ሱረቱ አል-አዕላ pdf — አውርድ (አማርኛ)
ሱረቱ አል-አዕላ pdf አማርኛ — አውርድ ሱረቱ አል-አዕላ ትርጉም. ሱረቱ አል-አዕላ (Meccan) 19 አንቀጽ.
Related
More ሱረቱ PDF
ሱረቱ አል-አዕላ

ﮟﮠﮡﮢﮣ
87:1
ከሁሉ በላይ የኾነውን ጌታህን ስም አሞግሥ፡፡
ﮤﮥﮦﮧ
87:2
የዚያን (ሁሉን ነገር) የፈጠረውን ያስተካከለውንም፡፡
ﮨﮩﮪﮫ
87:3
የዚያንም የወሰነውን፡፡ (ለተፈጠረለት ነገር) የመራውንም፡፡
ﮬﮭﮮﮯ
87:4
የዚያንም ግጦሽን (ለምለም አድርጎ) ያወጣውን፡፡
ﮰﮱﯓﯔ
87:5
(ከዚያ) ደረቅ ጥቁር ያደረገውንም (አምላክ ስም አሞግስ)፡፡
ﯕﯖﯗﯘ
87:6
(ቁርኣንን) በእርግጥ እናስነብብሃለን፤ አትረሳምም፡፡
ﯙﯚﯛﯜﯝﯞﯟﯠﯡﯢﯣ
87:7
አላህ ከሻው ነገር በስተቀር፡፡ እርሱ ግልጹን የሚሸሸገውንም ሁሉ ያውቃልና፡፡
ﯤﯥﯦ
87:8
ለገሪቱም (ሕግጋት) እንገጥምሃለን፡፡
ﯧﯨﯩﯪﯫ
87:9
ግሣጼይቱ ብትጠቅም (ሰዎችን) ገሥጽም፡፡
ﯬﯭﯮﯯ
87:10
(አላህን) የሚፈራ ሰው በእርግጥ ይገሠጻል፡፡
ﭑﭒﭓ
87:11
መናጢውም ይርቃታል፡፡
ﭔﭕﭖﭗﭘ
87:12
ያ ታላቂቱን እሳት የሚገባው፡፡
ﭙﭚﭛﭜﭝﭞﭟ
87:13
ከዚያም በእርሷ ውስጥ አይሞትም ሕያውም አይኾንም፡፡
ﭠﭡﭢﭣﭤ
87:14
የተጥራራ ሰው በእርግጥ ዳነ፡፡
ﭥﭦﭧﭨﭩ
87:15
የጌታውንም ስም ያወሳና የሰገደ፡፡
ﭪﭫﭬﭭﭮ
87:16
ይልቁንም ቅርቢቱን ሕይወት ትመርጣላችሁ፡፡
ﭯﭰﭱﭲ
87:17
መጨረሻይቱ (ሕይወት) በላጭ ሁል ጊዜ ዘውታሪም ስትኾን፡፡
ﭳﭴﭵﭶﭷﭸ
87:18
ይህ በፊተኞቹ መጻሕፍት ውስጥ ያልለ ነው፡፡
ﭹﭺﭻﭼ
87:19
በኢብራሂምና በሙሳ ጽሑፎች ውስጥ፡፡
ቅዱስ ቁርኣን
Wednesday, September 9, 2026
Don't forget us in your sincere prayers







