La sourate Al-Qiyamah en Amharique
لَا أُقْسِمُ بِيَوْمِ الْقِيَامَةِ(1) (ነገሩ ከሓዲዎች እንደሚሉት) አይደለም፡፡ በትንሣኤ ቀን እምላለሁ፡፡ |
وَلَا أُقْسِمُ بِالنَّفْسِ اللَّوَّامَةِ(2) (ራሷን) ወቃሽ በኾነች ነፍስም እምላለሁ፡፡ (በእርግጥ ትቀሰቀሳላችሁ)፡፡ |
أَيَحْسَبُ الْإِنسَانُ أَلَّن نَّجْمَعَ عِظَامَهُ(3) ሰው አጥንቶቹን አለመሰብሰባችንን ያስባልን? |
بَلَىٰ قَادِرِينَ عَلَىٰ أَن نُّسَوِّيَ بَنَانَهُ(4) አይደለም ጣቶቹን (ፊት እንደ ነበሩ) በማስተካከል ላይ ቻዮች ስንኾን (እንሰበስባቸዋለን)፡፡ |
بَلْ يُرِيدُ الْإِنسَانُ لِيَفْجُرَ أَمَامَهُ(5) ይልቁንም ሰው በፊቱ ባለው ነገር (በትንሣኤ) ሊያስተባብል ይፈልጋል፡፡ |
يَسْأَلُ أَيَّانَ يَوْمُ الْقِيَامَةِ(6) «የትንሣኤው ቀን መቼ ነው?» ሲል ይጠይቃል፡፡ |
فَإِذَا بَرِقَ الْبَصَرُ(7) ዓይንም በዋለለ ጊዜ፡፡ |
وَخَسَفَ الْقَمَرُ(8) ጨረቃም በጨለመ ጊዜ፡፡ |
وَجُمِعَ الشَّمْسُ وَالْقَمَرُ(9) ፀሐይና ጨረቃም በተሰበሰቡ ጊዜ፡፡ |
يَقُولُ الْإِنسَانُ يَوْمَئِذٍ أَيْنَ الْمَفَرُّ(10) «ሰው በዚያ ቀን መሸሻው የት ነው?» ይላል፡፡ |
كَلَّا لَا وَزَرَ(11) ይከልከል፤ ምንም መጠጊያ የለም፡፡ |
إِلَىٰ رَبِّكَ يَوْمَئِذٍ الْمُسْتَقَرُّ(12) በዚያ ቀን መርጊያው ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡ |
يُنَبَّأُ الْإِنسَانُ يَوْمَئِذٍ بِمَا قَدَّمَ وَأَخَّرَ(13) ሰው በዚያ ቀን ባስቀደመውና ባስቆየው ሁሉ ይነገራል፡፡ |
بَلِ الْإِنسَانُ عَلَىٰ نَفْسِهِ بَصِيرَةٌ(14) በእርግጥም ሰው በነፍሱ ላይ አስረጅ ነው፡፡ (አካሎቹ ይመሰክሩበታል)፡፡ |
وَلَوْ أَلْقَىٰ مَعَاذِيرَهُ(15) ምክንያቶቹን ሁሉ ቢያመጣም እንኳ (አይሰማም)፡፡ |
لَا تُحَرِّكْ بِهِ لِسَانَكَ لِتَعْجَلَ بِهِ(16) በእርሱ (በቁርኣን ንባብ) ልትቸኩል ምላስህን በእርሱ አታላውስ፡፡ |
إِنَّ عَلَيْنَا جَمْعَهُ وَقُرْآنَهُ(17) (በልብህ ውስጥ) መሰብሰቡና ማንበቡ በእኛ ላይ ነውና፡፡ |
فَإِذَا قَرَأْنَاهُ فَاتَّبِعْ قُرْآنَهُ(18) ባነበብነውም ጊዜ (ካለቀ በኋላ) ንባቡን ተከተል፡፡ |
ثُمَّ إِنَّ عَلَيْنَا بَيَانَهُ(19) ከዚያም ማብራራቱ በእኛ ላይ ነው፡፡ |
كَلَّا بَلْ تُحِبُّونَ الْعَاجِلَةَ(20) (ከመጣደፍ) ተከልከል፡፡ ይልቁንም (ሰዎች) ፈጣኒቱን (ዓለም) ትወዳላችሁ፡፡ |
وَتَذَرُونَ الْآخِرَةَ(21) መጨረሻይቱንም (ዓለም) ትተዋላችሁ፡፡ (አትዘጋጁላትም)፡፡ |
وُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ نَّاضِرَةٌ(22) ፊቶች በዚያ ቀን አብሪዎች ናቸው፡፡ |
إِلَىٰ رَبِّهَا نَاظِرَةٌ(23) ወደ ጌታቸው ተመልካቾች ናቸው፡፡ |
وَوُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ بَاسِرَةٌ(24) ፊቶችም በዚያ ቀን ጨፍጋጊዎች ናቸው፡፡ |
تَظُنُّ أَن يُفْعَلَ بِهَا فَاقِرَةٌ(25) በርሳቸውም ዐደጋ እንደሚሠራባቸው ያረጋግጣሉ፡፡ |
كَلَّا إِذَا بَلَغَتِ التَّرَاقِيَ(26) ንቁ (ነፍስ) ብሪዎችን በደረሰች ጊዜ፤ |
وَقِيلَ مَنْ ۜ رَاقٍ(27) «አሻሪው ማነው?» በተባለም ጊዜ፡፡ |
وَظَنَّ أَنَّهُ الْفِرَاقُ(28) (ሕመምተኛው) እርሱ (የሰፈረበት ነገር ከዚህ ዓለም) መልለየት መኾኑን ባረጋገጠም ጊዜ፡፡ |
وَالْتَفَّتِ السَّاقُ بِالسَّاقِ(29) ባትም በባት በተጣበቀች ጊዜ፡፡ |
إِلَىٰ رَبِّكَ يَوْمَئِذٍ الْمَسَاقُ(30) በዚያ ቀን መነዳቱ ወደ ጌታህ (ፍርድ) ነው፡፡ |
فَلَا صَدَّقَ وَلَا صَلَّىٰ(31) አላመነምም አልሰገደምም፡፡ |
وَلَٰكِن كَذَّبَ وَتَوَلَّىٰ(32) ግን አስተባበለ፤ (ከእምነት) ዞረም፡፡ |
ثُمَّ ذَهَبَ إِلَىٰ أَهْلِهِ يَتَمَطَّىٰ(33) ከዚያም እየተንጎባለለ ወደ ቤተሰቡ ኼደ፡፡ |
أَوْلَىٰ لَكَ فَأَوْلَىٰ(34) የምትጠላውን ነገር (አላህ) ያስከትልህ፡፡ ለአንተ ተገቢህም ነው፡፡ |
ثُمَّ أَوْلَىٰ لَكَ فَأَوْلَىٰ(35) ከዚያም ጥፋት ይጠጋህ ለአንተ የተገባህም ነው፡፡ |
أَيَحْسَبُ الْإِنسَانُ أَن يُتْرَكَ سُدًى(36) ሰው ስድ ኾኖ መትተውን ይጠረጥራልን? |
أَلَمْ يَكُ نُطْفَةً مِّن مَّنِيٍّ يُمْنَىٰ(37) የሚፈሰስ ከኾነ የፍትወት ጠብታ አልነበረምን? |
ثُمَّ كَانَ عَلَقَةً فَخَلَقَ فَسَوَّىٰ(38) ከዚያም የረጋ ደም ኾነ (አላህ ሰው አድርጎ) ፈጠረውም፡፡ አስተካከለውም፡፡ |
فَجَعَلَ مِنْهُ الزَّوْجَيْنِ الذَّكَرَ وَالْأُنثَىٰ(39) ከእርሱም ሁለት ዓይነቶችን ወንድና ሴትን አደረገ፡፡ |
أَلَيْسَ ذَٰلِكَ بِقَادِرٍ عَلَىٰ أَن يُحْيِيَ الْمَوْتَىٰ(40) ይህ (ጌታ) ሙታንን ሕያው በማድረግ ላይ ቻይ አይደለምን? |
Plus de sourates en Amharique :
Téléchargez la sourate avec la voix des récitants du Coran les plus célèbres :
Téléchargez le fichier mp3 de la sourate Al-Qiyamah : choisissez le récitateur pour écouter et télécharger la sourate Al-Qiyamah complète en haute qualité.















Donnez-nous une invitation valide