La sourate Al-Fajr en Amharique
وَالْفَجْرِ(1) በጎህ እምላለሁ፡፡ |
وَلَيَالٍ عَشْرٍ(2) በዐሥር ሌሊቶችም፡፡ |
وَالشَّفْعِ وَالْوَتْرِ(3) በጥንዱም በነጠላውም፡፡ |
وَاللَّيْلِ إِذَا يَسْرِ(4) በሌሊቱም በሚኼድ ጊዜ፡፡ |
هَلْ فِي ذَٰلِكَ قَسَمٌ لِّذِي حِجْرٍ(5) በዚህ (መሓላ) ለባለ አእምሮ ታላቅ መሓላ አለበትን? |
أَلَمْ تَرَ كَيْفَ فَعَلَ رَبُّكَ بِعَادٍ(6) ጌታህ በዓድ እንዴት እንደ ሠራ አታውቅምን? |
إِرَمَ ذَاتِ الْعِمَادِ(7) በኢረም በባለ ረዣዢሚቱ አዕማድ፡፡ |
الَّتِي لَمْ يُخْلَقْ مِثْلُهَا فِي الْبِلَادِ(8) በዚያች ብጤዋ በአገሮች ውስጥ ያልተፈጠረ በኾነችው፡፡ |
وَثَمُودَ الَّذِينَ جَابُوا الصَّخْرَ بِالْوَادِ(9) በሰሙድም በእነዚያ በሸለቆው ቋጥኝን የቆረጡ በኾኑት፡፡ |
وَفِرْعَوْنَ ذِي الْأَوْتَادِ(10) በፈርዖንም ባለ ችካሎች በኾነው፡፡ |
الَّذِينَ طَغَوْا فِي الْبِلَادِ(11) በእነዚያ በአገሮች ላይ ግፍ የሠሩ፡፡ |
فَأَكْثَرُوا فِيهَا الْفَسَادَ(12) በእርሷም ውስጥ ጥፋትን ያበዙ በኾኑት (እንዴት እንደሠራ አታውቅምን?) |
فَصَبَّ عَلَيْهِمْ رَبُّكَ سَوْطَ عَذَابٍ(13) በእነርሱ ላይም ጌታህ የቅጣትን አለንጋ አወረደባቸው፡፡ |
إِنَّ رَبَّكَ لَبِالْمِرْصَادِ(14) ጌታህ በመጠባበቂያ ላይ ነውና፡፡ |
فَأَمَّا الْإِنسَانُ إِذَا مَا ابْتَلَاهُ رَبُّهُ فَأَكْرَمَهُ وَنَعَّمَهُ فَيَقُولُ رَبِّي أَكْرَمَنِ(15) ሰውማ ጌታው በሞከረው ጊዜ፣ ባከበረውና ባጣቀመውም (ጊዜ) «ጌታዬ አከበረኝ (አበለጠኝ)» ይላል፡፡ |
وَأَمَّا إِذَا مَا ابْتَلَاهُ فَقَدَرَ عَلَيْهِ رِزْقَهُ فَيَقُولُ رَبِّي أَهَانَنِ(16) በሞከረውና በእርሱ ላይ ሲሳዩን ባጠበበ ጊዜማ «ጌታዬ አሳነሰኝ» ይላል፡፡ |
كَلَّا ۖ بَل لَّا تُكْرِمُونَ الْيَتِيمَ(17) ይከልከል፤ ይልቁንም የቲምን አታከብሩም፡፡ |
وَلَا تَحَاضُّونَ عَلَىٰ طَعَامِ الْمِسْكِينِ(18) ድኻንም በማብላት ላይ አትታዘዙም፡፡ |
وَتَأْكُلُونَ التُّرَاثَ أَكْلًا لَّمًّا(19) የውርስንም ገንዘብ የመሰብሰብን አበላል ትበላላችሁ፡፡ |
وَتُحِبُّونَ الْمَالَ حُبًّا جَمًّا(20) ገንዘብንም ብዙን መውደድ ትወዳላችሁ፡፡ |
كَلَّا إِذَا دُكَّتِ الْأَرْضُ دَكًّا دَكًّا(21) ተዉ፤ ምድር ደጋግማ በተሰባበረች ጊዜ፤ |
وَجَاءَ رَبُّكَ وَالْمَلَكُ صَفًّا صَفًّا(22) መላእክትም ሰልፍ ሰልፍ ኾነው ጌታህ (ትዕዛዙ) በመጣ ጊዜ፤ |
وَجِيءَ يَوْمَئِذٍ بِجَهَنَّمَ ۚ يَوْمَئِذٍ يَتَذَكَّرُ الْإِنسَانُ وَأَنَّىٰ لَهُ الذِّكْرَىٰ(23) ገሀነምም በዚያ ቀን በተመጣች ጊዜ በዚያ ቀን ሰው (ጥፋቱን) ይገነዘባል፡፡ መገንዘብም ለእርሱ ከየቱ? |
يَقُولُ يَا لَيْتَنِي قَدَّمْتُ لِحَيَاتِي(24) «ዋ እኔ! ምነው በሕይወቴ (መልካምን ሥራ) ባስቀደምኩ ኖሮ» ይላል፡፡ |
فَيَوْمَئِذٍ لَّا يُعَذِّبُ عَذَابَهُ أَحَدٌ(25) በዚያ ቀንም የርሱን አቀጣጥ አንድም አይቀጣም፡፡ |
وَلَا يُوثِقُ وَثَاقَهُ أَحَدٌ(26) የእርሱንም አስተሳሰር አንድም አያስርም፡፡ |
يَا أَيَّتُهَا النَّفْسُ الْمُطْمَئِنَّةُ(27) (ለአመነች ነፍስም) «አንቺ የረካሺው ነፍስ ሆይ! |
ارْجِعِي إِلَىٰ رَبِّكِ رَاضِيَةً مَّرْضِيَّةً(28) «ወዳጅ ተወዳጅ ኾነሽ ወደ ጌታሽ ተመለሺ፡፡ |
فَادْخُلِي فِي عِبَادِي(29) «በባሮቼም ውስጥ ግቢ፡፡ |
وَادْخُلِي جَنَّتِي(30) ገነቴንም ግቢ፤» (ትባላለች)፡፡ |
Plus de sourates en Amharique :
Téléchargez la sourate avec la voix des récitants du Coran les plus célèbres :
Téléchargez le fichier mp3 de la sourate Al-Fajr : choisissez le récitateur pour écouter et télécharger la sourate Al-Fajr complète en haute qualité.















Donnez-nous une invitation valide