PDF —
59 አንቀጽ Meccan PDF
Built right in your browser — download starts automatically

ሱረቱ አድ-ዱኻን pdf — አውርድ (አማርኛ)

ሱረቱ አድ-ዱኻን pdf አማርኛ — አውርድ ሱረቱ አድ-ዱኻን ትርጉም. ሱረቱ አድ-ዱኻን (Meccan) 59 አንቀጽ.



59 አንቀጽ · Meccan · አማርኛ
bismillah
ﭑﭒ
44:1 ሐ.መ (ሓ ሚም)፡፡
ﭓﭔﭕ
44:2 አብራሪ በኾነው መጽሐፍ እንምላለን፡፡
ﭖﭗﭘﭙﭚﭛﭜﭝﭞﭟ
44:3 እኛ (ቁርኣኑን) በተባረከች ሌሊት ውስጥ አወረድነው፡፡ እኛ አስፈራሪዎች ነበርንና፡፡
ﭠﭡﭢﭣﭤﭥ
44:4 በውስጧ የተወሰነው ነገር ሁሉ ይልለያል፡፡
ﭦﭧﭨﭩﭪﭫﭬﭭ
44:5 ከእኛ ዘንድ የኾነ ትእዛዝ ሲኾን (አወረድነው)፡፡ እኛ (መልክተኞችን) ላኪዎች ነበርን፡፡
ﭮﭯﭰﭱﭲﭳﭴﭵﭶ
44:6 ከጌታህ በኾነው ችሮታ (ተላኩ)፡፡ እነሆ እርሱ ሰሚው ዐዋቂው ነውና፡፡
ﭷﭸﭹﭺﭻﭼﭽﭾﭿﮀ
44:7 የሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ያለው ነገር ሁሉ ጌታ ከኾነው (ተላኩ)፡፡ የምታረጋግጡ እንደኾናችሁ (ነገሩ እንዳልነው መኾኑን እወቁ)፡፡
ﮁﮂﮃﮄﮅﮆﮇﮈﮉﮊﮋﮌ
44:8 ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ ሕያው ያደርጋል፡፡ ይገድላልም፡፡ ጌታችሁ የመጀመሪያዎቹ አባቶቻችሁም ጌታ ነው፡፡
ﮍﮎﮏﮐﮑﮒ
44:9 በእውነቱ እነርሱ የሚጫወቱ ሲኾኑ በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡
ﮓﮔﮕﮖﮗﮘﮙ
44:10 ሰማይም በግልጽ ጭስ የምትመጣበትን ቀን ተጠባበቅ፡፡
ﮚﮛﮜﮝﮞﮟﮠ
44:11 ሰዎችን የሚሸፍን (በኾነ ጭስ) ይህ አሳማሚ ቅጣት ነው፡፡
ﮡﮢﮣﮤﮥﮦﮧ
44:12 «ጌታችን ሆይ! ከእኛ ላይ ቅጣቱን ግለጥልን፡፡ እኛ አማኞች እንኾናለንና» (ይላሉም)፡፡
ﮨﮩﮪﮫﮬﮭﮮﮯ
44:13 (ቅጣቱ በወረደ ጊዜ) ለእነርሱ መግገሰጽ እንዴት ይኖራቸዋል? አስረጅ መልክተኛ የመጣቸው ሲኾን (የካዱም ሲኾኑ)፡፡
ﮰﮱﯓﯔﯕﯖﯗ
44:14 ከዚያም ከእርሱ የዞሩ፤ (ከሰው) «የተሰተማረ ዕብድ ነው» ያሉም ሲኾኑ፡፡
ﯘﯙﯚﯛﯜﯝﯞﯟ
44:15 እኛ ቅጣቱን ለጥቂት ጊዜ ገላጮች ነን፡፡ እናንተ (ወደ ክህደታችሁ) በእርግጥ ተመላሾች ናችሁ፡፡
ﯠﯡﯢﯣﯤﯥﯦ
44:16 ታላቂቱን ብርቱ አያያዝ በምንይዝበት ቀን፤ እኛ ተበቃዮች ነን፡፡
ﯧﯨﯩﯪﯫﯬﯭﯮﯯﯰ
44:17 ከእነርሱም በፊት የፈርዖንን ሕዝቦች በእርግጥ ሞከርን፡፡ ክቡር መልእክተኛም መጣላቸው፡፡
ﯱﯲﯳﯴﯵﯶﯷﯸﯹﯺﯻ
44:18 «የአላህን ባሮች ወደኔ አድርሱ፡፡ እኔ ለእናንተ ታማኝ መልክተኛ ነኝና፡፡
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖﭗﭘﭙﭚﭛ
44:19 «በአላህም ላይ አትኩሩ፡፡ እኔ ግልጽ የኾነን አስረጅ ያመጣሁላችሁ ነኝና (በማለት መጣላቸው)፡፡
ﭜﭝﭞﭟﭠﭡﭢ
44:20 «እኔም እንዳትወግሩኝ በጌታየና በጌታችሁ ተጠብቂያለሁ፡፡
ﭣﭤﭥﭦﭧﭨ
44:21 «በእኔም ባታምኑ ራቁኝ» (ተዉኝ አለ)፡፡
ﭩﭪﭫﭬﭭﭮﭯ
44:22 ቀጥሎም (ስለ ዛቱበት) «እነዚህ አመጸኞች ሕዝቦች ናቸው» (አጥፋቸው) ሲል ጌታውን ለመነ፡፡
ﭰﭱﭲﭳﭴﭵ
44:23 (ጌታው) «ባሮቼንም ይዘህ በሌሊት ኺድ፡፡ እናንተ የሚከተሉዋችሁ ናችሁና፡፡
ﭶﭷﭸﭹﭺﭻﭼﭽ
44:24 «ባሕሩንም የተከፈተ ኾኖ ተወው፡፡ እነርሱ የሚሰጥጠሙ ሰራዊት ናቸውና» (አለው)፡፡
ﭾﭿﮀﮁﮂﮃ
44:25 ከአትክልቶችና ከምንጮችም ብዙ ነገሮችን ተዉ፡፡
ﮄﮅﮆﮇ
44:26 ከአዝመራዎችም ከመልካም መቀመጫም፡፡
ﮈﮉﮊﮋﮌ
44:27 በእርሷ ተደሳቾች ከነበሩባትም ድሎት (ብዙን ነገር ተዉ)፡፡
ﮍﮎﮏﮐﮑﮒ
44:28 (ነገሩ) እንደዚሁ ኾነ፡፡ ሌሎችንም ሕዝቦች አወረስናት፡፡
ﮓﮔﮕﮖﮗﮘﮙﮚﮛ
44:29 ሰማይና ምድርም በእነርሱ ላይ አላለቀሱም፡፡ የሚቆዩም አልነበሩም፡፡
ﮜﮝﮞﮟﮠﮡﮢﮣ
44:30 የእስራኤልንም ልጆች አዋራጅ ከኾነ ስቃይ በእርግጥ አዳንናቸው፡፡
ﮤﮥﮦﮧﮨﮩﮪﮫﮬ
44:31 ከፈርዖን፤ እርሱ የኮራ ከወሰን አላፊዎቹ ነበርና፡፡
ﮭﮮﮯﮰﮱﯓﯔ
44:32 ከማወቅም ጋር በዓለማት ላይ በእርግጥ መረጥናቸው፡፡
ﯕﯖﯗﯘﯙﯚﯛﯜ
44:33 ከታምራቶችም በውስጡ ግልጽ የኾነ ፈተና ያለበትን ሰጠናቸው፡፡
ﯝﯞﯟﯠ
44:34 እነዚህ (የመካ ከሓዲዎች) በእርግጥ ይላሉ፡-
ﯡﯢﯣﯤﯥﯦﯧﯨﯩ
44:35 እርሷ የፊተኛይቱ ሞታችን እንጅ አይደለችም፡፡ እኛም የምንቀሰቀስ አይደለንም፡፡
ﯪﯫﯬﯭﯮﯯ
44:36 እውነተኞችም እንደ ኾናችሁ አባቶቻችንን አምጡልን፡፡
ﯰﯱﯲﯳﯴﯵﯶﯷﯸﯹﯺﯻﯼﯽ
44:37 እነርሱ በላጮች ናቸውን ወይስ የቱብበዕ ሕዝቦችና እነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩት? አጠፋናቸው፡፡ እነርሱ አመጸኞች ነበሩና፡፡
ﯾﯿﰀﰁﰂﰃﰄﰅ
44:38 ሰማያትንና ምድርንም በሁለቱ መካከል ያለውንም ሁሉ ቀላጆች ኾነን አልፈጠርንም፡፡
ﰆﰇﰈﰉﰊﰋﰌﰍﰎ
44:39 ሁለቱንም በምር እንጅ አልፈጠርናቸውም፡፡ ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖ
44:40 የመለያው ቀን ለሁሉም ቀጠሯቸው ነው፡፡
ﭗﭘﭙﭚﭛﭜﭝﭞﭟﭠﭡ
44:41 ዘመድ ከዘመዱ ምንንም የማይጠቅምበት እነርሱም የማይርረዱበት ቀን ነው፡፡
ﭢﭣﭤﭥﭦﭧﭨﭩﭪ
44:42 አላህ ያዘነለት ሰውና ያመነ ብቻ ሲቀር፡፡ (እርሱስ ይርረዳል)፡፡ እርሱ አሸናፊው አዛኙ ነውና፡፡
ﭫﭬﭭﭮ
44:43 የዘቁመ ዛፍ
ﭯﭰﭱ
44:44 የኀጢኣተኛው ምግብ ነው፡፡
ﭲﭳﭴﭵﭶ
44:45 እንደ ዘይት አተላ ነው፡፡ በሆዶች ውስጥ የሚፈላ ሲኾን፡፡
ﭷﭸﭹ
44:46 እንደ ገነፈለ ውሃ አፈላል (የሚፈላ ሲኾን)፡፡
ﭺﭻﭼﭽﭾﭿ
44:47 ያዙት፤ ወደ ገሀነም መካከልም በኀይል ጎትቱት፡፡
ﮀﮁﮂﮃﮄﮅﮆﮇ
44:48 ከዚያም «ከራሱ በላይ ከፈላ ውሃ ስቃይ አንቧቡበት፡፡»
ﮈﮉﮊﮋﮌﮍ
44:49 «ቅመስ፤ አንተ አሸናፊው ክብሩ ነህና» (ይባላል)፡፡
ﮎﮏﮐﮑﮒﮓﮔ
44:50 «ይህ ያ በእርሱ ትጠራጠሩበት የነበራችሁት ነው» (ይባላሉ)፡፡
ﮕﮖﮗﮘﮙﮚ
44:51 ጥንቁቆቹ በእርግጥ በጸጥተኛ መኖሪያ ውስጥ ናቸው፡፡
ﮛﮜﮝﮞ
44:52 በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ ናቸው፡፡
ﮟﮠﮡﮢﮣﮤ
44:53 ፊት ለፊት የተቅጣጩ ኾነው ከስስ ሐርና ከወፍራም ሐር ይለብሳሉ፡፡
ﮥﮦﮧﮨﮩ
44:54 (ነገሩ) እንደዚሁ ነው፤ ዓይናማዎች የኾኑን ነጫጭ ሴቶችም እናጠናዳቸዋለን፡፡
ﮪﮫﮬﮭﮮﮯ
44:55 በእርሷም ውስጥ የተማመኑ ኾነው፤ ከፍራፍሬ ሁሉ ያዝዛሉ፡፡
ﮰﮱﯓﯔﯕﯖﯗﯘﯙﯚﯛﯜ
44:56 የፊተኛይቱን ሞት እንጅ (ዳግመኛ) በእርሷ ውስጥ ሞትን አይቀምሱም፡፡ የገሀነምንም ቅጣት (አላህ) ጠበቃቸው፡፡
ﯝﯞﯟﯠﯡﯢﯣﯤﯥ
44:57 ከጌታህ በኾነ ችሮታ (ጠበቃቸው)፡፡ ይህ እርሱ ታላቅ ዕድል ነው፡፡
ﯦﯧﯨﯩﯪﯫ
44:58 (ቁርኣኑን) በቋንቋህም ያገራነው (ሕዝቦችህ) ይገነዘቡ ዘንድ ብቻ ነው፡፡
ﯬﯭﯮﯯ
44:59 ተጠባበቅም እነርሱ ተጠባባቂዎች ናቸውና፡፡

ቅዱስ ቁርኣን


Wednesday, September 9, 2026

Don't forget us in your sincere prayers