La sourate At-Tariq en Amharique
وَالسَّمَاءِ وَالطَّارِقِ(1) በሰማዩ በሌሊት መጪውም እምላለሁ፡፡ |
وَمَا أَدْرَاكَ مَا الطَّارِقُ(2) የሌሊት መጪውም ምን እንደ ኾነ ምን አሳወቀህ? |
النَّجْمُ الثَّاقِبُ(3) ጨለማን ቀዳጁ ኮከብ ነው፡፡ |
إِن كُلُّ نَفْسٍ لَّمَّا عَلَيْهَا حَافِظٌ(4) ነፍስ ሁሉ በእርሷ ላይ ጠባቂ ያለባት እንጅ ሌላ አይደለችም፡፡ |
فَلْيَنظُرِ الْإِنسَانُ مِمَّ خُلِقَ(5) ሰውም ከምን እንደተፈጠረ ይመልከት፡፡ |
خُلِقَ مِن مَّاءٍ دَافِقٍ(6) ከተስፈንጣሪ ውሃ ተፈጠረ፡፡ |
يَخْرُجُ مِن بَيْنِ الصُّلْبِ وَالتَّرَائِبِ(7) ከጀርባና ከእርግብግብቶች መካከል የሚወጣ ከኾነ (ውሃ)፡፡ |
إِنَّهُ عَلَىٰ رَجْعِهِ لَقَادِرٌ(8) እርሱ (አላህ) በመመለሱ ላይ በእርግጥ ቻይ ነው፡፡ |
يَوْمَ تُبْلَى السَّرَائِرُ(9) ምስጢሮች በሚገለጡበት ቀን፡፡ |
فَمَا لَهُ مِن قُوَّةٍ وَلَا نَاصِرٍ(10) ለእርሱም (ለሰው) ኀይልና ረዳት ምንም የለውም፡፡ |
وَالسَّمَاءِ ذَاتِ الرَّجْعِ(11) የመመለስ ባለቤት በኾነችው ሰማይም እምላለሁ፡፡ |
وَالْأَرْضِ ذَاتِ الصَّدْعِ(12) (በበቃይ) የመሰንጠቅ ባለቤት በኾነችው ምድርም፤ |
إِنَّهُ لَقَوْلٌ فَصْلٌ(13) እርሱ (እውነትን ከውሸት) የሚለይ ቃል ነው፡፡ |
وَمَا هُوَ بِالْهَزْلِ(14) እርሱም ቀልድ አይደለም፡፡ |
إِنَّهُمْ يَكِيدُونَ كَيْدًا(15) እነርሱ በእርግጥ ተንኮልን ይሠራሉ፡፡ |
وَأَكِيدُ كَيْدًا(16) (እኔ) ተንኮልንም እመልሳለሁ፡፡ |
فَمَهِّلِ الْكَافِرِينَ أَمْهِلْهُمْ رُوَيْدًا(17) ከሓዲዎችንም ቀን ስጣቸው፡፡ ጥቂትን ጊዜ አቆያቸው፡፡ |
Plus de sourates en Amharique :
Téléchargez la sourate avec la voix des récitants du Coran les plus célèbres :
Téléchargez le fichier mp3 de la sourate At-Tariq : choisissez le récitateur pour écouter et télécharger la sourate At-Tariq complète en haute qualité.















Donnez-nous une invitation valide