La sourate Al-Balad en Amharique
لَا أُقْسِمُ بِهَٰذَا الْبَلَدِ(1) በዚህ አገር (በመካ) እምላለሁ፡፡ |
وَأَنتَ حِلٌّ بِهَٰذَا الْبَلَدِ(2) አንተ በዚህ አገር ሰፋሪ ስትኾን፡፡ |
وَوَالِدٍ وَمَا وَلَدَ(3) በወላጂም በወለዳቸውም ሰዎች (በአዳምና በዘሮቹ ሁሉ እምላለሁ)፡፡ |
لَقَدْ خَلَقْنَا الْإِنسَانَ فِي كَبَدٍ(4) ሰውን ሁሉ በእርግጥ በልፋት ውስጥ ኾኖ ፈጠርነው፡፡ |
أَيَحْسَبُ أَن لَّن يَقْدِرَ عَلَيْهِ أَحَدٌ(5) በእርሱ ላይ አንድም የማይችል መኾኑን ይጠረጥራልን? |
يَقُولُ أَهْلَكْتُ مَالًا لُّبَدًا(6) «ብዙን ገንዘብ አጠፋሁ» ይላል፡፡ |
أَيَحْسَبُ أَن لَّمْ يَرَهُ أَحَدٌ(7) አንድም ያላየው መኾኑን ያስባልን? |
أَلَمْ نَجْعَل لَّهُ عَيْنَيْنِ(8) ለእርሱ ሁለት ዓይኖችን አላደረግንለትምን? |
وَلِسَانًا وَشَفَتَيْنِ(9) ምላስንና ሁለት ከንፈሮችንም፡፡ |
وَهَدَيْنَاهُ النَّجْدَيْنِ(10) ሁለትን መንገዶችም አልመራነውምን? |
فَلَا اقْتَحَمَ الْعَقَبَةَ(11) ዓቀበቲቱንም አልወጣም፡፡ |
وَمَا أَدْرَاكَ مَا الْعَقَبَةُ(12) ዓቀበቲቱም (መውጣቷ) ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ? |
فَكُّ رَقَبَةٍ(13) (እርሱ) ጫንቃን መልቀቅ ነው፡፡ |
أَوْ إِطْعَامٌ فِي يَوْمٍ ذِي مَسْغَبَةٍ(14) ወይም የረኃብ ባለቤት በኾነ ቀን ማብላት፡፡ |
يَتِيمًا ذَا مَقْرَبَةٍ(15) የዝምድና ባለቤት የኾነን የቲም፤ |
أَوْ مِسْكِينًا ذَا مَتْرَبَةٍ(16) ወይም የዐፈር ባለቤት የኾነን ድኻ (ማብላት ነው)፡፡ |
ثُمَّ كَانَ مِنَ الَّذِينَ آمَنُوا وَتَوَاصَوْا بِالصَّبْرِ وَتَوَاصَوْا بِالْمَرْحَمَةِ(17) (ዐቀበቲቱን አልወጣም)፡፡ ከዚያም ከነዚያ ከአመኑትና በመታገስ አደራ ከተባባሉት፣ በማዘንም አደራ ከተባባሉት ሰዎች አልኾነም፡፡ |
أُولَٰئِكَ أَصْحَابُ الْمَيْمَنَةِ(18) እነዚያ (ይህንን የፈጸሙ) የቀኝ ጓዶች ናቸው፡፡ |
وَالَّذِينَ كَفَرُوا بِآيَاتِنَا هُمْ أَصْحَابُ الْمَشْأَمَةِ(19) እነዚያም በአንቀጾቻችን የካዱት እነርሱ የግራ ጓዶች ናቸው፡፡ |
عَلَيْهِمْ نَارٌ مُّؤْصَدَةٌ(20) በእነርሱ ላይ የተዘጋች እሳት አልለች፡፡ |
Plus de sourates en Amharique :
Téléchargez la sourate avec la voix des récitants du Coran les plus célèbres :
Téléchargez le fichier mp3 de la sourate Al-Balad : choisissez le récitateur pour écouter et télécharger la sourate Al-Balad complète en haute qualité.
Ahmed Al Ajmy Bandar Balila Khalid Al Jalil Saad Al Ghamdi Saud Al Shuraim Abdul Basit Abdul Rashid Sufi Abdullah Basfar Abdullah Al Juhani Fares Abbad Maher Al Muaiqly Al Minshawi Al Hosary Mishari Al-afasi Yasser Al Dosari
Donnez-nous une invitation valide