La sourate At-Takwir en Amharique
إِذَا الشَّمْسُ كُوِّرَتْ(1) ፀሐይ በተጠቀለለች ጊዜ፤ |
وَإِذَا النُّجُومُ انكَدَرَتْ(2) ከዋክብትም በረገፉ ጊዜ፤ |
وَإِذَا الْجِبَالُ سُيِّرَتْ(3) ተራራዎችም በተነዱ ጊዜ፤ |
وَإِذَا الْعِشَارُ عُطِّلَتْ(4) የዐሥር ወር እርጉዞች ግመሎችም (ያለጠባቂ) በተተዉ ጊዜ፤ |
وَإِذَا الْوُحُوشُ حُشِرَتْ(5) እንስሳትም ሁሉ በተሰበሰቡ ጊዜ፤ |
وَإِذَا الْبِحَارُ سُجِّرَتْ(6) ባሕሮችም በተቃጠሉ ጊዜ፤ |
وَإِذَا النُّفُوسُ زُوِّجَتْ(7) ነፍሶችም (በየአካሎቻቸው) በተቆራኙ ጊዜ፤ |
وَإِذَا الْمَوْءُودَةُ سُئِلَتْ(8) በሕይወቷ የተቀበረችውም ሴት ልጅ በተጠየቀች ጊዜ፤ |
بِأَيِّ ذَنبٍ قُتِلَتْ(9) በምን ወንጀል እንደ ተገደለች፤ |
وَإِذَا الصُّحُفُ نُشِرَتْ(10) ጽሑፎችም በተዘረጉ ጊዜ፤ |
وَإِذَا السَّمَاءُ كُشِطَتْ(11) ሰማይም በተገሸለጠች ጊዜ፤ |
وَإِذَا الْجَحِيمُ سُعِّرَتْ(12) ገሀነምም በተነደደች ጊዜ፤ |
وَإِذَا الْجَنَّةُ أُزْلِفَتْ(13) ገነትም በተቀረበች ጊዜ፤ |
عَلِمَتْ نَفْسٌ مَّا أَحْضَرَتْ(14) ነፍስ ሁሉ (ከሥራ) ያቀረበችውን ታውቃለች፤ |
فَلَا أُقْسِمُ بِالْخُنَّسِ(15) ተመላሾችም በኾኑት (ዐዋድያት) እምላለሁ፡፡ |
الْجَوَارِ الْكُنَّسِ(16) ኺያጆች ገቢዎች በኾኑት (ከዋክብት)፡፡ |
وَاللَّيْلِ إِذَا عَسْعَسَ(17) በሌሊቱም (ጨለማውን) በጠነሰሰ ጊዜ፤ |
وَالصُّبْحِ إِذَا تَنَفَّسَ(18) በንጋቱም (በብርሃን) በተነፈሰ ጊዜ፤ (እምላለሁ)፡፡ |
إِنَّهُ لَقَوْلُ رَسُولٍ كَرِيمٍ(19) እርሱ (ቁርኣን) የክቡር መልክተኛ ቃል ነው፡፡ |
ذِي قُوَّةٍ عِندَ ذِي الْعَرْشِ مَكِينٍ(20) የኀይል ባለቤት በዙፋኑ ባለ ቤት ዘንድ ባለሟል የኾነ፡፡ |
مُّطَاعٍ ثَمَّ أَمِينٍ(21) በዚያ ስፍራ ትእዛዙ ተሰሚ፤ ታማኝ የኾነ (መልክተኛ ቃል) ነው፡፡ |
وَمَا صَاحِبُكُم بِمَجْنُونٍ(22) ነቢያችሁም በፍጹም ዕብድ አይደለም፡፡ |
وَلَقَدْ رَآهُ بِالْأُفُقِ الْمُبِينِ(23) በግልጹ አድማስም በእርግጥ አይቶታል፡፡ |
وَمَا هُوَ عَلَى الْغَيْبِ بِضَنِينٍ(24) እርሱም በሩቁ ወሬ ላይ ሰሳች (ንፉግ) አይደለም፡፡ |
وَمَا هُوَ بِقَوْلِ شَيْطَانٍ رَّجِيمٍ(25) እርሱም (ቁርኣን) የእርጉም ሰይጣን ቃል አይደለም፡፡ |
فَأَيْنَ تَذْهَبُونَ(26) ታዲያ ወዴት ትኼዳላችሁ? |
إِنْ هُوَ إِلَّا ذِكْرٌ لِّلْعَالَمِينَ(27) እርሱ የዓለማት መገሠጫ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ |
لِمَن شَاءَ مِنكُمْ أَن يَسْتَقِيمَ(28) ከናንተ ቀጥተኛ መኾንን ለሻ ሰው (መገሰጫ ነው)፡፡ |
وَمَا تَشَاءُونَ إِلَّا أَن يَشَاءَ اللَّهُ رَبُّ الْعَالَمِينَ(29) የዓለማት ጌታ አላህ ካልሻም አትሹም፡፡ |
Plus de sourates en Amharique :
Téléchargez la sourate avec la voix des récitants du Coran les plus célèbres :
Téléchargez le fichier mp3 de la sourate At-Takwir : choisissez le récitateur pour écouter et télécharger la sourate At-Takwir complète en haute qualité.















Donnez-nous une invitation valide