيۡلُ سَابِقُ ٱلنَّهَارِۚ وَكُلٌّ فِي فَلَكٍ يَسۡبَحُونَ  ۝٤٠
Lash shamsu yambaghee lahaaa an tudrikal qamara wa lal lailu saabiqun nahaar; wa kullun fee falaki yasbahoon
ፀሐይ ጨረቃን ልትደርስበት አይገባትም፡፡ ሌሊትም ቀንን (ያለ ጊዜው) ቀዳሚ አይኾንም፡፡ ሁሉም በመዞሪያቸው ውስጥ ይዋኛሉ፡፡
🎤 Your recording:
36:41 🔁 0/5
وَءَايَةٌ لَّهُمۡ أَنَّا حَمَلۡنَا ذُرِّيَّتَهُمۡ فِي ٱلۡفُلۡكِ ٱلۡمَشۡحُونِ  ۝٤١
Wa Aayatul lahum annaa hamalnaa zurriyatahum fil fulkil mashhoon
እኛም (የቀድሞ) ትውልዳቸውን በተሞላች መርከብ ውስጥ የጫን መኾናችን ለእነርሱ ምልክት ነው፡፡
🎤 Your recording:
36:42 🔁 0/5
وَخَلَقۡنَا لَهُم مِّن مِّثۡلِهِۦ مَا يَرۡكَبُونَ  ۝٤٢
Wa khalaqnaa lahum mim-mislihee maa yarkaboon
ከመሰሉም በእርሱ የሚሳፈሩበትን ለእነርሱ ፈጠርንላቸው፡፡
🎤 Your recording:
36:43 🔁 0/5
وَإِن نَّشَأۡ نُغۡرِقۡهُمۡ فَلَا صَرِيخَ لَهُمۡ وَلَا هُمۡ يُنقَذُونَ  ۝٤٣
Wa in nashaa nughriqhum falaa sareekha lahum wa laa hum yunqazoon
ብንሻም እናሰጥማቸዋለን፡፡ ለእነርሱም ረዳት የላቸውም፡፡ እነርሱም የሚድዳኑ አይደሉም፡፡
🎤 Your recording:
36:44 🔁 0/5
إِلَّا رَحۡمَةً مِّنَّا وَمَتَٰعًا إِلَىٰ حِينٍ  ۝٤٤
Illaa rahmatam minnaa wa mataa`an ilaa heen
ግን ከእኛ ለኾነው ችሮታና እስከ ጊዜ ሞታቸው ለማጣቀም (አዳንናቸው)፡፡
🎤 Your recording:
36:45 🔁 0/5
وَإِذَا قِيلَ لَهُمُ ٱتَّقُواْ مَا بَيۡنَ أَيۡدِيكُمۡ وَمَا خَلۡفَكُمۡ لَعَلَّكُمۡ تُرۡحَمُونَ  ۝٤٥
Wa izaa qeela lahumuttaqoo maa baina aideekum wa maa khalfakum la`allakum turhamoon
ለእነርሱም «በስተፊታችሁና በኋለችሁ ያለውን ነገር ተጠንቀቁ ይታዘንላችኋልና» በተባሉ ጊዜ (ፊታቸውን ያዞራሉ)፡፡
🎤 Your recording:
36:46 🔁 0/5
وَمَا تَأۡتِيهِم مِّنۡ ءَايَةٍ مِّنۡ ءَايَٰتِ رَبِّهِمۡ إِلَّا كَانُواْ عَنۡهَا مُعۡرِضِينَ  ۝٤٦
Wa maa taateehim min aayatim min ayataati Rabbihim illaa kaanoo `anhaa mu`rideen
ከጌታቸውም ተዓምራት ማንኛይቱም ተዓምር አትመጣላቸውም፤ ከእርሷ የሚሸሹ ቢኾኑ እንጅ፡፡
🎤 Your recording:
36:47 🔁 0/5
وَإِذَا قِيلَ لَهُمۡ أَنفِقُواْ مِمَّا رَزَقَكُمُ ٱللَّهُ قَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لِلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ أَنُطۡعِمُ مَن لَّوۡ يَشَآءُ ٱللَّهُ أَطۡعَمَهُۥٓ إِنۡ أَنتُمۡ إِلَّا فِي ضَلَٰلٍ مُّبِينٍ  ۝٤٧
Wa izaa qeela lahum anfiqoo mimmaa razaqakumul laahu qaalal lazeena kafaroo lillazeena aamanooo anut`imu mal-law yashaaa`ul laahu at`amahooo in antum illaa fee dalaalim mubeen
ለእነርሱም «አላህ ከሰጣችሁ ሲሳይ ለግሱ» በተባሉ ጊዜ እነዚያ የካዱት ለእነዚያ ላመኑት «አላህ ቢሻ ኖሮ የሚያበላውን ሰው እናበላለን? እናንተ በግልጽ ስህተት ውስጥ እንጂ በሌላ ላይ አይደላችሁም» ይላሉ፡፡
🎤 Your recording:
36:48 🔁 0/5
وَيَقُولُونَ مَتَىٰ هَٰذَا ٱلۡوَعۡدُ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ  ۝٤٨
Wa yaqooloona mataa haazal wa`du in kuntum saadiqeen
«እውነተኞችም እንደኾናችሁ ይህ ቀጠሮ መቼ ነው?» ይላሉ፡፡
🎤 Your recording:
36:49 🔁 0/5
مَا يَنظُرُونَ إِلَّا صَيۡحَةً وَٰحِدَةً تَأۡخُذُهُمۡ وَهُمۡ يَخِصِّمُونَ  ۝٤٩
Maa yanzuroona illaa saihatanw waahidatan taa khuzuhum wa hum yakhissimoon
እነርሱ የሚከራከሩ ሲኾኑ በድንገት የምትይዛቸው የኾነችን አንዲትን ጩኸት እንጂ ሌላን አይጠባበቁም፡፡
🎤 Your recording:
36:50 🔁 0/5
فَلَا يَسۡتَطِيعُونَ تَوۡصِيَةً وَلَآ إِلَىٰٓ أَهۡلِهِمۡ يَرۡجِعُونَ  ۝٥٠
Falaa yastatee`oona taw siyatanw-wa laaa ilaaa ahlihim yarji`oon
(ያን ጊዜ) መናዘዝንም አይችሉም፡፡ ወደ ቤተሰቦቻቸወም አይመለሱም፡፡
🎤 Your recording:
36:51 🔁 0/5
وَنُفِخَ فِي ٱلصُّورِ فَإِذَا هُم مِّنَ ٱلۡأَجۡدَاثِ إِلَىٰ رَبِّهِمۡ يَنسِلُونَ  ۝٥١
Wa nufikha fis-soori faizaa hum minal ajdaasi ilaa Rabbihim yansiloon
በቀንዱም ይነፋል፡፡ ወዲያውኑም እነርሱ ከመቃብሮቻቸው ወደ ጌታቸው በፍጥነት ይገሰግሳሉ፡፡
🎤 Your recording:
36:52 🔁 0/5
قَالُواْ يَٰوَيۡلَنَا مَنۢ بَعَثَنَا مِن مَّرۡقَدِنَاۜۗ هَٰذَا مَا وَعَدَ ٱلرَّحۡمَٰنُ وَصَدَقَ ٱلۡمُرۡسَلُونَ  ۝٥٢
Qaaloo yaa wailanaa mam ba`asanaa mim marqadinaa; haaza maa wa`adar Rahmanu wa sadaqal mursaloon
«ወይ ጥፋታችን! ከመኝታችን ማን ቀሰቀሰን? ይህ ያ አዛኙ ጌታ (በእርሱ) የቀጠረን መልክተኞቹም እውነትን የነገሩን ነው» ይላሉ፡፡
🎤 Your recording:
36:53 🔁 0/5
إِن كَانَتۡ إِلَّا صَيۡحَةً وَٰحِدَةً فَإِذَا هُمۡ جَمِيعٌ لَّدَيۡنَا مُحۡضَرُونَ  ۝٥٣
In kaanat illaa saihatanw waahidatan fa-izaa hum jamee`ul ladainaa muhdaroon
(እርሷ) አንዲት ጩኸት እንጂ አይደለችም፡፡ ወዲያውኑም እነርሱ እኛ ዘንድ የሚሰበሰቡ የሚቀርቡ ናቸው፡፡
🎤 Your recording:
36:54 🔁 0/5
فَٱلۡيَوۡمَ لَا تُظۡلَمُ نَفۡسٌ شَيۡـًٔا وَلَا تُجۡزَوۡنَ إِلَّا مَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ  ۝٥٤
Fal-Yawma laa tuzlamu nafsun shai`anw-wa laa tujzawna illaa maa kuntum ta`maloon
«ዛሬም ማንኛይቱም ነፍስ ምንም አትበደልም፡፡ ትሠሩትም የነበራችሁትን እንጂ ሌላን አትመነዱም» (ይባላሉ)፡፡
🎤 Your recording:
36:55 🔁 0/5
إِنَّ أَصۡحَٰبَ ٱلۡجَنَّةِ ٱلۡيَوۡمَ فِي شُغُلٍ فَٰكِهُونَ  ۝٥٥
Inna Ashaabal jannatil Yawma fee shughulin faakihoon
የገነት ሰዎች ዛሬ በእርግጥ በሥራዎች ውስጥ ተደሳቾች ናቸው፡፡
🎤 Your recording:
36:56 🔁 0/5
هُمۡ وَأَزۡوَٰجُهُمۡ فِي ظِلَٰلٍ عَلَى ٱلۡأَرَآئِكِ مُتَّكِـُٔونَ  ۝٥٦
Hum wa azwaajuhum fee zilaalin `alal araaa`iki muttaki`oon
እነርሱም ሚስቶቻቸውም በጥላዎች ውስጥ ናቸው፡፡ ባለ አጎበር አልጋዎች ላይ ተደጋፊዎች ናቸው፡፡
🎤 Your recording:
36:57 🔁 0/5
لَهُمۡ فِيهَا فَٰكِهَةٌ وَلَهُم مَّا يَدَّعُونَ  ۝٥٧
Lahum feehaa faakiha tunw-wa lahum maa yadda`oon
በውስጧ ለእነርሱ ፍራፍሬዎች አሏቸው፡፡ ለእነርሱም የሚፈልጉት ሁሉ አልላቸው፡፡
🎤 Your recording:
36:58 🔁 0/5
سَلَٰمٌ قَوۡلًا مِّن رَّبٍّ رَّحِيمٍ  ۝٥٨
Salaamun qawlam mir Rabbir Raheem
(ለእነርሱም) አዛኝ ከሆነው ጌታ በቃል ሰላምታ አላቸው።
🎤 Your recording:
36:59 🔁 0/5
وَٱمۡتَٰزُواْ ٱلۡيَوۡمَ أَيُّهَا ٱلۡمُجۡرِمُونَ  ۝٥٩
Wamtaazul Yawma ayyuhal mujrimoon
(ይላልም) «እናንተ አመጸኞች ሆይ! ዛሬ (ከምእምናን) ተለዩ፡፡»
🎤 Your recording:
36:60 🔁 0/5
۞ أَلَمۡ أَعۡهَدۡ إِلَيۡكُمۡ يَٰبَنِيٓ ءَادَمَ أَن لَّا تَعۡبُدُواْ ٱلشَّيۡطَٰنَۖ إِنَّهُۥ لَكُمۡ عَدُوٌّ مُّبِينٌ  ۝٦٠
Alam a`had ilaikum yaa Baneee Aadama al-laa ta`budush Shaitaana innahoo lakum `aduwwum mubeen
የአደም ልጆች ሆይ! ሰይጣንን አትገዙ፤ እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና በማለት ወደእናንተ አላዘዝኩምን?
🎤 Your recording:
36:61 🔁 0/5
وَأَنِ ٱعۡبُدُونِيۚ هَٰذَا صِرَٰطٌ مُّسۡتَقِيمٌ  ۝٦١
Wa ani`budoonee; haazaa Siraatum Mustaqeem
ተገዙኝም፤ ይህ ቀጥተኘ መንገድ ነው፤ (በማለትም)፡፡
🎤 Your recording:
36:62 🔁 0/5
وَلَقَدۡ أَضَلَّ مِنكُمۡ جِبِلًّا كَثِيرًاۖ أَفَلَمۡ تَكُونُواْ تَعۡقِلُونَ  ۝٦٢
Wa laqad adalla minkum jibillan kaseeraa; afalam takoonoo ta`qiloon
ከእናንተም ብዙን ፍጡር በእርግጥ አሳስቷል፡፡ የምታውቁም አልነበራችሁምን?
🎤 Your recording:
36:63 🔁 0/5
هَٰذِهِۦ جَهَنَّمُ ٱلَّتِي كُنتُمۡ تُوعَدُونَ  ۝٦٣
Haazihee Jahannamul latee kuntum too`adoon
ይህቺ ያቺ ትቀጠሩዋት የነበረችው ገሀነም ናት፡፡
🎤 Your recording:
36:64 🔁 0/5
ٱصۡلَوۡهَا ٱلۡيَوۡمَ بِمَا كُنتُمۡ تَكۡفُرُونَ  ۝٦٤
Islawhal Yawma bimaa kuntum takfuroon
ትክዱ በነበራችሁት ምክንያት ዛሬ ግቧት (ይባላሉ)፡፡
🎤 Your recording:
36:65 🔁 0/5
ٱلۡيَوۡمَ نَخۡتِمُ عَلَىٰٓ أَفۡوَٰهِهِمۡ وَتُكَلِّمُنَآ أَيۡدِيهِمۡ وَتَشۡهَدُ أَرۡجُلُهُم بِمَا كَانُواْ يَكۡسِبُونَ  ۝٦٥
Al-Yawma nakhtimu `alaaa afwaahihim wa tukallimunaaa aideehim wa tashhadu arjuluhum bimaa kaanoo yaksiboon
ዛሬ በአፎቻቸው ላይ እናትምና እጆቻቸው ያነጋግሩናል፡፡ እግሮቻቸውም ይሠሩት በነበሩት ሁሉ ይመሰክራሉ፡፡
🎤 Your recording:
36:66 🔁 0/5
وَلَوۡ نَشَآءُ لَطَمَسۡنَا عَلَىٰٓ أَعۡيُنِهِمۡ فَٱسۡتَبَقُواْ ٱلصِّرَٰطَ فَأَنَّىٰ يُبۡصِرُونَ  ۝٦٦
Wa law nashaaa`u lata masna `alaaa aiyunihim fasta baqus-siraata fa-annaa yubsiroon
ብንሻም ኖሮ በዐይኖቻቸው ላይ በአበስን ነበር፡፡ መንገድንም (እንደ ልመዳቸው) በተሽቀዳደሙ ነበር፡፡ እንዴትም ያያሉ?
🎤 Your recording:
36:67 🔁 0/5
وَلَوۡ نَشَآءُ لَمَسَخۡنَٰهُمۡ عَلَىٰ مَكَانَتِهِمۡ فَمَا ٱسۡتَطَٰعُواْ مُضِيًّا وَلَا يَرۡجِعُونَ  ۝٦٧
Wa law nashaaa`u lamasakhnaahum `alaa makaanatihim famas-tataa`oo mudiyyanw-wa laa yarji`oon
ብንሻም ኖሮ በስፍራቸው ላይ እንዳሉ ወደ ሌላ ፍጥረት በለወጠናቸው ነበር፡፡ መኼድንም መመለስንም ባልቻሉም ነበር፡፡
🎤 Your recording:
36:68 🔁 0/5
وَمَن نُّعَمِّرۡهُ نُنَكِّسۡهُ فِي ٱلۡخَلۡقِۚ أَفَلَا يَعۡقِلُونَ  ۝٦٨
Wa man nu `ammirhu nunakkishu fil-khalq; afalaa ya`qiloon
ዕድሜውንም የምናረዝመውን ሰው በፍጥረቱ (ወደ ደካማነት) እንመልሰዋለን፤ አያውቁምን?
🎤 Your recording:
36:69 🔁 0/5
وَمَا عَلَّمۡنَٰهُ ٱلشِّعۡرَ وَمَا يَنۢبَغِي لَهُۥٓۚ إِنۡ هُوَ إِلَّا ذِكۡرٌ وَقُرۡءَانٌ مُّبِينٌ  ۝٦٩
Wa maa `allamnaahush shi`ra wa maa yambaghee lah; in huwa illaa zikrunw-wa Qur-aanum mubeen
(ሙሐመድን) ቅኔንም አላስተማርነውም፡፡ ለእርሱም አይግገባውም፡፡ እርሱ (መጽሐፉ) መገሰጫና ገላጭ ቁርኣን እንጅ (ቅኔ) አይደለም፡፡
🎤 Your recording:
36:70 🔁 0/5
لِّيُنذِرَ مَن كَانَ حَيًّا وَيَحِقَّ ٱلۡقَوۡلُ عَلَى ٱلۡكَٰفِرِينَ  ۝٧٠
Liyunzira man kaana haiyanw-wa yahiqqal qawlu `alal-kaafireen
(ግሣጼነቱም ልቡ) ሕያው የኾነን ሰው ሊያስፈራራበትና ቃሉም በከሓዲዎች ላይ ይፈጸም ዘንድ ነው፡፡
🎤 Your recording:
36:71 🔁 0/5
أَوَلَمۡ يَرَوۡاْ أَنَّا خَلَقۡنَا لَهُم مِّمَّا عَمِلَتۡ أَيۡدِينَآ أَنۡعَٰمًا فَهُمۡ لَهَا مَٰلِكُونَ  ۝٧١
Awalam yaraw annaa khalaqnaa lahum mimmaa `amilat aideenaaa an`aaman fahum lahaa maalikoon
እኛ እጆቻችን (ኃይሎቻችን) ከሠሩት ለእነርሱ እንስሳዎችን መፍጠራችንን አያውቁምን? እነርሱም ለእርሷ ባለ መብቶች ናቸው፡፡
🎤 Your recording:
36:72 🔁 0/5
وَذَلَّلۡنَٰهَا لَهُمۡ فَمِنۡهَا رَكُوبُهُمۡ وَمِنۡهَا يَأۡكُلُونَ  ۝٧٢
Wa zallalnaahaa lahum faminhaa rakoobuhum wa minhaa yaakuloon
ለእነርሱም ገራናት፡፡ ስለዚህ ከእርሷ ውስጥ የሚጋልቡት አልለ፡፡ ከእርሷም ይበላሉ፡፡
🎤 Your recording:
36:73 🔁 0/5
وَلَهُمۡ فِيهَا مَنَٰفِعُ وَمَشَارِبُۚ أَفَلَا يَشۡكُرُونَ  ۝٧٣
Wa lahum feehaa manaa fi`u wa mashaarib; afalaa yashkuroon
ለእነርሱም በእርሷ ውስጥ (ሌሎች) ጥቅሞች መጠጦችም አሉዋቸው፡፡ ታዲያ አያመሰግኑምን;
🎤 Your recording:
36:74 🔁 0/5
وَٱتَّخَذُواْ مِن دُونِ ٱللَّهِ ءَالِهَةً لَّعَلَّهُمۡ يُنصَرُونَ  ۝٧٤
Wattakhazoo min doonil laahi aalihatal la`allahum yunsaroon
መረዳትንም በመከጀል ከአላህ ሌላ አማልክትን ያዙ፡፡
🎤 Your recording:
36:75 🔁 0/5
لَا يَسۡتَطِيعُونَ نَصۡرَهُمۡ وَهُمۡ لَهُمۡ جُندٌ مُّحۡضَرُونَ  ۝٧٥
Laa yastatee`oona nasrahum wa hum lahum jundum muhdaroon
መርዳታቸውን አይችሉም፡፡ እነርሱም ለእርሳቸው (ወደ እሳት) የተቀረቡ ሰራዊት ናቸው፡፡
🎤 Your recording:
36:76 🔁 0/5
فَلَا يَحۡزُنكَ قَوۡلُهُمۡۘ إِنَّا نَعۡلَمُ مَا يُسِرُّونَ وَمَا يُعۡلِنُونَ  ۝٧٦
Falaa yahzunka qawluhum; innaa na`lamu maa yusirroona wa maa yu`linoon
ንግግራቸውም አያሳዝንህ፡፡ እኛ የሚደብቁትንም የሚገልጹትንም እናውቃለንና፡፡
🎤 Your recording:
36:77 🔁 0/5
أَوَلَمۡ يَرَ ٱلۡإِنسَٰنُ أَنَّا خَلَقۡنَٰهُ مِن نُّطۡفَةٍ فَإِذَا هُوَ خَصِيمٌ مُّبِينٌ  ۝٧٧
Awalam yaral insaanu annaa khalaqnaahu min nutfatin fa-izaa huwa khaseemum mubeen
ሰውየው እኛ ከፍቶት ጠብታ የፈጠርነው መኾናችን አላወቀምን? ወዲያውም እርሱ (ትንሣኤን በመካድ) ግልጽ ተከራካሪ ይኾናልን?
🎤 Your recording:
36:78 🔁 0/5
وَضَرَبَ لَنَا مَثَلًا وَنَسِيَ خَلۡقَهُۥۖ قَالَ مَن يُحۡيِ ٱلۡعِظَٰمَ وَهِيَ رَمِيمٌ  ۝٧٨
Wa daraba lanaa maslanw-wa nasiya khalqahoo qaala mai-yuhyil`izaama wa hiya rameem
ለእኛም ምሳሌን አደረገልን፡፡ መፈጠሩንም ረሳ፡፡ «አጥንቶችን እነርሱ የበሰበሱ ሲኾኑ ሕያው የሚያደርጋቸው ማነው?» አለ፡፡
🎤 Your recording:
36:79 🔁 0/5
قُلۡ يُحۡيِيهَا ٱلَّذِيٓ أَنشَأَهَآ أَوَّلَ مَرَّةٍۖ وَهُوَ بِكُلِّ خَلۡقٍ عَلِيمٌ  ۝٧٩
Qul yuh yeehal lazeee ansha ahaaa awwala marrah; wa Huwa bikulli khalqin `Aleem
«ያ በመጀመሪያ ጊዜ (ከኢምንት) ያስገኛት ሕያው ያደርጋታል፡፡ እርሱም በፍጡሩ ሁሉ (ኹኔታ) ዐዋቂ ነው» በለው፡፡
🎤 Your recording:
36:80 🔁 0/5
ٱلَّذِي جَعَلَ لَكُم مِّنَ ٱلشَّجَرِ ٱلۡأَخۡضَرِ نَارًا فَإِذَآ أَنتُم مِّنۡهُ تُوقِدُونَ  ۝٨٠
Allazee ja`ala lakum minash shajaril akhdari naaran fa-izaaa antum minhu tooqidoon
ያ ለእናንተ በእርጥብ ዛፍ እሳትን ያደረገላችሁ ነው፡፡ ወዲያውኑም እናንተ ከእርሱ ታቀጣጥላላችሁ፡፡
🎤 Your recording:
36:81 🔁 0/5
أَوَلَيۡسَ ٱلَّذِي خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ بِقَٰدِرٍ عَلَىٰٓ أَن يَخۡلُقَ مِثۡلَهُمۚ بَلَىٰ وَهُوَ ٱلۡخَلَّٰقُ ٱلۡعَلِيمُ  ۝٨١
Awa laisal lazee khalaqas samaawaati wal arda biqaadirin `alaaa ai-yakhluqa mislahum; balaa wa Huwal Khallaaqul `Aleem
ያ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ብጤያቸውን በመፍጠር ላይ ቻይ አይደለምን? ነው እንጅ፡፡ እርሱም በብዙ ፈጣሪው ዐዋቂው ነው፡፡
🎤 Your recording:
36:82 🔁 0/5
إِنَّمَآ أَمۡرُهُۥٓ إِذَآ أَرَادَ شَيۡـًٔا أَن يَقُولَ لَهُۥ كُن فَيَكُونُ  ۝٨٢
Innamaa amruhooo izaaa araada shai`an ai-yaqoola lahoo kun fa-yakoon
ነገሩም አንዳችን በሻ ጊዜ ኹን ማለት ነው፡፡ ወዲያው ይኾናልም፡፡
🎤 Your recording:
36:83 🔁 0/5
فَسُبۡحَٰنَ ٱلَّذِي بِيَدِهِۦ مَلَكُوتُ كُلِّ شَيۡءٍ وَإِلَيۡهِ تُرۡجَعُونَ  ۝٨٣
Fa Subhaanal lazee biyadihee malakootu kulli shai-inw-wa ilaihi turja`oon
ያ የነገሩ ሁሉ ስልጣን በእጁ የኾነው ጌታ ጥራት ይገባው፡፡ ወደእርሱም ትመለሳላችሁ፡፡
🎤 Your recording:
💡 Tap any hidden word to reveal it temporarily — your progress is saved automatically in this browser.

🎉
🎊 Well Done! Memorization Complete
Mishary Rashid Alafasy
Mahmoud Khalil Al-Husary
Abdurrahman As-Sudais
Mohamed Siddiq Al-Minshawi
Abdul Basit Abdul Samad
Ali Al-Hudhaify
Ahmed ibn Ali al-Ajamy
Abu Bakr Ash-Shaatree
Muhammad Ayyoub
Abdullah Basfar
Abdullah Al-Juhani
Maher Al Muaiqly
0:00
0:00
-

ቅዱስ ቁርኣን


Tuesday, August 18, 2026

Don't forget us in your sincere prayers