PDF —
52 አንቀጽ Meccan PDF
Built right in your browser — download starts automatically

ሱረቱ አል-ሀቅቃ pdf — አውርድ (አማርኛ)

ሱረቱ አል-ሀቅቃ pdf አማርኛ — አውርድ ሱረቱ አል-ሀቅቃ ትርጉም. ሱረቱ አል-ሀቅቃ (Meccan) 52 አንቀጽ.



52 አንቀጽ · Meccan · አማርኛ
bismillah
ﮯﮰ
69:1 እውነትን አረጋጋጪቱ (ትንሣኤ)፡፡
ﮱﯓﯔ
69:2 አረጋጋጪቱም (እርሷ) ምንድን ናት!
ﯕﯖﯗﯘﯙ
69:3 አረጋጋጪቱም ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ?
ﯚﯛﯜﯝﯞ
69:4 ሰሙድና ዓድ በቆርቋሪይቱ (ትንሣኤ) አስተባበሉ፡፡
ﯟﯠﯡﯢﯣ
69:5 ሠሙድማ ወሰን በሌላት ጩኸት ተጠፋ፤ (ተወደሙ)፡፡
ﯤﯥﯦﯧﯨﯩﯪ
69:6 ዓድማ በኀይል በምትንሻሻ ብርቱ ነፋስ ተጠፉ፡፡
ﯫﯬﯭﯮﯯﯰﯱﯲﯳﯴﯵﯶﯷﯸﯹﯺﯻ
69:7 ተከታታይ በኾኑ ሰባት ሌሊቶችና ስምንት መዓልቶች ውስጥ በእነርሱ ላይ ለቀቃት፡፡ ሕዝቦቹንም፤ በውስጧ የተጣሉ ኾነው ልክ ክፍት የኾኑ የዘንባባ ግንዶች መስለው ታያቸዋለህ፡፡
ﯼﯽﯾﯿﰀﰁ
69:8 ለእነርሱም ቀሪን ታያለህን?
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖﭗ
69:9 ፈርዖን ከበፊቱ የነበሩትም ሰዎች ተገልባጮቹም (ከተሞች) በኀጢአት (ሥራዎች) መጡ፡፡
ﭘﭙﭚﭛﭜﭝﭞ
69:10 የጌታቸውንም መልእክተኛ ትዕዛዝ ጣሱ፡፡ የበረታችንም አያያዝ ያዛቸው፡፡
ﭟﭠﭡﭢﭣﭤﭥﭦ
69:11 እኛ ውሃው ባየለ ጊዜ በተንሻላይቱ ታንኳ ውስጥ ጫንናችሁ፡፡
ﭧﭨﭩﭪﭫﭬﭭ
69:12 ለእናንተ መገሰጫ ልናደርጋት አጥኒ የኾነችም ጆሮ ታጠናት ዘንድ፡፡
ﭮﭯﭰﭱﭲﭳﭴ
69:13 በቀንዱም አንዲት መንነፋት በተነፋች ጊዜ፡፡
ﭵﭶﭷﭸﭹﭺﭻ
69:14 ምድርና ጋራዎችም (ከስፍራቸው) በተነሱና አንዲትን መሰባበር በተሰባበሩ ጊዜ፡፡
ﭼﭽﭾﭿ
69:15 በዚያ ቀን ኋኝቱ (ትንሣኤ) ትኾናለች፡፡
ﮀﮁﮂﮃﮄﮅ
69:16 ሰማይም ትቀደዳለች፡፡ ስለዚህ እርሷ በዚያ ቀን ደካማ ናት፡፡
ﮆﮇﮈﮉﮊﮋﮌﮍﮎﮏﮐ
69:17 መላእክትም በየጫፎችዋ ላይ ይኾናሉ፡፡ የጌታህንም ዐርሽ በዚያ ቀን ስምንት መላእክት ከበላያቸው ይሸከማሉ፡፡
ﮑﮒﮓﮔﮕﮖﮗ
69:18 በዚያ ቀን ከእናንተ ተደባቂ (ነገሮች) የማይደበቁ ሲኾኑ ትቅቀረባላችሁ፡፡
ﮘﮙﮚﮛﮜﮝﮞﮟﮠﮡ
69:19 መጽሐፉን በቀኙ የተሰጠ ሰውማ (ለጓደኞቹ) «እንኩ፤ መጽሐፌን አንብቡ» ይላል፡፡
ﮢﮣﮤﮥﮦﮧ
69:20 «እኔ ምርመራየን የምገናኝ መኾኔን አረጋገጥኩ፤» (ተዘጋጀሁም ይላል)፡፡
ﮨﮩﮪﮫﮬ
69:21 እርሱም በተወደደች ኑሮ ውሰጥ ይኾናል፡፡
ﮭﮮﮯﮰ
69:22 በከፍተኛይቱ ገነት ውስጥ፡፡
ﮱﯓﯔ
69:23 ፍሬዎችዋ ቅርቦች የኾኑ፡፡
ﯕﯖﯗﯘﯙﯚﯛﯜﯝ
69:24 በአለፉት ቀናት ውስጥ (በምድረ ዓለም) ባስቀደማችሁት ምክንያት ብሉ፤ ጠጡም፤ (ይባላሉ)፡፡
ﯞﯟﯠﯡﯢﯣﯤﯥﯦﯧﯨ
69:25 መጽሐፉንም በግራው የተሰጠማ «ዋ ጥፋቴ! ምነው መጽሐፌን ባልተሰጠሁ» ይላል፡፡
ﯩﯪﯫﯬﯭ
69:26 «ምርመራየንም ምን እንደኾነ ባላወቅኩ፡፡
ﯮﯯﯰﯱ
69:27 «እርሷ (ሞት ሕይወቴን) ምነው ፈጻሚ በኾነች፡፡
ﯲﯳﯴﯵﯶﯷ
69:28 «ገንዘቤ ከእኔ ምንንም አላብቃቃኝ፤ (አልጠቀመኝም)፡፡
ﯸﯹﯺﯻ
69:29 «ኀይሌ ከእኔ ላይ ጠፋ» (ይላል)፡፡
ﯼﯽﯾ
69:30 «ያዙት፤ እሰሩትም፡፡
ﯿﰀﰁﰂ
69:31 «ከዚያም በእሳት ውሰጥ አግቡት፡፡
ﰃﰄﰅﰆﰇﰈﰉﰊ
69:32 «ከዚያም ርዝመቷ ሰባ ክንድ በኾነች ሰንሰለት ውስጥ አግቡት፡፡»
ﰋﰌﰍﰎﰏﰐﰑ
69:33 እርሱ ታላቅ በኾነው አላህ አያምንም ነበርና፡፡
ﰒﰓﰔﰕﰖﰗ
69:34 ድኾችንም በማብላት ላይ አያግባባም ነበርና፡፡
ﰘﰙﰚﰛﰜﰝ
69:35 ለእርሱም ዛሬ እዚህ ዘመድ የለውም፡፡
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖ
69:36 ምግብም ከእሳት ሰዎች ቁስል እጣቢ (እዥ) በስተቀር የለውም፡፡
ﭗﭘﭙﭚﭛ
69:37 ኀጢኣተኞች እንጅ ሌላ አይበላውም፤ (ይባላል)፡፡
ﭜﭝﭞﭟﭠ
69:38 በምታዩትም ነገር እምላለሁ፡፡
ﭡﭢﭣﭤ
69:39 በማታዩትም ነገር፡፡
ﭥﭦﭧﭨﭩ
69:40 እርሱ (ቁርኣን) የተከበረ መልክተኛ ቃል ነው፡፡
ﭪﭫﭬﭭﭮﭯﭰﭱﭲ
69:41 እርሱም የባለቅኔ ቃል (ግጥም) አይደለም፡፡ ጥቂትን ብቻ ታምናላችሁ፡፡
ﭳﭴﭵﭶﭷﭸﭹﭺ
69:42 የጠንቋይም ቃል አይደለም፡፡ ጥቂትን ብቻ ታስታውሳላችሁ፡፡
ﭻﭼﭽﭾﭿ
69:43 ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው፡፡
ﮀﮁﮂﮃﮄﮅ
69:44 በእኛ ላይም ከፊልን ቃላት (ያላልነውን) በቀጠፈ ኖሮ፤
ﮆﮇﮈﮉ
69:45 በኀይል በያዝነው ነበር፡፡
ﮊﮋﮌﮍﮎ
69:46 ከዚያም ከእርሱ የልቡን ሥር (የተንጠለጠለበትን ጅማት) በቆረጥን ነበር፡፡
ﮏﮐﮑﮒﮓﮔﮕ
69:47 ከእናንተም ውስጥ ከእርሱ ላይ ከልካዮች ምንም አይኖሩም፡፡
ﮖﮗﮘﮙ
69:48 እርሱም (ቁርኣን) ለጥንቁቆቹ መገሠጫ ነው፡፡
ﮚﮛﮜﮝﮞﮟ
69:49 እኛም ከእናንተ ውስጥ አስተባባዮች መኖራቸውን በእርግጥ እናውቃለን፡፡
ﮠﮡﮢﮣﮤ
69:50 እርሱም (ቁርኣን) በከሓዲዎቹ ላይ ጸጸት ነው፡፡
ﮥﮦﮧﮨ
69:51 እርሱም የተረጋገጠ እውነት ነው፡፡
ﮩﮪﮫﮬﮭ
69:52 የታላቁን ጌታህንም ስም አወድስ፡፡

ቅዱስ ቁርኣን


Wednesday, September 9, 2026

Don't forget us in your sincere prayers