ሱረቱ አል-በይይና
PDF —
8 አንቀጽ Medinan PDF
Built right in your browser — download starts automatically

ሱረቱ አል-በይይና pdf — አውርድ (አማርኛ)

ሱረቱ አል-በይይና pdf አማርኛ — አውርድ ሱረቱ አል-በይይና ትርጉም. አል-በይይና (Medinan) 8 አንቀጽ.



ሱረቱ አል-በይይና
8 አንቀጽ · Medinan · አማርኛ
bismillah
ﮗﮘﮙﮚﮛﮜﮝﮞﮟﮠﮡﮢﮣ
እነዚያ ከመጽሐፉ ባለቤቶች ከአጋሪዎቹም የካዱት ግልጹ አስረጅ እስከ መጣላቸው ድረስ (ከነበሩበት ላይ) ተወጋጆች አልነበሩም፡፡
ﮤﮥﮦﮧﮨﮩﮪ
(አስረጁም) ከአላህ የኾነ መልክተኛ የተጥራሩን መጽሐፎች የሚያነብ ነው፡፡
ﮫﮬﮭﮮ
በውስጧ ቀጥተኛ የኾኑ ጽሑፎች ያሉባት የኾነችን፡፡
ﮯﮰﮱﯓﯔﯕﯖﯗﯘﯙﯚﯛ
እነዚያም መጽሐፉን የተሰጡት ሰዎች ግልጽ አስረጅ ከመጣላቸው በኋላ እንጅ አልተለያዩም፡፡
ﯜﯝﯞﯟﯠﯡﯢﯣﯤﯥﯦﯧﯨﯩﯪﯫﯬﯭ
አላህን ሃይማኖትን ለእርሱ ብቻ አጥሪዎች፣ ቀጥተኞች ኾነው ሊግገዙት፣ ሶላትንም አስተካክለው ሊሰግዱ ዘካንም ሊሰጡ እንጅ ያልታዘዙ ሲኾኑ (ተለያዩ)፡፡ ይህም የቀጥተኛይቱ (ሃይማኖት) ድንጋጌ ነው፡፡
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖﭗﭘﭙﭚﭛﭜﭝﭞﭟﭠﭡﭢ
እነዚያ ከመጽሐፉ ሰዎች የካዱት፣ አጋሪዎቹም በገሀነም እሳት ውስጥ ናቸው፤ በውስጧ ዘውታሪዎች ሲኾኑ እነዚያ እነርሱ ከፍጥረት ሁሉ ክፉ ናቸው፡፡
ﭣﭤﭥﭦﭧﭨﭩﭪﭫﭬ
እነዚያ ያመኑትና መልካሞችንም የሠሩት፣ እነዚያ እነርሱ ከፍጥረት ሁሉ በላጭ ናቸው፡፡
ﭭﭮﭯﭰﭱﭲﭳﭴﭵﭶﭷﭸﭹﭺﭻﭼﭽﭾﭿﮀﮁﮂﮃﮄ
በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው የመኖሪያ ገነቶች ነው፡፡ በውስጣቸው ዘለዓለም ዘውታሪዎች ሲኾኑ (ይገቡባቸወል)፡፡ አላህ ከእነርሱ ወደደ፡፡ ከእርሱም ወደዱ፡፡ ይህ ጌታውን ለፈራ ሰው ነው፡፡

ቅዱስ ቁርኣን


Tuesday, August 18, 2026

Don't forget us in your sincere prayers