La sourate Al-Burooj en Amharique
وَالسَّمَاءِ ذَاتِ الْبُرُوجِ(1) የቡርጆች ባለቤት በኾነችው ሰማይ እምላለሁ፡፡ |
وَالْيَوْمِ الْمَوْعُودِ(2) በተቀጠረው ቀንም፤ |
وَشَاهِدٍ وَمَشْهُودٍ(3) በተጣጅና በሚጣዱትም፤ (እምላለሁ)፡፡ |
قُتِلَ أَصْحَابُ الْأُخْدُودِ(4) የጉድቡ ባለቤቶች ተረገሙ፡፡ |
النَّارِ ذَاتِ الْوَقُودِ(5) የማገዶ ባለቤት የኾነቺው እሳት (ባለቤቶች)፡፡ |
إِذْ هُمْ عَلَيْهَا قُعُودٌ(6) እነርሱ በርሷ (አፋፍ) ላይ ተቀማጮች በኾኑ ጊዜ፤ (ተረገሙ)፡፡ |
وَهُمْ عَلَىٰ مَا يَفْعَلُونَ بِالْمُؤْمِنِينَ شُهُودٌ(7) እነርሱም በምእምናኖቹ በሚሠሩት (ማሰቃየት) ላይ መስካሪዎች ናቸው፡፡ |
وَمَا نَقَمُوا مِنْهُمْ إِلَّا أَن يُؤْمِنُوا بِاللَّهِ الْعَزِيزِ الْحَمِيدِ(8) ከእነርሱም በአላህ አሸናፊው፣ ምስጉኑ በኾነው (ጌታ) ማመናቸውን እንጅ ሌላ ምንም አልጠሉም፡፡ |
الَّذِي لَهُ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ وَاللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ شَهِيدٌ(9) በእዚያ የሰማያትና የምድር ንግሥና ለእርሱ ብቻ በኾነው (አላህ ማመናቸውን)፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ መስካሪ ነው፡፡ |
إِنَّ الَّذِينَ فَتَنُوا الْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ ثُمَّ لَمْ يَتُوبُوا فَلَهُمْ عَذَابُ جَهَنَّمَ وَلَهُمْ عَذَابُ الْحَرِيقِ(10) እነዚያ ምእምንንና ምእምናትን ያሰቃዩ፣ ከዚያም ያልተጸጸቱ ለእነርሱ የገሀነም ቅጣት አልላቸው፡፡ ለእነርሱም የመቃጠሉ ስቃይ አልላቸው፡፡ |
إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ لَهُمْ جَنَّاتٌ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ ۚ ذَٰلِكَ الْفَوْزُ الْكَبِيرُ(11) እነዚያ ያመኑና መልካም ሥራዎችንም የሠሩ ለእነርሱ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች አሏቸው፡፡ ይህ ታላቅ ማግኘት ነው፡፡ |
إِنَّ بَطْشَ رَبِّكَ لَشَدِيدٌ(12) የጌታህ በኀይል መያዝ ብርቱ ነው፡፡ |
إِنَّهُ هُوَ يُبْدِئُ وَيُعِيدُ(13) እነሆ እርሱ መፍጠርን ይጀምራል፤ ይመልሳልም፡፡ |
وَهُوَ الْغَفُورُ الْوَدُودُ(14) እርሱም ምሕረተ ብዙ ወዳድ ነው፡፡ |
ذُو الْعَرْشِ الْمَجِيدُ(15) የዙፋኑ ባለቤት የላቀው ነው፡፡ |
فَعَّالٌ لِّمَا يُرِيدُ(16) የሚሻውን ሁሉ ሠሪ ነው፡፡ |
هَلْ أَتَاكَ حَدِيثُ الْجُنُودِ(17) የሰራዊቶቹ ወሬ መጣልህን? |
فِرْعَوْنَ وَثَمُودَ(18) የፈርዖንና የሰሙድ፤ (ወሬ)፡፡ |
بَلِ الَّذِينَ كَفَرُوا فِي تَكْذِيبٍ(19) በእውነቱ እነዚያ የካዱት በማስተባበል ውስጥ ናቸው፡፡ |
وَاللَّهُ مِن وَرَائِهِم مُّحِيطٌ(20) አላህም በዙሪያቸው (በዕውቀቱ) ከባቢ ነው፡፡ |
بَلْ هُوَ قُرْآنٌ مَّجِيدٌ(21) ይልቁንም እርሱ የከበረ ቁርኣን ነው፡፡ |
فِي لَوْحٍ مَّحْفُوظٍ(22) የተጠበቀ በኾነ ሰሌዳ ውስጥ ነው፡፡ |
Plus de sourates en Amharique :
Téléchargez la sourate avec la voix des récitants du Coran les plus célèbres :
Téléchargez le fichier mp3 de la sourate Al-Burooj : choisissez le récitateur pour écouter et télécharger la sourate Al-Burooj complète en haute qualité.















Donnez-nous une invitation valide