La sourate Al-Layl en Amharique
وَاللَّيْلِ إِذَا يَغْشَىٰ(1) በሌሊቱ እምላለሁ (በጨለማው) በሚሸፍን ጊዜ፡፡ |
وَالنَّهَارِ إِذَا تَجَلَّىٰ(2) በቀኑም፤ በተገለጸ ጊዜ፡፡ |
وَمَا خَلَقَ الذَّكَرَ وَالْأُنثَىٰ(3) ወንድንና ሴትን በፈጠረውም (አምላክ እምላለሁ)፡፡ |
إِنَّ سَعْيَكُمْ لَشَتَّىٰ(4) ሥራችሁ በእርግጥ የተለያየ ነው፡፡ |
فَأَمَّا مَنْ أَعْطَىٰ وَاتَّقَىٰ(5) የሰጠ ሰውማ ጌታውን የፈራም፡፡ |
وَصَدَّقَ بِالْحُسْنَىٰ(6) በመልካሚቱም (እምነት) ያረጋገጠ፤ |
فَسَنُيَسِّرُهُ لِلْيُسْرَىٰ(7) ለገሪቱ ሥራ እናዘጋጀዋለን፡፡ |
وَأَمَّا مَن بَخِلَ وَاسْتَغْنَىٰ(8) የሰሰተ ሰውማ የተብቃቃም፤ (በራሱ የተመካ)፤ |
وَكَذَّبَ بِالْحُسْنَىٰ(9) በመልካሚቱ (እምነት) ያሰተባበለም፤ |
فَسَنُيَسِّرُهُ لِلْعُسْرَىٰ(10) ለክፉይቱ ሥራ እናዘጋጀዋለን፡፡ |
وَمَا يُغْنِي عَنْهُ مَالُهُ إِذَا تَرَدَّىٰ(11) በወደቀም ጊዜ ገንዘቡ ከእርሱ ምንም አይጠቅመውም፡፡ |
إِنَّ عَلَيْنَا لَلْهُدَىٰ(12) ቅኑን መንገድ መግለጽ በእኛ ላይ አለብን፡፡ |
وَإِنَّ لَنَا لَلْآخِرَةَ وَالْأُولَىٰ(13) መጨረሻይቱም መጀመሪያይቱም ዓለም የእኛ ናቸው፡፡ |
فَأَنذَرْتُكُمْ نَارًا تَلَظَّىٰ(14) የምትንቀለቀልንም እሳት አስጠነቀቅኳችሁ (በላቸው)፡፡ |
لَا يَصْلَاهَا إِلَّا الْأَشْقَى(15) ከጠማማ በቀር ሌላ የማይገባት የኾነችን፡፡ |
الَّذِي كَذَّبَ وَتَوَلَّىٰ(16) ያ ያስተባበለና ከትዕዛዝ የሸሸው፡፡ |
وَسَيُجَنَّبُهَا الْأَتْقَى(17) አላህን በጣም ፈሪውም በእርግጥ ይርቃታል፡፡ |
الَّذِي يُؤْتِي مَالَهُ يَتَزَكَّىٰ(18) ያ የሚጥራራ ኾኖ ገንዘቡን (ለድኾች) የሚሰጠው፡፡ |
وَمَا لِأَحَدٍ عِندَهُ مِن نِّعْمَةٍ تُجْزَىٰ(19) ለአንድም ሰው እርሱ ዘንድ የምትመለስ ውለታ የለችም፡፡ |
إِلَّا ابْتِغَاءَ وَجْهِ رَبِّهِ الْأَعْلَىٰ(20) ግን የታላቅ ጌታውን ውዴታ ለመፈለግ (ይህንን ሠራ)፡፡ |
وَلَسَوْفَ يَرْضَىٰ(21) ወደፊትም በእርግጥ ይደሰታል፡፡ |
Plus de sourates en Amharique :
Téléchargez la sourate avec la voix des récitants du Coran les plus célèbres :
Téléchargez le fichier mp3 de la sourate Al-Layl : choisissez le récitateur pour écouter et télécharger la sourate Al-Layl complète en haute qualité.















Donnez-nous une invitation valide