La sourate Al-Mutaffifin en Amharique
وَيْلٌ لِّلْمُطَفِّفِينَ(1) ለሰላቢዎች ወዮላቸው፡፡ |
الَّذِينَ إِذَا اكْتَالُوا عَلَى النَّاسِ يَسْتَوْفُونَ(2) ለእነዚያ ከሰዎች ባስሰፈሩ ጊዜ የሚያስሞሉ፡፡ |
وَإِذَا كَالُوهُمْ أَو وَّزَنُوهُمْ يُخْسِرُونَ(3) ለእነርሱም (ለሰዎቹ) በሰፈሩ ወይም በመዘኑላቸው ጊዜ የሚያጎድሉ (ለኾኑት)፡፡ |
أَلَا يَظُنُّ أُولَٰئِكَ أَنَّهُم مَّبْعُوثُونَ(4) እነዚያ እነርሱ ተቀስቃሾች መኾናቸውን አያውቁምን? |
لِيَوْمٍ عَظِيمٍ(5) በታላቁ ቀን፡፡ |
يَوْمَ يَقُومُ النَّاسُ لِرَبِّ الْعَالَمِينَ(6) ሰዎች ሁሉ ለዓለማት ጌታ (ፍርድ)፤ በሚቆሙበት ቀን (ተቀስቃሾች መኾናቸውን)፡፡ |
كَلَّا إِنَّ كِتَابَ الْفُجَّارِ لَفِي سِجِّينٍ(7) በእውነት የከሓዲዎቹ (የሰላቢዎቹ) መጽሐፍ በእርግጥ በሲጂን ውስጥ ነው፡፡ |
وَمَا أَدْرَاكَ مَا سِجِّينٌ(8) ሲጂንም ምን እንደ ኾነ ምን አሳወቀህ? |
كِتَابٌ مَّرْقُومٌ(9) የታተመ መጽሐፍ ነው፡፡ |
وَيْلٌ يَوْمَئِذٍ لِّلْمُكَذِّبِينَ(10) ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡ |
الَّذِينَ يُكَذِّبُونَ بِيَوْمِ الدِّينِ(11) ለእነዚያ በፍርዱ ቀን ለሚያስተባብሉት፡፡ |
وَمَا يُكَذِّبُ بِهِ إِلَّا كُلُّ مُعْتَدٍ أَثِيمٍ(12) በእርሱም ወሰን አላፊ ኀጢአተኛ ሁሉ እንጅ ሌላ አያስተባብልም፡፡ |
إِذَا تُتْلَىٰ عَلَيْهِ آيَاتُنَا قَالَ أَسَاطِيرُ الْأَوَّلِينَ(13) አንቀጾቻችን በእርሱ ላይ በተነበቡ ጊዜ «የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች ናቸው» ይላል፡፡ |
كَلَّا ۖ بَلْ ۜ رَانَ عَلَىٰ قُلُوبِهِم مَّا كَانُوا يَكْسِبُونَ(14) ይከልከል፤ ይልቁንም በልቦቻቸው ላይ ይሠሩት የነበሩት (ኀጢአት) ደገደገባቸው፡፡ |
كَلَّا إِنَّهُمْ عَن رَّبِّهِمْ يَوْمَئِذٍ لَّمَحْجُوبُونَ(15) ይከልከሉ፤ እነርሱ በዚያ ቀን ከጌታቸው (ማየት) ተጋራጆች ናቸው፡፡ |
ثُمَّ إِنَّهُمْ لَصَالُو الْجَحِيمِ(16) ከዚያም እነርሱ በእርግጥ ገሀነምን ገቢዎች ናቸው፡፡ |
ثُمَّ يُقَالُ هَٰذَا الَّذِي كُنتُم بِهِ تُكَذِّبُونَ(17) ከዚያም «ይህ ያ በእርሱ ታስተባብሉበት የነበራችሁት ነው» ይባላሉ፡፡ |
كَلَّا إِنَّ كِتَابَ الْأَبْرَارِ لَفِي عِلِّيِّينَ(18) በእውነቱ የእውነተኞቹ ምእምናን መጽሐፍ በዒሊዮን ውስጥ ነው፡፡ |
وَمَا أَدْرَاكَ مَا عِلِّيُّونَ(19) ዒሊዮንም ምን እንደ ኾነ ምን አሳወቀህ? |
كِتَابٌ مَّرْقُومٌ(20) የታተመ መጽሐፍ ነው፡፡ |
يَشْهَدُهُ الْمُقَرَّبُونَ(21) ባለሟልዎቹ ይጣዱታል፡፡ |
إِنَّ الْأَبْرَارَ لَفِي نَعِيمٍ(22) እውነተኞቹ ምእምናን በእርግጥ በድሎት (ገነት) ውስጥ ናቸው፡፡ |
عَلَى الْأَرَائِكِ يَنظُرُونَ(23) በባለ አጎበር አልጋዎች ላይ ኾነው ይመለከታሉ፡፡ |
تَعْرِفُ فِي وُجُوهِهِمْ نَضْرَةَ النَّعِيمِ(24) በፊቶቻቸው ላይ የድሎትን ውበት ታውቃለህ፡፡ |
يُسْقَوْنَ مِن رَّحِيقٍ مَّخْتُومٍ(25) ተጣርቶ ከታተመ ጠጅ ይጠጣሉ፡፡ |
خِتَامُهُ مِسْكٌ ۚ وَفِي ذَٰلِكَ فَلْيَتَنَافَسِ الْمُتَنَافِسُونَ(26) ማተሚያው ምስክ ከኾነ፤ በዚህም ተሽቀዳዳሚዎች ይሽቀዳደሙ፡፡ |
وَمِزَاجُهُ مِن تَسْنِيمٍ(27) መበረዣውም ከተስኒም ነው፡፡ |
عَيْنًا يَشْرَبُ بِهَا الْمُقَرَّبُونَ(28) ባለሟሎቹ ከእርሷ የሚጠጡላት ምንጭ ናት፡፡ |
إِنَّ الَّذِينَ أَجْرَمُوا كَانُوا مِنَ الَّذِينَ آمَنُوا يَضْحَكُونَ(29) እነዚያ ያምመጹት በእነዚያ ባመኑት በእርግጥ ይስቁ ነበሩ፡፡ |
وَإِذَا مَرُّوا بِهِمْ يَتَغَامَزُونَ(30) በእነርሱም ላይ ባለፉ ጊዜ ይጠቃቀሱ ነበር፡፡ |
وَإِذَا انقَلَبُوا إِلَىٰ أَهْلِهِمُ انقَلَبُوا فَكِهِينَ(31) ወደ ቤተሰቦቻቸውም በተመለሱ ጊዜ (በመሳለቃቸው) ተደሳቾች ኾነው ይመለሱ ነበር፡፡ |
وَإِذَا رَأَوْهُمْ قَالُوا إِنَّ هَٰؤُلَاءِ لَضَالُّونَ(32) ባዩዋቸውም ጊዜ «እነዚህ በእርግጥ ተሳሳቾች ናቸው» ይሉ ነበር፡፡ |
وَمَا أُرْسِلُوا عَلَيْهِمْ حَافِظِينَ(33) በነርሱ ላይ ተጠባባቂዎች ተደርገው ያልተላኩ ሲኾኑ፡፡ |
فَالْيَوْمَ الَّذِينَ آمَنُوا مِنَ الْكُفَّارِ يَضْحَكُونَ(34) ዛሬ (በትንሣኤ ቀን) እነዚያ ያመኑት በከሓዲዎቹ ይስቃሉ፡፡ |
عَلَى الْأَرَائِكِ يَنظُرُونَ(35) በባለ አጎበር አልጋዎች ላይ ኾነው የሚመለከቱ ሲኾኑ (ይስቃሉ)፡፡ |
هَلْ ثُوِّبَ الْكُفَّارُ مَا كَانُوا يَفْعَلُونَ(36) ከሓዲዎች ይሠሩት የነበሩትን (ዋጋ) ተመነዱን? (ይላሉ)፡፡ |
Plus de sourates en Amharique :
Téléchargez la sourate avec la voix des récitants du Coran les plus célèbres :
Téléchargez le fichier mp3 de la sourate Al-Mutaffifin : choisissez le récitateur pour écouter et télécharger la sourate Al-Mutaffifin complète en haute qualité.















Donnez-nous une invitation valide