La sourate An-Naba en Amharique
عَمَّ يَتَسَاءَلُونَ(1) ከምን ነገር ይጠያየቃሉ? |
عَنِ النَّبَإِ الْعَظِيمِ(2) ከታላቁ ዜና (ከቁርኣን ይጠያየቃሉ)፡፡ |
الَّذِي هُمْ فِيهِ مُخْتَلِفُونَ(3) ከዚያ እነርሱ በእርሱ የተለያዩበት ከኾነው፡፡ |
كَلَّا سَيَعْلَمُونَ(4) ይከልከሉ፤ ወደፊት (የሚደርስበቸውን) በእርግጥ ያውቃሉ፡፡ |
ثُمَّ كَلَّا سَيَعْلَمُونَ(5) ከዚያም ይከልከሉ፤ ወደፊት ያውቃሉ፡፡ |
أَلَمْ نَجْعَلِ الْأَرْضَ مِهَادًا(6) ምድርን ምንጣፍ አላደረግንምን? |
وَالْجِبَالَ أَوْتَادًا(7) ጋራዎችንም ችካሎች አላደረግንምን? |
وَخَلَقْنَاكُمْ أَزْوَاجًا(8) ብዙ ዓይነቶችም አድርገን ፈጠርናችሁ፡፡ |
وَجَعَلْنَا نَوْمَكُمْ سُبَاتًا(9) እንቅልፋችሁንም ዕረፍት አደረግን፡፡ |
وَجَعَلْنَا اللَّيْلَ لِبَاسًا(10) ሌሊቱንም ልባስ አደረግን፡፡ |
وَجَعَلْنَا النَّهَارَ مَعَاشًا(11) ቀኑንም (ለኑሮ) መስሪያ አደረግን፡፡ |
وَبَنَيْنَا فَوْقَكُمْ سَبْعًا شِدَادًا(12) ከበላያችሁም ሰባትን ብርቱዎች (ሰማያት) ገነባን፡፡ |
وَجَعَلْنَا سِرَاجًا وَهَّاجًا(13) አንጸባራቂ ብርሃንንም አደረግን፡፡ |
وَأَنزَلْنَا مِنَ الْمُعْصِرَاتِ مَاءً ثَجَّاجًا(14) ከአረገዙት ደመናዎችም ተንቧቢ ውሃን አወረድን፡፡ |
لِّنُخْرِجَ بِهِ حَبًّا وَنَبَاتًا(15) በእርሱ እኽልንና ቅጠላ ቅጠልን እናወጣ ዘንድ (አወረድን)፡፡ |
وَجَنَّاتٍ أَلْفَافًا(16) የተቆላለፉ አትክልቶችንም፡፡ |
إِنَّ يَوْمَ الْفَصْلِ كَانَ مِيقَاتًا(17) የመለያው ቀን የተወሰነ ጊዜ ነው፡፡ |
يَوْمَ يُنفَخُ فِي الصُّورِ فَتَأْتُونَ أَفْوَاجًا(18) በቀንዱ በሚነፋና የተለያዩ ጭፍሮች ኾናችሁ በምትመጡ ቀን ነው፡፡ |
وَفُتِحَتِ السَّمَاءُ فَكَانَتْ أَبْوَابًا(19) ሰማይም በምትከፈትና (ባለ) ደጃፎችም በምትኾንበት፡፡ |
وَسُيِّرَتِ الْجِبَالُ فَكَانَتْ سَرَابًا(20) ጋራዎችም በሚነዱበት (እንደ) ሲሪብዱም በሚኾኑበት (ቀን) ነው፡፡ |
إِنَّ جَهَنَّمَ كَانَتْ مِرْصَادًا(21) ገሀነም መጠባበቂያ (ስፍራ) ናት፡፡ |
لِّلطَّاغِينَ مَآبًا(22) ለሕግ ተላላፊዎች መመለሻ ስትኾን፡፡ |
لَّابِثِينَ فِيهَا أَحْقَابًا(23) በውስጧ ብዙን ዘመናት ነዋሪዎች ሲኾኑ፤ |
لَّا يَذُوقُونَ فِيهَا بَرْدًا وَلَا شَرَابًا(24) በውስጧ ቅዝቃዜንም መጠጥንም አይቀምሱም፡፡ |
إِلَّا حَمِيمًا وَغَسَّاقًا(25) ግን ሙቅ ውሃንና እዥን (ይቀምሳሉ)፡፡ |
جَزَاءً وِفَاقًا(26) ተስማሚን ምንዳ ይምመነዳሉ፡፡ |
إِنَّهُمْ كَانُوا لَا يَرْجُونَ حِسَابًا(27) እነርሱ ምርመራን የማይፈሩ ነበሩና፡፡ |
وَكَذَّبُوا بِآيَاتِنَا كِذَّابًا(28) በአንቀጾቻችንም ማስተባበልን አስተባበሉና፡፡ |
وَكُلَّ شَيْءٍ أَحْصَيْنَاهُ كِتَابًا(29) ነገሩንም ሁሉ የተጻፈ ሲኾን አጠቃለልነው፡፡ |
فَذُوقُوا فَلَن نَّزِيدَكُمْ إِلَّا عَذَابًا(30) ቅመሱም ቅጣትንም እንጅ (ሌላን) አንጨምራችሁም (ይባላሉ)፡፡ |
إِنَّ لِلْمُتَّقِينَ مَفَازًا(31) ለጥንቁቆቹ መዳኛ ስፍራ አልላቸው፡፡ |
حَدَائِقَ وَأَعْنَابًا(32) አትክልቶችና ወይኖችም፡፡ |
وَكَوَاعِبَ أَتْرَابًا(33) እኩያዎች የኾኑ ጡተ ጉቻማዎችም፡፡ |
وَكَأْسًا دِهَاقًا(34) የተሞሉ ብርጭቆዎችም፡፡ |
لَّا يَسْمَعُونَ فِيهَا لَغْوًا وَلَا كِذَّابًا(35) በውስጧ ትርፍ ቃልንም ማስዋሸትንም አይሰሙም፡፡ |
جَزَاءً مِّن رَّبِّكَ عَطَاءً حِسَابًا(36) ከጌታህ የኾነን ምንዳ በቂ ስጦታን (ተሰጡ)፡፡ |
رَّبِّ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا الرَّحْمَٰنِ ۖ لَا يَمْلِكُونَ مِنْهُ خِطَابًا(37) የሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ያለው ሁሉ ጌታ በጣም አዛኝ ከኾነው (ተመነዱ)፡፡ ከእርሱ ጋር መነጋገርን አይችሉም፡፡ |
يَوْمَ يَقُومُ الرُّوحُ وَالْمَلَائِكَةُ صَفًّا ۖ لَّا يَتَكَلَّمُونَ إِلَّا مَنْ أَذِنَ لَهُ الرَّحْمَٰنُ وَقَالَ صَوَابًا(38) መንፈሱ (ጂብሪል) መላእክቶቹም የተሰለፉ ኾነው በሚቆሙ ቀን አል-ረሕማን ለእርሱ የፈቀደለትና ትክክለኛን ቃል ያለ ሰው ቢኾን እንጅ (መነጋገርን አይችሉም)፡፡ |
ذَٰلِكَ الْيَوْمُ الْحَقُّ ۖ فَمَن شَاءَ اتَّخَذَ إِلَىٰ رَبِّهِ مَآبًا(39) ይህ የተረጋገጠው ቀን ነው፡፡ የሻም ሰው ወደ ጌታው መመለስን ይይዛል፡፡ |
إِنَّا أَنذَرْنَاكُمْ عَذَابًا قَرِيبًا يَوْمَ يَنظُرُ الْمَرْءُ مَا قَدَّمَتْ يَدَاهُ وَيَقُولُ الْكَافِرُ يَا لَيْتَنِي كُنتُ تُرَابًا(40) እኛ ሰው ሁሉ እጆቹ ያስቀደሙትን በሚያይበትና ከሓዲውም ዋ ምኞቴ! ምንነው ዐፈር በኾንኩ በሚልበት ቀን ቅርብ የኾነን ቅጣት አስጠነቀቅናችሁ፡፡ |
Plus de sourates en Amharique :
Téléchargez la sourate avec la voix des récitants du Coran les plus célèbres :
Téléchargez le fichier mp3 de la sourate An-Naba : choisissez le récitateur pour écouter et télécharger la sourate An-Naba complète en haute qualité.















Donnez-nous une invitation valide