Alak suresi çevirisi Amharca
اقْرَأْ بِاسْمِ رَبِّكَ الَّذِي خَلَقَ(1) አንብብ በዚያ (ሁሉን) በፈጠረው ጌታህ ስም፡፡ |
خَلَقَ الْإِنسَانَ مِنْ عَلَقٍ(2) ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው (ጌታህ ስም)፡፡ |
اقْرَأْ وَرَبُّكَ الْأَكْرَمُ(3) አንብብ፤ ጌታህ በጣም ቸር ሲኾን፤ |
الَّذِي عَلَّمَ بِالْقَلَمِ(4) ያ በብርዕ ያስተማረ፡፡ |
عَلَّمَ الْإِنسَانَ مَا لَمْ يَعْلَمْ(5) ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲኾን፡፡ |
كَلَّا إِنَّ الْإِنسَانَ لَيَطْغَىٰ(6) በእውነቱ ሰው ወሰንን ያልፋል፡፡ |
أَن رَّآهُ اسْتَغْنَىٰ(7) ራሱን የተብቃቃ (ባለ ሀብት) ኾኖ ለማየቱ፡፡ |
إِنَّ إِلَىٰ رَبِّكَ الرُّجْعَىٰ(8) መመለሻው ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡ |
أَرَأَيْتَ الَّذِي يَنْهَىٰ(9) አየህን? ያንን የሚከለክለውን፡፡ |
عَبْدًا إِذَا صَلَّىٰ(10) ባሪያን በሰገደ ጊዜ፤ |
أَرَأَيْتَ إِن كَانَ عَلَى الْهُدَىٰ(11) አየህን? ንገረኝ (ተከልካዩ) በትክክለኛ መንገድ ላይ ቢኾን፤ |
أَوْ أَمَرَ بِالتَّقْوَىٰ(12) ወይም (ፈጣሪውን) በመፍራት ቢያዝ፤ |
أَرَأَيْتَ إِن كَذَّبَ وَتَوَلَّىٰ(13) አየህን? ንገረኝ (ከልካዩ) ቢያስተባብልና (ከእምነት) ቢሸሽ፤ |
أَلَمْ يَعْلَم بِأَنَّ اللَّهَ يَرَىٰ(14) አላህ የሚያይ መኾኑን አያውቅምን? |
كَلَّا لَئِن لَّمْ يَنتَهِ لَنَسْفَعًا بِالنَّاصِيَةِ(15) ይተው ባይከለከል አናቱን ይዘን እንጎትተዋለን፡፡ |
نَاصِيَةٍ كَاذِبَةٍ خَاطِئَةٍ(16) ውሸታም ስሕተተኛ የኾነችውን አናቱን፡፡ |
فَلْيَدْعُ نَادِيَهُ(17) ሸንጎውንም ይጥራ፡፡ |
سَنَدْعُ الزَّبَانِيَةَ(18) (እኛም) ዘበኞቻችንን እንጠራለን፡፡ |
كَلَّا لَا تُطِعْهُ وَاسْجُدْ وَاقْتَرِب ۩(19) ይከልከል አትታዘዘው፡፡ ስገድም፤ (ወደ አላህ) ተቃረብም፡፡ |
Amharca diğer sureler:
En ünlü okuyucuların sesiyle Alak Suresi indirin:
Surah Al-Alaq mp3: yüksek kalitede dinlemek ve indirmek için okuyucuyu seçerek
Ahmed El Agamy
Saad Al Ghamdi
Saud Al Shuraim
Abdul Basit
Abdullah Basfar
Abdullah Al Juhani
Ali Al Hudhaifi
Fares Abbad
Maher Al Muaiqly
Muhammad Jibril
Al Minshawi
Al Hosary
Mishari Al-afasi
Nasser Al Qatami
Yasser Al Dosari
Bizim için dua et, teşekkürler