PDF —
78 አንቀጽ Medinan PDF
Built right in your browser — download starts automatically

ሱረቱ አር-ራህማን pdf — አውርድ (አማርኛ)

ሱረቱ አር-ራህማን pdf አማርኛ — አውርድ ሱረቱ አር-ራህማን ትርጉም. ሱረቱ አር-ራህማን (Medinan) 78 አንቀጽ.

← አል-ቀመርሱረቱ አር-ራህማን አል-ዋቂዐ →


78 አንቀጽ · Medinan · አማርኛ
bismillah
ﭷﭸ
55:1 አል-ረሕማን፤
ﭹﭺﭻ
55:2 ቁርኣንን አስተማረ፡፡
ﭼﭽﭾ
55:3 ሰውን ፈጠረ፡፡
ﭿﮀﮁ
55:4 መናገርን አስተማረው፡፡
ﮂﮃﮄﮅ
55:5 ፀሐይና ጨረቃ በተወሰነ ልክ (ይኼዳሉ)፡፡
ﮆﮇﮈﮉ
55:6 ሐረግና ዛፍም (ለእርሱ) ይሰግዳሉ፡፡
ﮊﮋﮌﮍﮎ
55:7 ሰማይንም አጓናት፡፡ ትክክለኛነትንም ደነገገ፡፡
ﮏﮐﮑﮒﮓ
55:8 በሚዛን (ስትመዝኑ) እንዳትበድሉ፡፡
ﮔﮕﮖﮗﮘﮙﮚ
55:9 መመዘንንም በትክክል መዝኑ፡፡ ተመዛኙንም አታጉድሉ፡፡
ﮛﮜﮝﮞ
55:10 ምድርንም ለፍጡሩ አደላደላት፡፡
ﮟﮠﮡﮢﮣﮤ
55:11 በውስጧ እሸት ባለ ሺፋኖች የኾኑ ዘንባባዎችም ያሉባት ስትኾን፡፡
ﮥﮦﮧﮨﮩ
55:12 የገለባ ባለቤት የኾነ ቅንጣትም፡፡ ባለ መልካም መዐዛ ቅጠሎችም (ያሉባት ስትኾን)፡፡
ﮪﮫﮬﮭﮮ
55:13 (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ﮯﮰﮱﯓﯔﯕ
55:14 ሰውን እንደ ሸክላ ከሚቅጨለጨል ደረቅ ጭቃ ፈጠረው፡፡
ﯖﯗﯘﯙﯚﯛﯜ
55:15 ጃንንም ከእሳት ከኾነ ነበልባል ፈጠረው፡፡
ﯝﯞﯟﯠﯡ
55:16 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ﯢﯣﯤﯥﯦ
55:17 የሁለቱ ምሥራቆች ጌታ፤ የሁለቱ ምዕራቦችም ጌታ ነው፡፡
ﯧﯨﯩﯪﯫ
55:18 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ﭑﭒﭓﭔ
55:19 ሁለቱን ባሕሮች የሚገናኙ ሲኾኑ ለቀቃቸው፡፡
ﭕﭖﭗﭘﭙ
55:20 (እንዳይዋሐዱ) በመካከላቸው ጋራጅ አልለ፡፡ (አንዱ ባንዱ ላይ) ወሰን አያልፉም፡፡
ﭚﭛﭜﭝﭞ
55:21 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታሰተባብላላችሁ?›
ﭟﭠﭡﭢﭣ
55:22 ሉልና መርጃን ከሁለቱ ይወጣል፡፡
ﭤﭥﭦﭧﭨ
55:23 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ﭩﭪﭫﭬﭭﭮﭯ
55:24 እንደ ጋራዎች ኾነው በባሕር ውስጥ የተሠሩት ተንሻለዮቹም (ታንኳዎች) የእርሱ ናቸው፡፡
ﭰﭱﭲﭳﭴ
55:25 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ﭵﭶﭷﭸﭹ
55:26 በእርሷ (በምድር) ላይ ያለው ሁሉ ጠፊ ነው፡፡
ﭺﭻﭼﭽﭾﭿﮀ
55:27 የልቅናና የልግሥና ባለቤት የኾነው የጌታህ ፊትም ይቀራል፡፡ (አይጠፋም)፡፡
ﮁﮂﮃﮄﮅ
55:28 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ﮆﮇﮈﮉﮊﮋﮌﮍﮎﮏﮐﮑ
55:29 በሰማያትና በምድር ውስጥ ያሉት ሁሉ ይለምኑታል፡፡ በየቀኑ ሁሉ እርሱ በሥራ ላይ ነው፡፡
ﮒﮓﮔﮕﮖ
55:30 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታሰተባብላላችሁ?›
ﮗﮘﮙﮚﮛ
55:31 እናንተ ሁለት ከባዶች (ሰዎችና ጋኔኖች) ሆይ! ለእናንተ (መቆጣጠር) በእርግጥ እናስባለን፡፡
ﮜﮝﮞﮟﮠ
55:32 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ﮡﮢﮣﮤﮥﮦﮧﮨﮩﮪﮫﮬﮭﮮﮯﮰﮱﯓ
55:33 የጋኔንና የሰው ጭፍሮች ሆይ! ከሰማያትና ከምድር ቀበሌዎች መውጣትን ብትችሉ ውጡ፡፡ በስልጣን እንጅ አትወጡም፡፡ (ግን ስልጣን የላችሁም)
ﯔﯕﯖﯗﯘ
55:34 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ﯙﯚﯛﯜﯝﯞﯟﯠﯡ
55:35 በሁለታችሁም ላይ ከእሳት ነበልባል፣ ጭስም ይላክባችኋል፡፡ (ሁለታችሁም) አትርረዱምም፡፡
ﯢﯣﯤﯥﯦ
55:36 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ﯧﯨﯩﯪﯫﯬﯭ
55:37 ሰማይም በተሰነጠቀችና እንደ ጽጌረዳ፣ እንደታረበ ቆዳ በኾነች ጊዜ፤ (ጭንቁን ምን አበረታው)፡፡
ﯮﯯﯰﯱﯲ
55:38 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ﯳﯴﯵﯶﯷﯸﯹﯺﯻ
55:39 በዚያም ቀን ሰውም ጃንም ከኃጢኣቱ ገና አይጠየቅም፡፡
ﯼﯽﯾﯿﰀ
55:40 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ﰁﰂﰃﰄﰅﰆﰇ
55:41 ከሓዲዎች በምልክታቸው ይታወቃሉ፡፡ አናቶቻቸውንና ጫማዎቻቸውንም ይያዛሉ፡፡
ﭑﭒﭓﭔﭕ
55:42 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ፡፡
ﭖﭗﭘﭙﭚﭛﭜ
55:43 ይህቺ ያቺ አመጸኞች በእርሷ ያስተባብሉባት የነበረችው ገሀነም ናት (ይባላሉ)፡፡
ﭝﭞﭟﭠﭡﭢ
55:44 በእርሷና በጣም ሞቃት በኾነ ፍል ውሃ መካከል ይመላለሳሉ፡፡
ﭣﭤﭥﭦﭧ
55:45 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ﭨﭩﭪﭫﭬﭭ
55:46 በጌታውም ፊት መቆምን ለፈራ ሰው ሁለት ገነቶች አልሉት፡፡
ﭮﭯﭰﭱﭲ
55:47 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ﭳﭴﭵ
55:48 የቀንዘሎች ባለ ቤቶች የኾኑ (ገነቶች አልሉት)፡፡
ﭶﭷﭸﭹﭺ
55:49 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ﭻﭼﭽﭾ
55:50 በሁለቱ ውስጥ የሚፈስሱ ሁለት ምንጮች አልሉ፡፡
ﭿﮀﮁﮂﮃ
55:51 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ﮄﮅﮆﮇﮈﮉ
55:52 በሁለቱ ውስጥ ከፍራፍሬዎች ሁሉ ሁለት ዓይነቶች (እርጥብና ደረቅ) አልሉ፡፡
ﮊﮋﮌﮍﮎ
55:53 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ﮏﮐﮑﮒﮓﮔﮕﮖﮗﮘﮙ
55:54 የውስጥ ጉስጉሳቸው ከወፍራም ሐር በኾኑ ምንጣፎች ላይ የተመቻቹ ሲኾኑ (ይንፈላሰሳሉ)፡፡ የሁለቱም ገነቶች ፍሬ (ለለቃሚ) ቅርብ ነው፡፡
ﮚﮛﮜﮝﮞ
55:55 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ﮟﮠﮡﮢﮣﮤﮥﮦﮧﮨ
55:56 በውስጣቸው ከበፊታቸው (ከባሎቻቸው በፊት) ሰውም ጃንም ያልገሰሳቸው ዓይኖቻቸውን (በባሎቻቸው ላይ) አሳጣሪዎች (ሴቶች) አልሉ፡፡
ﮩﮪﮫﮬﮭ
55:57 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ﮮﮯﮰﮱ
55:58 ልክ ያቁትና መርጃን ይመስላሉ፡፡
ﯓﯔﯕﯖﯗ
55:59 ከጌታችሁም ጸጋዎቸ በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ﯘﯙﯚﯛﯜﯝ
55:60 የበጎ ሥራ ዋጋ በጎ እንጅ ሌላ ነውን?
ﯞﯟﯠﯡﯢ
55:61 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ﯣﯤﯥﯦ
55:62 ከሁለቱ ገነቶችም ሌላ ሁለት ገነቶች አልሉ፡፡
ﯧﯨﯩﯪﯫ
55:63 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?›
ﯬﯭ
55:64 ከልምላሜያቸው የተነሳ ወደ ጥቁረት ያዘነበሉ ናቸው፡፡
ﯮﯯﯰﯱﯲ
55:65 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ﯳﯴﯵﯶ
55:66 በውስጣቸው ሁለት የሚንፏፉ ምንጮች አልሉ፡፡
ﯷﯸﯹﯺﯻ
55:67 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ﯼﯽﯾﯿﰀ
55:68 በውስጣቸው ፍራፍሬ፣ ዘምባባም፣ ሩማንም አልለ፡፡
ﰁﰂﰃﰄﰅ
55:69 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ﭑﭒﭓﭔ
55:70 በውስጣቸው ጠባየ መልካሞች መልክ ውቦች (ሴቶች) አልሉ፡፡
ﭕﭖﭗﭘﭙ
55:71 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ﭚﭛﭜﭝﭞ
55:72 በድንኳኖች ውስጥ የተጨጎሉ የዓይኖቻቸው ጥቁረትና ንጣት ደማቅ የኾኑ ናቸው፡፡
ﭟﭠﭡﭢﭣ
55:73 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ﭤﭥﭦﭧﭨﭩﭪ
55:74 ከነርሱ በፊት ሰውም ጃንም አልገሰሳቸውም፡፡
ﭫﭬﭭﭮﭯ
55:75 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባበላላችሁ?
ﭰﭱﭲﭳﭴﭵﭶ
55:76 በሚያረገርጉ አረንጓዴ ምንጣፎችና በሚያማምሩ ስጋጃዎች ላይ የተደላደሉ ሲኾኑ (ይቀመጣሉ)፡፡
ﭷﭸﭹﭺﭻ
55:77 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?
ﭼﭽﭾﭿﮀﮁﮂ
55:78 የግርማና የመክበር ባለቤት የኾነው ጌታህ ስም ተባረከ፡፡

ቅዱስ ቁርኣን


Wednesday, September 9, 2026

Don't forget us in your sincere prayers