PDF —
200 አንቀጽ Medinan PDF
Built right in your browser — download starts automatically

ሱረቱ አል-ኢምራን pdf — አውርድ (አማርኛ)

ሱረቱ አል-ኢምራን pdf አማርኛ — አውርድ ሱረቱ አል-ኢምራን ትርጉም. ሱረቱ አል-ኢምራን (Medinan) 200 አንቀጽ.

← አል-በቀራሱረቱ አል-ኢምራን አን-ኒሳ →


200 አንቀጽ · Medinan · አማርኛ
bismillah
ﭑﭒ
3:1 አ.ለ.መ (አሊፍ ላም ሚም)፤
ﭓﭔﭕﭖﭗﭘﭙﭚ
3:2 አላህ ከርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ (እርሱ) ሕያው ሁሉን ነገር አስተናባሪ ነው፡፡
ﭛﭜﭝﭞﭟﭠﭡﭢﭣﭤﭥﭦ
3:3 ከርሱ በፊት ያሉትን መጻሕፍት የሚያረጋግጥ ሲኾን መጽሐፉን (ቁርኣንን) ባንተ ላይ ከፋፍሎ በእውነት አወረደ፡፡ ተውራትንና ኢንጂልንም አውርዷል፡፡
ﭧﭨﭩﭪﭫﭬﭭﭮﭯﭰﭱﭲﭳﭴﭵﭶﭷﭸﭹﭺﭻ
3:4 (ከቁርኣን) በፊት ለሰዎች መሪ አድርጎ (አወረዳቸው)፡፡ ፉርቃንንም አወረደ፡፡ እነዚያ በአላህ ተዓምራቶች የካዱ ለእነርሱ ብርቱ ቅጣት አላቸው፡፡ አላህም አሸናፊ የመበቀል ባለቤት ነው፡፡
ﭼﭽﭾﭿﮀﮁﮂﮃﮄﮅﮆﮇ
3:5 አላህ በምድርም በሰማይም ምንም ነገር በርሱ ላይ አይሰወርም፡፡
ﮈﮉﮊﮋﮌﮍﮎﮏﮐﮑﮒﮓﮔﮕﮖ
3:6 እርሱ ያ በማሕጸኖች ውስጥ እንደሚሻ አድርጎ የሚቀርጻችሁ ነው፡፡ ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡
ﮗﮘﮙﮚﮛﮜﮝﮞﮟﮠﮡﮢﮣﮤﮥﮦﮧﮨﮩﮪﮫﮬﮭﮮﮯﮰﮱﯓﯔﯕﯖﯗﯘﯙﯚﯛﯜﯝﯞﯟﯠﯡﯢﯣﯤﯥﯦﯧﯨﯩﯪ
3:7 እርሱ ያ በአንተ ላይ መጽሐፉን ያወረደ ነው፡፡ ከእርሱ (ከመጽሐፉ) ግልጽ የኾኑ አንቀጾች አልሉ፡፡ እነሱ የመጽሐፉ መሠረቶች ናቸው፡፡ ሌሎችም ተመሳሳዮች አልሉ፡፡ እነዚያማ በልቦቻቸው ውስጥ ጥመት ያለባቸው ሰዎች ማሳሳትን ለመፈለግና ትችቱን ለመፈለግ ከርሱ የተመሳሰለውን ይከታተላሉ፡፡ (ትክክለኛ) ትችቱንም አላህ ብቻ እንጅ ሌላ አያውቀውም፡፡ በዕውቀትም የጠለቁት «በርሱ አምነናል፤ ሁሉም ከጌታችን ዘንድ ነው» ይላሉ፡፡ የአእምሮ ባለቤቶችም እንጅ (ሌላው) አይገሰጽም፡፡
ﯫﯬﯭﯮﯯﯰﯱﯲﯳﯴﯵﯶﯷﯸﯹﯺﯻ
3:8 (እነሱም ይላሉ)፡- «ጌታችን ሆይ! ቅኑን መንገድ ከመራኸን በኋላ ልቦቻችንን አታዘምብልብን፡፡ ከአንተ ዘንድ የኾነን ችሮታም ለኛ ስጠን፡፡ አንተ በጣም ለጋስ ነህና፡፡»
ﯼﯽﯾﯿﰀﰁﰂﰃﰄﰅﰆﰇﰈﰉﰊ
3:9 «ጌታችን ሆይ! አንተ በርሱ (ለመምጣቱ) ጥርጥር የሌለበት በኾነ ቀን ሰውን ሁሉ ሰብሳቢ ነህ፡፡ ምንጊዜም አላህ ቀጠሮውን አያፈርስምና፡፡»
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖﭗﭘﭙﭚﭛﭜﭝﭞﭟﭠﭡﭢ
3:10 እነዚያ የካዱት ሰዎች ገንዘቦቻቸውና ልጆቻቸው ከአላህ (ቅጣት) ምንም አያስጥሉዋቸውም፡፡ እነዚያም እነርሱ የእሳት ማገዶዎች ናቸው፡፡
ﭣﭤﭥﭦﭧﭨﭩﭪﭫﭬﭭﭮﭯﭰﭱﭲﭳ
3:11 (ልማዳቸው ሁሉ) እንደፈርዖን ቤተሰብና እንደእነዚያ ከበፊታቸው እንደነበሩት ሕዝቦች ልማድ ነው፡፡ በአንቀጾቻችን አስተባበሉ፡፡ አላህም በኃጢአቶቻቸው ያዛቸው፡፡ አላህም ቅጣተብርቱ ነው፡፡
ﭴﭵﭶﭷﭸﭹﭺﭻﭼﭽﭾ
3:12 ለእነዚያ ለካዱት ሰዎች በላቸው፡- «በቅርብ ጊዜ ትሸነፉላችሁ፡፡ ወደ ገሀነምም ትሰበሰባላችሁ፡፡ ምንጣፊቱም ምን ትከፋ!»
ﭿﮀﮁﮂﮃﮄﮅﮆﮇﮈﮉﮊﮋﮌﮍﮎﮏﮐﮑﮒﮓﮔﮕﮖﮗﮘﮙﮚﮛﮜﮝﮞﮟ
3:13 (የበድር ቀን) በተጋጠሙት ሁለት ጭፍሮች ለናንተ በእርግጥ ተዓምር አልለ፡፡ አንደኛዋ ጭፍራ በአላህ መንገድ ትጋደላለች፡፡ ሌላይቱም ከሓዲ ናት፡፡ ከሓዲዎቹ (አማኞቹን) በዓይን አስተያየት እጥፋቸውን ኾነው ያዩዋቸዋል፡፡ አላህም በርዳታው የሚሻውን ሰው ያበረታል፡፡ በዚህ ውስጥ ለማስተዋል ባለቤቶች በእርግጥ መገሰጫ አለበት፡፡
ﮠﮡﮢﮣﮤﮥﮦﮧﮨﮩﮪﮫﮬﮭﮮﮯﮰﮱﯓﯔﯕﯖﯗﯘﯙﯚﯛ
3:14 ከሴቶች፣ ከወንዶች ልጆችም፣ ከወርቅና ከብር፣ ከተካመቹ ገንዘቦችም፣ ከተሰማሩ ፈረሶችም፣ ከግመል ከከብትና ከፍየልም፣ ከአዝመራም የኾኑ ፍላጎቶችን መውደድ ለሰዎች ተሸለመ፡፡ ይህ ሁሉ የቅርቢቱ ሕይወት መጠቀሚያ ነው፡፡ አላህም እርሱ ዘንድ መልካም መመለሻ (ገነት) አለ፡፡
ﯜﯝﯞﯟﯠﯡﯢﯣﯤﯥﯦﯧﯨﯩﯪﯫﯬﯭﯮﯯﯰﯱﯲﯳﯴﯵﯶﯷ
3:15 «ከዚህ ሁሉ ነገር የሚበልጥን ልንገራችሁን» በላቸው፡፡ (እርሱም) «ለእነዚያ ለተጠነቀቁት ሰዎች በጌታቸው ዘንድ በሥራቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች በውስጧ ሁልጊዜ ነዋሪዎች ሲኾኑ ንጹሕ የተደረጉ ሚስቶችም፣ ከአላህም የኾነ ውዴታ አላቸው፡፡ አላህም ባሮቹን ተመልካች ነው፡፡»
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖﭗﭘﭙﭚﭛﭜ
3:16 (እነርሱም) እነዚያ፡- «ጌታችን ሆይ! እኛ አመንን ኀጢአቶቻችንንም ለእኛ ማር፤ የእሳትንም ቅጣት ጠብቀን» የሚሉ ናቸው፡፡
ﭝﭞﭟﭠﭡﭢﭣ
3:17 ታጋሾች እውነተኞችም ታዛዦችም ለጋሶችና በሌሊት መጨረሻዎች ምሕረትን ለማኞች ናቸው፡፡
ﭤﭥﭦﭧﭨﭩﭪﭫﭬﭭﭮﭯﭰﭱﭲﭳﭴﭵﭶﭷ
3:18 አላህ በማስተካከል የቆመ (አስተናባሪ) ሲኾን ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የሌለ መኾኑን መሰከረ፡፡ መላእክቶችና የዕውቀት ባለቤቶችም (እንደዚሁ መሰከሩ)፡፡ ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡
ﭸﭹﭺﭻﭼﭽﭾﭿﮀﮁﮂﮃﮄﮅﮆﮇﮈﮉﮊﮋﮌﮍﮎﮏﮐﮑﮒﮓﮔ
3:19 አላህ ዘንድ (የተወደደ) ሃይማኖት ኢስላም ብቻ ነው፡፡ እነዚያም መጽሐፉን የተሰጡት ሰዎች በመካከላቸው ላለው ምቀኝነት ዕውቀቱ ከመጣላቸው በኋላ እንጅ አልተለያዩም፡፡ በአላህም አንቀጾች የሚክድ አላህ ምርመራው ፈጣን ነው፡፡
ﮕﮖﮗﮘﮙﮚﮛﮜﮝﮞﮟﮠﮡﮢﮣﮤﮥﮦﮧﮨﮩﮪﮫﮬﮭﮮﮯﮰﮱﯓﯔ
3:20 ቢከራከሩህም፡- «ፊቴን ለአላህ ሰጠሁ፤ የተከተሉኝም ሰዎች (እንደዚሁ ለአላህ ሰጡ)» በላቸው፡፡ ለእነዚያም መጽሐፍን ለተሰጡት ሰዎችና ለመሐይሞቹ፡- «ሰለማችሁን» በላቸው፡፡ ቢሰልሙም በእርግጥ ተመሩ፡፡ እምቢ ቢሉም በአንተ ላይ ያለብህ ማድረስ ብቻ ነው፡፡ አላህም ባሮቹን ተመልካች ነው፡፡
ﯕﯖﯗﯘﯙﯚﯛﯜﯝﯞﯟﯠﯡﯢﯣﯤﯥﯦﯧ
3:21 እነዚያ በአላህ አንቀጾች የሚክዱ ነቢያትንም ያለ አግባብ የሚገድሉ ከሰዎችም ውስጥ እነዚያን በትክክለኛነት የሚያዙትን የሚገድሉ በአሳማሚ ቅጣት አብስራቸው፡፡
ﯨﯩﯪﯫﯬﯭﯮﯯﯰﯱﯲﯳ
3:22 እነዚያ በቅርቢቱና በመጨረሻይቱ ዓለም ሥራዎቻቸው የተበላሹ ናቸው፡፡ ለእነርሱም ምንም ረዳቶች የሏቸውም፡፡
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖﭗﭘﭙﭚﭛﭜﭝﭞﭟﭠﭡﭢﭣﭤﭥ
3:23 ወደ እነዚያ ከመጽሐፉ (ትምህርት) ዕድልን ወደ ተሰጡት ሰዎች አላየህምን ወደ አላህ መጽሐፍ በመካከላቸው ይፈርድ ዘንድ ይጠራሉ፡፡ ከዚያም ከእነሱ ገሚሶቹ እነርሱ (እውነቱን) የተዉ ኾነው ይሸሻሉ፡፡
ﭦﭧﭨﭩﭪﭫﭬﭭﭮﭯﭰﭱﭲﭳﭴﭵﭶ
3:24 ይኸ እነርሱ «እሳት የተቆጠሩ ቀኖችን እንጅ አትነካንም» በማለታቸው ነው፡፡ በሃይማኖታቸውም ይቀጣጥፉት የነበሩት ነገር አታለላቸው፡፡
ﭷﭸﭹﭺﭻﭼﭽﭾﭿﮀﮁﮂﮃﮄﮅﮆ
3:25 በርሱ (መምጣት) ጥርጥር የሌለበት በኾነው ቀን በሰበሰብናቸውና ነፍስ ሁሉ የሠራችውን ሥራ በተሞላች ጊዜ እንዴት ይኾናሉ እነርሱም አይበደሉም፡፡
ﮇﮈﮉﮊﮋﮌﮍﮎﮏﮐﮑﮒﮓﮔﮕﮖﮗﮘﮙﮚﮛﮜﮝﮞﮟﮠﮡﮢ
3:26 (ሙሐመድ ሆይ!) በል፡- «የንግስና ባለቤት የኾንክ አላህ ሆይ! ለምትሻው ሰው ንግሥናን ትሰጣለህ፡፡ ከምትሻውም ሰው ንግሥናን ትገፍፋለህ፡፡ የምትሻውንም ሰው ታልቃለህ፡፡ የምትሻውንም ሰው ታዋርዳለህ፡፡ መልካም ነገር ሁሉ በእጅህ (በችሎታህ) ነው፤ አንተ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነህና፡፡»
ﮣﮤﮥﮦﮧﮨﮩﮪﮫﮬﮭﮮﮯﮰﮱﯓﯔﯕﯖﯗﯘﯙﯚﯛ
3:27 ሌሊቱን በቀን ውስጥ ታስገባለህ፡፡ ቀኑንም በሌሊቱ ውስጥ ታስገባለህ፡፡ ሕያውንም ከሙት ውስጥ ታወጣለህ፡፡ ሙትንም ከሕያው ውስጥ ታወጣለህ፡፡ ለምትሻውም ሰው ያለግምት ትሰጣለህ፡፡
ﯜﯝﯞﯟﯠﯡﯢﯣﯤﯥﯦﯧﯨﯩﯪﯫﯬﯭﯮﯯﯰﯱﯲﯳﯴﯵﯶﯷﯸﯹﯺ
3:28 ምእምናን ከሓዲዎችን ከምእምናን ሌላ ረዳቶች አድርገው አይያዙ፡፡ ይኼንንም የሚሠራ ሰው ከአላህ (ሃይማኖት) በምንም ውስጥ አይደለም፡፡ ከእነርሱ መጥጠበቅን ብትጠበቁ እንጂ፡፡ አላህም ነፍሱን (ቁጣውን) ያስጠነቅቃችኋል፡፡ መመለሻም ወደ አላህ ብቻ ነው፡፡
ﯻﯼﯽﯾﯿﰀﰁﰂﰃﰄﰅﰆﰇﰈﰉﰊﰋﰌﰍﰎﰏﰐﰑﰒﰓ
3:29 «በደረቶቻችሁ ውስጥ ያለውን ነገር ብትደብቁ ወይም ብትገልፁት አላህ ያውቀዋል፡፡ በሰማያት ያለውንና በምድርም ያለውን ሁሉ ያውቃል፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው» (በል)፡፡
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖﭗﭘﭙﭚﭛﭜﭝﭞﭟﭠﭡﭢﭣﭤﭥﭦﭧﭨﭩﭪﭫﭬﭭ
3:30 ነፍስ ሁሉ ከመልካም ነገር የሠራችውን የቀረበ ኾኖ የምታገኝበትን ቀን (አስታውስ)፡፡ ከመጥፎም የሠራችው በርስዋና በርሱ (በኀጢአትዋ) መካከል በጣም የሰፋ ርቀት ቢኖር ትመኛለች፡፡ አላህ ነፍሱን ያስጠነቅቃችኋል፡፡ አላህም ለባሮቹ ሩኅሩኅ ነው፡፡
ﭮﭯﭰﭱﭲﭳﭴﭵﭶﭷﭸﭹﭺﭻﭼﭽ
3:31 በላቸው፡- «አላህን የምትወዱ እንደኾናችሁ ተከተሉኝ፤ አላህ ይወዳችኋልና፡፡ ኀጢኣቶቻችሁንም ለናንተ ይምራልና፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡»
ﭾﭿﮀﮁﮂﮃﮄﮅﮆﮇﮈﮉﮊ
3:32 «አላህንና መልክተኛውን ታዘዙ፡፡ ብትሸሹም አላህ ከሓዲዎችን አይወድም» በላቸው፡፡
ﮋﮌﮍﮎﮏﮐﮑﮒﮓﮔﮕﮖﮗ
3:33 አላህ አደምን፣ ኑሕንም፣ የኢብራሂምንም ቤተሰብ፣ የዒምራንንም ቤተሰብ በዓለማት ላይ መረጠ፡፡
ﮘﮙﮚﮛﮜﮝﮞﮟﮠ
3:34 ከፊልዋ ከከፊሉ የኾነች ዝርያ አድርጎ (መረጣት)፡፡ አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡
ﮡﮢﮣﮤﮥﮦﮧﮨﮩﮪﮫﮬﮭﮮﮯﮰﮱﯓﯔﯕ
3:35 የዒምራን ባለቤት (ሐና) «ጌታዬ ሆይ! እኔ በሆዴ ውስጥ ያለውን (ፅንስ ከሥራ) ነጻ የተደረገ ሲኾን ለአንተ ተሳልኩ፡፡ ከእኔም ተቀበል አንተ ሰሚው ዐዋቂው ነህና» ባለች ጊዜ (አስታውስ)፡፡
ﯖﯗﯘﯙﯚﯛﯜﯝﯞﯟﯠﯡﯢﯣﯤﯥﯦﯧﯨﯩﯪﯫﯬﯭﯮﯯ
3:36 በወለደቻትም ጊዜ፡- «ጌታዬ ሆይ! እኔ ሴት ኾና ወለድኋት፡፡» አላህም የወለደችውን ዐዋቂ ነው፡፡ «ወንድም እንደ ሴት አይደለም፡፡ እኔም መርየም ብዬ ስም አወጣሁላት፡፡ እኔም እስዋንም ዝርያዋንም ከተረገመው ሰይጣን በአንተ እጠብቃቸዋለሁ» አለች፡፡
ﯰﯱﯲﯳﯴﯵﯶﯷﯸﯹﯺﯻﯼﯽﯾﯿﰀﰁﰂﰃﰄﰅﰆﰇﰈﰉﰊﰋﰌﰍﰎﰏﰐﰑﰒﰓﰔﰕﰖ
3:37 ጌታዋም በደህና አቀባበል ተቀበላት፡፡ በመልካም አስተዳደግም አፋፋት፡፡ ዘከሪያም አሳደጋት፤ ዘከሪያ በርሷ ላይ በምኹራቧ በገባ ቁጥር እርስዋ ዘንድ ሲሳይን አገኘ፡፡ «መርየም ሆይ! ይህ ለአንቺ ከየት ነው» አላት፡፡ «እርሱ ከአላህ ዘንድ ነው፡፡ አላህ ለሚሻው ሰው ሲሳዩን ያለ ድካም ይሰጣል» አለችው፡፡
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖﭗﭘﭙﭚﭛﭜﭝﭞﭟﭠﭡﭢ
3:38 እዚያ ዘንድ ዘከሪያ ጌታውን ለመነ፡፡ «ጌታዬ ሆይ! ከአንተ ዘንድ መልካም ዘርን ለኔ ስጠኝ አንተ ጸሎትን ሰሚነህና» አለ፡፡
ﭣﭤﭥﭦﭧﭨﭩﭪﭫﭬﭭﭮﭯﭰﭱﭲﭳﭴﭵﭶﭷ
3:39 እርሱም በጸሎት ማድረሻው ክፍል ቆሞ ሲጸልይ መላእክት ጠራችው፡፡ «አላህ በየሕያ ከአላህ በኾነ ቃል የሚያረጋግጥ ጌታም ድንግልም ከደጋጎቹ ነቢይም ሲኾን ያበስርሃል» በማለት (መላእክት ጠራችው)፡፡
ﭸﭹﭺﭻﭼﭽﭾﭿﮀﮁﮂﮃﮄﮅﮆﮇﮈﮉﮊ
3:40 «ጌታዬ ሆይ! እኔ እርጅና በእርግጥ የደረሰብኝ ስኾን ባልተቤቴም መሐን ስትሆን ለእኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል አለ፡፡ (መልአኩም) እንደዚሁ አላህ የሚሻውን ነገር ይሠራል» አለው፡፡
ﮋﮌﮍﮎﮏﮐﮑﮒﮓﮔﮕﮖﮗﮘﮙﮚﮛﮜﮝﮞﮟﮠﮡ
3:41 «ጌታዬ ሆይ! ለእኔ ምልክትን አድርግልኝ» አለ፡፡ «ምልክትህ ሦስት ቀን በጥቅሻ ቢኾን እንጅ ሰዎችን አለማናገርህ ነው፡፡ ጌታህንም በብዙ አውሳ፡፡ በማታና በጧትም አወድሰው» አለው፡፡
ﮢﮣﮤﮥﮦﮧﮨﮩﮪﮫﮬﮭﮮ
3:42 መላእክትም ያሉትን (አስታውስ)፡፡ «መርየም ሆይ! አላህ በእርግጥ መረጠሸ፡፡ አነጻሽም፡፡ በዓለማት ሴቶችም ላይ መረጠሽ፡፡»
ﮯﮰﮱﯓﯔﯕﯖﯗ
3:43 «መርየም ሆይ! ለጌታሽ ታዘዢ፡፡ ስገጂም፡፡ ከአጎንባሾቹም ጋር አጎንብሺ፡፡»
ﯘﯙﯚﯛﯜﯝﯞﯟﯠﯡﯢﯣﯤﯥﯦﯧﯨﯩﯪﯫﯬﯭ
3:44 ይኸ ወደ አንተ የምናወርደው የኾነ ከሩቅ ወሬዎች ነው፡፡ መርየምንም ማን እንደሚያሳድግ ብርኦቻቸውን (ለዕጣ) በጣሉ ጊዜ እነሱ ዘንድ አልነበርክም፡፡ በሚከራከሩም ጊዜ እነሱ ዘንድ አልነበርክም፡፡
ﯮﯯﯰﯱﯲﯳﯴﯵﯶﯷﯸﯹﯺﯻﯼﯽﯾﯿﰀﰁﰂ
3:45 መላእክት ያሉትን (አስታውስ)፡- «መርየም ሆይ! አላህ ከርሱ በኾነው ቃል ስሙ አልመሲሕ ዒሳ የመርየም ልጅ በዚህ ዓለምና በመጨረሻውም ዓለም የተከበረ ከባለሟሎችም በኾነ (ልጅ) ያበስርሻል፡፡»
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖﭗﭘ
3:46 «በሕፃንነቱና በከፈኒሳነቱ ሰዎቹን ያነጋግራል፡፡ ከመልካሞቹም ነው» (አላት)፡፡
ﭙﭚﭛﭜﭝﭞﭟﭠﭡﭢﭣﭤﭥﭦﭧﭨﭩﭪﭫﭬﭭﭮﭯﭰﭱﭲ
3:47 ፡-ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል አለች፡፡ ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ አንዳችን በሻ ጊዜ ለርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል አላት፡፡
ﭳﭴﭵﭶﭷﭸ
3:48 ጽሕፈትንና ጥበብንም ተውራትንና ኢንጂልንም ያስተምረዋል፡፡
ﭹﭺﭻﭼﭽﭾﭿﮀﮁﮂﮃﮄﮅﮆﮇﮈﮉﮊﮋﮌﮍﮎﮏﮐﮑﮒﮓﮔﮕﮖﮗﮘﮙﮚﮛﮜﮝﮞﮟﮠﮡﮢﮣﮤﮥﮦﮧﮨﮩﮪ
3:49 ወደ እስራኤልም ልጆች መልክተኛ ያደርገዋል፡፡ (ይላልም)፡- «እኔ ከጌታዬ ዘንድ በተዓምር ወደ እናንተ መጣሁ፡፡ እኔ ለናንተ ከጭቃ እንደ ወፍ ቅርፅ እፈጥራለሁ፡፡ በርሱም እተነፍስበታለሁ፡፡ በአላህም ፈቃድ ወፍ ይኾናል፡፡ በአላህም ፈቃድ ዕውር ኾኖ የተወለደን፣ ለምጸኛንም አድናለሁ፡፡ ሙታንንም አስነሳለሁ፡፡ የምትበሉትንና በቤታችሁ የምታደልቡትንም ሁሉ እነግራችኋለሁ፡፡ የምታምኑ እንደኾናችሁ ለእናንተ በዚህ ውስጥ በእርግጥ ተዓምር አለበት፡፡»
ﮫﮬﮭﮮﮯﮰﮱﯓﯔﯕﯖﯗﯘﯙﯚﯛﯜﯝﯞﯟﯠ
3:50 «ከተውራትም ከእኔ በፊት ያለውን ያረጋገጥሁ ስኾን የዚያንም በእናንተ ላይ እርም የተደረገውን ከፊል ለእናንተ እፈቅድ ዘንድ (መጣኋችሁ) ከጌታችሁም በኾነ ታምር መጣሁዋችሁ፡፡ አላህንም ፍሩ፤ ታዘዙኝም፡፡»
ﯡﯢﯣﯤﯥﯦﯧﯨﯩﯪ
3:51 «አላህ ጌታዬና ጌታችሁ ነው፤ ስለዚህ ተገዙት፤ ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው» (አላቸው)፡፡
ﯫﯬﯭﯮﯯﯰﯱﯲﯳﯴﯵﯶﯷﯸﯹﯺﯻﯼﯽﯾﯿﰀﰁ
3:52 ዒሳ ከነርሱ ክህደት በተሰማውም ጊዜ፡- «ወደ አላህ (ተጨምረው) ረዳቶቼ እነማን ናቸው» አለ፤ ሐዋርያት፡- «እኛ የአላህ ረዳቶች ነን፤ በአላህ አምነናል፤ እኛም ትክክለኛ ታዛዦች መኾናችንን መስክር» አሉ፡፡
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖﭗﭘﭙﭚ
3:53 «ጌታችን ሆይ! ባወረድኸው አመንን፤ መልክተኛውንም ተከተልን፤ ከመስካሪዎችም ጋር መዝግበን» (አሉ)፡፡
ﭛﭜﭝﭞﭟﭠﭡﭢ
3:54 (አይሁዶችም) አደሙ አላህም አድማቸውን መለሰባቸው፡፡ አላህም ከአድመኞች ሁሉ በላጭ ነው፡፡
ﭣﭤﭥﭦﭧﭨﭩﭪﭫﭬﭭﭮﭯﭰﭱﭲﭳﭴﭵﭶﭷﭸﭹﭺﭻﭼﭽﭾﭿﮀﮁﮂ
3:55 አላህም ባለ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ ዒሳ ሆይ! እኔ ወሳጂህ ወደ እኔም አንሺህ ነኝ፡፡ ከነዚያም ከካዱት ሰዎች አጥሪህ ነኝ እነዚያንም የተከተሉህን እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ ከነዚያ ከካዱት በላይ አድራጊ ነኝ፡፡ ከዚያም መመለሻችሁ ወደእኔ ነው፡፡ በርሱ ትለያዩበትም በነበራችሁት ነገር በመካከላችሁ እፈርዳለሁ፡፡
ﮃﮄﮅﮆﮇﮈﮉﮊﮋﮌﮍﮎﮏﮐ
3:56 «እነዚያማ የካዱትን ሰዎች በቅርቢቱ ዓለምና በመጨረሻይቱ ዓለም ብርቱን ቅጣት እቀጣቸዋለሁ፡፡ ለእነርሱም ምንም ረዳቶች የሏቸውም፡፡»
ﮑﮒﮓﮔﮕﮖﮗﮘﮙﮚﮛﮜﮝ
3:57 እነዚያም ያመኑትማ መልካም ሥራዎችንም የሠሩት ምንዳዎቻቸውን ይሞላላቸዋል፡፡ አላህም በዳዮችን አይወድም፡፡
ﮞﮟﮠﮡﮢﮣﮤﮥ
3:58 ይህ ከተዓምራቶችና ጥበብን ከያዘው ተግሳጽ ሲኾን በአንተ ላይ እናነበዋለን፡፡
ﮦﮧﮨﮩﮪﮫﮬﮭﮮﮯﮰﮱﯓﯔﯕﯖﯗ
3:59 አላህ ዘንድ የዒሳ ምሳሌ እንደ አዳም ብጤ ነው፡፡ ከዐፈር ፈጠረው፡፡ ከዚያም ለርሱ (ሰው) «ኹን» አለው፤ ኾነም፡፡
ﯘﯙﯚﯛﯜﯝﯞﯟ
3:60 ይህ ከጌታህ ዘንድ የኾነ እውነት ነው፡፡ ከተጠራጣሪዎቹም አትኹን፡፡
ﯠﯡﯢﯣﯤﯥﯦﯧﯨﯩﯪﯫﯬﯭﯮﯯﯰﯱﯲﯳﯴﯵﯶﯷﯸﯹ
3:61 ዕውቀቱም ከመጣልህ በኋላ በርሱ (በዒሳ) የተከራከሩህን ሰዎች «ኑ፤ ልጆቻችንንና ልጆቻችሁን፣ ሴቶቻችንንና ሴቶቻችሁንም፣ ነፍሶቻችንንና ነፍሶቻችሁንም እንጥራ፡፡ ከዚያም አጥብቀን አላህን እንለምን፤ የአላህንም ቁጣ በውሸታሞቹ ላይ እናድርግ» በላቸው፡፡
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖﭗﭘﭙﭚﭛﭜﭝﭞﭟﭠﭡﭢ
3:62 ይህ እርሱ በእርግጥ እውነተኛ ታሪክ ነው፡፡ አምላክም ከአላህ በስተቀር ምንም የለም፡፡ አላህም እርሱ በእርግጥ አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡
ﭣﭤﭥﭦﭧﭨﭩ
3:63 (ከማመን) እንቢ ቢሉም አላህ አጥፊዎቹን በእርግጥ ዐዋቂ ነው፡፡
ﭪﭫﭬﭭﭮﭯﭰﭱﭲﭳﭴﭵﭶﭷﭸﭹﭺﭻﭼﭽﭾﭿﮀﮁﮂﮃﮄﮅﮆﮇﮈﮉﮊ
3:64 የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በእኛና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ፡፡ (እርሷም) አላህን እንጅ ሌላን ላንገዛ፣ በርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርጎ ላይይዝ ነው፤ በላቸው፡፡ እምቢ ቢሉም፡- እኛ ሙስሊሞች መኾናችንን መስክሩ በሏቸው፡፡
ﮋﮌﮍﮎﮏﮐﮑﮒﮓﮔﮕﮖﮗﮘﮙﮚﮛ
3:65 እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በኢብራሂም ለምን ትከራከራላችሁ ተውራትና ኢንጂልም ከርሱ በኋላ እንጅ አልተወረዱም፡፡ ልብ አታደርጉምን በላቸው፡፡
ﮜﮝﮞﮟﮠﮡﮢﮣﮤﮥﮦﮧﮨﮩﮪﮫﮬﮭﮮﮯﮰ
3:66 ንቁ! እናንተ እነዚያ ለእናንተ በርሱ ዕውቀት ባላችሁ ነገር የተከራከራችሁ ናችሁ፡፡ ታዲያ ለእናንተ በርሱ ዕውቀት በሌላችሁ ነገር ለምን ትከራከራላችሁ አላህም ያውቃል፡፡ እናንተ ግን አታውቁም፡፡
ﮱﯓﯔﯕﯖﯗﯘﯙﯚﯛﯜﯝﯞﯟﯠ
3:67 ኢብራሂም ይሁዳዊም ክርስቲያንም አልነበረም፡፡ ግን ወደ ቀጥተኛው ሃይማኖት የተዘነበለ ሙስሊም ነበረ፡፡ ከአጋሪዎችም አልነበረም፡፡
ﯡﯢﯣﯤﯥﯦﯧﯨﯩﯪﯫﯬﯭﯮﯯ
3:68 ከሰው ሁሉ በኢብራሂም ተገቢዎቹ እነዚያ የተከተሉትና ይህ ነቢይ እነዚያም ያመኑት ናቸው፡፡ አላህም የምእምናን ረዳት ነው፡፡
ﯰﯱﯲﯳﯴﯵﯶﯷﯸﯹﯺﯻﯼﯽ
3:69 ከመጽሐፉ ባለቤቶች የኾኑ ጭፍሮች ነፍሶቻቸውን እንጂ የማያሳስቱ ሲኾኑ ሊያሳስቱዋችሁ ተመኙ ግን አያውቁም፡፡
ﯾﯿﰀﰁﰂﰃﰄﰅﰆ
3:70 የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! እናንተ የምታውቁ ስትኾኑ በአላህ አንቀጾች ለምን ትክዳላችሁ
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖﭗﭘﭙﭚﭛ
3:71 «የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! እውነቱን በውሸት ለምን ትቀላቅላላችሁ እውነቱንም እናንተ የምታውቁ ስትኾኑ ለምን ትደብቃላችሁ»
ﭜﭝﭞﭟﭠﭡﭢﭣﭤﭥﭦﭧﭨﭩﭪﭫﭬﭭ
3:72 ከመጽሐፉ ባለቤቶች የኾኑ ጭፍሮችም አሉ፡- «በነዚያ በአመኑት ላይ በተወረደው (ቁርኣን) በቀኑ መጀመሪያ ላይ እመኑበት፡፡ በመጨረሻውም ካዱት፡፡ እነርሱ ሊመለሱ ይከጀላልና፡፡»
ﭮﭯﭰﭱﭲﭳﭴﭵﭶﭷﭸﭹﭺﭻﭼﭽﭾﭿﮀﮁﮂﮃﮄﮅﮆﮇﮈﮉﮊﮋﮌﮍﮎﮏﮐ
3:73 እናንተ የተሰጣችሁትን ብጤ አንድም ሰው መሰጠቱን ወይም እጌታችሁ ዘንድ የሚከራከሩዋችሁ መኾንን ሃይማኖታችሁን ለተከተለ ሰው ቢኾን እንጂ አትመኑ (አትግለጹ አሉ)፡፡ «መምሪያው የአላህ መምሪያ ብቻ ነው» በላቸው፡፡ «ችሮታ በአላህ እጅ ነው፡፡ ለሚሻው ይሰጠዋል፡፡ አላህም ችሮታው ሰፊ ዐዋቂ ነው» በላቸው፡፡
ﮑﮒﮓﮔﮕﮖﮗﮘﮙﮚ
3:74 በችሮታው (በነቢይነት) የሚሻውን ይመርጣል፡፡ አላህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው፡፡
ﮛﮜﮝﮞﮟﮠﮡﮢﮣﮤﮥﮦﮧﮨﮩﮪﮫﮬﮭﮮﮯﮰﮱﯓﯔﯕﯖﯗﯘﯙﯚﯛﯜﯝﯞﯟﯠﯡﯢ
3:75 ከመጽሐፉ ሰዎችም በብዙ ገንዘብ ብታምነው ወዳንተ የሚመልስ ሰው አልለ፡፡ ከእነሱም በአንድ ዲናር እንኳ ብታምነው፤ ሁል ጊዜ በርሱ ላይ የምትጠባበቅ ካልኾንክ በስተቀር የማይመልስ ሰው አልለ፡፡ «ይህ በመሃይምናን (በምናደርገው) በእኛ ላይ ምንም መንገድ የለብንም» ስለሚሉ ነው፡፡ እነርሱ እያወቁም በአላህ ላይ ውሸትን ይናገራሉ፡፡
ﯣﯤﯥﯦﯧﯨﯩﯪﯫﯬﯭ
3:76 አይደለም (አለባቸው እንጅ)፡፡ በቃል ኪዳኑ የሞላና የተጠነቀቀ ሰው አላህ ጥንቁቆችን ይወዳል፡፡
ﯮﯯﯰﯱﯲﯳﯴﯵﯶﯷﯸﯹﯺﯻﯼﯽﯾﯿﰀﰁﰂﰃﰄﰅﰆﰇﰈﰉ
3:77 እነዚህ በአላህ ቃል ኪዳንና በመሐላዎቻቸው ጥቂትን ዋጋ የሚለውጡ እነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም ምንም ዕድል የላቸውም፡፡ በትንሣኤ ቀንም አላህ አያነጋግራቸውም፡፡ ወደ እነርሱም አይመለከትም አያነጻቸውምም፡፡ ለነሱም አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖﭗﭘﭙﭚﭛﭜﭝﭞﭟﭠﭡﭢﭣﭤﭥﭦﭧﭨﭩﭪﭫﭬﭭﭮ
3:78 ከእነሱም እርሱ ከመጽሐፉ ያይደለ ሲኾን ከመጽሐፉ መኾኑን እንድታስቡ በመጽሐፉ ምላሶቻቸውን የሚያጣምሙ ክፍሎች አሉ፡፡ እርሱ ከአላህ ዘንድ ያልኾነ ሲኾን «እርሱ ከአላህ ዘንድ ነውም» ይላሉ፡፡ እነርሱ የሚያውቁ ሲኾኑም በአላህ ላይ ውሸትን ይናገራሉ፡፡
ﭯﭰﭱﭲﭳﭴﭵﭶﭷﭸﭹﭺﭻﭼﭽﭾﭿﮀﮁﮂﮃﮄﮅﮆﮇﮈﮉﮊﮋ
3:79 ለማንም ሰው አላህ መጽሐፍንና ጥበብን ነቢይነትንም ሊሰጠውና ከዚያም ለሰዎች «ከአላህ ሌላ ለእኔ ባሮች ኾኑ» ሊል አይገባውም፡፡ «ግን መጽሐፍን የምታስተምሩ በነበራችሁትና የምታጠኑም በነበራችሁት በዕውቀታችሁ ሠሪዎች ኹኑ» (ይላቸዋል)፡፡
ﮌﮍﮎﮏﮐﮑﮒﮓﮔﮕﮖﮗﮘﮙﮚ
3:80 መላእክትንና ነቢያትንም አማልክቶች አድርጋችሁ እንድትይዙ ሊያዛችሁ (አይገባውም)፡፡ እናንተ ሙስሊሞች ከኾናችሁ በኋላ በክህደት ያዛችኋልን
ﮛﮜﮝﮞﮟﮠﮡﮢﮣﮤﮥﮦﮧﮨﮩﮪﮫﮬﮭﮮﮯﮰﮱﯓﯔﯕﯖﯗﯘﯙﯚﯛﯜﯝﯞﯟﯠ
3:81 አላህ የነቢያትን ቃል ኪዳን ከመጽሐፍና ከጥበብ ሰጥቻችሁ ከዚያም «ከእናንተ ጋር ላለው (መጽሐፍ) የሚያረጋግጥ መልክተኛ ቢመጣላችሁ በርሱ በእርግጥ እንደምታምኑበት በእርግጥም እንድትረዱት ሲል በያዘ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ አረጋገጣችሁን በዚህም ላይ ኪዳኔን ያዛችሁምን» አላቸው፡፡ «አረጋገጥን» አሉ፡፡ «እንግዲያስ መስክሩ፤ እኔም ከእናንተ ጋር ከመስካሪዎቹ ነኝ» አላቸው፡፡
ﯡﯢﯣﯤﯥﯦﯧﯨ
3:82 ከዚህም በኋላ የሸሹ ሰዎች እነዚያ እነሱ አመጸኞቹ ናቸው፡፡
ﯩﯪﯫﯬﯭﯮﯯﯰﯱﯲﯳﯴﯵﯶﯷ
3:83 በሰማያትና በምድር ያሉ ሁሉ፤ በውድም በግድም ለርሱ የታዘዙ ወደርሱም የሚመለሱ ሲኾኑ (ከሓዲዎች) ከአላህ ሃይማኖት ሌላን ይፈልጋሉን
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖﭗﭘﭙﭚﭛﭜﭝﭞﭟﭠﭡﭢﭣﭤﭥﭦﭧﭨﭩﭪﭫﭬﭭﭮ
3:84 «በአላህ አመንን፡፡ በእኛ ላይ በተወረደውም (በቁርኣን)፣ በኢብራሂምና በኢስማዒልም፣ በኢስሓቅም፣ በያዕቆብም፣ በነገዶችም ላይ በተወረደው፤ ለሙሳና ለዒሳም ለነቢያትም ሁሉ ከጌታቸው በተሰጠው (አመንን)፡፡ ከእነርሱ መካከል አንድንም አንለይም፡፡ እኛ ለእርሱ ታዛዦች ነን» በል፡፡
ﭯﭰﭱﭲﭳﭴﭵﭶﭷﭸﭹﭺﭻﭼ
3:85 ከኢስላም ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰው ፈጽሞ ከርሱ ተቀባይ የለውም፡፡ እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎቹ ነው፡፡
ﭽﭾﭿﮀﮁﮂﮃﮄﮅﮆﮇﮈﮉﮊﮋﮌﮍﮎﮏﮐ
3:86 ከእምነታቸውና መልክተኛውም እውነት መኾኑን ከመሰከሩ የተብራሩ አንቀጾችም ከመጡላቸው በኋላ የካዱን ሕዝቦች አላህ እንዴት ያቀናል! አላህ በዳዮችንም ሕዝቦች አያቀናም፡፡
ﮑﮒﮓﮔﮕﮖﮗﮘﮙﮚ
3:87 እነዚያ ቅጣታቸው የአላህና የመላእክት የሰዎችም ሁሉ ርግማን በእነሱ ላይ መኾን ነው፡፡
ﮛﮜﮝﮞﮟﮠﮡﮢﮣﮤ
3:88 በውስጧ ዘውታሪዎች ሲኾኑ ቅጣቱም ከነሱ ላይ አይቃለልላቸውም፡፡ እነሱም ቀን አይስሰጡም፡፡
ﮥﮦﮧﮨﮩﮪﮫﮬﮭﮮﮯﮰ
3:89 እነዚያ ከዚህ በኋላ ንስሓ የገቡና (ሥራቸውን) ያሳመሩ ሲቀሩ፡፡ (እነዚህንስ ይምራቸዋል)፤ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡
ﮱﯓﯔﯕﯖﯗﯘﯙﯚﯛﯜﯝﯞﯟﯠ
3:90 እነዚያ ከእምነታቸው በኋላ የካዱ ከዚያም ክህደትን የጨመሩ ጸጸታቸው ፈጽሞ ተቀባይ የላትም፡፡ እነዚያም የተሳሳቱ እነርሱ ናቸው፡፡
ﯡﯢﯣﯤﯥﯦﯧﯨﯩﯪﯫﯬﯭﯮﯯﯰﯱﯲﯳﯴﯵﯶﯷﯸﯹﯺ
3:91 እነዚያ የካዱና እነርሱም በክህደታቸው ላይ እንዳሉ የሞቱ ከእነሱ ከአንዳቸው በምድር ሙሉ የኾነ ወርቅ (ቢኖረውና) በርሱ ቢበዥበትም እንኳ ፈጽሞ ተቀባይን አያገኝም፡፡ እነዚያ ለእነርሱ የሚያሰቃይ ቅጣት አላቸው፡፡ ለነርሱም ምንም ረዳቶች የሏቸውም፡፡
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖﭗﭘﭙﭚﭛﭜﭝﭞﭟﭠﭡ
3:92 የምትወዱትን እስከምትለግሱ ድረስ በጎን ሥራ (ዋጋውን) አታገኙም፡፡ ከምንም ነገር ብትለግሱ አላህ ያውቀዋል፡፡
ﭢﭣﭤﭥﭦﭧﭨﭩﭪﭫﭬﭭﭮﭯﭰﭱﭲﭳﭴﭵﭶﭷﭸﭹﭺﭻﭼ
3:93 ተውራት ከመወረድዋ በፊት እስራኤል በራሱ ላይ እርም ካደረገው ነገር በስተቀር ምግብ ሁሉ ለእስራኤል ልጆች የተፈቀደ ነበር፡፡ እውነተኞችም እንደኾናችሁ ተውራትን አምጡ አንብቡዋትም በላቸው፡፡
ﭽﭾﭿﮀﮁﮂﮃﮄﮅﮆﮇﮈ
3:94 ከዚህም በኋላ በአላህ ላይ ውሸትን የቀጣጠፉ ሰዎች እነዚያ እነርሱ በደለኞች ናቸው፡፡
ﮉﮊﮋﮌﮍﮎﮏﮐﮑﮒﮓﮔﮕﮖ
3:95 «አላህ እውነትን ተናገረ፡፡ የኢብራሂምንም መንገድ ወደ እውነት ያዘነበለ ሲኾን ተከተሉ፡፡ ከአጋሪዎቹም አልነበረም» በላቸው፡፡
ﮗﮘﮙﮚﮛﮜﮝﮞﮟﮠﮡ
3:96 ለሰዎች (መጸለያ) መጀመሪያ የተኖረው ቤት ብሩክና ለዓለማት ሁሉ መመሪያ ሲኾን ያ በበካህ (በመካ) ያለው ነው፡፡
ﮢﮣﮤﮥﮦﮧﮨﮩﮪﮫﮬﮭﮮﮯﮰﮱﯓﯔﯕﯖﯗﯘﯙﯚﯛﯜﯝﯞﯟ
3:97 በውስጡ ግልጽ የኾኑ ተዓምራቶች የኢብራሒምም መቆሚያ አልለ፡፡ ወደ ውስጡ የገባ ሰው ጸጥተኛ ይኾናል፡፡ ለአላህም በሰዎች ላይ ወደርሱ መኼድን በቻለ ሁሉ ላይ ቤቱን መጎብኘት ግዴታ አለባቸው፡፡ የካደም ሰው አላህ ከዓለማት ሁሉ የተብቃቃ ነው፡፡
ﯠﯡﯢﯣﯤﯥﯦﯧﯨﯩﯪﯫﯬ
3:98 «የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! አላህ በምትሠሩት ሁሉ ላይ ዐዋቂ ሲኾን በአላህ ተዓምራት ለምን ትክዳላችሁ» በላቸው፡፡
ﯭﯮﯯﯰﯱﯲﯳﯴﯵﯶﯷﯸﯹﯺﯻﯼﯽﯾﯿﰀﰁ
3:99 «የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! እናንተ መስካሪዎች ኾናችሁ ከአላህ መንገድ መጥመሟን የምትፈልጓት ስትኾኑ ያመነን ሰው ለምን ትከለክላላችሁ አላህም ከምትሰሩት ነገር ሁሉ ዘንጊ አይደለም» በላቸው፡፡
ﰂﰃﰄﰅﰆﰇﰈﰉﰊﰋﰌﰍﰎﰏﰐ
3:100 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከነዚያ መጽሐፉን ከተሰጡት ሰዎች ከፊሉን ብትታዘዙ ከእምነታችሁ በኋላ ከሓዲዎች አድርገው ይመልሱዋችኋል፡፡
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖﭗﭘﭙﭚﭛﭜﭝﭞﭟﭠﭡﭢﭣ
3:101 የአላህም አንቀጾች በእናንተ ላይ የሚነበቡ ሲኾኑ መልክተኛውም በውስጣችሁ ያለ ሲኾን እናንተ እንዴት ትክዳላችሁ በአላህም የሚጠበቅ ሰው ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ተመራ፡፡
ﭤﭥﭦﭧﭨﭩﭪﭫﭬﭭﭮﭯﭰ
3:102 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገቢውን መጠንቀቅ ተጠንቀቁት፡፡ እናንተም ሙስሊሞች ኾናችሁ እንጅ አትሙቱ፡፡
ﭱﭲﭳﭴﭵﭶﭷﭸﭹﭺﭻﭼﭽﭾﭿﮀﮁﮂﮃﮄﮅﮆﮇﮈﮉﮊﮋﮌﮍﮎﮏﮐﮑﮒﮓﮔﮕ
3:103 የአላህንም (የማመን) ገመድ ሁላችሁም ያዙ፡፡ አትለያዩም፡፡ ጠበኞችም በነበራችሁ ጊዜ በእናንተ ላይ (የዋለውን) የአላህን ጸጋ አስታውሱ፡፡ በልቦቻችሁም መካከል አስማማ፡፡ በጸጋውም ወንድማማቾች ኾናችሁ፡፡ በእሳት ጉድጓድ አፋፍም ላይ ነበራችሁ፡፡ ከእርስዋም አዳናችሁ፡፡ እንደዚሁ ትመሩ ዘንድ አላህ ለእናንተ አንቀጾቹን ያብራራል፡፡
ﮖﮗﮘﮙﮚﮛﮜﮝﮞﮟﮠﮡﮢﮣﮤﮥ
3:104 ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ በመልካም ሥራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ፡፡ እነዚያም እነሱ የሚድኑ ናቸው፡፡
ﮦﮧﮨﮩﮪﮫﮬﮭﮮﮯﮰﮱﯓﯔﯕﯖ
3:105 እንደነዚያም ግልጽ ተዓምራት ከመጣላቸው በኋላ እንደተለያዩትና እንደ ተጨቃጨቁት አትኹኑ፡፡ እነዚያም ለእነርሱ ታላቅ ቅጣት አላቸው፡፡
ﯗﯘﯙﯚﯛﯜﯝﯞﯟﯠﯡﯢﯣﯤﯥﯦﯧﯨﯩ
3:106 ፊቶች የሚያበሩበትን ፊቶችም የሚጠቁሩበትን ቀን (አስታውስ)፡፡ እነዚያ ፊቶቻቸው የጠቆሩትማ «ከእምነታችሁ በኋላ ካዳችሁን ትክዱት በነበራችሁት ነገር ቅጣቱን ቅመሱ» (ይባላሉ)፡፡
ﯪﯫﯬﯭﯮﯯﯰﯱﯲﯳﯴﯵ
3:107 እነዚያም ፊቶቻቸው ያበሩትማ በአላህ ችሮታ (ገነት) ውስጥ ናቸው፡፡ እነርሱ በውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡
ﯶﯷﯸﯹﯺﯻﯼﯽﯾﯿﰀﰁﰂ
3:108 ይህች በአንተ ላይ በእውነት የምናነባት ስትኾን የአላህ ተዓምራት ናት፡፡ አላህም ለዓለማት በደልን የሚሻ አይደለም፡፡
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖﭗﭘﭙﭚﭛﭜﭝ
3:109 በሰማያት ያለውና በምድር ያለውም ሁሉ የአላህ ነው፡፡ ነገሮችም ሁሉ ወደ አላህ ብቻ ይመለሳሉ፡፡
ﭞﭟﭠﭡﭢﭣﭤﭥﭦﭧﭨﭩﭪﭫﭬﭭﭮﭯﭰﭱﭲﭳﭴﭵﭶﭷ
3:110 ለሰዎች ከተገለጸች ሕዝብ ሁሉ በላጭ ኾናችሁ በጽድቅ ነገር ታዛላችሁ፤ ከመጥፎም ነገር ታዛላችሁ፤ በአላህም (አንድነት) ታምናላችሁ፡፡ የመጽሐፉም ሰዎች ባመኑ ኖሮ ለነርሱ የተሻለ በኾነ ነበር፡፡ ከነርሱ አማኞች አሉ፡፡ አብዛኞቻቸው ግን አመጸኞች ናቸው፡፡
ﭸﭹﭺﭻﭼﭽﭾﭿﮀﮁﮂﮃﮄ
3:111 ማስከፋትን እንጅ ፈጽሞ አይጎዱዋችሁም፡፡ ቢዋጉዋችሁም ጀርባዎችን ያዙሩላችኋል (ይሸሻሉ)፡፡ ከዚያም አይረዱም፡፡
ﮅﮆﮇﮈﮉﮊﮋﮌﮍﮎﮏﮐﮑﮒﮓﮔﮕﮖﮗﮘﮙﮚﮛﮜﮝﮞﮟﮠﮡﮢﮣﮤﮥﮦﮧﮨﮩﮪ
3:112 የትም በተገኙበት ስፍራ ከአላህ በኾነ ቃል ኪዳን ከሰዎችም በኾነ ቃል ኪዳን (የተጠበቁ) ካልኾኑ በስተቀር በነርሱ ላይ ውርደት ተመታችባቸው፡፡ ከአላህም በኾነ ቁጣ ተመለሱ፡፡ በእነርሱም ላይ ድኽነት ተመታችባቸው፡፡ ይኸ እነርሱ በአላህ ተዓምራት ይክዱ ስለ ነበሩና ነቢያትንም ያለ ሕግ ይገድሉ ስለነበሩ ነው፡፡ ይህ በማመጻቸውና ወሰንን ይተላለፉ ስለነበሩ ነው፡፡
ﮫﮬﮭﮮﮯﮰﮱﯓﯔﯕﯖﯗﯘﯙﯚﯛﯜ
3:113 (የመጽሐፉ ሰዎች ሁሉ) እኩል አይደሉም፡፡ ከመጽሐፉ ሰዎች ቀጥ ያሉ በሌሊት ሰዓቶች እነርሱ የሚሰግዱ ኾነው የአላህን አንቀጾች የሚያነቡ ሕዝቦች አሉ፡፡
ﯝﯞﯟﯠﯡﯢﯣﯤﯥﯦﯧﯨﯩﯪﯫﯬﯭ
3:114 በአላህና በመጨረሻው ቀን ያምናሉ፡፡ በጽድቅ ነገርም ያዛሉ፡፡ ከመጥፎ ነገርም ይከለክላሉ፡፡ በበጎ ሥራዎችም ይጣደፋሉ፡፡ እነዚያም ከመልካሞቹ ናቸው፡፡
ﯮﯯﯰﯱﯲﯳﯴﯵﯶﯷﯸ
3:115 ከበጎ ሥራ ማንኛውንም ቢሠሩ አይካዱትም፡፡ አላህም ጥንቁቆቹን ዐዋቂ ነው፡፡
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖﭗﭘﭙﭚﭛﭜﭝﭞﭟﭠﭡﭢﭣﭤﭥ
3:116 እነዚያ የካዱት ሰዎች ገንዘቦቻቸውና ልጆቻቸው ከአላህ (ቅጣት) እነርሱን ምንንም አያድኑዋቸውም፡፡ እነዚያም የእሳት ጓዶች ናቸው፡፡ እነርሱ በእርስዋ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡
ﭦﭧﭨﭩﭪﭫﭬﭭﭮﭯﭰﭱﭲﭳﭴﭵﭶﭷﭸﭹﭺﭻﭼﭽﭾ
3:117 የዚያ በዚህች በቅርቢቱ ሕይወት የሚለግሱት ነገር ምሳሌ በውስጧ ውርጭ ያለባት ነፋስ ነፍሶቻቸውን የበደሉን ሕዝቦች አዝመራ እንደነካችና እንዳጠፋችው ብጤ ነው፡፡ አላህም አልበደላቸውም ግን ነፍሶቻቸውን ይበድላሉ፡፡
ﭿﮀﮁﮂﮃﮄﮅﮆﮇﮈﮉﮊﮋﮌﮍﮎﮏﮐﮑﮒﮓﮔﮕﮖﮗﮘﮙﮚﮛﮜﮝﮞﮟ
3:118 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከእናንተ ሌላ ምስጢረኛን አትያዙ፡፡ ማበላሸትን አይገቱላችሁም፡፡ ጉዳታችሁን ይወዳሉ፡፡ ጥላቻይቱ ከአፎቻቸው በእርግጥ ተገለጸች፡፡ ልቦቻቸውም የሚደብቁት ይበልጥ ትልቅ ነው፡፡ ልብ የምታደርጉ እንደኾናችሁ ለእናንተ ማብራሪያዎችን በእርግጥ ገለጽን፡፡
ﮠﮡﮢﮣﮤﮥﮦﮧﮨﮩﮪﮫﮬﮭﮮﮯﮰﮱﯓﯔﯕﯖﯗﯘﯙﯚﯛﯜﯝﯞ
3:119 እነሆ እናንተ እነዚያ የምትወዱዋቸው ናችሁ፡፡ (እነሱ) ግን አይወዱዋችሁም፡፡ በመጽሐፉም በሁሉም ታምናላችሁ፡፡ ባገኙዋችሁም ጊዜ «አምነናል» ይላሉ፡፡ ባገለሉም ጊዜ ከቁጭታቸው የተነሳ በእናንተ ላይ ዐጽቆቻቸውን ይነክሳሉ፡፡ «በቁጭታችሁ ሙቱ፤ አላህ ልቦች የቋጠሩትን ዐዋቂ ነውና» በላቸው፡፡
ﯟﯠﯡﯢﯣﯤﯥﯦﯧﯨﯩﯪﯫﯬﯭﯮﯯﯰﯱﯲﯳﯴﯵﯶ
3:120 ደግ ነገር ብትነካችሁ ታስከፋቸዋለች፡፡ መጥፎም ነገር ብታገኛችሁ በእርሷ ይደሰታሉ፡፡ ብትታገሱና ብትጠነቀቁም ተንኮላቸው ምንም አይጎዳችሁም፡፡ አላህ በሚሠሩት ሁሉ (በዕውቀቱ) ከባቢ ነውና፡፡
ﯷﯸﯹﯺﯻﯼﯽﯾﯿﰀﰁﰂﰃ
3:121 ለምእምኖቹም ለውጊያ ሥራዎችን የምታዘጋጅ ኾነህ ከቤተሰብህ በማለድክ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖﭗﭘﭙﭚﭛﭜﭝﭞ
3:122 ከእናንተ ሁለት ጭፍሮች አላህ ረዳታቸው ሲኾን ለመፍራት ባሰቡ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ በአላህም ላይ ብቻ ምእምናኖች ይመኩ፡፡
ﭟﭠﭡﭢﭣﭤﭥﭦﭧﭨﭩﭪ
3:123 በበድርም እናንተ ጥቂቶች ኾናችሁ ሳለ አላህ በእርግጥ ረዳችሁ፡፡ አላህንም ታመሰግኑ ዘንድ ፍሩት፡፡
ﭫﭬﭭﭮﭯﭰﭱﭲﭳﭴﭵﭶﭷﭸ
3:124 ለምእምናን «ጌታችሁ በሦስት ሺህ መላእክት የተወረዱ ሲኾኑ ቢረዳችሁ አይበቃችሁምን» በምትል ጊዜ (አስታውስ)፡፡
ﭹﭺﭻﭼﭽﭾﭿﮀﮁﮂﮃﮄﮅﮆﮇﮈﮉ
3:125 «አዎን ብትታገሱና ብትጠነቀቁ ከዚህም ፍጥነታቸው (ጠላቶቻችሁ) ቢመጡባችሁ ጌታችሁ ምልክት ባላቸው አምስት ሺህ መላእክት ይረዳችኋል፡፡»
ﮊﮋﮌﮍﮎﮏﮐﮑﮒﮓﮔﮕﮖﮗﮘﮙﮚﮛﮜ
3:126 አላህም (እርዳታውን) ለእናንተ ብስራትና ልቦቻችሁ በእርሱ እንዲረኩ እንጂ አላደረገውም፡፡ ድልም መንሳት አሸናፊ ጥበበኛ ከኾነው አላህ ዘንድ እንጅ ከሌላ አይደለም፡፡
ﮝﮞﮟﮠﮡﮢﮣﮤﮥﮦ
3:127 (ድልን ያጎናጸፋችሁ) ከእነዚያ ከካዱት ከፊልን ሊቆርጥ (ሊያጠፋ) ወይም ሊያዋርዳቸውና ያፈሩ ኾነው እንዲመለሱ ነው፡፡
ﮧﮨﮩﮪﮫﮬﮭﮮﮯﮰﮱﯓﯔ
3:128 (አላህ) በእነርሱ ላይ ይቅርታ እስኪያደርግ ወይም እነርሱ በዳዮች ናቸውና እስኪቀጣቸው ድረስ ላንተ ከነገሩ ምንም የለህም፡፡
ﯕﯖﯗﯘﯙﯚﯛﯜﯝﯞﯟﯠﯡﯢﯣﯤﯥﯦﯧ
3:129 በሰማያት ያለው በምድርም ያለው ሁሉ የአላህ ነው፡፡ ለሚሻው ሰው ይምራል፤ የሚሻውንም ሰው ይቀጣል፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡
ﯨﯩﯪﯫﯬﯭﯮﯯﯰﯱﯲﯳﯴﯵ
3:130 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አራጣን የተነባበሩ እጥፎች ሲኾኑ አትብሉ፡፡ ትድኑም ዘንድ አላህን ፍሩ፡፡
ﯶﯷﯸﯹﯺﯻ
3:131 ያችንም ለከሓዲዎች የተደገሰችውን እሳት ተጠንቀቁ፡፡
ﯼﯽﯾﯿﰀﰁ
3:132 ይታዘንላችሁም ዘንድ አላህንና መልክተኛውን ታዘዙ፡፡
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖﭗﭘﭙﭚﭛﭜﭝ
3:133 ከጌታችሁ ወደ ኾነችም ምሕረትና ስፋትዋ እንደ ሰማያትና ምድር ወደ ኾነች ገነት አላህን ለሚፈሩ የተዘጋጀች ስትኾን ተቻኮሉ፡፡
ﭞﭟﭠﭡﭢﭣﭤﭥﭦﭧﭨﭩﭪﭫﭬ
3:134 ለእነዚያ በድሎትም ኾነ በችግር ለሚለግሱት፣ ቁጭትንም ገቺዎች ከሰዎችም ይቅርታ አድራጊዎች ለኾኑት (ተደግሳለች)፡፡ አላህም በጎ ሠሪዎችን ይወዳል፡፡
ﭭﭮﭯﭰﭱﭲﭳﭴﭵﭶﭷﭸﭹﭺﭻﭼﭽﭾﭿﮀﮁﮂﮃﮄ
3:135 ለእነዚያም መጥፎ ሥራን በሠሩ ወይም ነፍሶቻቸውን በበደሉ ጊዜ አላህን የሚያስታውሱና ለኀጢአቶቻቸው ምሕረትን የሚለምኑ ለኾኑት ከአላህም ሌላ ኀጢአቶችን የሚምር አንድም የለ፡፡ (በስሕተት) በሠሩትም ላይ እነርሱ የሚያውቁ ሲኾኑ የማይዘወትሩ ለኾኑት (ተደግሳለች)፡፡
ﮅﮆﮇﮈﮉﮊﮋﮌﮍﮎﮏﮐﮑﮒﮓﮔﮕ
3:136 እነዚያ ምንዳቸው ከጌታቸው ምሕረትና በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲኾኑ በሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶችም ናቸው፡፡ የሠሪዎችም ምንዳ (ገነት) ምንኛ አማረች!፡፡
ﮖﮗﮘﮙﮚﮛﮜﮝﮞﮟﮠﮡﮢﮣ
3:137 ከእናንተ በፊት ድርጊቶች በእርግጥ አልፈዋል፡፡ በምድርም ላይ ኺዱ፡፡ የአስተባባዮችም ፍጻሜ እንዴት እንደነበረ ተመልከቱ፡፡
ﮤﮥﮦﮧﮨﮩﮪ
3:138 ይህ ለሰዎች ገላጭ፤ ለጥንቁቆች መሪና ገሳጭ ነው፡፡
ﮫﮬﮭﮮﮯﮰﮱﯓﯔﯕ
3:139 እናንተም የበላዮች ስትኾኑ ምእመናን እንደኾናችሁ አትስነፉ፤ አትዘኑም፡፡
ﯖﯗﯘﯙﯚﯛﯜﯝﯞﯟﯠﯡﯢﯣﯤﯥﯦﯧﯨﯩﯪﯫﯬﯭﯮﯯﯰ
3:140 ቁስል ቢያገኛችሁ ሰዎቹንም መሰሉ ቁስል አግኝቷቸዋል፡፡ ይኽችንም ቀናት በሰዎች መካከል እናዘዋውራታለን፡፡ (እንድትገሰጹና) አላህም እነዚያን ያመኑትን እንዲያውቅ (እንዲለይ) ከእናንተም ሰማዕታትን እንዲይዝ ነው፡፡ አላህም በዳዮችን አይወድም፡፡
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖﭗ
3:141 አላህም እነዚያን ያመኑትን (ከኀጢአት) ሊያነጻና ከሓዲዎችንም ሊያጠፋ ነው፡፡
ﭘﭙﭚﭛﭜﭝﭞﭟﭠﭡﭢﭣﭤﭥ
3:142 በእውነቱ አላህ ከናንተ እነዚያን የታገሉትን ሳያውቅ (ሳይለይ) ታጋሾቹንም ሳያውቅ ገነትን ልትገቡ አሰባችሁን
ﭦﭧﭨﭩﭪﭫﭬﭭﭮﭯﭰﭱﭲ
3:143 (በጦርነት ላይ) መሞትንም ሳታገኙት በፊት በርግጥ የምትመኙት ነበራችሁ፡፡ እናንተም የምትመለከቱ ስትኾኑ በርግጥ አያችሁት (ታዲያ ለምን ሸሻችሁ)
ﭳﭴﭵﭶﭷﭸﭹﭺﭻﭼﭽﭾﭿﮀﮁﮂﮃﮄﮅﮆﮇﮈﮉﮊﮋﮌﮍﮎﮏﮐﮑ
3:144 ሙሐመድም ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ ታዲያ ቢሞት ወይም ቢገደል ወደ ኋላችሁ ትገለበጣላችሁን ወደኋላው የሚገለበጥም ሰው አላህን ምንም አይጎዳም፡፡ አላህም አመስጋኞቹን በእርግጥ ይመነዳል፡፡
ﮒﮓﮔﮕﮖﮗﮘﮙﮚﮛﮜﮝﮞﮟﮠﮡﮢﮣﮤﮥﮦﮧﮨﮩﮪﮫﮬ
3:145 ለማንኛይቱም ነፍስ በአላህ ፍርድ ቢኾን እንጅ ልትሞት አይገባትም፡፡ (ጊዜውም) ተወስኖ ተጽፏል፡፡ የቅርቢቱንም ምንዳ የሚፈልግ ሰው ከእርስዋ እንሰጠዋለን፡፡ የመጨረሻይቱንም ምንዳ የሚፈልግ ሰው ከእርስዋ እንሰጠዋለን፤ አመስጋኞችንም በእርግጥ እንመነዳለን፡፡
ﮭﮮﮯﮰﮱﯓﯔﯕﯖﯗﯘﯙﯚﯛﯜﯝﯞﯟﯠﯡﯢﯣﯤ
3:146 ከነቢይም ብዙ ሊቃውንት ከርሱ ጋር ኾነው የተዋጉ ብዙ ናቸው፡፡ በአላህም መንገድ ለሚደርስባቸው ነገር አልፈሩም፤ አልደከሙምም፡፡ (ለጠላት) አልተዋረዱምም፡፡ አላህም ትዕግስተኞችን ይወዳል፡፡
ﯥﯦﯧﯨﯩﯪﯫﯬﯭﯮﯯﯰﯱﯲﯳﯴﯵﯶﯷﯸ
3:147 ንግግራቸውም «ጌታችን ሆይ! ኃጢአቶቻችንንና በነገራችን ሁሉ ወሰን ማለፋችንን ለእኛ ማር፣ ይዞታችንንም አደላድል፣ በከሓዲዎችም ሕዝቦች ላይ እርዳን» ማለታቸው እንጅ ሌላ አልነበረም፡፡
ﯹﯺﯻﯼﯽﯾﯿﰀﰁﰂﰃﰄ
3:148 አላህም የቅርቢቱን ምንዳና የመጨረሻይቱን መልካም ምንዳ ሰጣቸው፡፡ አላህም በጎ አድራጊዎችን ይወዳል፡፡
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖﭗﭘﭙﭚﭛﭜﭝ
3:149 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እነዚያን የካዱትን ሰዎች ብትታዘዙ ወደ ኋላችሁ ይመልሱዋችኋል፡፡ ከሳሪዎች ኾናችሁም ትገለበጣላችሁ፡፡
ﭞﭟﭠﭡﭢﭣﭤﭥ
3:150 (አይረዷችሁም)፤ ይልቁን አላህ ብቻ ረዳታችሁ ነው፡፡ እርሱም ከረዳቶች ሁሉ በላጭ ነው፡፡
ﭦﭧﭨﭩﭪﭫﭬﭭﭮﭯﭰﭱﭲﭳﭴﭵﭶﭷﭸﭹﭺﭻ
3:151 በእነዚያ በካዱት ሰዎች ልቦች ውስጥ አላህ በእርሱ አስረጅ ያላወረደበትን ነገር በአላህ በማጋራታቸው ምክንያት ፍርሃትን እንጥላለን፡፡ መኖሪያቸውም እሳት ናት፡፡ የበዳዮችም መኖሪያ ምን ትከፋ!
ﭼﭽﭾﭿﮀﮁﮂﮃﮄﮅﮆﮇﮈﮉﮊﮋﮌﮍﮎﮏﮐﮑﮒﮓﮔﮕﮖﮗﮘﮙﮚﮛﮜﮝﮞﮟﮠﮡﮢﮣﮤﮥﮦﮧﮨﮩ
3:152 አላህም በፈቃዱ በምትጨፈጭፏቸው ጊዜ ኪዳኑን በእርግጥ አረጋገጠላችሁ፡፡ የምትወዱትንም ነገር ካሳያችሁ በኋላ በፈራችሁ በትዕዛዙም በተጨቃጨቃችሁና ባመጻችሁ ጊዜ (እርዳታውን ከለከላችሁ)፡፡ ከእናንተ ውስጥ ቅርቢቱን ዓለም የሚሻ አለ፡፡ ከእናንተም የመጨረሻይቱን ዓለም የሚሻ አልለ፡፡ ከዚያም ሊሞክራችሁ ከእነርሱ አዞራችሁ፡፡ በእርግጥም ከእናንተ ይቅርታ አደረገላችሁ፡፡ አላህም በምእምናን ላይ የችሮታ ባለቤት ነው፡፡
ﮪﮫﮬﮭﮮﮯﮰﮱﯓﯔﯕﯖﯗﯘﯙﯚﯛﯜﯝﯞﯟﯠﯡﯢﯣﯤﯥﯦ
3:153 መልክተኛው ከኋላችሁ የሚጠራችሁ ሲኾን ርቃችሁ በምትሸሹና በአንድም ላይ የማትዞሩ በኾናችሁ ጊዜ (አስታውሱ)፡፡ ባመለጣችሁና በደረሰባችሁም ነገር እንድታዝኑ በሐሳብ ላይ ሐሳብን መነዳችሁ፡፡ አላህም በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖﭗﭘﭙﭚﭛﭜﭝﭞﭟﭠﭡﭢﭣﭤﭥﭦﭧﭨﭩﭪﭫﭬﭭﭮﭯﭰﭱﭲﭳﭴﭵﭶﭷﭸﭹﭺﭻﭼﭽﭾﭿﮀﮁﮂﮃﮄﮅﮆﮇﮈﮉﮊﮋﮌﮍﮎﮏﮐﮑﮒﮓﮔﮕﮖﮗﮘﮙﮚﮛﮜﮝﮞﮟﮠﮡﮢﮣﮤ
3:154 ከዚያም ከጭንቅ በኋላ ጸጥታን ከእናንተ ከፊሎችን የሚሸፍንን እንቅልፍ በእናንተ ላይ አወረደ፡፡ ከፊሎቹም ነፍሶቻቸው በእርግጥ አሳሰቧቸው፡፡ እውነት ያልኾነውን የመሃይምነትን መጠራጠር በአላህ ይጠራጠራሉ፤ «ከነገሩ ለእኛ ምንም የለንም» ይላሉ፡፡ «ነገሩ ሁሉም ለአላህ ነው» በላቸው፡፡ ለአንተ የማይገልጹትን በነፍሶቻቸው ውስጥ ይደብቃሉ፡፡ «ከነገሩ ለእኛ አንዳች በነበረን ኖሮ እዚህ ባልተገደልን ነበር» ይላሉ፡፡ «በቤታችሁ ውስጥ በኾናችሁም ኖሮ እነዚያ በእነርሱ ላይ መገደል የተጻፈባቸው ወደ መውደቂያቸው በወጡ ነበር» በላቸው፡፡ አላህ (ፍርዱን ሊፈጽምና) በደረቶቻችሁም ውስጥ ያለውን ሊፈትን በልቦቻችሁም ውስጥ ያለውን ነገር ሊገልጽ (ይህን ሠራ)፡፡ አላህም በደረቶች ውስጥ ያለን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡
ﮥﮦﮧﮨﮩﮪﮫﮬﮭﮮﮯﮰﮱﯓﯔﯕﯖﯗﯘﯙﯚﯛﯜﯝ
3:155 እነዚያ ሁለቱ ጭፍሮች በተገናኙ ቀን ከእናንተ የሸሹት ሰዎች በዚያ በሠሩት ከፊል ምክንያት ያሳሳታቸው ሰይጣን ነው፡፡ አላህም ከነሱ በእርግጥ ይቅር አለ፡፡ አላህ መሓሪ በቅጣት የማይቸኩል ነውና፡፡
ﯞﯟﯠﯡﯢﯣﯤﯥﯦﯧﯨﯩﯪﯫﯬﯭﯮﯯﯰﯱﯲﯳﯴﯵﯶﯷﯸﯹﯺﯻﯼﯽﯾﯿﰀﰁﰂﰃﰄ
3:156 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እንደነዚያ እንደ ካዱትና ስለ ወንድሞቻቸው በምድር ላይ በተጓዙ ወይም ዘማቾች በኾኑ ጊዜ «እኛ ዘንድ በነበሩ ኖሮ ባልሞቱም ባልተገደሉም ነበር» እንደሚሉት አትኹኑ፡፡ አላህ ይህንን በልቦቻቸው ውስጥ ጸጸት ያደርግባቸው ዘንድ (ይህንን አሉ)፡፡ አላህም ሕያው ያደርጋል፤ ይገድላልም፡፡ አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው፡፡
ﰅﰆﰇﰈﰉﰊﰋﰌﰍﰎﰏﰐﰑﰒﰓ
3:157 በአላህም መንገድ ብትገደሉ ወይም፤ ብትሞቱ ከአላህ የኾነው ምሕረትና እዝነት (እነርሱ) ከሚሰበስቡት ሀብት በእርግጥ በላጭ ነው፡፡
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖﭗﭘ
3:158 ብትሞቱም ወይም ብትገደሉ በእርግጥ ወደ አላህ ብቻ ትሰበሰባላችሁ፡፡
ﭙﭚﭛﭜﭝﭞﭟﭠﭡﭢﭣﭤﭥﭦﭧﭨﭩﭪﭫﭬﭭﭮﭯﭰﭱﭲﭳﭴﭵﭶﭷﭸﭹﭺﭻ
3:159 ከአላህም በኾነች ችሮታ ለዘብክላቸው፡፡ ዐመለ መጥፎ ልበ ደረቅም በኾንክ ኖሮ ከዙሪያህ በተበተኑ ነበር፡፡ ከእነርሱም ይቅር በል፡፡ ለእነርሱም ምሕረትን ለምንላቸው፡፡ በነገሩም ሁሉ አማክራቸው፡፡ ቁርጥ ሐሳብም ባደረግህ ጊዜ በአላህ ላይ ተመካ፡፡ አላህ በርሱ ላይ ተመኪዎችን ይወዳልና፡፡
ﭼﭽﭾﭿﮀﮁﮂﮃﮄﮅﮆﮇﮈﮉﮊﮋﮌﮍﮎﮏﮐ
3:160 አላህ ቢረዳችሁ ለእናንተ አሸናፊ የለም፡፡ ቢያዋርዳችሁም ያ ከርሱ (ማዋረድ) በኋላ የሚረዳችሁ ማነው በአላህም ላይ ብቻ ምእምናን ይመኩ፡፡
ﮑﮒﮓﮔﮕﮖﮗﮘﮙﮚﮛﮜﮝﮞﮟﮠﮡﮢﮣﮤﮥﮦﮧﮨ
3:161 ለነቢይም ሰለባን መደበቅ አይገባውም፡፡ ሰለባንም የሚደብቅ ሰው በትንሣኤ ቀን በደበቀው ነገር (ተሸክሞ) ይመጣል፡፡ ከዚያም ነፍስ ሁሉ የሥራዋን ዋጋ ትሞላለች፡፡ እነርሱም አይበደሉም፡፡
ﮩﮪﮫﮬﮭﮮﮯﮰﮱﯓﯔﯕﯖﯗﯘ
3:162 የአላህን ውዴታ የተከተለ ሰው ከአላህ በኾነ ቁጣ እንደ ተመለሰና መኖሪያው ገሀነም እንደ ኾነ ሰው ነውን መመለሻውም ምን ይከፋ!
ﯙﯚﯛﯜﯝﯞﯟﯠﯡﯢ
3:163 እነርሱ አላህ ዘንድ ባለ ደረጃዎች ናቸው፡፡ አላህም የሚሠሩትን ነገር ተመልካች ነው፡፡
ﯣﯤﯥﯦﯧﯨﯩﯪﯫﯬﯭﯮﯯﯰﯱﯲﯳﯴﯵﯶﯷﯸﯹﯺﯻﯼ
3:164 አላህ በምእምናን ላይ ከጎሳቸው የኾነን፤ በእነርሱ ላይ አንቀጾቹን የሚያነብ፣ የሚጠራቸውም፣ መጽሐፍንና ጥበብን የሚያስተምራቸውም የኾነን መልእክተኛ በውስጣቸው በላከ ጊዜ፤ በእርግጥ ለገሰላቸው፡፡ እነርሱም ከዚያ በፊት በግልጽ ስህተት ውስጥ ነበሩ፡፡
ﯽﯾﯿﰀﰁﰂﰃﰄﰅﰆﰇﰈﰉﰊﰋﰌﰍﰎﰏﰐﰑﰒﰓ
3:165 ሁለት ብጤዎችዋን በእርግጥ ያገኛችሁ የኾነች መከራ (መጠቃት) ባገኘቻችሁ ጊዜ «ይህ ከየት ነው» አላችሁን «እርሱ ከነፍሶቻችሁ ዘንድ ነው፡፡» አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና በላቸው፡፡
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖﭗﭘﭙﭚ
3:166 ሁለቱ ጭፍሮችም በተጋጠሙ ቀን የደረሰባችሁ በአላህ ፈቃድ ነው፡፡ ምእምናንንም (ሊፈትንና) ሊገልጽ ነው፡፡
ﭛﭜﭝﭞﭟﭠﭡﭢﭣﭤﭥﭦﭧﭨﭩﭪﭫﭬﭭﭮﭯﭰﭱﭲﭳﭴﭵﭶﭷﭸﭹﭺﭻﭼﭽﭾﭿﮀﮁ
3:167 እነዚያንም የነፈቁትንና ለነርሱ «ኑ፤ በአላህ መንገድ ተጋደሉ፤ ወይም ተከላከሉ፤» የተባሉትን ሊገልጽ ነው፡፡ «መዋጋት (መኖሩን) ብናውቅ ኖሮ በተከተልናችሁ ነበር» አሉ፡፡ እነርሱ ያን ጊዜ ከእምነት ይልቅ ወደ ክህደት የቀረቡ ናቸው፡፡ በልቦቻቸው የሌለውን በአፎቻቸው ይናገራሉ፡፡ አላህም የሚደብቁትን ዐዋቂ ነው፡፡
ﮂﮃﮄﮅﮆﮇﮈﮉﮊﮋﮌﮍﮎﮏﮐﮑﮒﮓ
3:168 እነዚያ (ከትግል) የቀሩ ሲኾኑ ለወንድሞቻቸው፡- «በታዘዙን ኖሮ ባልተገደሉ ነበር» ያሉ ናቸው፡፡ «እውነተኞች እንደኾናችሁ ከነፍሶቻችሁ ላይ ሞትን ገፍትሩ» በላቸው፡፡
ﮔﮕﮖﮗﮘﮙﮚﮛﮜﮝﮞﮟﮠﮡﮢ
3:169 እነዚያን በአላህ መንገድ የተገደሉትን ሙታን አድርገህ አትገምታቸው፡፡ በእርግጥ እነርሱ እጌታቸው ዘንድ ሕያዋን ናቸው፤ ይመገባሉ፡፡
ﮣﮤﮥﮦﮧﮨﮩﮪﮫﮬﮭﮮﮯﮰﮱﯓﯔﯕﯖﯗ
3:170 አላህ ከችሮታው በሰጣቸው ነገር ተደሳቾች ሲኾኑ (ይመገባሉ)፡፡ በነዚያም ከኋላቸው ገና በእነርሱ ባልተከተሉት በእነርሱ ላይ ፍርሃት ባለመኖሩና እነርሱም የማያዝኑ በመኾናቸው ይደሰታሉ፡፡
ﯘﯙﯚﯛﯜﯝﯞﯟﯠﯡﯢﯣﯤ
3:171 ከአላህ በኾነ ጸጋና ልግስና አላህም የምእምናንን ምንዳ የማያጠፉ በመኾኑ ይደሰታሉ፡፡
ﯥﯦﯧﯨﯩﯪﯫﯬﯭﯮﯯﯰﯱﯲﯳﯴﯵ
3:172 እነዚያ መቁሰል ካገኛቸው በኋላ ለአላህና ለመልክተኛው የታዘዙት ከእነሱ ለነዚያ በጎ ለሠሩትና ለተጠነቀቁት ታላቅ ምንዳ አላቸው፡፡
ﯶﯷﯸﯹﯺﯻﯼﯽﯾﯿﰀﰁﰂﰃﰄﰅﰆﰇ
3:173 እነዚያ ሰዎቹ ለእነርሱ፡- «ሰዎች ለእናንተ (ጦርን) አከማችተዋልና ፍሩዋቸው» ይሉዋቸውና (ይህም) እምነትን የጨመረላቸው «በቂያችንም አላህ ነው ምን ያምርም መጠጊያ!» ያሉ ናቸው፡፡
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖﭗﭘﭙﭚﭛﭜﭝﭞﭟﭠﭡ
3:174 ከአላህም በኾነ ጸጋና ችሮታ ክፉ ነገር ያልነካቸው ኾነው ተመለሱ፡፡ የአላህንም ውዴታ ተከተሉ፤ አላህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው፡፡
ﭢﭣﭤﭥﭦﭧﭨﭩﭪﭫﭬﭭ
3:175 እንዲህ የሚላችሁ ሰይጣን ብቻ ነው፡፡ ወዳጆቹን ያስፈራራችኋል፡፡ አትፍሩዋቸውም፡፡ ምእምናንም እንደኾናችሁ ፍሩኝ፡፡
ﭮﭯﭰﭱﭲﭳﭴﭵﭶﭷﭸﭹﭺﭻﭼﭽﭾﭿﮀﮁﮂﮃﮄﮅﮆﮇ
3:176 እነዚያም በክህደት የሚቻኮሉት አያሳዝኑህ፡፡ ከነርሱ ፈጽሞ አላህን በምንም አይጎዱምና፡፡ አላህ በመጨረሻይቱ ዓለም ለእነሱ ዕድልን ላያደርግ ይሻል፡፡ ለእነርሱም ታላቅ ቅጣት አላቸው፡፡
ﮈﮉﮊﮋﮌﮍﮎﮏﮐﮑﮒﮓﮔﮕ
3:177 እነዚያ ክህደትን በእምነት የለወጡ አላህን በምንም ነገር ፈጽሞ አይጎዱትም፡፡ ለእነሱም አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡
ﮖﮗﮘﮙﮚﮛﮜﮝﮞﮟﮠﮡﮢﮣﮤﮥﮦﮧﮨﮩ
3:178 እነዚያ የካዱት ሰዎች እነርሱን ማዘግየታችንን ለነፍሶቻቸው ደግ ነገር ነው ብለው አያስቡ፡፡ እነርሱን የምናዘገያቸው ኃጢኣትን እንዲጨምሩ ብቻ ነው፡፡ ለነሱም አዋራጅ ስቃይ አላቸው፡፡
ﮪﮫﮬﮭﮮﮯﮰﮱﯓﯔﯕﯖﯗﯘﯙﯚﯛﯜﯝﯞﯟﯠﯡﯢﯣﯤﯥﯦﯧﯨﯩﯪﯫﯬﯭﯮﯯﯰﯱﯲ
3:179 አላህ መጥፎውን ከመልካሙ እስከሚለይ ድረስ ምእምናንን እናንተ በርሱ ላይ ባላችሁበት (ኹኔታ) ላይ የሚተው አይደለም፡፡ አላህም ሩቁን ነገር የሚያሳውቃችሁ አይደለም፡፡ ግን አላህ ከመልክተኞቹ የሚሻውን ይመርጣል፡፡ በአላህና በመልክተኞቹም እመኑ፡፡ ብታምኑና ብትጠነቀቁም ለናንተ ታላቅ ምንዳ አላችሁ፡፡
ﯳﯴﯵﯶﯷﯸﯹﯺﯻﯼﯽﯾﯿﰀﰁﰂﰃﰄﰅﰆﰇﰈﰉﰊﰋﰌﰍﰎﰏﰐﰑﰒﰓﰔﰕ
3:180 እነዚያም አላህ ከችሮታው በሰጣቸው ገንዘብ የሚነፍጉ እርሱ ለእነሱ ደግ አይምሰላቸው፡፡ ይልቁንም፤ እርሱ ለነሱ መጥፎ ነው፡፡ ያንን በርሱ የነፈጉበትን በትንሣኤ ቀን (እባብ ኾኖ) ይጠለቃሉ፡፡ የሰማያትና የምድርም ውርስ ለአላህ ብቻ ነው፡፡ አላህም በሚሠሩት ሁሉ ውስጥ ዐዋቂ ነው፡፡
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖﭗﭘﭙﭚﭛﭜﭝﭞﭟﭠﭡﭢﭣﭤﭥﭦﭧﭨ
3:181 የእነዚያን «አላህ ድኻ ነው እኛ ግን ከበርቴዎች ነን» ያሉትን ሰዎች ቃል አላህ በእርግጥ ሰማ፡፡ ያንን ያሉትንና ነቢያትን ያለ ሕግ መግደላቸውን በእርግጥ እንጽፋለን፡፡ «የእሳትንም ስቃይ ቅመሱ» እንላቸዋለን፡፡
ﭩﭪﭫﭬﭭﭮﭯﭰﭱﭲ
3:182 ያ (ስቃይ) እጆቻችሁ ባሳለፉት ሥራ ነው፡፡ አላህም ለባሮቹ በዳይ ባለመኾኑ ነው፡፡
ﭳﭴﭵﭶﭷﭸﭹﭺﭻﭼﭽﭾﭿﮀﮁﮂﮃﮄﮅﮆﮇﮈﮉﮊﮋﮌﮍﮎﮏﮐ
3:183 እነዚያ ለማንኛውም መልክተኛ «እሳት የምትበላው የኾነን ቁርባን እስከሚያመጣልን ድረስ ላናምን አላህ ወደኛ አዟል» ያሉ ናቸው፡፡«መልክተኞች ከእኔ በፊት በተዓምራትና በዚያም ባላችሁት (ቁርባን) በእርግጥ መጥተውላችኋል፡፡ እውነተኞች ከኾናችሁ ታዲያ ለምን ገደላችኋቸው» በላቸው፡፡
ﮑﮒﮓﮔﮕﮖﮗﮘﮙﮚﮛﮜﮝ
3:184 ቢያስተባብሉህም ከአንተ በፊት በግልጽ ተዓምራትና በጽሑፎች፣ በብሩህ መጽሐፍም የመጡት መልክተኞች በእርግጥ ተስተባብለዋል፡፡
ﮞﮟﮠﮡﮢﮣﮤﮥﮦﮧﮨﮩﮪﮫﮬﮭﮮﮯﮰﮱﯓﯔﯕﯖﯗﯘﯙ
3:185 ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት፡፡ ምንዳዎቻችሁንም የምትሞሉት በትንሣኤ ቀን ብቻ ነው፡፡ ከእሳትም የተራቀና ገነትን የተገባ ሰው በእርግጥ ምኞቱን አገኘ፡፡ ቅርቢቱም ሕይወት የመታለያ መሳሪያ እንጅ ሌላ አይደለችም፡፡
ﯚﯛﯜﯝﯞﯟﯠﯡﯢﯣﯤﯥﯦﯧﯨﯩﯪﯫﯬﯭﯮﯯﯰﯱﯲﯳﯴ
3:186 በገንዘቦቻችሁና በነፍሶቻችሁ በእርግጥ ትፈተናላችሁ፡፡ ከእነዚያም ከእናንተ በፊት መጽሐፍን ከተሰጡትና ከእነዚያም ከአጋሩት ብዙን ማሰቃየት ትሰማላችሁ፡፡ ብትታገሱና ብትጠነቀቁ ይህ ከጥብቅ ነገሮች ነው፡፡
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖﭗﭘﭙﭚﭛﭜﭝﭞﭟﭠﭡﭢﭣﭤﭥﭦﭧ
3:187 አላህ የነዚያን መጽሐፉን የተሰጡትን ቃል ኪዳን ለሰዎች በእርግጥ ታብራሩታላችሁ አትደብቁትምም በማለት የያዘባቸውን (አስታውሱ)፡፡ በጀርባዎቻቸውም ኋላ ጣሉት፡፡ በርሱም ጥቂትን ዋጋ ገዙ፡፡ የሚገዙትም ነገር ከፋ!
ﭨﭩﭪﭫﭬﭭﭮﭯﭰﭱﭲﭳﭴﭵﭶﭷﭸﭹﭺﭻﭼﭽ
3:188 እነዚያን በሠሩት ነገር የሚደሰቱትንና ባልሠሩትም መመስገንን የሚወዱትን አታስብ፤ ከቅጣት በመዳን ላይ ናቸው ብለህ አታሰባቸው፡፡ ለእነሱ አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡
ﭾﭿﮀﮁﮂﮃﮄﮅﮆﮇﮈ
3:189 የሰማያትና የምድር ንግሥና ለአላህ ብቻ ነው፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡
ﮉﮊﮋﮌﮍﮎﮏﮐﮑﮒﮓﮔ
3:190 ሰማያትንና ምድርን በመፍጠር ሌሊትና ቀንንም በመተካካት ለባለ አእምሮዎች በእርግጥ ምልክቶች አሉ፡፡
ﮕﮖﮗﮘﮙﮚﮛﮜﮝﮞﮟﮠﮡﮢﮣﮤﮥﮦﮧﮨﮩﮪ
3:191 (እነርሱም) እነዚያ ቆመው፣ ተቀምጠውም፣ በጎኖቻቸው ተጋድመውም አላህን የሚያወሱ በሰማያትና በምድር አፈጣጠርም የሚያስተነትኑ፡- «ጌታችን ሆይ! ይኸን በከንቱ አልፈጠርከውም፤ ጥራት ይገባህ፤ ከእሳትም ቅጣት ጠብቀን» የሚሉ ናቸው፡፡
ﮫﮬﮭﮮﮯﮰﮱﯓﯔﯕﯖﯗﯘ
3:192 «ጌታችን ሆይ! አንተ እሳት የምታገባውን ሰው በእርግጥ አዋረድከው፤ ለበደለኞችም ምንም ረዳቶች የሉዋቸውም፡፡»
ﯙﯚﯛﯜﯝﯞﯟﯠﯡﯢﯣﯤﯥﯦﯧﯨﯩﯪﯫﯬﯭﯮ
3:193 «ጌታችን ሆይ! እኛ በጌታችሁ እመኑ በማለት ወደ እምነት የሚጠራን ጠሪ ሰማን፡፡ አመንም፡፡ ጌታችን ሆይ! ኃጢአቶቻችንንም ለኛ ማር፡፡ ክፉ ሥራዎቻችንንም ከኛ አብስ፡፡ ከንጹሖቹም ሰዎች ጋር ግደለን፤»
ﯯﯰﯱﯲﯳﯴﯵﯶﯷﯸﯹﯺﯻﯼﯽﯾ
3:194 «ጌታችን ሆይ! በመልክተኞችህም ላይ ተስፋ ቃል ያደረግክልንን ስጠን፡፡ በትንሣኤ ቀንም አታዋርደን፡፡ አንተ ቀጠሮን አታፈርስምና» (የሚሉ ናቸው)፡፡
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖﭗﭘﭙﭚﭛﭜﭝﭞﭟﭠﭡﭢﭣﭤﭥﭦﭧﭨﭩﭪﭫﭬﭭﭮﭯﭰﭱﭲﭳﭴﭵﭶﭷﭸﭹﭺﭻﭼﭽﭾﭿ
3:195 ጌታቸውም «እኔ ከእናንተ ከወንድ ወይም ከሴት የሠሪን ሥራ አላጠፋም፡፡ ከፊላችሁ ከከፊሉ ነው፤ በማለት ለነርሱ ልመናቸውን ተቀበለ፡፡ እነዚያም የተሰደዱ ከአገሮቻቸውም የተባረሩ በመንገዴም የተጠቁ የተጋደሉም የተገደሉም ክፉ ሥራዎቻቸውን ከእነርሱ በእርግጥ አብሳለሁ፡፡ በሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በእርግጥ አገባቸዋለሁ፡፡ ከአላህ ዘንድ የኾነን ምንዳ (ይመነዳሉ)፡፡ አላህም እርሱ ዘንድ መልካም ምንዳ አልለ፡፡ »
ﮀﮁﮂﮃﮄﮅﮆﮇ
3:196 የእነዚያ የካዱት ሰዎች በአገሮች መንፈላሰስ አያታልህ፡፡
ﮈﮉﮊﮋﮌﮍﮎﮏﮐ
3:197 አነስተኛ ጥቅም ነው፡፡ ከዚያም መኖሪያቸው ገሀነም ናት፡፡ ምን ትከፋም ምንጣፍ!
ﮑﮒﮓﮔﮕﮖﮗﮘﮙﮚﮛﮜﮝﮞﮟﮠﮡﮢﮣﮤﮥﮦﮧ
3:198 ግን እነዚያ ጌታቸውን የፈሩ ለእነሱ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች በውስጧ ዘውታሪዎች ሲኾኑ ከአላህ ዘንድ (የተሰጡ) መስተንግዶዎች አሏቸው፡፡ አላህም ዘንድ ያለው (ምንዳ) ለበጎ ሠሪዎች በላጭ ነው፡፡
ﮨﮩﮪﮫﮬﮭﮮﮯﮰﮱﯓﯔﯕﯖﯗﯘﯙﯚﯛﯜﯝﯞﯟﯠﯡﯢﯣﯤﯥﯦﯧﯨﯩ
3:199 ከመጽሐፉም ባለቤቶች ለአላህ ፈሪዎች በአላህ አንቀጾችም ጥቂትን ዋጋ የማይለወጡ ሲኾኑ በአላህና በዚያ ወደ እናንተ በተወረደው በዚያም ወደእነርሱ በተወረደው የሚያምኑ ሰዎች አልሉ፡፡ እነዚያ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አላቸው፡፡ አላህ ምርመራው ፈጣን ነው፡፡
ﯪﯫﯬﯭﯮﯯﯰﯱﯲﯳﯴ
3:200 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ታገሱ ተበራቱም፡፡ (በጦር ኬላ ላይ) ተሰለፉም፡፡ ትድኑም ዘንድ አላህን ፍሩ፡፡

ቅዱስ ቁርኣን


Wednesday, September 9, 2026

Don't forget us in your sincere prayers