PDF —
26 አንቀጽ Meccan PDF
Built right in your browser — download starts automatically

ሱረቱ አል-ጋሺያ pdf — አውርድ (አማርኛ)

ሱረቱ አል-ጋሺያ pdf አማርኛ — አውርድ ሱረቱ አል-ጋሺያ ትርጉም. ሱረቱ አል-ጋሺያ (Meccan) 26 አንቀጽ.

← አል-አዕላሱረቱ አል-ጋሺያ አል-ፈጅር →


26 አንቀጽ · Meccan · አማርኛ
bismillah
ﭽﭾﭿﮀﮁ
88:1 የሸፋኝቱ (ትንሣኤ) ወሬ መጣህን?
ﮂﮃﮄﮅ
88:2 ፊቶች በዚያ ቀን ተዋራጆች ናቸው፡፡
ﮆﮇﮈ
88:3 ሠሪዎች ለፊዎች ናቸው፡፡
ﮉﮊﮋﮌ
88:4 ተኳሳን እሳት ይገባሉ፡፡
ﮍﮎﮏﮐﮑ
88:5 በጣም ከፈላች ምንጭ ይጋታሉ፡፡
ﮒﮓﮔﮕﮖﮗﮘ
88:6 ለእነርሱ ዶሪዕ ከሚባል (እሾሃም) ዛፍ እንጅ ሌላ ምግብ የላቸውም፡፡
ﮙﮚﮛﮜﮝﮞﮟ
88:7 የማያሰባ ከረኃብም የማያብቃቃ ከኾነው፡፡
ﮠﮡﮢﮣ
88:8 ፊቶች በዚያ ቀን ተቀማጣዮች ናቸው፡፡
ﮤﮥﮦ
88:9 ለሥራቸው ተደሳቾች ናቸው፡፡
ﮧﮨﮩﮪ
88:10 በከፍተኛ ገነት ውስጥ ናቸው፡፡
ﮫﮬﮭﮮﮯ
88:11 በውስጧ ውድቅን ነገር አይሰሙም፡፡
ﮰﮱﯓﯔ
88:12 በውስጧ ፈሳሾች ምንጮች አልሉ፡፡
ﯕﯖﯗﯘ
88:13 በውስጧ ከፍ የተደረጉ አልጋዎች አልሉ፡፡
ﯙﯚﯛ
88:14 በተርታ የተኖሩ ብርጭቆዎችም፡፡
ﯜﯝﯞ
88:15 የተደረደሩ መከዳዎችም፡፡
ﯟﯠﯡ
88:16 የተነጠፉ ስጋጃዎችም (አልሉ)፡፡
ﯢﯣﯤﯥﯦﯧﯨ
88:17 (ከሓዲዎች) አይመለከቱምን? ወደ ግመል እንዴት እነደተፈጠረች!
ﯩﯪﯫﯬﯭ
88:18 ወደ ሰማይም እንዴት ከፍ እንደ ተደረገች!
ﯮﯯﯰﯱﯲ
88:19 ወደ ተራራዎችም እንዴት እንደ ተቸከሉ!
ﯳﯴﯵﯶﯷ
88:20 ወደ ምድርም እንዴ እንደተዘረጋች (አይመለከቱምን?)
ﯸﯹﯺﯻﯼ
88:21 አስታውስም፤ አንተ አስታዋሽ ብቻ ነህና፡፡
ﯽﯾﯿﰀ
88:22 በእነርሱ ላይ ተሿሚ (አስገዳጅ) አይደለህም፡፡
ﭑﭒﭓﭔﭕ
88:23 ግን (ከእውነት) የዞረና የካደ ሰው፤
ﭖﭗﭘﭙﭚ
88:24 አላህ ታላቁን ቅጣት ይቀጣዋል፡፡
ﭛﭜﭝﭞ
88:25 መመለሻቸው ወደእኛ ብቻ ነው፡፡
ﭟﭠﭡﭢﭣ
88:26 ከዚያም ምርመራቸው በእኛ ላይ ብቻ ነው፡፡

ቅዱስ ቁርኣን


Wednesday, September 9, 2026

Don't forget us in your sincere prayers