La sourate Al-Ala en Amharique
سَبِّحِ اسْمَ رَبِّكَ الْأَعْلَى(1) ከሁሉ በላይ የኾነውን ጌታህን ስም አሞግሥ፡፡ |
الَّذِي خَلَقَ فَسَوَّىٰ(2) የዚያን (ሁሉን ነገር) የፈጠረውን ያስተካከለውንም፡፡ |
وَالَّذِي قَدَّرَ فَهَدَىٰ(3) የዚያንም የወሰነውን፡፡ (ለተፈጠረለት ነገር) የመራውንም፡፡ |
وَالَّذِي أَخْرَجَ الْمَرْعَىٰ(4) የዚያንም ግጦሽን (ለምለም አድርጎ) ያወጣውን፡፡ |
فَجَعَلَهُ غُثَاءً أَحْوَىٰ(5) (ከዚያ) ደረቅ ጥቁር ያደረገውንም (አምላክ ስም አሞግስ)፡፡ |
سَنُقْرِئُكَ فَلَا تَنسَىٰ(6) (ቁርኣንን) በእርግጥ እናስነብብሃለን፤ አትረሳምም፡፡ |
إِلَّا مَا شَاءَ اللَّهُ ۚ إِنَّهُ يَعْلَمُ الْجَهْرَ وَمَا يَخْفَىٰ(7) አላህ ከሻው ነገር በስተቀር፡፡ እርሱ ግልጹን የሚሸሸገውንም ሁሉ ያውቃልና፡፡ |
وَنُيَسِّرُكَ لِلْيُسْرَىٰ(8) ለገሪቱም (ሕግጋት) እንገጥምሃለን፡፡ |
فَذَكِّرْ إِن نَّفَعَتِ الذِّكْرَىٰ(9) ግሣጼይቱ ብትጠቅም (ሰዎችን) ገሥጽም፡፡ |
سَيَذَّكَّرُ مَن يَخْشَىٰ(10) (አላህን) የሚፈራ ሰው በእርግጥ ይገሠጻል፡፡ |
وَيَتَجَنَّبُهَا الْأَشْقَى(11) መናጢውም ይርቃታል፡፡ |
الَّذِي يَصْلَى النَّارَ الْكُبْرَىٰ(12) ያ ታላቂቱን እሳት የሚገባው፡፡ |
ثُمَّ لَا يَمُوتُ فِيهَا وَلَا يَحْيَىٰ(13) ከዚያም በእርሷ ውስጥ አይሞትም ሕያውም አይኾንም፡፡ |
قَدْ أَفْلَحَ مَن تَزَكَّىٰ(14) የተጥራራ ሰው በእርግጥ ዳነ፡፡ |
وَذَكَرَ اسْمَ رَبِّهِ فَصَلَّىٰ(15) የጌታውንም ስም ያወሳና የሰገደ፡፡ |
بَلْ تُؤْثِرُونَ الْحَيَاةَ الدُّنْيَا(16) ይልቁንም ቅርቢቱን ሕይወት ትመርጣላችሁ፡፡ |
وَالْآخِرَةُ خَيْرٌ وَأَبْقَىٰ(17) መጨረሻይቱ (ሕይወት) በላጭ ሁል ጊዜ ዘውታሪም ስትኾን፡፡ |
إِنَّ هَٰذَا لَفِي الصُّحُفِ الْأُولَىٰ(18) ይህ በፊተኞቹ መጻሕፍት ውስጥ ያልለ ነው፡፡ |
صُحُفِ إِبْرَاهِيمَ وَمُوسَىٰ(19) በኢብራሂምና በሙሳ ጽሑፎች ውስጥ፡፡ |
Plus de sourates en Amharique :
Téléchargez la sourate avec la voix des récitants du Coran les plus célèbres :
Téléchargez le fichier mp3 de la sourate Al-Ala : choisissez le récitateur pour écouter et télécharger la sourate Al-Ala complète en haute qualité.















Donnez-nous une invitation valide