PDF —
96 አንቀጽ Meccan PDF
Built right in your browser — download starts automatically

ሱረቱ አል-ዋቂዐ pdf — አውርድ (አማርኛ)

ሱረቱ አል-ዋቂዐ pdf አማርኛ — አውርድ ሱረቱ አል-ዋቂዐ ትርጉም. ሱረቱ አል-ዋቂዐ (Meccan) 96 አንቀጽ.



96 አንቀጽ · Meccan · አማርኛ
bismillah
ﮃﮄﮅﮆ
56:1 መከራይቱ በወደቀች ጊዜ፡፡
ﮇﮈﮉﮊ
56:2 ለመውደቋ አስተባባይ (ነፍስ) የለችም፡፡
ﮋﮌﮍ
56:3 ዝቅ አድራጊና ከፍ አድራጊ ናት፡፡
ﮎﮏﮐﮑﮒ
56:4 ምድር መናወጥን በተናወጠች ጊዜ፡፡
ﮓﮔﮕﮖ
56:5 ተራራዎችም መፍፈርፈርን በተፈረፈሩ ጊዜ (እንደተፈጨ ዱቄት በኾኑ ጊዜ)፡፡
ﮗﮘﮙﮚ
56:6 የተበተነ ብናኝ በኾኑም ጊዜ
ﮛﮜﮝﮞ
56:7 ሦስት ዓይነቶችም በኾናችሁ ጊዜ (ታዋርዳለች፤ ታነሳለችም)፡፡
ﮟﮠﮡﮢﮣﮤ
56:8 የቀኝ ጓዶችም ምን (የተከበሩ) የቀኝ ጓዶች ናቸው፡፡
ﮥﮦﮧﮨﮩﮪ
56:9 የግራ ጓዶችም ምን (የተዋረዱ) የግራ ጓዶች ናቸው፡፡
ﮫﮬﮭ
56:10 (ለበጎ ሥራ) ቀዳሚዎቹም (ለገነት) ቀዳሚዎች ናቸው፡፡
ﮮﮯﮰ
56:11 እነዚያ ባለሟሎቹ ናቸው፡፡
ﮱﯓﯔﯕ
56:12 በመጠቀሚያ ገነቶች ውስጥ ሲኾኑ፡፡
ﯖﯗﯘﯙ
56:13 ከፊተኞቹ ብዙ ጭፍሮች ናቸው፡፡
ﯚﯛﯜﯝ
56:14 ከኋለኞቹም ጥቂቶች ናቸው፡፡
ﯞﯟﯠﯡ
56:15 በተታቱ አልጋዎች ላይ ይኾናሉ፡፡
ﯢﯣﯤﯥ
56:16 በእርሷ ላይ የተመቻቹና ፊት ለፊት የተቅጣጩ ሲኾኑ፡፡
ﭑﭒﭓﭔﭕ
56:17 በእነርሱ ላይ ሁል ጊዜ የማያረጁ ወጣቶች ልጆች ይዘዋወራሉ፡፡
ﭖﭗﭘﭙﭚﭛ
56:18 ከጠጅ ምንጭም በብርጭቆዎችና በኩስኩስቶች በጽዋም (በእነርሱ ላይ ይዝዞራሉ)፡፡
ﭜﭝﭞﭟﭠﭡ
56:19 ከእርሷ የራስ ምታት አያገኛቸውም፤ አይሰክሩምም፡፡
ﭢﭣﭤﭥ
56:20 ከሚመርጡትም ዓይነት በእሸቶች፡፡
ﭦﭧﭨﭩﭪ
56:21 ከሚሹትም በኾነ የበራሪ ሥጋ (ይዞሩባቸዋል)፡፡
ﭫﭬﭭ
56:22 ዓይናማዎች የኾኑ ነጫጭ ቆንጆዎችም አሏቸው፡፡
ﭮﭯﭰﭱ
56:23 ልክ እንደተሸፈነ ሉል መሰሎች የኾኑ፡፡
ﭲﭳﭴﭵﭶ
56:24 በዚያ ይሠሩት በነበሩት ምክንያት ዋጋ ይኾን ዘንድ (ይህንን አደረግንላቸው)፡፡
ﭷﭸﭹﭺﭻﭼﭽ
56:25 በውስጥዋ ውድቅ ንግግርንና መውወንጀልን አይሰሙም፡፡
ﭾﭿﮀﮁﮂ
56:26 ግን ሰላም መባባልን (ይሰማሉ)፡፡
ﮃﮄﮅﮆﮇﮈ
56:27 የቀኝም ጓዶች ምንኛ (የከበሩ) የቀኝ ጓዶች!
ﮉﮊﮋﮌ
56:28 በተቀፈቀፈ (እሾህ በሌለው) ቁርቁራ ውስጥ ናቸው፡፡
ﮍﮎﮏ
56:29 (ፍሬው) በተነባበረ በሙዝ ዛፍም፡፡
ﮐﮑﮒ
56:30 በተዘረጋ ጥላ ሥርም፡፡
ﮓﮔﮕ
56:31 በሚንቧቧ ውሃ አጠገብም፡፡
ﮖﮗﮘ
56:32 ብዙ (ዓይነት) በኾኑ ፍራፍሬዎችም፡፡
ﮙﮚﮛﮜﮝ
56:33 የማትቋረጥም የማትከለከልም የኾነች፡፡
ﮞﮟﮠ
56:34 ከፍ በተደረጉ ምንጣፎችም (ሴቶችም መካከል)፡፡
ﮡﮢﮣﮤ
56:35 እኛ አዲስ ፍጥረት አድርገን (ለእነርሱ) ፈጠርናቸው፡፡
ﮥﮦﮧ
56:36 ደናግሎችም አደረግናቸው፡፡
ﮨﮩﮪ
56:37 ለባሎቻቸው ተሽሞርሟሪዎች እኩያዎች (አደረግናቸው)፡፡
ﮫﮬﮭ
56:38 ለቀኝ ጓዶች (አዘጋጀናቸው)፡፡
ﮮﮯﮰﮱ
56:39 ከፊተኞቹ ብዙ ጭፍሮች ናቸው፡፡
ﯓﯔﯕﯖ
56:40 ከኋለኞቹም ብዙ ጭፍሮች ናቸው፡፡
ﯗﯘﯙﯚﯛﯜ
56:41 የግራ ጓደኞችም ምንኛ (የተዋረዱ) የግራ ጓዶች! ናቸው፡፡
ﯝﯞﯟﯠ
56:42 በመርዛም ነፋስ በጣም በፈላ ውሃም ውስጥ ናቸው፡፡
ﯡﯢﯣﯤ
56:43 ከጥቁር ጭስም በኾነ ጥላ ውስጥ፡፡
ﯥﯦﯧﯨﯩ
56:44 ቀዝቃዛም መልካምም ያልኾነ፡፡
ﯪﯫﯬﯭﯮﯯ
56:45 እነርሱ ከዚህ በፊት ቅምጥሎች ነበሩና፡፡
ﯰﯱﯲﯳﯴﯵ
56:46 በታላቅ ኀጢአትም ላይ ይዘወትሩ ነበሩና፡፡
ﯶﯷﯸﯹﯺﯻﯼﯽﯾﯿ
56:47 ይሉም ነበሩ፡- «በሞትንና ዐፈር፣ ዐጥንቶችም በኾን ጊዜ እኛ በእርግጥ የምንቀሰቀስ ነን?
ﰀﰁﰂ
56:48 «የፊተኞቹ አባቶቻችንም?»
ﰃﰄﰅﰆﰇ
56:49 በላቸው፡- «ፊተኞቹም ኋለኞቹም፡፡
ﰈﰉﰊﰋﰌﰍ
56:50 «በተወሰነ ቀን ቀጠሮ በእርግጥ ተሰብሳቢዎች ናቸው፡፡
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖ
56:51 «ከዚያም እናንተ ጠማሞች አስተባባዮች ሆይ!
ﭗﭘﭙﭚﭛﭜ
56:52 « ከዘቁም ዛፍ በእርግጥ በይዎች ናችሁ፡፡
ﭝﭞﭟﭠ
56:53 «ከእርሷም ሆዶቻችሁን ሞይዎች ናችሁ፡፡
ﭡﭢﭣﭤﭥ
56:54 «በእርሱ ላይም ከፈላ ውሃ ጠጪዎች ናችሁ፡፡
ﭦﭧﭨﭩ
56:55 «የተጠሙንም ግመሎች አጠጣጥ ብጤ ጠጪዎች ናችሁ፡፡»
ﭪﭫﭬﭭﭮ
56:56 ይህ በፍርዱ ቀን መስተንግዷቸው ነው፡፡
ﭯﭰﭱﭲﭳ
56:57 እኛ ፈጠርናችሁ አታምኑምን?
ﭴﭵﭶﭷ
56:58 (በማኅፀኖች) የምታፈሱትን አያችሁን?
ﭸﭹﭺﭻﭼﭽ
56:59 እናንተ ትፈጥሩታላችሁን? ወይስ እኛ ፈጣሪዎቹን ነን?
ﭾﭿﮀﮁﮂﮃﮄﮅ
56:60 እኛ ሞትን (ጊዜውን) በመካከላችሁ ወሰንን፡፡ እኛም ተሸናፊዎች አይደለንም፡፡
ﮆﮇﮈﮉﮊﮋﮌﮍﮎﮏ
56:61 ብጤዎቻችሁን በመለወጥና በዚያ በማታውቁትም (ቅርጽ) እናንተን በመፍጠር ላይ (አንሸነፍም)፡፡
ﮐﮑﮒﮓﮔﮕﮖ
56:62 የፊተኛይቱንም አፈጣጠር በእርግጥ ዐውቃችኋል፡፡ አትገነዘቡምን?
ﮗﮘﮙﮚ
56:63 የምትዘሩትንም አያችሁን?
ﮛﮜﮝﮞﮟﮠ
56:64 እናንተ ታበቅሉታላችሁን? ወይስ እኛ አብቃዮቹ ነን?
ﮡﮢﮣﮤﮥﮦﮧ
56:65 ብነሻ ኖሮ ደረቅ ስብርብር ባደረግነውና የምትደነቁም በኾናችሁ ነበር፡፡
ﮨﮩﮪ
56:66 «እኛ በዕዳ ተያዦች ነን፡፡
ﮫﮬﮭﮮ
56:67 «በእርግጥም እኛ (ከመጠቀም) የተከለከልን ነን» (ትሉ ነበር)፡፡
ﮯﮰﮱﯓﯔ
56:68 ያንንም የምትጠጡትን ውሃ አየችሁን?
ﯕﯖﯗﯘﯙﯚﯛﯜ
56:69 እናንተ ከደመናው አወረዳችሁትን? ወይስ እኛ አውራጆቹ ነን?
ﯝﯞﯟﯠﯡﯢﯣ
56:70 ብንሻ ኖሮ መርጋጋ ባደረግነው ነበር፡፡ አታመሰግኑምን?
ﯤﯥﯦﯧﯨ
56:71 ያቺንም የምትሰብቋትን እሳት አያችሁን?
ﯩﯪﯫﯬﯭﯮﯯ
56:72 እናንተ ዛፏን ፈጠራችሁን? ወይስ እኛ ፈጣሪዎችዋ ነን?
ﯰﯱﯲﯳﯴﯵ
56:73 እኛ (ለገሀናም) ማስታወሻ ለመንገደኞችም መጠቀሚያ አደረግናት፡፡
ﯶﯷﯸﯹﯺ
56:74 የታላቁን ጌታህንም ስም አወድስ፡፡
ﯻﯼﯽﯾﯿﰀ
56:75 በከዋክብትም መጥለቂያዎች እምላለሁ፡፡
ﰁﰂﰃﰄﰅﰆ
56:76 እርሱም ብታወቁ ታላቅ መሓላ ነው፡፡
ﭑﭒﭓﭔ
56:77 እርሱ የከበረ ቁርኣን ነው፡፡
ﭕﭖﭗﭘ
56:78 በተጠበቀ መጽሐፍ ውስጥ ነው፡፡
ﭙﭚﭛﭜﭝ
56:79 የተጥራሩት እንጅ ሌላ አይነካውም፡፡
ﭞﭟﭠﭡﭢ
56:80 ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው፡፡
ﭣﭤﭥﭦﭧ
56:81 በዚህ ንግግር እናንተ ቸልተኞች ናችሁን?
ﭨﭩﭪﭫﭬ
56:82 ሲሳያችሁንም (ዝናምን) እናንተ የምታስተባብሉት ታደርጋላችሁን?
ﭭﭮﭯﭰﭱ
56:83 (ነፍስ) ጉረሮንም በደረሰች ጊዜ፡፡
ﭲﭳﭴﭵ
56:84 እናንተ ያን ጊዜ የምታዩ ስትኾኑ፡፡
ﭶﭷﭸﭹﭺﭻﭼﭽ
56:85 እኛም ግን አታዩም እንጅ ከእናንተ ይልቅ ወደእርሱ የቀረብን ስንኾን፡፡
ﭾﭿﮀﮁﮂﮃ
56:86 የማትዳኙም ከኾናችሁ፡፡
ﮄﮅﮆﮇﮈ
56:87 እውነተኞች እንደ ኾናችሁ (ነፍሲቱን ወደ አካሉ) ለምን አትመልሷትም፡፡
ﮉﮊﮋﮌﮍﮎ
56:88 (ሟቹ) ከባለሟሎቹ ቢኾንማ፡፡
ﮏﮐﮑﮒﮓ
56:89 (ለእርሱ) ዕረፍት፣ መልካም ሲሳይም፣ የመጠቀሚያ ገነትም አልለው፡፡
ﮔﮕﮖﮗﮘﮙﮚ
56:90 ከቀኝ ጓዶችም ቢኾንማ፡፡
ﮛﮜﮝﮞﮟﮠ
56:91 ከቀኝ ጓዶች ስለ ኾንክ ላንተ ሰላም አልለህ (ይባላል)፡፡
ﮡﮢﮣﮤﮥﮦﮧ
56:92 ከሚያስዋሹት ጠማማዎችም ቢኾንማ፡፡
ﮨﮩﮪﮫ
56:93 ከፈላ ውሃ የኾነ መስተንግዶ አልለው፡፡
ﮬﮭﮮ
56:94 በገሀነም መቃጠልም (አልለው)፡፡
ﮯﮰﮱﯓﯔﯕ
56:95 ይህ እርሱ እርግጠኛ እውነት ነው፡፡
ﯖﯗﯘﯙﯚ
56:96 የታላቁንም ጌታህን ስም አወድስ፡፡

ቅዱስ ቁርኣን


Wednesday, September 9, 2026

Don't forget us in your sincere prayers