سورة الانشقاق بالأمهرية
إِذَا السَّمَاءُ انشَقَّتْ(1) ሰማይ በተቀደደች ጊዜ፤ |
وَأَذِنَتْ لِرَبِّهَا وَحُقَّتْ(2) ለጌታዋም (ትዕዛዝ) በሰማች ጊዜ፤ (ልትሰማ) ተገባትም፤ |
وَإِذَا الْأَرْضُ مُدَّتْ(3) ምድርም በተለጠጠች ጊዜ፤ |
وَأَلْقَتْ مَا فِيهَا وَتَخَلَّتْ(4) በውስጧ ያለውንም ሁሉ በጣለችና ባዶ በኾነች ጊዜ፤ |
وَأَذِنَتْ لِرَبِّهَا وَحُقَّتْ(5) ለጌታዋም በሰማች ጊዜ፤ (መስማት) ተገባትም፤ (ሰው ሁሉ ሥራውን ይገናኛል)፡፡ |
يَا أَيُّهَا الْإِنسَانُ إِنَّكَ كَادِحٌ إِلَىٰ رَبِّكَ كَدْحًا فَمُلَاقِيهِ(6) አንተ ሰው ሆይ! አንተ ጌታህን (በሞት) እስከምትገናኝ ድረስ ልፋትን ለፊ ነህ፤ ተገናኚውም ነህ፡፡ |
فَأَمَّا مَنْ أُوتِيَ كِتَابَهُ بِيَمِينِهِ(7) መጽሐፉን በቀኙ የተሰጠ ሰውማ፤ |
فَسَوْفَ يُحَاسَبُ حِسَابًا يَسِيرًا(8) በእርግጥ ቀላልን ምርመራ ይመረመራል፡፡ |
وَيَنقَلِبُ إِلَىٰ أَهْلِهِ مَسْرُورًا(9) ወደ ቤተሰቦቹም ተደሳች ኾኖ ይመለሳል፡፡ |
وَأَمَّا مَنْ أُوتِيَ كِتَابَهُ وَرَاءَ ظَهْرِهِ(10) መጽሐፉን በጀርባው ኋላ የተሰጠ ሰውማ፤ |
فَسَوْفَ يَدْعُو ثُبُورًا(11) (ዋ! ጥፋቴ በማለት) ጥፋትን በእርግጥ ይጠራል፡፡ |
وَيَصْلَىٰ سَعِيرًا(12) የተጋጋመች እሳትንም ይገባል፡፡ |
إِنَّهُ كَانَ فِي أَهْلِهِ مَسْرُورًا(13) እርሱ በቤተሰቡ ውስጥ ተደሳች ነበርና፡፡ |
إِنَّهُ ظَنَّ أَن لَّن يَحُورَ(14) እርሱ (ወደ አላህ) የማይመለስ መኾኑን አስቧልና፡፡ |
بَلَىٰ إِنَّ رَبَّهُ كَانَ بِهِ بَصِيرًا(15) አይደለም (ይመለሳል)፡፡ ጌታው በእርሱ (መመለስ) ዐዋቂ ነበር፤ (ነውም)፡፡ |
فَلَا أُقْسِمُ بِالشَّفَقِ(16) አትካዱ፤ በወጋገኑ እምላለሁ፡፡ |
وَاللَّيْلِ وَمَا وَسَقَ(17) በሌሊቱም በሰበሰውም ሁሉ፤ |
وَالْقَمَرِ إِذَا اتَّسَقَ(18) በጨረቃውም በሞላ ጊዜ (እምላለሁ)፡፡ |
لَتَرْكَبُنَّ طَبَقًا عَن طَبَقٍ(19) ከኹነታ በኋላ ወደ ሌላ ኹነታ ትለዋወጣላችሁ፡፡ |
فَمَا لَهُمْ لَا يُؤْمِنُونَ(20) የማያምኑት ለእነርሱ ምን አላቸው? |
وَإِذَا قُرِئَ عَلَيْهِمُ الْقُرْآنُ لَا يَسْجُدُونَ ۩(21) በእነርሱም ላይ ቁርኣን በተነበበ ጊዜ የማይሰግዱት፤ (ምንአላቸው?) |
بَلِ الَّذِينَ كَفَرُوا يُكَذِّبُونَ(22) በእርግጡ እነዚያ የካዱት (በትንሣኤ) ያስተባብላሉ፡፡ |
وَاللَّهُ أَعْلَمُ بِمَا يُوعُونَ(23) አላህም (በልቦቻቸው) የሚቆጥሩትን ዐዋቂ ነው፡፡ |
فَبَشِّرْهُم بِعَذَابٍ أَلِيمٍ(24) በአሳማሚ ቅጣትም አብስራቸው፡፡ |
إِلَّا الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ لَهُمْ أَجْرٌ غَيْرُ مَمْنُونٍ(25) ግን እነዚያ ያመኑና መልካሞችን የሠሩ ለእነርሱ የማይቆረጥ ምንዳ አልላቸው፡፡ |
المزيد من السور باللغة الأمهرية:
تحميل سورة الانشقاق بصوت أشهر القراء :
قم باختيار القارئ للاستماع و تحميل سورة الانشقاق كاملة بجودة عالية
أحمد العجمي
خالد الجليل
سعد الغامدي
سعود الشريم
عبد الباسط
عبد الله الجهني
علي الحذيفي
فارس عباد
ماهر المعيقلي
محمد جبريل
المنشاوي
الحصري
مشاري العفاسي
ناصر القطامي
ياسر الدوسري
Thursday, November 21, 2024
لا تنسنا من دعوة صالحة بظهر الغيب