አል-በቀራ · 177/286
ትርጉም ፊደሎች — ሱረቱ አል-በቀራ
۞ لَّيْسَ الْبِرَّ أَن تُوَلُّوا وُجُوهَكُمْ قِبَلَ الْمَشْرِقِ وَالْمَغْرِبِ وَلَٰكِنَّ الْبِرَّ مَنْ آمَنَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ وَالْمَلَائِكَةِ وَالْكِتَابِ وَالنَّبِيِّينَ وَآتَى الْمَالَ عَلَىٰ حُبِّهِ ذَوِي الْقُرْبَىٰ وَالْيَتَامَىٰ وَالْمَسَاكِينَ وَابْنَ السَّبِيلِ وَالسَّائِلِينَ وَفِي الرِّقَابِ وَأَقَامَ الصَّلَاةَ وَآتَى الزَّكَاةَ وَالْمُوفُونَ بِعَهْدِهِمْ إِذَا عَاهَدُوا ۖ وَالصَّابِرِينَ فِي الْبَأْسَاءِ وَالضَّرَّاءِ وَحِينَ الْبَأْسِ ۗ أُولَٰئِكَ الَّذِينَ صَدَقُوا ۖ وَأُولَٰئِكَ هُمُ الْمُتَّقُونَ ۝١٧٧
Laisal birra an tuwalloo wujoohakum qibalal mashriqi walmaghribi wa laakinnal birra man aamana billaahi wal yawmil aakhiri wal malaaa `ikati wal kitaabi wan nabiyyeena wa aatalmaala `alaa hubbihee zawilqurbaa walyataa maa walmasaakeena wabnas sabeeli wassaaa`ileena wa firriqaabi wa aqaamas salaata wa aataz zakaata walmoofoona bi ahdihim izaa `aahadoo wasaabireena fil baasaaa`i waddarraaa`i wa heenal baas; ulaaa`ikal lazeena sadaqoo wa ulaaa `ika humul muttaqoon
📖 በአማርኛ
መልካም ሥራ ፊቶቻችሁን ወደ ምሥራቅና ምዕራብ አቅጣጫ ማዞር አይደለም፡፡ ግን መልካም ሥራ በአላህና በመጨረሻው ቀን፣ በመላእክትም፣ በመጻሕፍትም፣ በነቢያትም፣ ያመነ ሰው ገንዘብንም ከመውደዱ ጋር ለዝምድና ባለቤቶችና ለየቲሞች ለምስኪኖችም፣ ለመንገደኞችም፣ ለለማኞችም፣ ለጫንቃዎችም (ማስለቀቅ) የሰጠ ሰውና ሶላትንም ደንቡን ጠብቆ የሰገደ፣ ዘካንም የሰጠ፣ ቃል ኪዳንም በገቡ ጊዜ በኪዳናቸው የሞሉ (ሰዎች ሥራ) ነው፡፡ በችግር በበሽታና በጦር ጊዜም ታጋሾችን (እናወድሳለን)፡፡ እነዚህ እነዚያ እውነትን የያዙ ናቸው፡፡ እነዚያም ተጠንቃቂዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡

M Mishary Rashid Alafasy ✓
M Mahmoud Khalil Al-Husary ✓
A Abdurrahman As-Sudais ✓
M Mohamed Siddiq Al-Minshawi ✓
A Abdul Basit Abdul Samad ✓
A Ali Al-Hudhaify ✓
A Ahmed ibn Ali al-Ajamy ✓
A Abu Bakr Ash-Shaatree ✓
M Muhammad Ayyoub ✓
A Abdullah Basfar ✓
A Abdullah Al-Juhani ✓
M Maher Al Muaiqly ✓
0:00
0:00
📜

ትርጉም — Tafsir

የቃላት ማብራሪያ፦

  • አል-ብር (الْبِرّ)፦ ሁሉንም የበጎ ሥራዎች የሚያካትት ሰፊ ቃል ነው፤ ትርጉሙም በጎነት፣ ቅንነትና አላህን የሚያስደስት ሁሉንም መልካም ሥራ ነው።
  • ቂበለል-መሽሪቂ ወል-መግሪብ (قِبَلَ الْمَشْرِقِ وَالْمَغْرِبِ)፦ ወደ ምሥራቅና ወደ ምዕራብ መላምት (መዞር) ማለት ነው።
  • ዘዊል-ቁርባ (ذَوِي الْقُرْبَى)፦ የዘመድ ወገኖች ማለት ነው።
  • ኢብነስ-ሰቢል (ابْنَ السَّبِيلِ)፦ በጉዞ ላይ ያለና ርቆ የቀረ ተጓዥ ማለት ነው።
  • ፊር-ሪቃብ (فِي الرِّقَابِ)፦ ባሪያዎችን ከባርነት ለመፍታትና እስረኞችን ለመልቀቅ ገንዘብ ማዋል ማለት ነው።
  • አል-በእሳእ (الْبَأْسَاءِ)፦ ድህነትና የኑሮ ጭንቀት ማለት ነው።
  • ደርራእ (الضَّرَّاءِ)፦ ሕመምና የበሽታ ጭንቀት ማለት ነው።
  • ሒነል-በእስ (حِينَ الْبَأْسِ)፦ በጦርነት ጊዜ የሚደርስ ጭንቀት ማለት ነው።

የአንቀጹ ትርጉምና ማብራሪያ፦

አላህ ሱብሐነሁ ወተዓላ በዚህች አንቀጽ ውስጥ የበጎነትን (አል-ብርን) እውነተኛ ትርጉም ገልጿል። በጎነት ወደ ምሥራቅ ወይም ወደ ምዕራብ መዞር ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም በጎነት ሰው በእውነት በአላህ ማመን፣ በመጨረሻው ቀን (የትንሳኤ ቀን) ማመን፣ በመላእክት ሁሉ ማመን፣ በአላህ ያወረዳቸው መጻሕፍት ሁሉ ማመን፣ በነቢያት ሁሉ ሳይለይ ማመን ነው። ከዚያም ሰው ለገንዘቡ ፍቅር ቢኖረውም በፈቃደኝነት ለዘመዶች፣ ለወላጅ አልባ ሕፃናት፣ ለድሆች፣ በጉዞ ላይ ለቀሩ ተጓዦች፣ ለሚለምኑ ሰዎችና ባሪያዎችን ከባርነት ለመፍታት መስጠት ነው። በተጨማሪም ሶላትን በትክክ



📜 አንቀጽ 175-179 — ሱረቱ አል-በቀራ

175أُولَٰئِكَ الَّذِينَ اشْتَرَوُا الضَّلَالَةَ بِالْهُدَىٰ وَالْعَذَابَ بِالْمَغْفِرَةِ ۚ فَمَا أَصْبَرَهُمْ عَلَى النَّارِ
እነዚያ ጥመትን በቅንነት ቅጣትንም በምሕረት የገዙ ናቸው፡፡ በእሳት ላይም ምን ታጋሽ አደረጋቸው!
176ذَٰلِكَ بِأَنَّ اللَّهَ نَزَّلَ الْكِتَابَ بِالْحَقِّ ۗ وَإِنَّ الَّذِينَ اخْتَلَفُوا فِي الْكِتَابِ لَفِي شِقَاقٍ بَعِيدٍ
ይህ (ቅጣት) አላህ መጽሐፍን በእውነት ያወረደ በመኾኑ ምክንያት (እና በርሱ በመካዳቸው) ነው፡፡ እነዚያም በመጽሐፉ የተለያዩት (ከእውነት) በራቀ ጭቅጭቅ ውስጥ ናቸው፡፡
177۞ لَّيْسَ الْبِرَّ أَن تُوَلُّوا وُجُوهَكُمْ قِبَلَ الْمَشْرِقِ وَالْمَغْرِبِ وَلَٰكِنَّ الْبِرَّ مَنْ آمَنَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ وَالْمَلَائِكَةِ وَالْكِتَابِ وَالنَّبِيِّينَ وَآتَى الْمَالَ عَلَىٰ حُبِّهِ ذَوِي الْقُرْبَىٰ وَالْيَتَامَىٰ وَالْمَسَاكِينَ وَابْنَ السَّبِيلِ وَالسَّائِلِينَ وَفِي الرِّقَابِ وَأَقَامَ الصَّلَاةَ وَآتَى الزَّكَاةَ وَالْمُوفُونَ بِعَهْدِهِمْ إِذَا عَاهَدُوا ۖ وَالصَّابِرِينَ فِي الْبَأْسَاءِ وَالضَّرَّاءِ وَحِينَ الْبَأْسِ ۗ أُولَٰئِكَ الَّذِينَ صَدَقُوا ۖ وَأُولَٰئِكَ هُمُ الْمُتَّقُونَ
መልካም ሥራ ፊቶቻችሁን ወደ ምሥራቅና ምዕራብ አቅጣጫ ማዞር አይደለም፡፡ ግን መልካም ሥራ በአላህና በመጨረሻው ቀን፣ በመላእክትም፣ በመጻሕፍትም፣ በነቢያትም፣ ያመነ ሰው ገንዘብንም ከመውደዱ ጋር ለዝምድና ባለቤቶችና ለየቲሞች ለምስኪኖችም፣ ለመንገደኞችም፣ ለለማኞችም፣ ለጫንቃዎችም (ማስለቀቅ) የሰጠ ሰውና ሶላትንም ደንቡን ጠብቆ የሰገደ፣ ዘካንም የሰጠ፣ ቃል ኪዳንም በገቡ ጊዜ በኪዳናቸው የሞሉ (ሰዎች ሥራ) ነው፡፡ በችግር በበሽታና በጦር ጊዜም ታጋሾችን (እናወድሳለን)፡፡ እነዚህ እነዚያ እውነትን የያዙ ናቸው፡፡ እነዚያም ተጠንቃቂዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡
178يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُتِبَ عَلَيْكُمُ الْقِصَاصُ فِي الْقَتْلَى ۖ الْحُرُّ بِالْحُرِّ وَالْعَبْدُ بِالْعَبْدِ وَالْأُنثَىٰ بِالْأُنثَىٰ ۚ فَمَنْ عُفِيَ لَهُ مِنْ أَخِيهِ شَيْءٌ فَاتِّبَاعٌ بِالْمَعْرُوفِ وَأَدَاءٌ إِلَيْهِ بِإِحْسَانٍ ۗ ذَٰلِكَ تَخْفِيفٌ مِّن رَّبِّكُمْ وَرَحْمَةٌ ۗ فَمَنِ اعْتَدَىٰ بَعْدَ ذَٰلِكَ فَلَهُ عَذَابٌ أَلِيمٌ
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በተገደሉ ሰዎች ማመሳሰል በናንተ ላይ ተጻፈ፡፡ ነጻ በነጻ ባሪያም በባሪያ ሴትም በሴት (ይገደላሉ)፡፡ ለእርሱም (ለገዳዩ) ከወንድሙ (ደም) ትንሽ ነገር ምሕረት የተደረገለት ሰው (በመሓሪው ላይ ጉማውን) በመልካም መከታተል ወደርሱም (ወደ መሓሪው) ገዳዩ በመልካም አኳኋን መክፈል አለባቸው፡፡ ይህ ከጌታችሁ የኾነ ማቃለልና እዝነት ነው፡፡ ከዚህም በኋላ ሕግን የተላለፈ ሰው ለርሱ አሳማሚ ቅጣት አለው፡፡
179وَلَكُمْ فِي الْقِصَاصِ حَيَاةٌ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ
ለእናንተም ባለ አእምሮዎች ሆይ! በማመሳሰል (ሕግ) ውስጥ ሕይወት አላችሁ፡፡ ትጠነቀቁ ዘንድ (ገዳይን መግደል ተደነገገላችሁ)፡፡
አል-በቀራቁርአን ማውጫ
286አንቀጽ
MedinanRevelation
177አንቀጽ

ትርጉም — አል-በቀራ 177

ሱረቱ አል-በቀራ አንቀጽ 177 - ማንበብ, ስሙ, ትርጉም, አማርኛ : መልካም ሥራ ፊቶቻችሁን ወደ ምሥራቅና ምዕራብ አቅጣጫ ማዞር አይደለም፡፡ ግን…

ሱረቱ አንቀጽ 177/286 — ሱረቱ አል-በቀራ البقرة (Medinan). ማንበብ ስሙ ትርጉም (አማርኛ). ስሙ: ሱረቱ አል-በቀራ ስሙ, ሱረቱ አል-በቀራ ትርጉም, ሱረቱ አል-በቀራ mp3, ሱረቱ አል-በቀራ pdf. አንቀጽ 175–179. በአማርኛ: العربية.





ቅዱስ ቁርኣን


Monday, October 19, 2026

Don't forget us in your sincere prayers