ሱረቱ አል-ኢንሺቃቅ pdf — አውርድ (አማርኛ)
ሱረቱ አል-ኢንሺቃቅ pdf አማርኛ — አውርድ ሱረቱ አል-ኢንሺቃቅ ትርጉም. ሱረቱ አል-ኢንሺቃቅ (Meccan) 25 አንቀጽ.
Related
More ሱረቱ PDF
ሱረቱ አል-ኢንሺቃቅ

ﭣﭤﭥﭦ
84:1
ሰማይ በተቀደደች ጊዜ፤
ﭧﭨﭩﭪ
84:2
ለጌታዋም (ትዕዛዝ) በሰማች ጊዜ፤ (ልትሰማ) ተገባትም፤
ﭫﭬﭭﭮ
84:3
ምድርም በተለጠጠች ጊዜ፤
ﭯﭰﭱﭲﭳ
84:4
በውስጧ ያለውንም ሁሉ በጣለችና ባዶ በኾነች ጊዜ፤
ﭴﭵﭶﭷ
84:5
ለጌታዋም በሰማች ጊዜ፤ (መስማት) ተገባትም፤ (ሰው ሁሉ ሥራውን ይገናኛል)፡፡
ﭸﭹﭺﭻﭼﭽﭾﭿﮀ
84:6
አንተ ሰው ሆይ! አንተ ጌታህን (በሞት) እስከምትገናኝ ድረስ ልፋትን ለፊ ነህ፤ ተገናኚውም ነህ፡፡
ﮁﮂﮃﮄﮅﮆ
84:7
መጽሐፉን በቀኙ የተሰጠ ሰውማ፤
ﮇﮈﮉﮊﮋ
84:8
በእርግጥ ቀላልን ምርመራ ይመረመራል፡፡
ﮌﮍﮎﮏﮐ
84:9
ወደ ቤተሰቦቹም ተደሳች ኾኖ ይመለሳል፡፡
ﮑﮒﮓﮔﮕﮖﮗ
84:10
መጽሐፉን በጀርባው ኋላ የተሰጠ ሰውማ፤
ﮘﮙﮚﮛ
84:11
(ዋ! ጥፋቴ በማለት) ጥፋትን በእርግጥ ይጠራል፡፡
ﮜﮝﮞ
84:12
የተጋጋመች እሳትንም ይገባል፡፡
ﮟﮠﮡﮢﮣﮤ
84:13
እርሱ በቤተሰቡ ውስጥ ተደሳች ነበርና፡፡
ﮥﮦﮧﮨﮩﮪ
84:14
እርሱ (ወደ አላህ) የማይመለስ መኾኑን አስቧልና፡፡
ﮫﮬﮭﮮﮯﮰﮱﯓ
84:15
አይደለም (ይመለሳል)፡፡ ጌታው በእርሱ (መመለስ) ዐዋቂ ነበር፤ (ነውም)፡፡
ﯔﯕﯖﯗ
84:16
አትካዱ፤ በወጋገኑ እምላለሁ፡፡
ﯘﯙﯚﯛ
84:17
በሌሊቱም በሰበሰውም ሁሉ፤
ﯜﯝﯞﯟ
84:18
በጨረቃውም በሞላ ጊዜ (እምላለሁ)፡፡
ﯠﯡﯢﯣﯤ
84:19
ከኹነታ በኋላ ወደ ሌላ ኹነታ ትለዋወጣላችሁ፡፡
ﯥﯦﯧﯨﯩ
84:20
የማያምኑት ለእነርሱ ምን አላቸው?
ﯪﯫﯬﯭﯮﯯﯰﯱ
84:21
በእነርሱም ላይ ቁርኣን በተነበበ ጊዜ የማይሰግዱት፤ (ምንአላቸው?)
ﯲﯳﯴﯵﯶ
84:22
በእርግጡ እነዚያ የካዱት (በትንሣኤ) ያስተባብላሉ፡፡
ﯷﯸﯹﯺﯻ
84:23
አላህም (በልቦቻቸው) የሚቆጥሩትን ዐዋቂ ነው፡፡
ﯼﯽﯾﯿ
84:24
በአሳማሚ ቅጣትም አብስራቸው፡፡
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖﭗﭘﭙﭚ
84:25
ግን እነዚያ ያመኑና መልካሞችን የሠሩ ለእነርሱ የማይቆረጥ ምንዳ አልላቸው፡፡
ቅዱስ ቁርኣን
Wednesday, September 9, 2026
Don't forget us in your sincere prayers







