Перевод суры Аль-Гашия на амхарский язык
هَلْ أَتَاكَ حَدِيثُ الْغَاشِيَةِ(1) የሸፋኝቱ (ትንሣኤ) ወሬ መጣህን? |
وُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ خَاشِعَةٌ(2) ፊቶች በዚያ ቀን ተዋራጆች ናቸው፡፡ |
عَامِلَةٌ نَّاصِبَةٌ(3) ሠሪዎች ለፊዎች ናቸው፡፡ |
تَصْلَىٰ نَارًا حَامِيَةً(4) ተኳሳን እሳት ይገባሉ፡፡ |
تُسْقَىٰ مِنْ عَيْنٍ آنِيَةٍ(5) በጣም ከፈላች ምንጭ ይጋታሉ፡፡ |
لَّيْسَ لَهُمْ طَعَامٌ إِلَّا مِن ضَرِيعٍ(6) ለእነርሱ ዶሪዕ ከሚባል (እሾሃም) ዛፍ እንጅ ሌላ ምግብ የላቸውም፡፡ |
لَّا يُسْمِنُ وَلَا يُغْنِي مِن جُوعٍ(7) የማያሰባ ከረኃብም የማያብቃቃ ከኾነው፡፡ |
وُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ نَّاعِمَةٌ(8) ፊቶች በዚያ ቀን ተቀማጣዮች ናቸው፡፡ |
لِّسَعْيِهَا رَاضِيَةٌ(9) ለሥራቸው ተደሳቾች ናቸው፡፡ |
فِي جَنَّةٍ عَالِيَةٍ(10) በከፍተኛ ገነት ውስጥ ናቸው፡፡ |
لَّا تَسْمَعُ فِيهَا لَاغِيَةً(11) በውስጧ ውድቅን ነገር አይሰሙም፡፡ |
فِيهَا عَيْنٌ جَارِيَةٌ(12) በውስጧ ፈሳሾች ምንጮች አልሉ፡፡ |
فِيهَا سُرُرٌ مَّرْفُوعَةٌ(13) በውስጧ ከፍ የተደረጉ አልጋዎች አልሉ፡፡ |
وَأَكْوَابٌ مَّوْضُوعَةٌ(14) በተርታ የተኖሩ ብርጭቆዎችም፡፡ |
وَنَمَارِقُ مَصْفُوفَةٌ(15) የተደረደሩ መከዳዎችም፡፡ |
وَزَرَابِيُّ مَبْثُوثَةٌ(16) የተነጠፉ ስጋጃዎችም (አልሉ)፡፡ |
أَفَلَا يَنظُرُونَ إِلَى الْإِبِلِ كَيْفَ خُلِقَتْ(17) (ከሓዲዎች) አይመለከቱምን? ወደ ግመል እንዴት እነደተፈጠረች! |
وَإِلَى السَّمَاءِ كَيْفَ رُفِعَتْ(18) ወደ ሰማይም እንዴት ከፍ እንደ ተደረገች! |
وَإِلَى الْجِبَالِ كَيْفَ نُصِبَتْ(19) ወደ ተራራዎችም እንዴት እንደ ተቸከሉ! |
وَإِلَى الْأَرْضِ كَيْفَ سُطِحَتْ(20) ወደ ምድርም እንዴ እንደተዘረጋች (አይመለከቱምን?) |
فَذَكِّرْ إِنَّمَا أَنتَ مُذَكِّرٌ(21) አስታውስም፤ አንተ አስታዋሽ ብቻ ነህና፡፡ |
لَّسْتَ عَلَيْهِم بِمُصَيْطِرٍ(22) በእነርሱ ላይ ተሿሚ (አስገዳጅ) አይደለህም፡፡ |
إِلَّا مَن تَوَلَّىٰ وَكَفَرَ(23) ግን (ከእውነት) የዞረና የካደ ሰው፤ |
فَيُعَذِّبُهُ اللَّهُ الْعَذَابَ الْأَكْبَرَ(24) አላህ ታላቁን ቅጣት ይቀጣዋል፡፡ |
إِنَّ إِلَيْنَا إِيَابَهُمْ(25) መመለሻቸው ወደእኛ ብቻ ነው፡፡ |
ثُمَّ إِنَّ عَلَيْنَا حِسَابَهُم(26) ከዚያም ምርመራቸው በእኛ ላይ ብቻ ነው፡፡ |
Больше сур в амхарский:
Скачать суру Al-Ghashiyah с голосом самых известных рекитаторов Корана:
Сура Al-Ghashiyah mp3: выберите рекитатора, чтобы прослушать и скачать главу Al-Ghashiyah полностью в высоком качестве
Ahmed Al Ajmy
Bandar Balila
Khalid Al Jalil
Saad Al Ghamdi
Saud Al Shuraim
Abdul Basit
Abdul Rashid Sufi
Abdullah Basfar
Abdullah Al Juhani
Fares Abbad
Maher Al Muaiqly
Al Minshawi
Al Hosary
Mishari Al-afasi
Yasser Al Dosari
Помолитесь за нас хорошей молитвой