🔥 0 day streak
📖 Long surah — split into smaller parts to help you focus (128 አንቀጽ)
📚 All Surahs
30%
🎤 Tap the microphone icon 🎙️ next to any verse to record yourself reciting it, then listen back and compare with the reciter.
0/128
16:1 🔁 0/5
أَتَىٰٓ أَمۡرُ ٱللَّهِ فَلَا تَسۡتَعۡجِلُوهُۚ سُبۡحَٰنَهُۥ وَتَعَٰلَىٰ عَمَّا يُشۡرِكُونَ  ۝١
Ataaa amrullaahi falaa tasta`jilooh; Subhaanahoo wa Ta`aalaa `ammaa yushrikoon
የአላህ ትዕዛዝ መጣ፤ ስለዚህ አታስቸኩሉት፤ ከማይገባው ሁሉ ጠራ ከሚያጋሩትም ሁሉ ላቀ፤
🎤 Your recording:
16:2 🔁 0/5
يُنَزِّلُ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةَ بِٱلرُّوحِ مِنۡ أَمۡرِهِۦ عَلَىٰ مَن يَشَآءُ مِنۡ عِبَادِهِۦٓ أَنۡ أَنذِرُوٓاْ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱتَّقُونِ  ۝٢
Yunazzilul malaaa `ikata birroohi min amrihee `alaa mai yashaaa`u min `ibaadiheee an anzirooo annahoo laaa ilaaha illaaa ana fattaqoon
ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ መላእክትን ከራእይ ጋር በፈቃዱ ያወርዳል (ከሓዲዎችን በቅጣት) አስጠንቅቁ፤ እነሆ ከኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ ፍሩኝም ማለትን (አስታውቁ በማለት ያወርዳል)፡፡
🎤 Your recording:
16:3 🔁 0/5
خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ بِٱلۡحَقِّۚ تَعَٰلَىٰ عَمَّا يُشۡرِكُونَ  ۝٣
Khalaqas samaawaati wal arda bilhaqq; Ta`aalaa `ammaa yushrikoon
ሰማያትንና ምድርን በእውነት ፈጠረ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ፡፡
🎤 Your recording:
16:4 🔁 0/5
خَلَقَ ٱلۡإِنسَٰنَ مِن نُّطۡفَةٍ فَإِذَا هُوَ خَصِيمٌ مُّبِينٌ  ۝٤
Khalaqal insaana min nutfatin fa izaa huwa khaseemum mubeen
ሰውን ከፍትወት ጠብታ ፈጠረው፡፡ ከዚያም እርሱ ወዲያውኑ (ትንሣኤን በመካድ) ግልጽ ተከራካሪ ይኾናል፡፡
🎤 Your recording:
16:5 🔁 0/5
وَٱلۡأَنۡعَٰمَ خَلَقَهَاۖ لَكُمۡ فِيهَا دِفۡءٌ وَمَنَٰفِعُ وَمِنۡهَا تَأۡكُلُونَ  ۝٥
Wal an `amaa khalaqahaa; lakum feehaa dif`unw wa manaafi`u wa minhaa taakuloon
ግመልን፣ ከብትን፣ ፍየልንም በርሷ (ብርድ መከላከያ) ሙቀት ጥቅሞችም ያሉባት ስትኾን ለእናንተ ፈጠረላችሁ፡፡ ከርሷም ትበላላችሁ፡፡
🎤 Your recording:
16:6 🔁 0/5
وَلَكُمۡ فِيهَا جَمَالٌ حِينَ تُرِيحُونَ وَحِينَ تَسۡرَحُونَ  ۝٦
Wa lakum feehaa jamaalun heena tureehoona wa heena tasrahoon
ለእናንተም በእርሷ ወደ ማረፊያዋ በምትመልሷት ጊዜ በምታሰማሩዋትም ጊዜ ውበት አላችሁ፡፡
🎤 Your recording:
16:7 🔁 0/5
وَتَحۡمِلُ أَثۡقَالَكُمۡ إِلَىٰ بَلَدٍ لَّمۡ تَكُونُواْ بَٰلِغِيهِ إِلَّا بِشِقِّ ٱلۡأَنفُسِۚ إِنَّ رَبَّكُمۡ لَرَءُوفٌ رَّحِيمٌ  ۝٧
Wa tahmilu asqaalakum ilaa baladil lam takoonoo baaligheehi illaa bishiqqil anfus; inna Rabbakum la Ra`oofur Raheem
ጓዞቻችሁንም በነፍሶች ችግር እንጂ ወደማትደርሱበት አገር ትሸከማለች፡፡ ጌታችሁ በእርግጥ ሩኅሩኅ አዛኝ ነውና፡፡
🎤 Your recording:
16:8 🔁 0/5
وَٱلۡخَيۡلَ وَٱلۡبِغَالَ وَٱلۡحَمِيرَ لِتَرۡكَبُوهَا وَزِينَةًۚ وَيَخۡلُقُ مَا لَا تَعۡلَمُونَ  ۝٨
Walkhaila wal bighaala wal hameera litarkaboohaa wa zeenah; wa yakhluqu maa laa ta`lamoon
ፈረሶችንም፣ በቅሎዎችንም፣ አህዮችንም ልትቀመጡዋቸውና ልታጌጡባቸው (ፈጠረላችሁ)፡፡ የማታውቁትንም ድንቅ ነገር ይፈጥራል፡፡
🎤 Your recording:
16:9 🔁 0/5
وَعَلَى ٱللَّهِ قَصۡدُ ٱلسَّبِيلِ وَمِنۡهَا جَآئِرٌۚ وَلَوۡ شَآءَ لَهَدَىٰكُمۡ أَجۡمَعِينَ  ۝٩
Wa `alal laahi qasdus sabeeli wa minhaa jaaa`ir; wa law shaaa`a lahadaakum ajma`een
በአላህም ላይ (በችሮታው) ቀጥተኛውን መንገድ መግለጽ አለበት፡፡ ከእርሷም (ከመንገድ) ጠማማ አልለ፡፡ በሻም ኖሮ ሁላችሁንም በእርግጥ ባቀናችሁ ነበር፡፡
🎤 Your recording:
16:10 🔁 0/5
هُوَ ٱلَّذِيٓ أَنزَلَ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءًۖ لَّكُم مِّنۡهُ شَرَابٌ وَمِنۡهُ شَجَرٌ فِيهِ تُسِيمُونَ  ۝١٠
Huwal lazeee anzala minas samaaa`i maaa`al lakum minhu sharaabunw wa minhu shajarun feehi tuseemoon
እርሱ ያ ከሰማይ ውሃን ያወረደ ነው፡፡ ከእርሱ ለእናንተ መጠጥ አላችሁ፡፡ ከእርሱም (እንስሳዎችን) በእርሱ የምታሰማሩበት ዛፍ (ይበቅልበታል)፡፡
🎤 Your recording:
16:11 🔁 0/5
يُنۢبِتُ لَكُم بِهِ ٱلزَّرۡعَ وَٱلزَّيۡتُونَ وَٱلنَّخِيلَ وَٱلۡأَعۡنَٰبَ وَمِن كُلِّ ٱلثَّمَرَٰتِۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةً لِّقَوۡمٍ يَتَفَكَّرُونَ  ۝١١
Yumbitu lakum bihiz zar`a wazzaitoona wanna kheela wal-a`naaba wa min kullis samaraat, inna fee zaalika la Aayatal liqawminy yatafakkaroon
በእርሱ ለእናንተ አዝመራን፣ (የዘይት) ወይራንም፣ ዘምባባዎችንም (ተምርን)፣ ወይኖችንም፣ ከፍሬዎችም ሁሉ ያበቅልላችኋል፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች በእርግጥ ተዓምርአልለ፡፡
🎤 Your recording:
16:12 🔁 0/5
وَسَخَّرَ لَكُمُ ٱلَّيۡلَ وَٱلنَّهَارَ وَٱلشَّمۡسَ وَٱلۡقَمَرَۖ وَٱلنُّجُومُ مُسَخَّرَٰتُۢ بِأَمۡرِهِۦٓۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٍ لِّقَوۡمٍ يَعۡقِلُونَ  ۝١٢
Wa sakkhkhara lakumul laila wannahaara wash shamsa walqamara wannujoomu musakhkharaatum bi amrih; inna fee zaalika la Aayaatil liqawminy ya`qiloon
ለእናንተም ሌሊትንና ቀንን፣ ፀሐይንና ጨረቃንም ገራላችሁ፡፡ ከዋክብትም በፈቃዱ የተገሩ ናቸው፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚያውቁ ሕዝቦች በእርግጥ ተዓምራቶች አልሉ፡፡
🎤 Your recording:
16:13 🔁 0/5
وَمَا ذَرَأَ لَكُمۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ مُخۡتَلِفًا أَلۡوَٰنُهُۥٓۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةً لِّقَوۡمٍ يَذَّكَّرُونَ  ۝١٣
Wa maa zara a lakum fil ardi mukhtalifan alwaanuh; inna fee zaalika la Aayatal liqawminy yazakkaroon
በምድርም ላይ መልኮቹ የተለያዩ ኾኖ ለእናንተ የፈጠረላችሁን ሁሉ (ገራላችሁ)፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚገሰጹ ሕዝቦች በእርግጥ ተዓምር አልለ፡፡
🎤 Your recording:
16:14 🔁 0/5
وَهُوَ ٱلَّذِي سَخَّرَ ٱلۡبَحۡرَ لِتَأۡكُلُواْ مِنۡهُ لَحۡمًا طَرِيًّا وَتَسۡتَخۡرِجُواْ مِنۡهُ حِلۡيَةً تَلۡبَسُونَهَاۖ وَتَرَى ٱلۡفُلۡكَ مَوَاخِرَ فِيهِ وَلِتَبۡتَغُواْ مِن فَضۡلِهِۦ وَلَعَلَّكُمۡ تَشۡكُرُونَ  ۝١٤
Wa Huwal lazee sakhkharal bahra litaakuloo minhu lahman tariyyanw wa tastakhrijoo minhu hilyatan talbasoonahaa wa taral fulka mawaakhira feehi wa litabtaghoo min fadlihee wa la`allakum tashkuroon
እርሱም ያ ባሕርን ከእርሱ እርጥብ ስጋን ልትበሉና ከእርሱም የምትለብሱትን ጌጣጌጥ ታወጡ ዘንድ የገራ ነው፡፡ መርከቦችንም በውስጡ (ውሃውን) ቀዳጆች ኾነው (ሲንሻለሉ) ታያለህ፡፡ ከችሮታው ልትፈልጉና ልታመሰግኑም (ገራላችሁ)፡፡
🎤 Your recording:
16:15 🔁 0/5
وَأَلۡقَىٰ فِي ٱلۡأَرۡضِ رَوَٰسِيَ أَن تَمِيدَ بِكُمۡ وَأَنۡهَٰرًا وَسُبُلًا لَّعَلَّكُمۡ تَهۡتَدُونَ  ۝١٥
Wa alqaa fil ardi rawaasiya an tameeda bikum wa anhaaranw wa sublulal la `allakum tahtadoon
በምድርም ውስጥ በእናንተ እንዳታረገርግ ተራራዎችን ጣለባት፡፡ ጂረቶችንም፣ መንገዶችንም ትመሩ ዘንድ (አደረገ)፡፡
🎤 Your recording:
16:16 🔁 0/5
وَعَلَٰمَٰتٍۚ وَبِٱلنَّجۡمِ هُمۡ يَهۡتَدُونَ  ۝١٦
Wa `alaamaat; wa bin najmi hum yahtadoon
ምልክቶችንም (አደረገ)፡፡ በከዋክብትም እነሱ ይምመራሉ፡፡
🎤 Your recording:
16:17 🔁 0/5
أَفَمَن يَخۡلُقُ كَمَن لَّا يَخۡلُقُۚ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ  ۝١٧
Afamany yakhluqu kamallaa yakhluq; afalaa tazak karoon
የሚፈጥር እንደማይፈጥር ነውን አትገሰጹምን
🎤 Your recording:
16:18 🔁 0/5
وَإِن تَعُدُّواْ نِعۡمَةَ ٱللَّهِ لَا تُحۡصُوهَآۗ إِنَّ ٱللَّهَ لَغَفُورٌ رَّحِيمٌ  ۝١٨
Wa in ta`uddoo ni`matal laahi laa tuhsoohaa; innal laaha la Ghafoorur Raheem
የአላህንም ጸጋ ብትቆጥሩ አትዘልቋትም፡፡ አላህ በእርግጥ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡
🎤 Your recording:
16:19 🔁 0/5
وَٱللَّهُ يَعۡلَمُ مَا تُسِرُّونَ وَمَا تُعۡلِنُونَ  ۝١٩
Wallaahu ya`lamu maa tusirroona wa maa tu`linoon
አላህም የምትደብቁትንና የምትገልጹትን ሁሉ ያውቃል፡፡
🎤 Your recording:
16:20 🔁 0/5
وَٱلَّذِينَ يَدۡعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ لَا يَخۡلُقُونَ شَيۡـًٔا وَهُمۡ يُخۡلَقُونَ  ۝٢٠
Wallazeena yad`oona min doonil laahi laa yakhluqoona shai`anw wa hum yukhlaqoon
እነዚያም ከአላህ ሌላ የምትገዟቸው ምንንም አይፈጥሩም፡፡ እነርሱም ይፈጠራሉ፤
🎤 Your recording:
16:21 🔁 0/5
أَمۡوَٰتٌ غَيۡرُ أَحۡيَآءٍۖ وَمَا يَشۡعُرُونَ أَيَّانَ يُبۡعَثُونَ  ۝٢١
Amwaatun ghairu ahyaaa`inw wa maa yash`uroona aiyaana yub`asoon
ሕያው ያልኾኑ ሙታን ናቸው፡፡ መቼ እንደሚቀሰቀሱም አያውቁም፡፡
🎤 Your recording:
16:22 🔁 0/5
إِلَٰهُكُمۡ إِلَٰهٌ وَٰحِدٌۚ فَٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ بِٱلۡأٓخِرَةِ قُلُوبُهُم مُّنكِرَةٌ وَهُم مُّسۡتَكۡبِرُونَ  ۝٢٢
Illahukum Ilaahunw Waahid; fallazeena laa yu`minoona bil Aakhirati quloobuhum munkiratunw wa hum mustakbiroon
አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ እነዚያም በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት ልቦቻቸው ከሓዲዎች ናቸው፡፡ እነሱም የኮሩ ናቸው፤ (አያምኑም)፡፡
🎤 Your recording:
16:23 🔁 0/5
لَا جَرَمَ أَنَّ ٱللَّهَ يَعۡلَمُ مَا يُسِرُّونَ وَمَا يُعۡلِنُونَۚ إِنَّهُۥ لَا يُحِبُّ ٱلۡمُسۡتَكۡبِرِينَ  ۝٢٣
Laa jarama annal laaha ya`lamu maa yusirrona wa ma yu`linoon; innahoo laa yuhibbul mustakbireen
አላህ የሚደብቁትንና የሚገልጹትን ሁሉ የሚያውቅ ለመኾኑ ጥርጣሬ የለበትም፡፡ እርሱ ኩሩዎችን አይወድም፡፡
🎤 Your recording:
16:24 🔁 0/5
وَإِذَا قِيلَ لَهُم مَّاذَآ أَنزَلَ رَبُّكُمۡ قَالُوٓاْ أَسَٰطِيرُ ٱلۡأَوَّلِينَ  ۝٢٤
Wa izaa qeela lahum maazaaa anzala Rabbukum qaaloo asaateerul awwaleen
ለእነርሱም «ጌታችሁ (በሙሐመድ ላይ) ምንን አወረደ» በተባሉ ጊዜ «(እርሱ) የመጀመሪያዎቹ ሕዝቦች ተረቶች ነው» ይላሉ፡፡
🎤 Your recording:
16:25 🔁 0/5
لِيَحۡمِلُوٓاْ أَوۡزَارَهُمۡ كَامِلَةً يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ وَمِنۡ أَوۡزَارِ ٱلَّذِينَ يُضِلُّونَهُم بِغَيۡرِ عِلۡمٍۗ أَلَا سَآءَ مَا يَزِرُونَ  ۝٢٥
Liyahmilooo awzaarahum kaamilatany Yawmal Qiyaamati wa min awzaaril lazeena yudilloonahum bighairi `ilm; alaa saaa`a maa yaziroon
(ይህንንም የሚሉት) በትንሣኤ ቀን ኀጢኣቶቻቸውን በሙሉ ከእነዚያም ያለ ዕውቀት ኾነው ከሚያጠሟቸው ሰዎች ኀጢአቶች ከፊሉን ሊሸከሙ ነው፡፡ ንቁ! የሚሸከሙት ኃጢኣት ምንኛ ከፋ!
🎤 Your recording:
16:26 🔁 0/5
قَدۡ مَكَرَ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡ فَأَتَى ٱللَّهُ بُنۡيَٰنَهُم مِّنَ ٱلۡقَوَاعِدِ فَخَرَّ عَلَيۡهِمُ ٱلسَّقۡفُ مِن فَوۡقِهِمۡ وَأَتَىٰهُمُ ٱلۡعَذَابُ مِنۡ حَيۡثُ لَا يَشۡعُرُونَ  ۝٢٦
Qad makaral lazeena min qablihim fa atal laahu bunyaa nahum minal qawaa`idi fakharra `alaihimus saqfu min fawqihim wa ataahumul `azaabu min haisu laa yash`uroon
እነዚያ ከእነሱ (ከቁረይሾች) በፊት የነበሩት በእርግጥ መከሩ፡፡ አላህም ሕንጻዎቻቸውን ከመሠረቶቻቸው አፈረሰ፡፡ ጣሪያውም በእነሱ ላይ ከበላያቸው ወደቀባቸው፡፡ ቅጣቱም ከማያውቁት ሥፍራ መጣባቸው፡፡
🎤 Your recording:
16:27 🔁 0/5
ثُمَّ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ يُخۡزِيهِمۡ وَيَقُولُ أَيۡنَ شُرَكَآءِيَ ٱلَّذِينَ كُنتُمۡ تُشَٰٓقُّونَ فِيهِمۡۚ قَالَ ٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡعِلۡمَ إِنَّ ٱلۡخِزۡيَ ٱلۡيَوۡمَ وَٱلسُّوٓءَ عَلَى ٱلۡكَٰفِرِينَ  ۝٢٧
Summa Yawmal Qiyaamati yukhzeehim wa yaqoolu aina shurakaaa`iyal lazeena kuntum tushaaaqqoona feehim; qaalal lazeena ootul `ilma innal khizyal Yawma wassooo`a `alal kaafireen
ከዚያም በትንሣኤ ቀን ያዋርዳቸዋል፡፡ እነዚያም «በእነሱ (ጉዳይ) ትከራከሩኝ የነበራችሁት ተጋሪዎቼ የት ናቸው» ይላቸዋል፡፡ «እነዚያ ዕውቀትን የተሰጡት ዛሬ ሐፍረቱና ቅጣቱ በእርግጥ በከሓዲዎች ላይ ነው» ይላሉ፡፡
🎤 Your recording:
16:28 🔁 0/5
ٱلَّذِينَ تَتَوَفَّىٰهُمُ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ ظَالِمِيٓ أَنفُسِهِمۡۖ فَأَلۡقَوُاْ ٱلسَّلَمَ مَا كُنَّا نَعۡمَلُ مِن سُوٓءِۭۚ بَلَىٰٓۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلِيمُۢ بِمَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ  ۝٢٨
Allazeena tatawaf faahu mul malaaa`ikatu zaalimeee anfusihim fa alqawus salama maa kunnaa na`malu min sooo`; balaaa innal laaha `aleemum bimaa kuntum ta`maloon
(እነርሱ) «እነዚያ ነፍሶቻቸውን በዳይ ኾነው መላእክት የሚገድሏቸው ናቸው፡፡ ከክፉ ሥራ ምንም ነገር የምንሠራም አልነበርን» (ሲሉ) ታዛዥነታቸውን ይገልጻሉ፡፡ «በእውነት አላህ ትሰሩት የነበራችሁትን ነገር ዐዋቂ ነው» (ይባላሉ)፡፡
🎤 Your recording:
16:29 🔁 0/5
فَٱدۡخُلُوٓاْ أَبۡوَٰبَ جَهَنَّمَ خَٰلِدِينَ فِيهَاۖ فَلَبِئۡسَ مَثۡوَى ٱلۡمُتَكَبِّرِينَ  ۝٢٩
Fadkhulooo abwaaba jahannama khaalideena feeha falabi`sa maswal mutakab bireen
«የገሀነምንም ደጃፎች በውስጧ ዘውታሪዎች ስትኾኑ ግቡ» (ይባላሉ)፡፡ የኩሩዎችም መኖሪያ (ገሀነም) በእርግጥ ከፋች!
🎤 Your recording:
16:30 🔁 0/5
۞ وَقِيلَ لِلَّذِينَ ٱتَّقَوۡاْ مَاذَآ أَنزَلَ رَبُّكُمۡۚ قَالُواْ خَيۡرًاۗ لِّلَّذِينَ أَحۡسَنُواْ فِي هَٰذِهِ ٱلدُّنۡيَا حَسَنَةٌۚ وَلَدَارُ ٱلۡأٓخِرَةِ خَيۡرٌۚ وَلَنِعۡمَ دَارُ ٱلۡمُتَّقِينَ  ۝٣٠
Wa qeela lillazeenat taqaw maazaaa anzala Rabbukum; qaaloo khairaa; lillazeena absanoo fee haazihid dunyaa hasanah; wa la Daarul Aakhirati khair; wa lani`ma daarul muttaqeen
ለእነዚያም ለተጠነቀቁት «ጌታችሁ ምንን ነገር አወረደ» ተባሉ፡፡ «መልካምን ነገር» አሉ፡፡ ለእነዚያ ደግ ለሠሩት በዚሀች በቅርቢቱ ዓለም መልካም ኑሮ አላቸው፡፡ የመጨረሻይቱም አገር በእርግጥ በላጭ ናት፡፡ የጥንቁቆቹም አገር ምን ታምር!
🎤 Your recording:
16:31 🔁 0/5
جَنَّٰتُ عَدۡنٍ يَدۡخُلُونَهَا تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُۖ لَهُمۡ فِيهَا مَا يَشَآءُونَۚ كَذَٰلِكَ يَجۡزِي ٱللَّهُ ٱلۡمُتَّقِينَ  ۝٣١
Jannaatu `Adniny yadkhuloonahaa tajree min tahtihal anhaaru lahum feehaa maa yashaaa`oon; kazaalika yajzil laahul muttaqeen
(እርሷም) የሚገቡዋትና በሥርዋ ወንዞች የሚፈሱባት ስትኾን የመኖሪያ አትክልቶች ናት፡፡ ለእነሱም በወስጧ የሚሹት ሁሉ አላቸው፡፡ እንደዚሁ አላህ ጥንቁቆችን ይመነዳል፡፡
🎤 Your recording:
16:32 🔁 0/5
ٱلَّذِينَ تَتَوَفَّىٰهُمُ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ طَيِّبِينَ يَقُولُونَ سَلَٰمٌ عَلَيۡكُمُ ٱدۡخُلُواْ ٱلۡجَنَّةَ بِمَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ  ۝٣٢
Allazeena tatawaf faahumul malaaa`ikatu taiyibeena yaqooloona salaamun `alai kumud khulul Jannata bimaa kuntum ta`maloon
እነዚያ በመልካም ኹኔታ ላይ ኾነው መላእክት «ሰላም በእናንተ ላይ» እያሉ የሚገድሏቸው ናቸው፡፡ «ትሠሩት በነበራችሁት ሥራ ገነትን ግቡ» (ይባላሉ)፡፡
🎤 Your recording:
16:33 🔁 0/5
هَلۡ يَنظُرُونَ إِلَّآ أَن تَأۡتِيَهُمُ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ أَوۡ يَأۡتِيَ أَمۡرُ رَبِّكَۚ كَذَٰلِكَ فَعَلَ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡۚ وَمَا ظَلَمَهُمُ ٱللَّهُ وَلَٰكِن كَانُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ يَظۡلِمُونَ  ۝٣٣
Hal yanzuroona illaaa an taatiyahumul malaaa`ikatu aw yaatiya amru Rabbik; kazaalika fa`alal lazeena min qablihim; wa maa zalamahumul laahu wa laakin kaanoo anfusahum yazlimoon
(ከሓዲዎች) መላእክት ወደ እነሱ መምጣትን ወይም የጌታህ ትእዛዝ መምጣቱን እንጂ አይጠባበቁም፡፡ ከእነሱ በፊት የነበሩት እንደዚህ ሠርተዋል፡፡ አላህም አልበደላቸውም፤ ግን ነፍሶቻቸውን የሚበድሉ ነበሩ፡፡
🎤 Your recording:
16:34 🔁 0/5
فَأَصَابَهُمۡ سَيِّـَٔاتُ مَا عَمِلُواْ وَحَاقَ بِهِم مَّا كَانُواْ بِهِۦ يَسۡتَهۡزِءُونَ  ۝٣٤
Fa asaabahum saiyi aatu maa `amiloo wa haaqa bihim maa kaano bihee yastahzi`oon
የሠሩዋቸውም ኀጢአቶች (ቅጣት) አገኛቸው፡፡ በእርሱም ይሳለቁበት የነበሩት ሁሉ በነሱ ላይ ወረደባቸው፡፡
🎤 Your recording:
16:35 🔁 0/5
وَقَالَ ٱلَّذِينَ أَشۡرَكُواْ لَوۡ شَآءَ ٱللَّهُ مَا عَبَدۡنَا مِن دُونِهِۦ مِن شَيۡءٍ نَّحۡنُ وَلَآ ءَابَآؤُنَا وَلَا حَرَّمۡنَا مِن دُونِهِۦ مِن شَيۡءٍۚ كَذَٰلِكَ فَعَلَ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡۚ فَهَلۡ عَلَى ٱلرُّسُلِ إِلَّا ٱلۡبَلَٰغُ ٱلۡمُبِينُ  ۝٣٥
Wa qaalal lazeena ashrakoo law shaaa`al laahu ma `abadnaa min doonihee min shai`in nahnu wa laaa aabaaa`unaa wa laa harramnaa min doonihee min shai`; kazaalika fa`alal lazeena min qablihim fahal `alar Rusuli illal balaaghul mubeen
እነዚያም (ጣዖታትን) ያጋሩት «አላህ በሻ ኖሮ ከእርሱ ሌላ እኛም አባቶቻችንም ምንንም ባልተገዛን ነበር፤ ያለእርሱም (ትእዛዝ) ምንንም እርም ባላደረግን ነበር አሉ፡፡» እነዚያም ከነሱ በፊት የነበሩት እነደዚሁ ሠሩ፡፡ በመልክተኞቹም ላይ ግልፅ ማድረስ ብቻ እንጂ ሌላ የለባቸውም፡፡
🎤 Your recording:
16:36 🔁 0/5
وَلَقَدۡ بَعَثۡنَا فِي كُلِّ أُمَّةٍ رَّسُولًا أَنِ ٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ وَٱجۡتَنِبُواْ ٱلطَّٰغُوتَۖ فَمِنۡهُم مَّنۡ هَدَى ٱللَّهُ وَمِنۡهُم مَّنۡ حَقَّتۡ عَلَيۡهِ ٱلضَّلَٰلَةُۚ فَسِيرُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ فَٱنظُرُواْ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلۡمُكَذِّبِينَ  ۝٣٦
Wa laqad ba`asnaa fee kulli ummatir Rasoolan ani`budul laaha wajtanibut Taaghoota faminhum man hadal laahu wa minhum man haqqat `alaihid dalaalah; faseeroo fil ardi fanzuroo kaifa kaana `aaqibatul mukazzibeen
በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ «አላህን ተገዙ፤ ጣዖትንም ራቁ» በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል፡፡ ከእነሱም ውስጥ አላህ ያቀናው ሰው አልለ፡፡ ከእነሱም ውስጥ በእርሱ ላይ ጥመት የተረጋገጠበት ሰው አልለ፡፡ በምድርም ላይ ኺዱ፤ የአስተባባዮችም መጨረሻ እንዴት እንደ ነበረ ተመልከቱ፡፡
🎤 Your recording:
16:37 🔁 0/5
إِن تَحۡرِصۡ عَلَىٰ هُدَىٰهُمۡ فَإِنَّ ٱللَّهَ لَا يَهۡدِي مَن يُضِلُّۖ وَمَا لَهُم مِّن نَّٰصِرِينَ  ۝٣٧
In tahris `alaa hudaahum fa innal laaha laa yahdee mai yudillu wa maa lahum min naasireen
በመቅናታቸው ላይ ብትጓጓ (ምንም ልታደርግ አትችልም)፡፡ አላህ የሚጠመውን ሰው አያቀናውምና፡፡ ለእነሱም ከረዳቶች ምንም የላቸውም፡፡
🎤 Your recording:
16:38 🔁 0/5
وَأَقۡسَمُواْ بِٱللَّهِ جَهۡدَ أَيۡمَٰنِهِمۡ لَا يَبۡعَثُ ٱللَّهُ مَن يَمُوتُۚ بَلَىٰ وَعۡدًا عَلَيۡهِ حَقًّا وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعۡلَمُونَ  ۝٣٨
Wa aqsamoo billaahi jahda aimaanihim laa yab`asul laahu mai yamoot; balaa wa`dan `alaihi haqqanw wa laakinna aksaran naasi laa ya`lamoon
መሓሎቻቸውምን አላህ የሚሞትን ሰው አያስነሳም ሲሉ በአላህ ስም ማሉ፡፡ ሐሰት ነው (ያስነሳቸዋል)፡፡ በእርሱ ላይ ቃል ኪዳን ገብቷል፡፡ አረጋግጧል፤ ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም፡፡
🎤 Your recording:
16:39 🔁 0/5
لِيُبَيِّنَ لَهُمُ ٱلَّذِي يَخۡتَلِفُونَ فِيهِ وَلِيَعۡلَمَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ أَنَّهُمۡ كَانُواْ كَٰذِبِينَ  ۝٣٩
Liyubaiyina lahumul lazee yakhtalifoona feehi wa liya`lamal lazeena kafarooo annahum kaanoo kaazibeen
(የሚቀሰቅሳቸውም) ለእነሱ ያንን በእርሱ የሚለያዩበትን ሊገልጽላቸው፤ እነዚያ የካዱትም እነሱ ውሸታሞች የነበሩ መኾናቸውን እንዲያውቁ ነው፡፡
🎤 Your recording:
16:40 🔁 0/5
إِنَّمَا قَوۡلُنَا لِشَيۡءٍ إِذَآ أَرَدۡنَٰهُ أَن نَّقُولَ لَهُۥ كُن فَيَكُونُ  ۝٤٠
Innamaa qawlunaa lisha y`in izaa aradnaahu an naqoola lahoo kun fa yakoon
ለማንኛውም ነገር (መኾኑን) በሻነው ጊዜ ቃላችን ለእርሱ «ኹን» ማለት ብቻ ነው፤ ወዲውም ይኾናል፡፡
🎤 Your recording:
16:41 🔁 0/5
وَٱلَّذِينَ هَاجَرُواْ فِي ٱللَّهِ مِنۢ بَعۡدِ مَا ظُلِمُواْ لَنُبَوِّئَنَّهُمۡ فِي ٱلدُّنۡيَا حَسَنَةًۖ وَلَأَجۡرُ ٱلۡأٓخِرَةِ أَكۡبَرُۚ لَوۡ كَانُواْ يَعۡلَمُونَ  ۝٤١
Wallazeena haajaroo fil laahi mim ba`di maa zulimoo lanubawwi` annahum fiddunyaa hasanatanw wa la ajrul Aakhirati akbar; law kaanoo ya`lamoon
እነዚያም ከተበደሉ በኋላ በአላህ (መንገድ ላይ) የተሰደዱት በቅርቢቱ ዓለም መልካሚቱን አገር (መዲናን) በእርግጥ እናሰፍራቸዋለን፡፡ የመጨረሻይቱም ዓለም ምንዳ ታላቅ ነው፡፡ (ከሓዲዎች) ቢያውቁ ኖሮ (በተከተሏቸው ነበር)፡፡
🎤 Your recording:
16:42 🔁 0/5
ٱلَّذِينَ صَبَرُواْ وَعَلَىٰ رَبِّهِمۡ يَتَوَكَّلُونَ  ۝٤٢
Allazeena sabaroo wa `alaa Rabbihim yatawak kaloon
(እነርሱ) እነዚያ የታገሱት በጌታቸውም ላይ የሚጠጉት ናቸው፡፡
🎤 Your recording:
16:43 🔁 0/5
وَمَآ أَرۡسَلۡنَا مِن قَبۡلِكَ إِلَّا رِجَالًا نُّوحِيٓ إِلَيۡهِمۡۖ فَسۡـَٔلُوٓاْ أَهۡلَ ٱلذِّكۡرِ إِن كُنتُمۡ لَا تَعۡلَمُونَ  ۝٤٣
Wa maaa arsalnaa min qablika illaa rijaalan nooheee ilaihim; fas`alooo ahlaz zikri in kuntum laa ta`lamoon
ከአንተም በፊት ወደእነሱ ወሕይን (ራእይን) የምናወርድላቸውን ሰዎችን እንጂ ሌላን አልላክንም፡፡ የማታውቁም ብትኾኑ የዕውቀትን ባለቤቶች ጠይቁ፡፡
🎤 Your recording:
16:44 🔁 0/5
بِٱلۡبَيِّنَٰتِ وَٱلزُّبُرِۗ وَأَنزَلۡنَآ إِلَيۡكَ ٱلذِّكۡرَ لِتُبَيِّنَ لِلنَّاسِ مَا نُزِّلَ إِلَيۡهِمۡ وَلَعَلَّهُمۡ يَتَفَكَّرُونَ  ۝٤٤
Bilbaiyinaati waz Zubur; wa anzalnaaa ilaikaz Zikra litubaiyina linnaasi maa nuzzila ilaihim wa la`allahum yatafakkaroon
በግልጽ ማስረጃዎችና በመጻሕፍት (ላክናቸው)፡፡ ወደ አንተም ለሰዎች ወደእነሱ የተወረደውን (ፍች) ልትገልጽላቸውና ያስተነትኑም ዘንድ ቁርኣንን አወረድን፡፡
🎤 Your recording:
16:45 🔁 0/5
أَفَأَمِنَ ٱلَّذِينَ مَكَرُواْ ٱلسَّيِّـَٔاتِ أَن يَخۡسِفَ ٱللَّهُ بِهِمُ ٱلۡأَرۡضَ أَوۡ يَأۡتِيَهُمُ ٱلۡعَذَابُ مِنۡ حَيۡثُ لَا يَشۡعُرُونَ  ۝٤٥
Afa aminal lazeena makarus saiyi aati ai yakhsifal laahu bihimul arda aw yaaa tiyahumul `azaabu min haisu laa yash`uroon
እነዚያ መጥፎዎችን የዶለቱ አላህ በእነሱ ምድርን የሚገለብጥባቸው ወይም ከማያውቁት ስፍራ ቅጣት የሚመጣባቸው መኾኑን አይፈሩምን
🎤 Your recording:
16:46 🔁 0/5
أَوۡ يَأۡخُذَهُمۡ فِي تَقَلُّبِهِمۡ فَمَا هُم بِمُعۡجِزِينَ  ۝٤٦
Aw yaakhuzahum fee taqallubihim famaa hum bi mu`jizeen
ወይም (ካገር ወደ አገር) በሚዛወሩበት ጊዜ የሚይዛቸው መኾኑን (አይፈሩምን) እነሱም አሸናፊዎች አይደሉም፡፡
🎤 Your recording:
16:47 🔁 0/5
أَوۡ يَأۡخُذَهُمۡ عَلَىٰ تَخَوُّفٍ فَإِنَّ رَبَّكُمۡ لَرَءُوفٌ رَّحِيمٌ  ۝٤٧
Aw yaakhuzahum `alaa takhawwuf; fa inna Rabbakum la Ra`oofur Raheem
ወይም ቀስ በቀስ በማጉደል ላይ የሚይዛቸው መኾኑን (አይፈሩምን) ጌታችሁም በእርግጥ ርኅሩኅ አዛኝ ነው፡፡
🎤 Your recording:
16:48 🔁 0/5
أَوَلَمۡ يَرَوۡاْ إِلَىٰ مَا خَلَقَ ٱللَّهُ مِن شَيۡءٍ يَتَفَيَّؤُاْ ظِلَٰلُهُۥ عَنِ ٱلۡيَمِينِ وَٱلشَّمَآئِلِ سُجَّدًا لِّلَّهِ وَهُمۡ دَٰخِرُونَ  ۝٤٨
Awa lam yaraw ilaa maa khalaqal laahu min shai`iny-yatafaiya`u zilaaluhoo `anil yameeni washshamaaa` ili sujjadal lillaahi wa hum daakhiroon
ወደዚያ ከማንኛውም ነገር አላህ ወደ ፈጠረው ጥላዎቹ እነርሱ የተዋረዱ ሲኾኑ ለአላህ ሰጋጆች ኾነው ከቀኝና ከግራዎች ወደሚዛወሩት አላዩምን
🎤 Your recording:
16:49 🔁 0/5
وَلِلَّهِۤ يَسۡجُدُۤ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِ مِن دَآبَّةٍ وَٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ وَهُمۡ لَا يَسۡتَكۡبِرُونَ  ۝٤٩
Wa lillaahi yasjudu maa fis samaawaati wa maa fil ardi min daaabbatinw walma laaa`ikatu wa hum laa yastakbiroon
ለአላህም በሰማያት ያለው ከተንቀሳቃሽም በምድር ያለው ሁሉ፣ መላእክትም ይሰግዳሉ፡፡ እነርሱም አይኮሩም፡፡
🎤 Your recording:
16:50 🔁 0/5
يَخَافُونَ رَبَّهُم مِّن فَوۡقِهِمۡ وَيَفۡعَلُونَ مَا يُؤۡمَرُونَ۩  ۝٥٠
yakhaafoona Rabbahum min fawqihim wa yaf`aloona maa yu`maroon
ጌታቸውን ከበላያቸው ሲኾን ይፈሩታል፡፡ የታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ፡፡
🎤 Your recording:
16:51 🔁 0/5
۞ وَقَالَ ٱللَّهُ لَا تَتَّخِذُوٓاْ إِلَٰهَيۡنِ ٱثۡنَيۡنِۖ إِنَّمَا هُوَ إِلَٰهٌ وَٰحِدٌ فَإِيَّٰيَ فَٱرۡهَبُونِ  ۝٥١
Wa qaalal laahu laa tatta khizooo ilaahainis naini innamaa Huwa Ilaahunw Waahid; fa iyyaaya farhaboon
አላህም አለ «ሁለት አማልክትን አትያዙ፡፡ እርሱ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ እኔንም ብቻ ፍሩ፡፡»
🎤 Your recording:
16:52 🔁 0/5
وَلَهُۥ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَلَهُ ٱلدِّينُ وَاصِبًاۚ أَفَغَيۡرَ ٱللَّهِ تَتَّقُونَ  ۝٥٢
Wa lahoo maa fis samaawaati wal ardi wa lahud deenu waasibaa; afaghairal laahi tattaqoon
በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የርሱ ብቻ ነው፡፡ መገዛትም ዘወትር ሲኾን ለርሱ ብቻ ነው፡፡ ከአላህም ሌላ ያለን ትፈራላችሁን
🎤 Your recording:
16:53 🔁 0/5
وَمَا بِكُم مِّن نِّعۡمَةٍ فَمِنَ ٱللَّهِۖ ثُمَّ إِذَا مَسَّكُمُ ٱلضُّرُّ فَإِلَيۡهِ تَجۡـَٔرُونَ  ۝٥٣
Wa maa bikum minni`matin faminal laahi summa izaa massakumud durru fa ilaihi taj`aroon
ማንኛውም በእናንተ ላይ ያለው ጸጋ ከአላህ ነው፡፡ ከዚያም ችግር በደረሰባችሁ ጊዜ ወደርሱ ብቻ ትጮሃላችሁ፡፡
🎤 Your recording:
16:54 🔁 0/5
ثُمَّ إِذَا كَشَفَ ٱلضُّرَّ عَنكُمۡ إِذَا فَرِيقٌ مِّنكُم بِرَبِّهِمۡ يُشۡرِكُونَ  ۝٥٤
Summaa izaa kashafad durra `ankum izaa fareequm minkum bi Rabbihim yushrikoon
ከዚያም ከእናንተ ላይ ችግርን ባነሳላችሁ ጊዜ ከእናንተው የኾኑ ጭፍሮች ወዲያውኑ በጌታቸው (ጣዖትን) ያጋራሉ፡፡
🎤 Your recording:
16:55 🔁 0/5
لِيَكۡفُرُواْ بِمَآ ءَاتَيۡنَٰهُمۡۚ فَتَمَتَّعُواْ فَسَوۡفَ تَعۡلَمُونَ  ۝٥٥
Liyakfuroo bimaa aatainaahum; fatamatta`oo, faswfa ta`lamoon
(የሚያጋሩትም) በሰጠናቸው ሊክዱ ነው፡፡ ተጠቀሙም ወደ ፊትም (የሚደርስባችሁን) በእርግጥ ታውቃላችሁ፡፡
🎤 Your recording:
16:56 🔁 0/5
وَيَجۡعَلُونَ لِمَا لَا يَعۡلَمُونَ نَصِيبًا مِّمَّا رَزَقۡنَٰهُمۡۗ تَٱللَّهِ لَتُسۡـَٔلُنَّ عَمَّا كُنتُمۡ تَفۡتَرُونَ  ۝٥٦
Wa yaj`aloona limaa laa ya`lamoona naseebam mimmaa razaqnnaahum; tallaahi latus`alunaa `ammaa kuntum taftaroon
ለማያውቁትም (ጣዖታት) ከሰጠናቸው ሲሳይ ፈንታን ያደርጋሉ፡፡ በአላህ እምላለሁ፤ ትቀጣጥፉት ከነበራችሁት ሁሉ በእርግጥ ትጠየቃላችሁ፡፡
🎤 Your recording:
16:57 🔁 0/5
وَيَجۡعَلُونَ لِلَّهِ ٱلۡبَنَٰتِ سُبۡحَٰنَهُۥ وَلَهُم مَّا يَشۡتَهُونَ  ۝٥٧
Wa yaj`aloona lillaahil banaati Subhaanahoo wa lahum maa yashtahoon
ለአላህም (ከመላእክት) ሴቶች ልጆችን ያደርጋሉ፡፡ ጥራት ተገባው፡፡ ለእነርሱም የሚፈልጉትን (ወንዶች ልጆችን) ያደርጋሉ፡፡
🎤 Your recording:
16:58 🔁 0/5
وَإِذَا بُشِّرَ أَحَدُهُم بِٱلۡأُنثَىٰ ظَلَّ وَجۡهُهُۥ مُسۡوَدًّا وَهُوَ كَظِيمٌ  ۝٥٨
Wa izaa bushshira ahaduhum bil unsaa zalla wajhuhoo muswaddanw wa huwa kazeem
አንዳቸውም በሴት ልጅ በተበሰረ ጊዜ እርሱ የተቆጨ ኾኖ ፊቱ ጠቁሮ ይውላል፡፡
🎤 Your recording:
16:59 🔁 0/5
يَتَوَٰرَىٰ مِنَ ٱلۡقَوۡمِ مِن سُوٓءِ مَا بُشِّرَ بِهِۦٓۚ أَيُمۡسِكُهُۥ عَلَىٰ هُونٍ أَمۡ يَدُسُّهُۥ فِي ٱلتُّرَابِۗ أَلَا سَآءَ مَا يَحۡكُمُونَ  ۝٥٩
yatawaaraa minal qawmimin sooo`i maa bushshira bih; a-yumsikuhoo `alaa hoonin am yadussuhoo fit turaab; alaa saaa`a maa yahkumoon
በእርሱ ከተበሰረበት ነገር መጥፎነት በውርደት ላይ ኾኖ ይያዘውን ወይስ በዐፈር ውስጥ ይደብቀውን (በማለት እያምታታ) ከሰዎች ይደበቃል፡፡ ንቁ! የሚፈርዱት (ፍርድ) ምንኛ ከፋ!
🎤 Your recording:
16:60 🔁 0/5
لِلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ بِٱلۡأٓخِرَةِ مَثَلُ ٱلسَّوۡءِۖ وَلِلَّهِ ٱلۡمَثَلُ ٱلۡأَعۡلَىٰۚ وَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ  ۝٦٠
Lillazeena laa yu`minoona bil Aakhirati masalus saw`i wa lillaahil masalul a`laa; wa Huwal `Azeezul Hakeem
ለእነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም ለማያምኑት መጥፎ ጠባይ አላቸው፡፡ ለአላህም ታላቅ ባሕርይ አለው፡፡ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡
🎤 Your recording:
16:61 🔁 0/5
وَلَوۡ يُؤَاخِذُ ٱللَّهُ ٱلنَّاسَ بِظُلۡمِهِم مَّا تَرَكَ عَلَيۡهَا مِن دَآبَّةٍ وَلَٰكِن يُؤَخِّرُهُمۡ إِلَىٰٓ أَجَلٍ مُّسَمًّىۖ فَإِذَا جَآءَ أَجَلُهُمۡ لَا يَسۡتَـٔۡخِرُونَ سَاعَةً وَلَا يَسۡتَقۡدِمُونَ  ۝٦١
Wa law yu`aakhizul laahun naasa bizulminhim maa taraka `alaihaa min daaabbatinw wa laakiny yu`akhkhiruhum ilaaa ajalim musamman fa izaa jaaa`a ajaluhum laa yastaakhiroona saa`atanw wa laa yastaqdimoon
አላህም ሰዎችን በበደላቸው በያዛቸው ኖሮ በርሷ (በምድር ላይ) ከተንቀሳቃሽ ምንንም ባልተወ ነበር፡፡ ግን እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ ያቆያቸዋል፡፡ ጊዜያቸውም በመጣ ወቅት አንዲትን ሰዓት አይቆዩም፤ አይቀደሙምም፡፡
🎤 Your recording:
16:62 🔁 0/5
وَيَجۡعَلُونَ لِلَّهِ مَا يَكۡرَهُونَۚ وَتَصِفُ أَلۡسِنَتُهُمُ ٱلۡكَذِبَ أَنَّ لَهُمُ ٱلۡحُسۡنَىٰۚ لَا جَرَمَ أَنَّ لَهُمُ ٱلنَّارَ وَأَنَّهُم مُّفۡرَطُونَ  ۝٦٢
Wa yaj`aloona lillaahi maa yakrahoona wa tasifu alsinatuhumul kaziba anna lahumul husnaa laa jarama anna lahumun Naara wa annahum mufratoon
ለአላህም የሚጠሉትን ነገር ያደረጋሉ፡፡ ለእነሱም መልካሚቱ (አገር) አለቻቸው በማለት ምላሶቸቸው ውሸትን ይናገራሉ፡፡ ለእነሱ እሳት ያለቻቸው መኾናቸውና እነሱም (ወደርሷ) በቅድሚያ የሚነዱ መኾናቸው ጥርጥር የለበትም፡፡
🎤 Your recording:
16:63 🔁 0/5
تَٱللَّهِ لَقَدۡ أَرۡسَلۡنَآ إِلَىٰٓ أُمَمٍ مِّن قَبۡلِكَ فَزَيَّنَ لَهُمُ ٱلشَّيۡطَٰنُ أَعۡمَٰلَهُمۡ فَهُوَ وَلِيُّهُمُ ٱلۡيَوۡمَ وَلَهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٌ  ۝٦٣
Tallaahi laqad arsalnaaa ilaaa umamim min qablika fazayyana lahumush Shaitaanu a`maalahum fahuwa waliyyuhumul yawma wa lahum `azaabun aleem
በአላህ እንምላለን፤ ካንተ በፊት ወደ ነበሩት ሕዝቦች በእርግጥ (መልክተኞችን) ልከናል፡፡ ሰይጣንም ለእነርሱ ሥራዎቻቸውን ሸለመላቸው፡፡ እርሱም ዛሬ ረዳታቸው ነው፡፡ ለእነሱም (ኋላ) አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡
🎤 Your recording:
16:64 🔁 0/5
وَمَآ أَنزَلۡنَا عَلَيۡكَ ٱلۡكِتَٰبَ إِلَّا لِتُبَيِّنَ لَهُمُ ٱلَّذِي ٱخۡتَلَفُواْ فِيهِ وَهُدًى وَرَحۡمَةً لِّقَوۡمٍ يُؤۡمِنُونَ  ۝٦٤
Wa maaa anzalnaa `alaikal Kitaaba illaa litubaiyina lahumul lazikh talafoo feehi wa hudanw wa rahmatal liqawminy yu`minoon
ባንተም ላይ መጽሐፉን አላወረድንም፤ ያንን በርሱ የተለያዩበትን ለነርሱ ልታብራራላቸውና ለሚያምኑትም ሕዝቦች መሪና እዝነት ሊኾን እንጂ፡፡
🎤 Your recording:
16:65 🔁 0/5
وَٱللَّهُ أَنزَلَ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءً فَأَحۡيَا بِهِ ٱلۡأَرۡضَ بَعۡدَ مَوۡتِهَآۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةً لِّقَوۡمٍ يَسۡمَعُونَ  ۝٦٥
Wallaahu anzala minas samaaa`i maaa`an fa ahyaa bihil arda ba`da mawtihaa; inna fee zaalika la aayatal liqaw miny yasma`oon
አላህም ከሰማይ ውሃን አወረደ፡፡ በእርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ሕያው አደረገ፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚሰሙ ሕዝቦች በእርግጥ ተዓምር አልለ፡፡
🎤 Your recording:
16:66 🔁 0/5
وَإِنَّ لَكُمۡ فِي ٱلۡأَنۡعَٰمِ لَعِبۡرَةًۖ نُّسۡقِيكُم مِّمَّا فِي بُطُونِهِۦ مِنۢ بَيۡنِ فَرۡثٍ وَدَمٍ لَّبَنًا خَالِصًا سَآئِغًا لِّلشَّٰرِبِينَ  ۝٦٦
Wa inna lakum fil an`aami la`ibrah; nusqeekum mimmmaa fee butoonihee mim baini farsinw wa damil labanann khaalisan saaa`ighallish shaaribeen
ለናንተም በግመል፣ በከብት፣ በፍየል በእርግጥ መገምገሚያ አልላችሁ፡፡ በሆዶቹ ውስጥ ካለው ከፈረስና ከደም መካከል ጥሩ ወተትን ለጠጪዎች ተዋጭ ሲሆን እናጠጣችኋለን፡፡
🎤 Your recording:
16:67 🔁 0/5
وَمِن ثَمَرَٰتِ ٱلنَّخِيلِ وَٱلۡأَعۡنَٰبِ تَتَّخِذُونَ مِنۡهُ سَكَرًا وَرِزۡقًا حَسَنًاۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةً لِّقَوۡمٍ يَعۡقِلُونَ  ۝٦٧
Wa min samaraatin nakheeli wal a`nnaabi tattakhizoona minhu sakaranw wa rizqann hasanaa; inna fee zaalika la Aayatal liqawminy ya`qiloon
ከዘምባባዎችና ከወይኖችም ፍሬዎች (እንመግባችኋለን)፡፡ ከእርሱ ጠጅንና መልካም ምግብንም ትሠራላችሁ፡፡ በዚህም ውስጥ ለሚያስቡ ሕዝቦች በእርግጥ ተዓምር አልለ፡፡
🎤 Your recording:
16:68 🔁 0/5
وَأَوۡحَىٰ رَبُّكَ إِلَى ٱلنَّحۡلِ أَنِ ٱتَّخِذِي مِنَ ٱلۡجِبَالِ بُيُوتًا وَمِنَ ٱلشَّجَرِ وَمِمَّا يَعۡرِشُونَ  ۝٦٨
Wa awhaa Rabbuka ilannnabli anit takhizee minal jabaali buyootanw wa minash shajari wa mimmaa ya`rishoon
ጌታህም ወደ ንብ እንዲህ ሲል አስታወቀ «ከተራራዎች፣ ከዛፍም፣ (ሰዎች) ከሚሠሩትም (ቀፎ) ቤቶችን ያዢ፡፡
🎤 Your recording:
16:69 🔁 0/5
ثُمَّ كُلِي مِن كُلِّ ٱلثَّمَرَٰتِ فَٱسۡلُكِي سُبُلَ رَبِّكِ ذُلُلًاۚ يَخۡرُجُ مِنۢ بُطُونِهَا شَرَابٌ مُّخۡتَلِفٌ أَلۡوَٰنُهُۥ فِيهِ شِفَآءٌ لِّلنَّاسِۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةً لِّقَوۡمٍ يَتَفَكَّرُونَ  ۝٦٩
Summma kulee min kullis samaraati faslukee subula Rabbiki zululaa; yakhruju mim butoonihaa sharaabum mukh talifun alwaanuhoo feehi shifaaa`ul linnaas, innna fee zaalika la Aayatal liqawminy yatafakkaroon
«ከዚያም ከፍሬዎች ሁሉ ብይ፡፡ የጌታሽንም መንገዶች (ላንቺ) የተገሩ ሲኾኑ ግቢ፡፡» ከሆዶችዋ መልኮቹ የተለያዩ መጠጥ ይወጣል፡፡ በእርሱ ውስጥ ለሰዎች መድኃኒት አለበት፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች በእርግጥ ተዓምር አልለበት፡፡
🎤 Your recording:
16:70 🔁 0/5
وَٱللَّهُ خَلَقَكُمۡ ثُمَّ يَتَوَفَّىٰكُمۡۚ وَمِنكُم مَّن يُرَدُّ إِلَىٰٓ أَرۡذَلِ ٱلۡعُمُرِ لِكَيۡ لَا يَعۡلَمَ بَعۡدَ عِلۡمٍ شَيۡـًٔاۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلِيمٌ قَدِيرٌ  ۝٧٠
Wallaahu khalaqakum suma tatawaffaakum; wa minkum many-yuradu ilaaa arzalil `umuri likai laa ya`lama ba`da `ilmin shai`aa; innal laaha `Aleemun Qadeer
አላህም ፈጠራችሁ፤ ከዚያም ይገድላችኋል፡፡ ከእናንተም ከዕወቅት በኋላ ምንንም ነገር እንዳያውቅ ወደ ወራዳ ዕድሜ የሚመለስ ሰው አልለ፡፡ አላህ ዐዋቂ ቻይ ነው፡፡
🎤 Your recording:
16:71 🔁 0/5
وَٱللَّهُ فَضَّلَ بَعۡضَكُمۡ عَلَىٰ بَعۡضٍ فِي ٱلرِّزۡقِۚ فَمَا ٱلَّذِينَ فُضِّلُواْ بِرَآدِّي رِزۡقِهِمۡ عَلَىٰ مَا مَلَكَتۡ أَيۡمَٰنُهُمۡ فَهُمۡ فِيهِ سَوَآءٌۚ أَفَبِنِعۡمَةِ ٱللَّهِ يَجۡحَدُونَ  ۝٧١
Wallaahu faddala ba`dakum `alaa ba`din fir rizq; famal lazeena fuddiloo biraaaddee rizqihim `alaa maa malakat aimaanuhum fahum feehi sawaaa`; afabini`matil laahi yajhadoon
አላህም ከፊላችሁን በከፊሉ ላይ በሲሳይ አበለጠ፡፡ እነዚያም በላጭ የተደረጉት ሲሳያቸውን እጆቻቸው በያዙዋቸው (ባሮች) ላይ እነሱ በእርሱ ይተካከሉ ዘንድ መላሾች አይደሉም፡፡ ታዲያ በአላህ ጸጋ (ለእርሱ ተጋሪ በማድረግ) ይክዳሉን
🎤 Your recording:
16:72 🔁 0/5
وَٱللَّهُ جَعَلَ لَكُم مِّنۡ أَنفُسِكُمۡ أَزۡوَٰجًا وَجَعَلَ لَكُم مِّنۡ أَزۡوَٰجِكُم بَنِينَ وَحَفَدَةً وَرَزَقَكُم مِّنَ ٱلطَّيِّبَٰتِۚ أَفَبِٱلۡبَٰطِلِ يُؤۡمِنُونَ وَبِنِعۡمَتِ ٱللَّهِ هُمۡ يَكۡفُرُونَ  ۝٧٢
Wallaahu ja`ala lakum min anfusikum azwaajanw wa ja`ala lakum min azwaajikum baneena wa hafadatanw wa razaqakum minat yaiyibaat; afabil baatili yu`minoona wa bini`matil laahi hum yakkfuroon
አላህም ከነፍሶቻችሁ (ከጎሶቻችሁ) ለእናንተ ሚስቶችን አደረገ፡፡ ለእናንተም ከሚስቶቻችሁ ወንዶች ልጆችን፣ የልጅ ልጆችንም አደረገላችሁ፡፡ ከመልካሞችም ጸጋዎች ሰጣችሁ፡፡ ታድያ በውሸት (በጣኦት) ያምናሉን በአላህም ጸጋ እነሱ ይክዳሉን
🎤 Your recording:
16:73 🔁 0/5
وَيَعۡبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَا لَا يَمۡلِكُ لَهُمۡ رِزۡقًا مِّنَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ شَيۡـًٔا وَلَا يَسۡتَطِيعُونَ  ۝٧٣
Wa ya`budoona min doonil laahi maa laa yamliku lahum rizqam minas samaawaati wal ardi shai`anw wa laa yastatee`oon
ከአላህም ሌላ ከሰማያትም ከምድርም ምንንም ሲሳይ የማይሰጧቸውን (ምንንም) የማይችሉትንም ይግገዛሉ፡፡
🎤 Your recording:
16:74 🔁 0/5
فَلَا تَضۡرِبُواْ لِلَّهِ ٱلۡأَمۡثَالَۚ إِنَّ ٱللَّهَ يَعۡلَمُ وَأَنتُمۡ لَا تَعۡلَمُونَ  ۝٧٤
Falaa tadriboo lillaahil amsaal; innal laaha ya`lamu wa antum laa ta`lamoon
ለአላህም አምሳያዎችን አታድርጉ፡፡ አላህ (መሳይ እንደሌለው) ያውቃል፡፡ እናንተ ግን አታውቁም፡፡
🎤 Your recording:
16:75 🔁 0/5
۞ ضَرَبَ ٱللَّهُ مَثَلًا عَبۡدًا مَّمۡلُوكًا لَّا يَقۡدِرُ عَلَىٰ شَيۡءٍ وَمَن رَّزَقۡنَٰهُ مِنَّا رِزۡقًا حَسَنًا فَهُوَ يُنفِقُ مِنۡهُ سِرًّا وَجَهۡرًاۖ هَلۡ يَسۡتَوُۥنَۚ ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِۚ بَلۡ أَكۡثَرُهُمۡ لَا يَعۡلَمُونَ  ۝٧٥
Darabal laahu masalan `abdam mammlookal laa yaqdiru `alaa shai`inw wa marrazaqnaahu mminnaa rizqan hasanan fahuwa yunfiqu minhu sirranw wa jahra; hal yasta-woon; alhamdu lillaah; bal aksaruhum laa ya`lamoon
በምንም ላይ የማይችለውን በይዞታ ያለውን ባሪያና ከእኛ መልካም ሲሳይን የሰጠነውን እርሱም ከእርሱ (ከሰጠነው) በምስጢርና በግልጽ የሚለግሰውን (ነጻ) ሰው አላህ (ለጣዖትና ለርሱ) ምሳሌ አደረገ፡፡ (ሁለቱ) ይተካከላሉን ምስጋና ለአላህ ይኹን፡፡ በእውነቱ አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡
🎤 Your recording:
16:76 🔁 0/5
وَضَرَبَ ٱللَّهُ مَثَلًا رَّجُلَيۡنِ أَحَدُهُمَآ أَبۡكَمُ لَا يَقۡدِرُ عَلَىٰ شَيۡءٍ وَهُوَ كَلٌّ عَلَىٰ مَوۡلَىٰهُ أَيۡنَمَا يُوَجِّههُّ لَا يَأۡتِ بِخَيۡرٍ هَلۡ يَسۡتَوِي هُوَ وَمَن يَأۡمُرُ بِٱلۡعَدۡلِ وَهُوَ عَلَىٰ صِرَٰطٍ مُّسۡتَقِيمٍ  ۝٧٦
Wa darabal laahu masalar rajulaini ahaduhumaaa abkamu laa yaqdiru `alaa shai`inw wa huwa kallun `alaa mawlaahu ainamaa yuwajjihhu laa yaati bikhairin hal yastawee huwa wa many-yaamuru bil`adli wa huwa `alaa Siraatim MMustaqeem
አላህም ሁለትን ወንዶች (ለከሓዲና ለምእመን) ምሳሌ አደረገ፡፡ አንደኛቸው በምንም ነገር ላይ የማይችል ዲዳ ነው፡፡ እርሱም በጌታው ላይ ሸክም ነው፡፡ ወደ የትም ቢያዞረው በደግ ነገር አይመጣም፡፡ እርሱና ያ እርሱ በቀጥተናው መንገድ ላይ ኾኖ በማስተካከል የሚያዘው ሰው ይስተካከላሉን
🎤 Your recording:
16:77 🔁 0/5
وَلِلَّهِ غَيۡبُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ وَمَآ أَمۡرُ ٱلسَّاعَةِ إِلَّا كَلَمۡحِ ٱلۡبَصَرِ أَوۡ هُوَ أَقۡرَبُۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٍ قَدِيرٌ  ۝٧٧
Wa lillaahi ghaibus samaawaati wal ard; wa maaa amrus Saa`ati illaa kalamhil basari aw huwa aqrab; innal laaha `alaaa kulli shai`in Qadeer
በሰማያትና በምድርም ያለው ሩቅ ምስጢር የአላህ ነው፡፡ የሰዓቲቱም ነገር (መምጣቷ) እንደዓይን ቅጽበት እንጂ አይደለም፡፡ ወይ እርሱ ይበልጥ የቀረበ ነው፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡
🎤 Your recording:
16:78 🔁 0/5
وَٱللَّهُ أَخۡرَجَكُم مِّنۢ بُطُونِ أُمَّهَٰتِكُمۡ لَا تَعۡلَمُونَ شَيۡـًٔا وَجَعَلَ لَكُمُ ٱلسَّمۡعَ وَٱلۡأَبۡصَٰرَ وَٱلۡأَفۡـِٔدَةَ لَعَلَّكُمۡ تَشۡكُرُونَ  ۝٧٨
Wallaahu akhrajakum mim butooni ummahaatikum laa ta`lamoona shai`anw wa ja`ala lakumus sam`a wal absaara wal af`idata la`allakum tashkuroon
አላህም ከእናቶቻችሁ ሆዶች ምንም የማታውቁ ሆናችሁ አወጣችሁ፡፡ ታመሰግኑም ዘንድ ለእናንተ መስሚያን ማያዎችንም ልቦችንም አደረገላችሁ፡፡
🎤 Your recording:
16:79 🔁 0/5
أَلَمۡ يَرَوۡاْ إِلَى ٱلطَّيۡرِ مُسَخَّرَٰتٍ فِي جَوِّ ٱلسَّمَآءِ مَا يُمۡسِكُهُنَّ إِلَّا ٱللَّهُۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٍ لِّقَوۡمٍ يُؤۡمِنُونَ  ۝٧٩
Alam yaraw ilat tairi musakhkharaatin fee jawwis samaaa`i maa yumsikuhunna illal laah; inna fee zaalika la Aayaatil liqawminy yu`minoon
ወደ በራሪዎች በሰማይ አየር ውስጥ (ለመብረር) የተገሩ ሲኾኑ (ከመውደቅ) አላህ እንጂ ሌላ የማይዛቸው ኾነው አይመለከቱምን በዚህ ውስጥ ለሚያምኑ ሕዝቦች በእርግጥ ተዓምራቶች አሉ፡፡
🎤 Your recording:
16:80 🔁 0/5
وَٱللَّهُ جَعَلَ لَكُم مِّنۢ بُيُوتِكُمۡ سَكَنًا وَجَعَلَ لَكُم مِّن جُلُودِ ٱلۡأَنۡعَٰمِ بُيُوتًا تَسۡتَخِفُّونَهَا يَوۡمَ ظَعۡنِكُمۡ وَيَوۡمَ إِقَامَتِكُمۡ وَمِنۡ أَصۡوَافِهَا وَأَوۡبَارِهَا وَأَشۡعَارِهَآ أَثَٰثًا وَمَتَٰعًا إِلَىٰ حِينٍ  ۝٨٠
Wallaahu ja`ala lakum min juloodil an`aami buyootan tastakhif foonahaa yawma za`nikum wa yawma iqaamatikum wa min aswaafihaa wa awbaarihaa wa ash`aarihaaa asaasanw wa mataa`an ilaa been
አላህም ከቤቶቻችሁ ለእናንተ መርጊያን አደረገላችሁ፡፡ ከእንስሳዎችም ቆዳዎች በጉዟችሁ ቀን በመቀመጫችሁም ቀን የምታቀልላቸውን ቤቶች ለናንተ አደረገላችሁ፡፡ ከበግዋ ሱፎች፣ ከግመልዋም ጠጉሮች፣ ከፍየልዋም ጠጉሮች የቤት ዕቃዎችን እስከ ጊዜም ድረስ መጠቃቀሚያን (አደረገላችሁ)፡፡
🎤 Your recording:
16:81 🔁 0/5
وَٱللَّهُ جَعَلَ لَكُم مِّمَّا خَلَقَ ظِلَٰلًا وَجَعَلَ لَكُم مِّنَ ٱلۡجِبَالِ أَكۡنَٰنًا وَجَعَلَ لَكُمۡ سَرَٰبِيلَ تَقِيكُمُ ٱلۡحَرَّ وَسَرَٰبِيلَ تَقِيكُم بَأۡسَكُمۡۚ كَذَٰلِكَ يُتِمُّ نِعۡمَتَهُۥ عَلَيۡكُمۡ لَعَلَّكُمۡ تُسۡلِمُونَ  ۝٨١
Wallaahu ja`ala lakum mimmaa khalaqa zilaalanw wa ja`ala lakum minal jibaali aknaananw wa ja`ala lakum saraabeela taqeekumul harra wa saraabeela taqeekum baasakum; kazaalika yutimmu ni`matahoo alaikum la`allakum tuslimoon
አላህም ከፈጠረው ነገር ለእናንተ ጥላዎችን አደረገላችሁ፡፡ ከጋራዎችም ለእናንተ መከለያዎችን አደረገላችሁ፡፡ ሐሩርንም (ብርድንም) የሚጠብቋችሁን ልብሶች የጦራችሁንም አደጋ የሚጠብቋችሁን ጥሩሮች ለእናንተ አደረገላችሁ፡፡ እንደዚሁ ትሰልሙ ዘንድ ጸጋውን በእናንተ ላይ ይሞላል፡፡
🎤 Your recording:
16:82 🔁 0/5
فَإِن تَوَلَّوۡاْ فَإِنَّمَا عَلَيۡكَ ٱلۡبَلَٰغُ ٱلۡمُبِينُ  ۝٨٢
Fa in tawallaw fa innamaa `alaikal balaaghul mubeen
(ከኢስላም) ቢሸሹም ባንተ ላይ ያለብህ ግልጽ ማድረስ ብቻ ነው፡፡
🎤 Your recording:
16:83 🔁 0/5
يَعۡرِفُونَ نِعۡمَتَ ٱللَّهِ ثُمَّ يُنكِرُونَهَا وَأَكۡثَرُهُمُ ٱلۡكَٰفِرُونَ  ۝٨٣
Ya`rifoona ni`matal laahi summa yunkiroonahaa wa aksaruhumul kaafiroon
የአላህን ጸጋ ያውቃሉ፡፡ ከዚያም ይክዷታል፡፡ አብዛኞቻቸውም ከሓዲዎቹ ናቸው፡፡
🎤 Your recording:
16:84 🔁 0/5
وَيَوۡمَ نَبۡعَثُ مِن كُلِّ أُمَّةٍ شَهِيدًا ثُمَّ لَا يُؤۡذَنُ لِلَّذِينَ كَفَرُواْ وَلَا هُمۡ يُسۡتَعۡتَبُونَ  ۝٨٤
Wa yawma nab`asu min kulli ummatin shaheedan summa laa yu`zanu lillazeena kafaroo wa laa hum yusta`taboon
ከየሕዝቡም ሁሉ መስካሪን የምንቀሰቅስበትን ቀን (አስታውስ)፡፡ ከዚያም ለእነዚያ ለካዱት (ንግግር) አይፈቀድላቸውም፡፡ እነሱም በወቀሳ አይታለፉም፡፡
🎤 Your recording:
16:85 🔁 0/5
وَإِذَا رَءَا ٱلَّذِينَ ظَلَمُواْ ٱلۡعَذَابَ فَلَا يُخَفَّفُ عَنۡهُمۡ وَلَا هُمۡ يُنظَرُونَ  ۝٨٥
Wa izaa ra al lazeena zalamul `azaaba falaa yukhaf fafu `anhum wa laa hum yunzaroon
እነዚያም የበደሉት ቅጣቱን ባዩ ጊዜ ከእነሱ (ቅጣቱ) አይቀለልላቸውም፡፡ እነሱም ጊዜ አይስሰጡም፡፡
🎤 Your recording:
16:86 🔁 0/5
وَإِذَا رَءَا ٱلَّذِينَ أَشۡرَكُواْ شُرَكَآءَهُمۡ قَالُواْ رَبَّنَا هَٰٓؤُلَآءِ شُرَكَآؤُنَا ٱلَّذِينَ كُنَّا نَدۡعُواْ مِن دُونِكَۖ فَأَلۡقَوۡاْ إِلَيۡهِمُ ٱلۡقَوۡلَ إِنَّكُمۡ لَكَٰذِبُونَ  ۝٨٦
Wa izaa ra al lazeena ashrakoo shurakaaa`ahum qaaloo Rabbana haaa`ulaaa`i shurakaaa`unal lazeena kunnaa nad`oo min doonika fa alqaw ilaihimul qawla innakum lakaaziboon
እነዚያም ያጋሩት የሚያጋሩዋቸውን ባዩ ጊዜ «ጌታችን ሆይ! እነዚህ ከአንተ ሌላ እንገዛቸው የነበርነው ተጋሪዎቻችን ናቸው» ይላሉ፡፡ (አማልክቶች) «እናንተ በእርግጥ ውሸታሞች ናችሁ» የማለትንም ቃል ወደእነሱ ይጥላሉ፡፡
🎤 Your recording:
16:87 🔁 0/5
وَأَلۡقَوۡاْ إِلَى ٱللَّهِ يَوۡمَئِذٍ ٱلسَّلَمَۖ وَضَلَّ عَنۡهُم مَّا كَانُواْ يَفۡتَرُونَ  ۝٨٧
Wa alqaw ilal laahi yawma`izinis salama wa dalla `anhum maa kaanoo yaftaroon
(አጋሪዎቹ) በዚያ ቀንም ታዛዥነታቸውን ወደ አላህ ያቀርባሉ፡፡ ይቀጣጥፉት የነበሩትም ሁሉ ከእነርሱ ይጠፋቸዋል፡፡
🎤 Your recording:
16:88 🔁 0/5
ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ وَصَدُّواْ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ زِدۡنَٰهُمۡ عَذَابًا فَوۡقَ ٱلۡعَذَابِ بِمَا كَانُواْ يُفۡسِدُونَ  ۝٨٨
Allazeena kafaroo wa saddoo `an sabeelil laahi zidnaahum `azaaban fawqal `azaabi bimaa kaanoo yufsidoon
እነዚያ የካዱ፣ ከአላህም መንገድ የከለከሉ ያጠፉ በነበሩት ምክንያት ቅጣትን በቅጣት ላይ ጨመርንባቸው፡፡
🎤 Your recording:
16:89 🔁 0/5
وَيَوۡمَ نَبۡعَثُ فِي كُلِّ أُمَّةٍ شَهِيدًا عَلَيۡهِم مِّنۡ أَنفُسِهِمۡۖ وَجِئۡنَا بِكَ شَهِيدًا عَلَىٰ هَٰٓؤُلَآءِۚ وَنَزَّلۡنَا عَلَيۡكَ ٱلۡكِتَٰبَ تِبۡيَٰنًا لِّكُلِّ شَيۡءٍ وَهُدًى وَرَحۡمَةً وَبُشۡرَىٰ لِلۡمُسۡلِمِينَ  ۝٨٩
Wa yawma nab`asu fee kulli ummmatin shaheedan `alaihim min anfusihim wa ji`naa bika shaheedan `alaa haaa`ulaaa`; wa nazzalnaa `alaikal Kitaaba tibyaanal likulli shai`inw wa hudanw wa rahmatanw wa bushraa lilmuslimeen
በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ ከጎሳቸው በእነሱ ላይ መስካሪን የምንቀሰቅስበትን አንተንም በእነዚህ (ሕዝቦች) ላይ መስካሪ አድርገን የምናመጣህን ቀን (አስታውስ)፡፡ መጽሐፉንም ለሁሉ ነገር አብራሪ፣ መሪም፣ እዝነትም፣ ለሙስሊሞችም አብሳሪ ኾኖ ባንተ ላይ አወረድነው፡፡
🎤 Your recording:
16:90 🔁 0/5
۞ إِنَّ ٱللَّهَ يَأۡمُرُ بِٱلۡعَدۡلِ وَٱلۡإِحۡسَٰنِ وَإِيتَآيِٕ ذِي ٱلۡقُرۡبَىٰ وَيَنۡهَىٰ عَنِ ٱلۡفَحۡشَآءِ وَٱلۡمُنكَرِ وَٱلۡبَغۡيِۚ يَعِظُكُمۡ لَعَلَّكُمۡ تَذَكَّرُونَ  ۝٩٠
Innal laaha yaamaru bil `adli wal ihsaani wa eetaaa`i zil qurbaa wa yanhaa `anil fahshaaa`i wal munkari walbagh-i` ya`izukum la`allakum tazakkkaroon
አላህ በማስተካከል፣ በማሳመርም፣ ለዝምድና ባለቤት በመስጠትም ያዛል፡፡ ከአስከፊም (ከማመንዘር)፣ ከሚጠላም ነገር ሁሉ፣ ከመበደልም ይከለክላል፡፡ ትገነዘቡ ዘንድ ይገስጻችኋል፡፡
🎤 Your recording:
16:91 🔁 0/5
وَأَوۡفُواْ بِعَهۡدِ ٱللَّهِ إِذَا عَٰهَدتُّمۡ وَلَا تَنقُضُواْ ٱلۡأَيۡمَٰنَ بَعۡدَ تَوۡكِيدِهَا وَقَدۡ جَعَلۡتُمُ ٱللَّهَ عَلَيۡكُمۡ كَفِيلًاۚ إِنَّ ٱللَّهَ يَعۡلَمُ مَا تَفۡعَلُونَ  ۝٩١
Wa awfoo bi Ahdil laahi izaa `aahattum wa laa tanqudul aimaana ba`da tawkeedihaa wa qad ja`altumul laaha `alaikum kafeelaa; innal laaha ya`lamu maa taf`aloon
ቃል ኪዳንም በገባችሁ ጊዜ በአላህ ቃል ኪዳን ሙሉ፡፡ መሓሎቻችሁንም ከአጠነከራችኋት በኋላ አላህን በእናንተ ላይ በእርግጥ መስካሪ ያደረጋችሁ ስትኾኑ አታፍርሱ፡፡ አላህ የምትሠሩትን ሁሉ ያውቃልና፡፡
🎤 Your recording:
16:92 🔁 0/5
وَلَا تَكُونُواْ كَٱلَّتِي نَقَضَتۡ غَزۡلَهَا مِنۢ بَعۡدِ قُوَّةٍ أَنكَٰثًا تَتَّخِذُونَ أَيۡمَٰنَكُمۡ دَخَلَۢا بَيۡنَكُمۡ أَن تَكُونَ أُمَّةٌ هِيَ أَرۡبَىٰ مِنۡ أُمَّةٍۚ إِنَّمَا يَبۡلُوكُمُ ٱللَّهُ بِهِۦۚ وَلَيُبَيِّنَنَّ لَكُمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ مَا كُنتُمۡ فِيهِ تَخۡتَلِفُونَ  ۝٩٢
Wa laa takoonoo kallatee naqadat ghazlahaa mim ba`di quwwatin ankaasaa; tattakhizoona aimaanakum dakhlalam bainakum an takoona ummatun hiya arbaa min ummah; innnamaa yablookumul laahu bih; wa la yubaiyinanna lakum yawmal Qiyaamati maa kuntum fee takhtalifoon
(ቃል ኪዳናችሁን በማፍረስ አንዲቱ) ሕዝብ እርሷ ከ(ሌላይቱ) ሕዝብ የበዛች ለመኾንዋ በመካከላችሁ መሓሎቻችሁን (ለክዳት) መግቢያ አድርጋችሁ የምትይዙ ስትኾኑ እንደዚያች ፈትልዋን ከጠነከረ በኋላ ትርትሮች አድርጋ እንዳፈረሰችው (ሴት) አትኹኑ፡፡ አላህ በእርሱ ይሞክራችኋል፤ በትንሣኤ ቀንም በእርሱ ትለያዩበት የነበራችሁትን ነገር ለእናንተ በእርግጥ ያብራራላችኋል፡፡
🎤 Your recording:
16:93 🔁 0/5
وَلَوۡ شَآءَ ٱللَّهُ لَجَعَلَكُمۡ أُمَّةً وَٰحِدَةً وَلَٰكِن يُضِلُّ مَن يَشَآءُ وَيَهۡدِي مَن يَشَآءُۚ وَلَتُسۡـَٔلُنَّ عَمَّا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ  ۝٩٣
Wa law shaaa`al laahu laja`alakum ummmatanw waahidatanw wa laakiny yudillu many-yashaaa`u wa yahdee many-yashaaa`; wa latus`alunna `ammaa kuntum ta`maloon
አላህም በሻ ኖሮ አንዲት ሕዝብ ባደረጋችሁ ነበር፡፡ ግን የሚሻውን ሰው ያጠማል፡፡ የሚሻውንም ሰው ያቀናል፡፡ ትሠሩት ከነበራችሁትም ሁሉ በእርግጥ ትጠየቃላችሁ፡፡
🎤 Your recording:
16:94 🔁 0/5
وَلَا تَتَّخِذُوٓاْ أَيۡمَٰنَكُمۡ دَخَلَۢا بَيۡنَكُمۡ فَتَزِلَّ قَدَمُۢ بَعۡدَ ثُبُوتِهَا وَتَذُوقُواْ ٱلسُّوٓءَ بِمَا صَدَدتُّمۡ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ وَلَكُمۡ عَذَابٌ عَظِيمٌ  ۝٩٤
Wa laa tattakhizooo aimaanakum dakhalam bainakum ftazilla qadamum ba`da subootihaa wa tazooqus sooo`a bimmaa sadattum `an sabeelil laahi wa lakum `azaabun `azeem
ጫማዎች ከተደላደሉ በኋላ እንዳይንዳለጡ ከአላህም መንገድ በመከልከላችሁ ምክንያት ቅጣትን እንዳትቀምሱ መሓሎቻችሁን በመካከላችሁ ለክዳት መግቢያ አድርጋችሁ አትያዙ፡፡ ለእናንተም (ያን ጊዜ) ታላቅ ቅጣት አላችሁ፡፡
🎤 Your recording:
16:95 🔁 0/5
وَلَا تَشۡتَرُواْ بِعَهۡدِ ٱللَّهِ ثَمَنًا قَلِيلًاۚ إِنَّمَا عِندَ ٱللَّهِ هُوَ خَيۡرٌ لَّكُمۡ إِن كُنتُمۡ تَعۡلَمُونَ  ۝٩٥
Wa laa tashtaroo bi `ahdil laahi samanan qaleelaa; innamaa `indal laahi huwa khairul lakum in kuntum ta`lamoon
በአላህም ቃል ኪዳን ጥቂትን ዋጋ አትግዙ፡፡ የምታውቁ ብትኾኑ አላህ ዘንድ ያለው ምንዳ እርሱ ለእናንተ በላጭ ነውና፡፡
🎤 Your recording:
16:96 🔁 0/5
مَا عِندَكُمۡ يَنفَدُ وَمَا عِندَ ٱللَّهِ بَاقٍۗ وَلَنَجۡزِيَنَّ ٱلَّذِينَ صَبَرُوٓاْ أَجۡرَهُم بِأَحۡسَنِ مَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ  ۝٩٦
maa `indakum yanfadu wa maa `indal laahi baaq; wa lanajziyannal lazeena sabarooo ajjrahum bi ahsani maa kaanoo ya`maloon
እናንተ ዘንድ ያለው ሁሉ ያልቃል፡፡ አላህ ዘንድ ያለው ግን (ዘለዓለም) ቀሪ ነው፡፡ እነዚያንም የታገሱትን ይሠሩት በነበሩት በመልካሙ ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን፡፡
🎤 Your recording:
16:97 🔁 0/5
مَنۡ عَمِلَ صَٰلِحًا مِّن ذَكَرٍ أَوۡ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤۡمِنٌ فَلَنُحۡيِيَنَّهُۥ حَيَوٰةً طَيِّبَةًۖ وَلَنَجۡزِيَنَّهُمۡ أَجۡرَهُم بِأَحۡسَنِ مَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ  ۝٩٧
Man `amila saaliham min zakarin aw unsaa wa huwa mu`minun falanuhyiyannahoo hayaatan taiiyibatanw wa lanajzi yannnahum ajrahum bi ahsani maa kaanoo ya`maloon
ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ኾኖ በጎን የሰራ መልካም ኑሮን በእርግጥ እናኖረዋለን፡፡ ይሠሩትም ከነበሩት ነገር በመልካሙ ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን፡፡
🎤 Your recording:
16:98 🔁 0/5
فَإِذَا قَرَأۡتَ ٱلۡقُرۡءَانَ فَٱسۡتَعِذۡ بِٱللَّهِ مِنَ ٱلشَّيۡطَٰنِ ٱلرَّجِيمِ  ۝٩٨
Fa izaa qara tal Quraana fasta`iz billaahi minashh Shai taanir rajeem
ቁርኣንንም ባነበብህ ጊዜ እርጉም ከኾነው ሰይጣን በአላህ ተጠበቅ፡፡
🎤 Your recording:
16:99 🔁 0/5
إِنَّهُۥ لَيۡسَ لَهُۥ سُلۡطَٰنٌ عَلَى ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَلَىٰ رَبِّهِمۡ يَتَوَكَّلُونَ  ۝٩٩
Innahoo laisa lahoo sultaanun `alal lazeena aamanoo wa `alaa Rabbihim yatawakkaloon
እርሱ በእነዚያ ባመኑትና በጌታቸው ላይ በሚጠጉት ላይ ለእርሱ ስልጣን የለውምና፡፡
🎤 Your recording:
16:100 🔁 0/5
إِنَّمَا سُلۡطَٰنُهُۥ عَلَى ٱلَّذِينَ يَتَوَلَّوۡنَهُۥ وَٱلَّذِينَ هُم بِهِۦ مُشۡرِكُونَ  ۝١٠٠
Innnamaa sultaanuhoo `alal lazeena yatawallawnahoo wallazeena hum bihee mushrikoon
ስልጣኑ በእነዚያ በሚታዘዙት ላይና በእነዚያም እነርሱ በእርሱ (ምክንያት) አጋሪዎች በኾኑት ላይ ብቻ ነው፡፡
🎤 Your recording:
16:101 🔁 0/5
وَإِذَا بَدَّلۡنَآ ءَايَةً مَّكَانَ ءَايَةٍ وَٱللَّهُ أَعۡلَمُ بِمَا يُنَزِّلُ قَالُوٓاْ إِنَّمَآ أَنتَ مُفۡتَرِۭۚ بَلۡ أَكۡثَرُهُمۡ لَا يَعۡلَمُونَ  ۝١٠١
Wa izaa baddalnaaa Aayatam makaana Aayatinw wal laahu a`lamu bimaa yunazzilu qaalooo innamaa anta muftar; bal aksaruhum laa ya`lamoon
በአንቀጽም ስፍራ አንቀጽን በለወጥን ጊዜ አላህም የሚያወርደውን ነገር አዋቂ ነው፡፡ «አንተ ቀጣፊ እንጂ ሌላ አይደለህም» ይላሉ፡፡ በእውነቱ አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡
🎤 Your recording:
16:102 🔁 0/5
قُلۡ نَزَّلَهُۥ رُوحُ ٱلۡقُدُسِ مِن رَّبِّكَ بِٱلۡحَقِّ لِيُثَبِّتَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَهُدًى وَبُشۡرَىٰ لِلۡمُسۡلِمِينَ  ۝١٠٢
Qul nazzalahoo Roohul Qudusi mir Rabbika bilhaqqi liyusabbital lazeena aamanoo wa hudanw wa bushraa lilmuslimeen
እነዚያን ያመኑትን ለማረጋጋት ሙስሊሞቹንም ለመምራትና ለማብሰር (ቁርኣንን) ቅዱሱ መንፈስ (ጂብሪል) እውነተኛ ሲኾን ከጌታህ አወረደው በላቸው፡፡
🎤 Your recording:
16:103 🔁 0/5
وَلَقَدۡ نَعۡلَمُ أَنَّهُمۡ يَقُولُونَ إِنَّمَا يُعَلِّمُهُۥ بَشَرٌۗ لِّسَانُ ٱلَّذِي يُلۡحِدُونَ إِلَيۡهِ أَعۡجَمِيٌّ وَهَٰذَا لِسَانٌ عَرَبِيٌّ مُّبِينٌ  ۝١٠٣
Wa laqad na`lamu annahum yaqooloona innamaa yu`allimuhoo bashar; lisaanul lazee yulhidoona ilaihi a`ja miyyunw wa haaza lisaanun `Arabiyyum mubeen
እነርሱም «እርሱን (ቁርኣንን) የሚያስተምረው ሰው ብቻ ነው» ማለታቸውን በእርግጥ እናውቃለን፡፡ የዚያ ወደርሱ የሚያስጠጉበት ሰው ቋንቋ ዐጀም ነው፡፡ ይህ (ቁርአን) ግን ግልጽ ዐረብኛ ቋንቋ ነው፡፡
🎤 Your recording:
16:104 🔁 0/5
إِنَّ ٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ لَا يَهۡدِيهِمُ ٱللَّهُ وَلَهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٌ  ۝١٠٤
Innal lazeena laa yu`minoona bi Aayaatil laahi laa yahdehimul laahu wa lahum `azaabun aleem
እነዚያን በአላህ አንቀጾች የማያምኑትን አላህ አይመራቸውም፤ ለነሱም አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡
🎤 Your recording:
16:105 🔁 0/5
إِنَّمَا يَفۡتَرِي ٱلۡكَذِبَ ٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِۖ وَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡكَٰذِبُونَ  ۝١٠٥
Innamaa yaftaril kazibal lazeena laa yu`minoona bi Aayaatil laahi wa ulaaa`ika humul kaaziboon
ውሸትን የሚቀጣጥፉት እነዚያ በአላህ አንቀጾች የማያምኑት ብቻ ናቸው፡፡ እነዚያም ውሸታሞቹ እነሱ ብቻ ናቸው፡፡
🎤 Your recording:
16:106 🔁 0/5
مَن كَفَرَ بِٱللَّهِ مِنۢ بَعۡدِ إِيمَٰنِهِۦٓ إِلَّا مَنۡ أُكۡرِهَ وَقَلۡبُهُۥ مُطۡمَئِنُّۢ بِٱلۡإِيمَٰنِ وَلَٰكِن مَّن شَرَحَ بِٱلۡكُفۡرِ صَدۡرًا فَعَلَيۡهِمۡ غَضَبٌ مِّنَ ٱللَّهِ وَلَهُمۡ عَذَابٌ عَظِيمٌ  ۝١٠٦
man kafara billaahi mim ba`di eemaanihee illaa man ukriha wa qalbuhoo mutmma`innum bil eemaani wa laakim man sharaha bilkufri sadran fa`alaihim ghadabum minal laahi wa lahum `azaabun `azeem
ከእምነቱ በኋላ በአላህ የካደ ሰው (ብርቱ ቅጣት አልለው)፡፡ ልቡ በእምነት የረጋ ኾኖ (በክህደት ቃል በመናገር) የተገደደ ሰው ብቻ ሲቀር፡፡ ግን ልባቸውን በክሕደት የከፈቱ ሰዎች በነሱ ላይ ከአላህ ቁጣ አለባቸው፡፡ ለእነሱም ታላቅ ቅጣት አልላቸው፡፡
🎤 Your recording:
16:107 🔁 0/5
ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمُ ٱسۡتَحَبُّواْ ٱلۡحَيَوٰةَ ٱلدُّنۡيَا عَلَى ٱلۡأٓخِرَةِ وَأَنَّ ٱللَّهَ لَا يَهۡدِي ٱلۡقَوۡمَ ٱلۡكَٰفِرِينَ  ۝١٠٧
Zaalika bi annahumus tahabbul hayaatad dunyaa `alal Aakhirati wa annal laaha laa yahdil qawmal kaafireen
ይህ (ቅጣት) እነሱ ቅርቢቱን ሕይወት ከመጨረሻይቱ በመምረጣቸው ምክንያትና አላህም ከሓዲዎችን ሕዝቦች የማያቀና በመኾኑ ነው፡፡
🎤 Your recording:
16:108 🔁 0/5
أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ طَبَعَ ٱللَّهُ عَلَىٰ قُلُوبِهِمۡ وَسَمۡعِهِمۡ وَأَبۡصَٰرِهِمۡۖ وَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡغَٰفِلُونَ  ۝١٠٨
Ulaaa`ikal lazeena taba`al laahu `alaa quloobihim wa sam`ihim wa absaarihim wa ulaaa`ika humul ghaafiloon
እነዚያ እነርሱ በልቦቻቸው፣ በዓይኖቻቸውም፣ በጆሮዎቻቸውም ላይ አላህ ያተመባቸው ናቸው፡፡ እነዚያም ዝንጉዎቹ እነሱ ናቸው፡፤
🎤 Your recording:
16:109 🔁 0/5
لَا جَرَمَ أَنَّهُمۡ فِي ٱلۡأٓخِرَةِ هُمُ ٱلۡخَٰسِرُونَ  ۝١٠٩
Laa jarama annnahum fil Aakhirati humul khassiroon
እነርሱ በመጨረሻይቱ ዓለም ከሳሪዎቹ እነሱ ለመኾናቸው ጥርጥር የለም፡፡
🎤 Your recording:
16:110 🔁 0/5
ثُمَّ إِنَّ رَبَّكَ لِلَّذِينَ هَاجَرُواْ مِنۢ بَعۡدِ مَا فُتِنُواْ ثُمَّ جَٰهَدُواْ وَصَبَرُوٓاْ إِنَّ رَبَّكَ مِنۢ بَعۡدِهَا لَغَفُورٌ رَّحِيمٌ  ۝١١٠
Summa inna Rabbaka lillazeena haajaroo mim ba`dimaa futinoo summma jaahadoo wa sabaroo inna Rabbaka mim ba`dihaa la Ghafoorur Raheem
ከዚያም ጌታህ ለእነዚያ ከተፈተኑ በኋላ ለተሰደዱት ከዚያም ለታገሉትና ለታገሱት (መሓሪ አዛኝ ነው)፡፡ ጌታህ ከእርሷ (ከፈተናዋ) በኋላ በእርግጥ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡
🎤 Your recording:
16:111 🔁 0/5
۞ يَوۡمَ تَأۡتِي كُلُّ نَفۡسٍ تُجَٰدِلُ عَن نَّفۡسِهَا وَتُوَفَّىٰ كُلُّ نَفۡسٍ مَّا عَمِلَتۡ وَهُمۡ لَا يُظۡلَمُونَ  ۝١١١
Yawma taatee kullu nafsin tujaadilu `an nafsihaa wa tuwaffaa kullu nafsim maa `amilat wa hum laa yuzlamoon
ነፍስ ሁሉ ከራሷ ላይ የምትከራከር ኾና የምትመጣበትን ነፍስም ሁሉ የሠራችውን (ዋጋ) የምትቀበልበትን ቀን (አስታውስ)፡፡ እነርሱም አይበደሉም፡፡
🎤 Your recording:
16:112 🔁 0/5
وَضَرَبَ ٱللَّهُ مَثَلًا قَرۡيَةً كَانَتۡ ءَامِنَةً مُّطۡمَئِنَّةً يَأۡتِيهَا رِزۡقُهَا رَغَدًا مِّن كُلِّ مَكَانٍ فَكَفَرَتۡ بِأَنۡعُمِ ٱللَّهِ فَأَذَٰقَهَا ٱللَّهُ لِبَاسَ ٱلۡجُوعِ وَٱلۡخَوۡفِ بِمَا كَانُواْ يَصۡنَعُونَ  ۝١١٢
Wa darabal laahu masalan qaryatan kaanat aaminatam mutma`innatany yaaateehaa rizquhaa rghadam min kulli makaanin fakafarat bi an`umil laahi fa azaaqahal laahu libaasal joo`i walkhawfi bimaa kaanoo yasna`oon
አላህ ጸጥተኛ፣ የረካች፣ ሲሳይዋ ሰፊ ኾኖ ከየስፍራው ይመጣላት የነበረችውንና በአላህ ጸጋዎች የካደችውን አላህም ይሠሩት በነበሩት ኃጢኣት የረኃብንና የፍርሃትን ቅጣቶች ያቀመሳትን ከተማ (መካን) ምሳሌ አደረገ፡፡
🎤 Your recording:
16:113 🔁 0/5
وَلَقَدۡ جَآءَهُمۡ رَسُولٌ مِّنۡهُمۡ فَكَذَّبُوهُ فَأَخَذَهُمُ ٱلۡعَذَابُ وَهُمۡ ظَٰلِمُونَ  ۝١١٣
Wa laqad jaaa`ahum Rasoolum minhum fakazzaboohu fa akhazahumul `azaabu wa hum zaalimoon
ከእነርሱ ውስጥ የኾነ መልክተኛም በእርግጥ መጣላቸው፡፡ አስተባበሉትም፡፡ እነሱም በዳዮች ኾነው ቅጣቱ ያዛቸው፡፡
🎤 Your recording:
16:114 🔁 0/5
فَكُلُواْ مِمَّا رَزَقَكُمُ ٱللَّهُ حَلَٰلًا طَيِّبًا وَٱشۡكُرُواْ نِعۡمَتَ ٱللَّهِ إِن كُنتُمۡ إِيَّاهُ تَعۡبُدُونَ  ۝١١٤
Fakuloo mimmaa razaqa kumul laahu halaalan taiyibanw washkuroo ni`matal laahi in kuntum iyyaahu ta`budoon
አላህም ከሰጣችሁ ሲሳይ የተፈቀደ ንጹሕ ሲኾን ብሉ፡፡ የአላህንም ጸጋ እርሱን የምትገዙት ብትሆኑ አመስግኑ፡፡
🎤 Your recording:
16:115 🔁 0/5
إِنَّمَا حَرَّمَ عَلَيۡكُمُ ٱلۡمَيۡتَةَ وَٱلدَّمَ وَلَحۡمَ ٱلۡخِنزِيرِ وَمَآ أُهِلَّ لِغَيۡرِ ٱللَّهِ بِهِۦۖ فَمَنِ ٱضۡطُرَّ غَيۡرَ بَاغٍ وَلَا عَادٍ فَإِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ  ۝١١٥
Innamaa harrma `alai kumul maitata waddama wa lahmal khinzeeri wa maaa uhilla lighairil laahi bihee famanid turra ghaira baaghinw wa laa `aadin fa innal laaha Ghafoorur Raheem
በእናንተ ላይ እርም ያደረገው በክትንና ደምን፣ የአሳማንም ስጋ፣ ያንንም (በመታረድ ጊዜ) በእርሱ ከአላህ ስም ሌላ የተነሳበትን ብቻ ነው፡፡ አመጸኛም ወሰን አላፊም ሳይኾን (ለመብላት) የተገደደ ሰው (ይፈቀድለታል)፡፡ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡
🎤 Your recording:
16:116 🔁 0/5
وَلَا تَقُولُواْ لِمَا تَصِفُ أَلۡسِنَتُكُمُ ٱلۡكَذِبَ هَٰذَا حَلَٰلٌ وَهَٰذَا حَرَامٌ لِّتَفۡتَرُواْ عَلَى ٱللَّهِ ٱلۡكَذِبَۚ إِنَّ ٱلَّذِينَ يَفۡتَرُونَ عَلَى ٱللَّهِ ٱلۡكَذِبَ لَا يُفۡلِحُونَ  ۝١١٦
Wa laa taqooloo limaa tasifu alsinatukumul kaziba haaza halaalunw wa haazaa haraamul litaftaroo `alal laahil kazib; innal lazeena yaftaroona `alal laahil kaziba laa yuflihoon
በአላህም ላይ ውሸትን ልትቀጣጥፉ ምላሶቻችሁ በሚመጥኑት ውሸት «ይህ የተፈቀደ ነው፤ ይህም እርም ነው» አትበሉ፡፡ እነዚያ በአላህ ላይ ውሸትን የሚቀጣጥፉ አይድኑም፡፡
🎤 Your recording:
16:117 🔁 0/5
مَتَٰعٌ قَلِيلٌ وَلَهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٌ  ۝١١٧
Mata`un qaleelunw wa lahum `azaabun aleem
ጥቂት መጣቀም አላቸው፡፡ ለእነሱም አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡
🎤 Your recording:
16:118 🔁 0/5
وَعَلَى ٱلَّذِينَ هَادُواْ حَرَّمۡنَا مَا قَصَصۡنَا عَلَيۡكَ مِن قَبۡلُۖ وَمَا ظَلَمۡنَٰهُمۡ وَلَٰكِن كَانُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ يَظۡلِمُونَ  ۝١١٨
Wa `alal lazeena haadoo harramnaa ma qasasnaa `alaika min qablu wa maa zalamanaahum wa laakin kaanoo anfusahum wa laakin kaanoo anfusahum yazlimoon
በእነዚያም ይሁዳውያን በኾኑት ላይ ከአሁን በፊት በአንተ ላይ የተረክነውን ነገር እርም አድርገንባቸዋል፡፡ እኛም አልበደልናቸውም፡፡ ግን ነፍሶቻቸውን ይበድሉ ነበሩ፡፡
🎤 Your recording:
16:119 🔁 0/5
ثُمَّ إِنَّ رَبَّكَ لِلَّذِينَ عَمِلُواْ ٱلسُّوٓءَ بِجَهَٰلَةٍ ثُمَّ تَابُواْ مِنۢ بَعۡدِ ذَٰلِكَ وَأَصۡلَحُوٓاْ إِنَّ رَبَّكَ مِنۢ بَعۡدِهَا لَغَفُورٌ رَّحِيمٌ  ۝١١٩
Summma inna Rabbaka lillazeena `amilus sooo`a bijahaalatin summa taaboo mim ba`di zaaalika wa aslahoo inna Rabbaka mim ba`dihaa la Ghafoorur Raheem
ከዚያም ጌታህ ለእነዚያ በስሕተት መጥፎን ለሠሩና ከዚያም ከዚህ በኋላ ለተጸጸቱ ሥራቸውንም ላበጁ ጌታህ ከእርሷ በኋላ በእርግጥ መሓሪ አዛኝ ነው፡፡
🎤 Your recording:
16:120 🔁 0/5
إِنَّ إِبۡرَٰهِيمَ كَانَ أُمَّةً قَانِتًا لِّلَّهِ حَنِيفًا وَلَمۡ يَكُ مِنَ ٱلۡمُشۡرِكِينَ  ۝١٢٠
Inna Ibraaheema kaana ummatan qaanital lillaahi Haneefanw wa lam yakuminal mushrikeen
ኢብራሂም ለአላህ ታዛዥ ወደ ቀጥተኛ ሃይማኖት ተዘንባይ ሕዝብ ነበር፡፡ ከአጋሪዎቹም አልነበረም፡፡
🎤 Your recording:
16:121 🔁 0/5
شَاكِرًا لِّأَنۡعُمِهِۚ ٱجۡتَبَىٰهُ وَهَدَىٰهُ إِلَىٰ صِرَٰطٍ مُّسۡتَقِيمٍ  ۝١٢١
Shaakiral li an`umih; ijtabaahu wa hadaahu ilaa Siraatim Muustaqeem
ለጸጋዎቹ አመስጋኝ ነበር፤ መረጠው፡፡ ወደ ቀጥተኛውም መንገድ መራው፡፡
🎤 Your recording:
16:122 🔁 0/5
وَءَاتَيۡنَٰهُ فِي ٱلدُّنۡيَا حَسَنَةًۖ وَإِنَّهُۥ فِي ٱلۡأٓخِرَةِ لَمِنَ ٱلصَّٰلِحِينَ  ۝١٢٢
Wa aatainaahu fid dunyaa hasanah; wa innahoo fil Aakhirati laminas saaliheen
በቅርቢቱም ዓለም በጎን ነገር ሰጠነው፡፡ እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም በእርግጥ ከመልካሞቹ ነው፡፡
🎤 Your recording:
16:123 🔁 0/5
ثُمَّ أَوۡحَيۡنَآ إِلَيۡكَ أَنِ ٱتَّبِعۡ مِلَّةَ إِبۡرَٰهِيمَ حَنِيفًاۖ وَمَا كَانَ مِنَ ٱلۡمُشۡرِكِينَ  ۝١٢٣
Summma awhainaa ilaika anit tabi` Millata Ibraaheema haneefaa; wa maa kaana minal mushrikeen
ከዚያም ወደ አንተ የኢብራሂምን ሃይማኖት ቀጥተኛ ሲኾን ተከተል፤ ከአጋሪዎቹም አልነበረም ማለት አወረድን፡፡
🎤 Your recording:
16:124 🔁 0/5
إِنَّمَا جُعِلَ ٱلسَّبۡتُ عَلَى ٱلَّذِينَ ٱخۡتَلَفُواْ فِيهِۚ وَإِنَّ رَبَّكَ لَيَحۡكُمُ بَيۡنَهُمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ فِيمَا كَانُواْ فِيهِ يَخۡتَلِفُونَ  ۝١٢٤
Innnamaa ju`ilas Sabtu `alal lazeenakhtalafoo feeh; wa inna Rabbaka la yahkumu bainahum Yawmal Qiyaamati feemaa kaanoo feehi yakhtalifoon
ሰንበት (ክልክል) የተደረገው በእነዚያ በእርሱ በተለያዩበት ሰዎች ላይ ብቻ ነው፡፡ ጌታህም በትንሣኤ ቀን ይለያዩበት በነበሩት ነገር በመካከላቸው በእርግጥ ይፈርዳል፡፡
🎤 Your recording:
16:125 🔁 0/5
ٱدۡعُ إِلَىٰ سَبِيلِ رَبِّكَ بِٱلۡحِكۡمَةِ وَٱلۡمَوۡعِظَةِ ٱلۡحَسَنَةِۖ وَجَٰدِلۡهُم بِٱلَّتِي هِيَ أَحۡسَنُۚ إِنَّ رَبَّكَ هُوَ أَعۡلَمُ بِمَن ضَلَّ عَن سَبِيلِهِۦ وَهُوَ أَعۡلَمُ بِٱلۡمُهۡتَدِينَ  ۝١٢٥
Ud`u ilaa sabeeli Rabbika bilhikmati walmaw `izatil hasanati wa jaadilhum billatee hiya ahsan; inna Rabbaka huwa a`almu biman dalla `an sabeelihee wa Huwa a`lamu bilmuhtadeen
ወደ ጌታህ መንገድ በብልሃትና በመልካም ግሳጼ (በለዘብታ ቃል) ጥራ፡፡ በዚያችም እርሷ መልካም በኾነችው (ዘዴ) ተከራከራቸው፡፡ ጌታህ እርሱ ከመንገዱ የተሳሳተውን ሰው ዐዋቂ ነው፡፡ እርሱም ቅን የኾኑትን ሰዎች ዐዋቂ ነው፡፡
🎤 Your recording:
16:126 🔁 0/5
وَإِنۡ عَاقَبۡتُمۡ فَعَاقِبُواْ بِمِثۡلِ مَا عُوقِبۡتُم بِهِۦۖ وَلَئِن صَبَرۡتُمۡ لَهُوَ خَيۡرٌ لِّلصَّٰبِرِينَ  ۝١٢٦
Wa in `aaqabtum fa`aaqiboo bimisli maa `ooqibtum bihee wa la`in sabartum lahuwa khairul lissaabireen
ብትበቀሉም በርሱ በተቀጣችሁበት ብጤ ተበቀሉ፡፡ ብትታገሱም እርሱ ለታጋሾች በእርግጥ በላጭ ነው፡፡
🎤 Your recording:
16:127 🔁 0/5
وَٱصۡبِرۡ وَمَا صَبۡرُكَ إِلَّا بِٱللَّهِۚ وَلَا تَحۡزَنۡ عَلَيۡهِمۡ وَلَا تَكُ فِي ضَيۡقٍ مِّمَّا يَمۡكُرُونَ  ۝١٢٧
Wasbir wa maa sabruka illaa billaah; wa laa tahzan `alaihim wa laa taku fee daiqim mimmaa yamkuroon
ታገስም፤ መታገስህም በአላህ (ማስቻል) እንጂ አይደለም፡፡ በእነርሱም ላይ (ባያምኑ) አትተክዝ፡፡ (ባንተ ላይ) ከሚመክሩትም ተንኮል በጭንቀት ውስጥ አትኹን፡፡
🎤 Your recording:
16:128 🔁 0/5
إِنَّ ٱللَّهَ مَعَ ٱلَّذِينَ ٱتَّقَواْ وَّٱلَّذِينَ هُم مُّحۡسِنُونَ  ۝١٢٨
Innal laaha ma`al lazeenat taqaw wal lazeena hum muhsinoon
አላህ ከእነዚያ ከሚፈሩትና ከእነዚያም እነሱ መልካም ሠሪዎች ከኾኑት ጋር ነውና፡፡
🎤 Your recording:
💡 Tap any hidden word to reveal it temporarily — your progress is saved automatically in this browser.

🎉
🎊 Well Done! Memorization Complete
Mishary Rashid Alafasy
Mahmoud Khalil Al-Husary
Abdurrahman As-Sudais
Mohamed Siddiq Al-Minshawi
Abdul Basit Abdul Samad
Ali Al-Hudhaify
Ahmed ibn Ali al-Ajamy
Abu Bakr Ash-Shaatree
Muhammad Ayyoub
Abdullah Basfar
Abdullah Al-Juhani
Maher Al Muaiqly
0:00
0:00
-

ቅዱስ ቁርኣን


Tuesday, August 18, 2026

Don't forget us in your sincere prayers