PDF —
99 አንቀጽ Meccan PDF
Built right in your browser — download starts automatically

ሱረቱ አል-ሂጅር pdf — አውርድ (አማርኛ)

ሱረቱ አል-ሂጅር pdf አማርኛ — አውርድ ሱረቱ አል-ሂጅር ትርጉም. ሱረቱ አል-ሂጅር (Meccan) 99 አንቀጽ.

← ኢብራሂምሱረቱ አል-ሂጅር አን-ናህል →


99 አንቀጽ · Meccan · አማርኛ
bismillah
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖﭗﭘ
15:1 አ.ለ.ረ (አሊፍ ላም ራ) ይህች (አናቅጽ) ከመጽሐፉ አንቀጾችና ገላጭ ከኾነው ቁርኣን ናት፡፡
ﭙﭚﭛﭜﭝﭞﭟﭠ
15:2 እነዚያ የካዱት (በትንሣኤ ቀን) ሙስሊሞች በኾኑ ኖሩ በብዛት ይመኛሉ፡፡
ﭡﭢﭣﭤﭥﭦﭧﭨﭩ
15:3 ተዋቸው ይብሉ፤ ይጠቀሙም፡፡ ተስፋም ያዘናጋቸው፡፡ በእርግጥም (መጥፎ ፍጻሜያቸውን) ያውቃሉ፡፡
ﭪﭫﭬﭭﭮﭯﭰﭱﭲ
15:4 ማንኛይቱንም ከተማ ለእርሷ የተወሰነ መጽሐፍ (ጊዜያት) ያላት ኾና እንጂ አላጠፋንም፡፡
ﭳﭴﭵﭶﭷﭸﭹﭺ
15:5 ማንኛይቱም ሕዝብ ጊዜዋን ምንም አትቀድምም፡፡ (ከእርሱ) አይቆዩምም፡፡
ﭻﭼﭽﭾﭿﮀﮁﮂﮃ
15:6 «አንተ ያ በእርሱ ላይ ቁርኣን የተወረደለት ሆይ! አንተ በእርግጥ ዕብድ ነህ» አሉም፡፡
ﮄﮅﮆﮇﮈﮉﮊﮋﮌ
15:7 «ከእውነተኞቹ እንደ ኾንክ በመላእክት (መስካሪ) ለምን አትመጣንም» (አሉ)፡፡
ﮍﮎﮏﮐﮑﮒﮓﮔﮕﮖ
15:8 መላእክትን በእውነት (በቅጣት) እንጂ አናወርድም፡፡ ያን ጊዜም የሚቆዩ አይደሉም፡፡
ﮗﮘﮙﮚﮛﮜﮝﮞ
15:9 እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን፡፡
ﮟﮠﮡﮢﮣﮤﮥﮦ
15:10 ከአንተም በፊት በነበሩት በመጀመሪያዎቹ ሕዝቦች ውስጥ (መልክተኞችን) በእርግጥ ልከናል፡፡
ﮧﮨﮩﮪﮫﮬﮭﮮﮯ
15:11 ማንኛውም መልእክተኛ በእርሱ የሚያላግጡበት ኾነው እንጅ አይመጣቸውም ነበር፡፡
ﮰﮱﯓﯔﯕﯖ
15:12 እንደዚሁ (ማስተባበልን) በአመጸኞቹ ልቦች ውስጥ እናገባዋለን፡፡
ﯗﯘﯙﯚﯛﯜﯝﯞ
15:13 በእርሱ አያምኑበትም፡፡ የቀድሞዎቹም ድርጊት በእርግጥ አልፋለች፤ (እንደጠፉ ይጠፋሉ)፡፡
ﯟﯠﯡﯢﯣﯤﯥﯦﯧﯨ
15:14 በእነርሱም ላይ ከሰማይ ደጃፍን በከፈትንላቸውና በእርሱ ሲወጡ በዋሉ ኖሮ፤
ﯩﯪﯫﯬﯭﯮﯯﯰﯱ
15:15 «የተዘጉት ዓይኖቻችን ናቸው፡፡ እንዲያውም እኛ የተደገመብን ሰዎች ነን» ባሉ ነበር፡፡
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖﭗﭘ
15:16 በሰማይም ላይ ቡርጆችን በእርግጥ አድርገናል፡፡ ለተመልካቾችም (በከዋክብት) አጊጠናታል፡፡
ﭙﭚﭛﭜﭝﭞ
15:17 ከተባረረ ሰይጣንም ሁሉ ጠብቀናታል፡፡
ﭟﭠﭡﭢﭣﭤﭥﭦ
15:18 ግን (ወሬ) መስማትን የሚሰርቅ ወዲየውኑ አብሪ ችቦ ይከተለዋል፡፡ (ያቃጥለዋል)፡፡
ﭧﭨﭩﭪﭫﭬﭭﭮﭯﭰﭱﭲ
15:19 ምድርንም ዘረጋናት፡፡ በውስጧም ኮረብታዎችን ጣልናባት፡፡ በውስጧም (የተለካን) በቃይ ሁሉ አበቀልንባት፡፡
ﭳﭴﭵﭶﭷﭸﭹﭺﭻ
15:20 በእርሷም ውስጥ ለእናንተ መኖሪያዎችንና ለእርሱ መጋቢዎቹ ያልኾናችሁትንም (እንስሳትን) አደረግንላችሁ፡፡
ﭼﭽﭾﭿﮀﮁﮂﮃﮄﮅﮆﮇ
15:21 መካዚኖቹም (መክፈቻቸው) እኛ ዘንድ ያልሆነ ምንም ነገር የለም፡፡ በተወሰነም ልክ እንጂ አናወርደውም፡፡
ﮈﮉﮊﮋﮌﮍﮎﮏﮐﮑﮒﮓﮔ
15:22 ነፋሶችንም (ደመናን) ተሸካሚዎች አድርገን ላክን፡፡ ከሰማይም (ከደመና) ዝናብን አወረድን፡፡ እርሱንም አጠጣናችሁ፡፡ እናንተም ለእርሱ አድላቢዎች አይደላችሁም፡፡
ﮕﮖﮗﮘﮙﮚﮛ
15:23 እኛም ሕያው የምናደርግና የምንገድል እኛው ብቻ ነን፡፡ እኛም (ፍጡርን ሁሉ ) የምንወርስ (ቀሪ) ነን፡፡
ﮜﮝﮞﮟﮠﮡﮢﮣ
15:24 ከእናንተም ተቀዳሚዎቹን በእርግጥ ዐውቀናል፡፡ ወደ ኋላም ቀሪዎቹን በእርግጥ ዐውቀናል፡፡
ﮤﮥﮦﮧﮨﮩﮪﮫﮬ
15:25 ጌታህም እርሱ ይሰበስባችኋል፡፡ እርሱ ጥበበኛ ዐዋቂ ነውና፡፡
ﮭﮮﮯﮰﮱﯓﯔﯕﯖ
15:26 ሰውንም ከሚቅጨለጨል ሸክላ ከሚገማ ጥቁር ጭቃ በእርግጥ ፈጠርነው፡፡
ﯗﯘﯙﯚﯛﯜﯝﯞ
15:27 ጃንንም (ከሰው) በፊት ከእሳት ነበልባል ፈጠርነው፡፡
ﯟﯠﯡﯢﯣﯤﯥﯦﯧﯨﯩﯪﯫ
15:28 ጌታህም ለመላእክት ባለጊዜ (አስታውስ)፡፡ እኔ ሰውን ከሚቅጨለጨል ሸክላ ከሚገማ ጭቃ እፈጥራለሁ፡፡
ﯬﯭﯮﯯﯰﯱﯲﯳﯴﯵ
15:29 (ፍጥረቱን) ባስተካከልኩትና በውስጡ ከመንፈሴ በነፋሁበትም ጊዜ ለእርሱ ሰጋጆች ኾናችሁ ውደቁ፡፡
ﯶﯷﯸﯹﯺ
15:30 መላእክትም መላውም ተሰብስበው ሰገዱ፡፡
ﯻﯼﯽﯾﯿﰀﰁﰂ
15:31 ኢብሊስ (ዲያብሎስ) ብቻ ሲቀር፡፡ ከሰጋጆቹ ጋር ከመኾን እንቢ አለ፡፡
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖﭗﭘﭙ
15:32 (አላህም) «ኢብሊስ ሆይ! ከሰጋጆቹ ጋር የማትኾን ላንተ ምን ምክንያት አለህ» አለው፡፡
ﭚﭛﭜﭝﭞﭟﭠﭡﭢﭣﭤﭥ
15:33 «ከሚቅጨለጨል ሸክላ ከግም ጭቃ ለፈጠርከው ሰው ልሰግድ አይገባኝም» አለ፡፡
ﭦﭧﭨﭩﭪﭫ
15:34 (አላህ) አለው «ከርሷም ውጣ፡፡ አንተ የተባረርክ እርጉም ነህና፡፡»
ﭬﭭﭮﭯﭰﭱﭲ
15:35 «ባንተ ላይም እስከ ፍርዱ ቀን ድረስ እርግማን አለብህ፡፡»
ﭳﭴﭵﭶﭷﭸﭹ
15:36 «ጌታዬ ሆይ! እንግዲውያስ (ሰዎች) እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ አቆየኝ» አለ፡፡
ﭺﭻﭼﭽﭾ
15:37 (አላህም) አለ «አንተ ከሚቆዩት ነህ፡፡
ﭿﮀﮁﮂﮃ
15:38 «እስከታወቀው ወቅት ቀን ድረስ፡፡»
ﮄﮅﮆﮇﮈﮉﮊﮋﮌﮍﮎ
15:39 (ኢብሊስ) አለ «ጌታዬ ሆይ! እኔን በማጥመምህ ይኹንብኝ ለነርሱ በምድር ላይ (ኀጢአትን) እሸልምላቸዋለሁ፡፡ ሁሉንም አጠማቸዋለሁም፡፡»
ﮏﮐﮑﮒﮓ
15:40 «ከነርሱ ፍጹሞቹ ባሮችህ ብቻ ሲቀሩ፡፡»
ﮔﮕﮖﮗﮘﮙ
15:41 (አላህም) አለ «ይህ በእኔ ላይ (መጠበቁ የተገባ) ቀጥተኛ መንገድ ነው፡፡»
ﮚﮛﮜﮝﮞﮟﮠﮡﮢﮣﮤﮥ
15:42 «እነሆ ባሮቼ በእነሱ ላይ ላንተ ስልጣን የለህም፡፡ ከጠማሞቹ የተከተለህ ሰው ብቻ ሲቀር፡፡»
ﮦﮧﮨﮩﮪ
15:43 «ገሀነምም (ለርሱና ለተከተሉት) ለመላውም በእርግጥ ቀጠሯቸው ናት፡፡
ﮫﮬﮭﮮﮯﮰﮱﯓﯔ
15:44 «ለእርሷ ሰባት ደጃፎች አሏት፡፡ ለየደጀፉም ሁሉ ከእነሱ የተከፈለ ፋንታ አለ፡፡
ﯕﯖﯗﯘﯙﯚ
15:45 «እነዚያ (ከኀጢአት) የተጠነቀቁት በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ ናቸው፡፡
ﯛﯜﯝﯞ
15:46 «ጸጥተኞች ኾናችሁ በሰላም ግቧት (ይባላሉ)፡፡
ﯟﯠﯡﯢﯣﯤﯥﯦﯧﯨﯩ
15:47 «ባልጋዎችም ላይ ፊት ለፊት የሚቅጣጩ ወንድማማቾች ኾነው በደረቶቻቸው ውስጥ ከቂም ያለውን ሁሉ እናስወግዳለን፡፡
ﯪﯫﯬﯭﯮﯯﯰﯱﯲ
15:48 «በእርሷም ውስጥ ድካም አይነካቸውም፡፡ እነሱም ከእርሷ የሚወጡ አይደሉም፡፡»
ﯳﯴﯵﯶﯷﯸﯹﯺ
15:49 ባሮቼን እኔ መሓሪው አዛኙ እኔው ብቻ መኾኔን ንገራቸው፡፡
ﯻﯼﯽﯾﯿﰀ
15:50 ቅጣቴም እርሱ አሳማሚ ቅጣት መኾኑን (ንገራቸው)፡፡
ﰁﰂﰃﰄﰅ
15:51 ከኢብራሂም እንግዶችም (ወሬ) ንገራቸው፡፡
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖﭗﭘﭙﭚ
15:52 በእርሱ ላይ በገቡና ሰላም ባሉት ጊዜ የኾነውን (አስታውስ)፡፡ (እርሱም) «እኛ ከእናንተ ፈሪዎች ነን» አላቸው፡፡
ﭛﭜﭝﭞﭟﭠﭡﭢ
15:53 «አትፍራ፤ እኛ ዐዋቂ በኾነ ወንድ ልጅ እናበስርሃለን» አሉት፡፡
ﭣﭤﭥﭦﭧﭨﭩﭪﭫ
15:54 «እርጅና የደረሰብኝ ከመኾኔ ጋር አበሰራችሁኝን በምን ታበስሩኛላችሁ» አለ፡፡
ﭬﭭﭮﭯﭰﭱﭲﭳ
15:55 «በእውነት አበሰርንህ፡፡ ከተሰፋ ቆራጮችም አትኹን» አሉ፡፡
ﭴﭵﭶﭷﭸﭹﭺﭻﭼ
15:56 «ከጠማማዎችም በስተቀር ከጌታው እዝነት ተስፋን የሚቆርጥ ማነው» አለ፡፡
ﭽﭾﭿﮀﮁﮂ
15:57 «እናንተ መልክተኞች ሆይ! ኧረ ለመኾኑ ነገራችሁ ምንድን ነው» አለ፡፡
ﮃﮄﮅﮆﮇﮈﮉ
15:58 «እኛ አመጸኞች ወደ ኾኑ ሕዝቦች ተልከናል» አሉት፡፡
ﮊﮋﮌﮍﮎﮏﮐ
15:59 «የሉጥ ቤተሰቦች ብቻ ሲቀሩ፡፡ (እነርሱን) እኛ ሁላቸውንም በእርግጥ የምናድናቸው ነን፡፡
ﮑﮒﮓﮔﮕﮖﮗ
15:60 «ሚስቱ ብቻ ስትቀር፡፡ እርሷን (በቅጣቱ ውስጥ) ከሚቀሩት መኾኗን ወሰነናል» (አሉ)፡፡
ﮘﮙﮚﮛﮜﮝ
15:61 መልክተኞቹም የሉጥን ቤተሰቦች በመጡባቸው ጊዜ፤
ﮞﮟﮠﮡﮢ
15:62 (ሉጥ) «እናንተ የተሳታችሁ ሕዝቦች ናችሁ» አላቸው፡፡
ﮣﮤﮥﮦﮧﮨﮩﮪ
15:63 «አይደለም እኛ ሕዝቦችህ በርሱ ይጠራጠሩበት በነበሩት ቅጣት መጣንህ» አሉት፡፡
ﮫﮬﮭﮮﮯ
15:64 «እውነትንም ይዘን መጣንህ፡፡ እኛም በእርግጥ እውነተኞች ነን፡፡
ﮰﮱﯓﯔﯕﯖﯗﯘﯙﯚﯛﯜﯝﯞﯟ
15:65 ከቤተሰብህም ጋር በሌሊቱ ከፊል ኺድ፡፡ ከኋላቸውም ተከተል፡፡ ከእናንተም አንድም ሰው ወደ ኋላው አይገላመጥ፡፡ ወደ ታዘዛችሁበትም ስፍራ እለፉ» (አሉት)፡፡
ﯠﯡﯢﯣﯤﯥﯦﯧﯨﯩ
15:66 ወደርሱም ያንን ትእዛዝ አወረድን፡፡ (እርሱም) የእነዚህ (ሕዝቦች) መጨረሻ ያነጉ ሲኾኑ (ሥራቸው) መቆረጥ ነው፡፡
ﯪﯫﯬﯭﯮ
15:67 የከተማይቱም ሰዎች የሚበሳሰሩ ኾነው መጡ፡፡
ﯯﯰﯱﯲﯳﯴﯵ
15:68 (ሉጥም) አለ «እነዚህ እንግዶቼ ናቸውና አታጋልጡኝ፡፡
ﯶﯷﯸﯹﯺ
15:69 «አላህንም ፍሩ፤ አታሳፍሩኝም፡፡»
ﯻﯼﯽﯾﯿﰀ
15:70 «ከዓለማት (ማንንም እንዳታስተናግድ) አልከለከልንህምን» አሉት፡፡
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖﭗ
15:71 (ሉጥም) «እነኝህ ሴቶች ልጆቼ ናቸው፡፡ ሠሪዎች ብትኾኑ (አግቧቸው)» አለ፡፡
ﭘﭙﭚﭛﭜﭝ
15:72 በዕድሜህ እንምላለን እነሱ በእርግጥ በስከራቸው ውስጥ ይዋልላሉ፡፡
ﭞﭟﭠﭡ
15:73 ጩኸቲቱም ፀሐይ የወጣችባቸው ሲኾኑ ያዘቻቸው፡፡
ﭢﭣﭤﭥﭦﭧﭨﭩﭪ
15:74 ላይዋንም ከታችዋ አደረግን፡፡ በእነሱም ላይ የሸክላ ደንጊያዎችን አዘነብንባቸው፡፡
ﭫﭬﭭﭮﭯﭰ
15:75 በዚህ ውስጥ ለተመልካቾች በእርግጥ መገምገሚያዎች አሉበት፡፡
ﭱﭲﭳﭴ
15:76 እሷም (ከተማይቱ) በቀጥታ መንገድ ላይ ናት፡፡
ﭵﭶﭷﭸﭹﭺ
15:77 በዚህ ውስጥ በእርግጥ ለምእምናን መገሰጫ አለ፡፡
ﭻﭼﭽﭾﭿﮀ
15:78 እነሆ የአይከት ሰዎችም በእርግጥ በዳዮች ነበሩ፤
ﮁﮂﮃﮄﮅﮆ
15:79 ከነሱም ተበቀልን ሁለቱም (የሉጥና የአይከት ሕዝቦች ከተሞች) በእርግጥ በግልጽ መንገድ ላይ ናቸው፡፡
ﮇﮈﮉﮊﮋﮌ
15:80 የሒጅርም ሰዎች መልክተኞቹን በእርግጥ አስተባበሉ፡፡
ﮍﮎﮏﮐﮑﮒ
15:81 ተዓምራታችንንም ሰጠናቸው፡፡ ከእርሷም ዘንጊዎች ነበሩ፡፡
ﮓﮔﮕﮖﮗﮘﮙ
15:82 ከኮረብታዎችም ቤቶችን ጸጥተኞች ኾነው ይጠርቡ ነበር፡፡
ﮚﮛﮜﮝ
15:83 ያነጉም ሲኾኑ ጩኸት ያዘቻቸው፤ (ወደሙ)፡፡
ﮞﮟﮠﮡﮢﮣﮤ
15:84 ይሠሩትም የነበሩት ሕንጻ ምንም አልጠቀማቸውም፡፡
ﮥﮦﮧﮨﮩﮪﮫﮬﮭﮮﮯﮰﮱﯓﯔﯕﯖ
15:85 ሰማያትንና ምድርንም በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በእውነት እንጂ (በላግጣ) አልፈጠርንም፡፡ ሰዓቲቱም በእርግጥ መጪ ናት፡፡ መልካምንም ይቅርታ አድርግላቸው፡፡
ﯗﯘﯙﯚﯛﯜ
15:86 ጌታህ እርሱ (ያልነበረን) ፈጣሪው ዐዋቂው ነው፡፡
ﯝﯞﯟﯠﯡﯢﯣﯤ
15:87 ከሚደጋገሙ የኾኑን ሰባትንና ታላቁንም ቁርኣን (በሙሉ) በእርግጥ ሰጠንህ፡፡
ﯥﯦﯧﯨﯩﯪﯫﯬﯭﯮﯯﯰﯱﯲﯳﯴ
15:88 ከእነርሱ (ከከሓዲዎች) ብዙዎችን ወገኖች በእርሱ ወደ አጣቀምንበት ጸጋ ዓይኖችህን አትዘርጋ፡፡ በእነሱም ላይ (ባያምኑ) አትዘን፡፡ ክንፍህንም ለምእምናን አለዝብ፡፡
ﯵﯶﯷﯸﯹﯺ
15:89 በልም «እኔ ግልጽ አስፈራሪው እኔ ነኝ፡፡»
ﯻﯼﯽﯾﯿ
15:90 (ሰዎችን ለማገድ የመካን በሮች) በተከፋፈሉት ላይ እንደ አወረድነው (በኾነ ቅጣት አሰፈራሪያችሁ ነኝ በል)፡፡
ﭑﭒﭓﭔﭕ
15:91 (እነርሱም) እነዚያ ቁርኣንንን ክፍልፍሎች ያደረጉ ናቸው፡፡
ﭖﭗﭘﭙ
15:92 በጌታህም እንምላለን፡፡ ሁላቸውንም እንጠይቃቸዋለን፤
ﭚﭛﭜﭝ
15:93 ይሠሩት ከነበሩት ነገር ሁሉ፡፡
ﭞﭟﭠﭡﭢﭣﭤ
15:94 የታዘዝክበትንም ነገር በይፋ ግለጽ፡፡ አጋሪዎችንም ተዋቸው፡፡
ﭥﭦﭧﭨ
15:95 ተሳላቂዎችን ሁሉ እኛ በቅተንሃል፡፡
ﭩﭪﭫﭬﭭﭮﭯﭰﭱﭲ
15:96 (እነሱም) እነዚያ ከአላህ ጋር ሌላ አምላክን ያደረጉ ናቸው፡፡ በእርግጥም (ፍጻሜያቸውን) ወደፊት ያውቃሉ፡፡
ﭳﭴﭵﭶﭷﭸﭹﭺ
15:97 አንተም በሚሉት ነገር ልብህ የሚጠብ መኾኑን በእርግጥ እናውቃለን፡፡
ﭻﭼﭽﭾﭿﮀﮁ
15:98 ጌታህንም ከማመስገን ጋር አጥራው ከሰጋጆቹም ኹን፡፡
ﮂﮃﮄﮅﮆﮇ
15:99 እውነቱም (ሞት) እስኪመጣህ ድረስ ጌታህን ተገዛ፡፡

ቅዱስ ቁርኣን


Wednesday, September 9, 2026

Don't forget us in your sincere prayers