La sourate An-Naziat en Amharique
وَالنَّازِعَاتِ غَرْقًا(1) በኃይል አውጪዎች በኾኑት፤ |
وَالنَّاشِطَاتِ نَشْطًا(2) በቀስታ መምዘዝንም መዘዦች በኾኑት፤ |
وَالسَّابِحَاتِ سَبْحًا(3) መዋኘትም ዋኚዎች በኾኑት፤ |
فَالسَّابِقَاتِ سَبْقًا(4) መቅደምንም ቀዳሚዎች በኾኑት፤ |
فَالْمُدَبِّرَاتِ أَمْرًا(5) ነገርንም አስተናባሪዎች በኾኑት (መላእክት) እምላለሁ፡፡ (በእርግጥ ትቀሰቀሳላችሁ)፡፡ |
يَوْمَ تَرْجُفُ الرَّاجِفَةُ(6) ተርገፍጋፊይቱ (ምድር) በምትርገፈገፍበት ቀን፤ |
تَتْبَعُهَا الرَّادِفَةُ(7) ለጣቂይቱ የምትከተላት ስትኾን (ትቀሰቀሳላችሁ)፡፡ |
قُلُوبٌ يَوْمَئِذٍ وَاجِفَةٌ(8) በዚያ ቀን ልቦች ተሸባሪዎች ናቸው፡፡ |
أَبْصَارُهَا خَاشِعَةٌ(9) ዓይኖቻቸው ተዋራጆች (አቀርቃሪዎች) ናቸው፡፡ |
يَقُولُونَ أَإِنَّا لَمَرْدُودُونَ فِي الْحَافِرَةِ(10) «እኛ ወደ መጀመሪያይቱ ኹነታ ተመላሾች ነን?» ይላሉ፡፡ |
أَإِذَا كُنَّا عِظَامًا نَّخِرَةً(11) «የበሰበሱ አጥንቶች በኾን ጊዜ (እንቀሰቀሳለን?)» |
قَالُوا تِلْكَ إِذًا كَرَّةٌ خَاسِرَةٌ(12) «ይህቺ ያን ጊዜ ባለ ከሳራ መመለስ ናት» ይላሉ፡፡ |
فَإِنَّمَا هِيَ زَجْرَةٌ وَاحِدَةٌ(13) እርሷም አንዲት ጩኸት ብቻ ናት፡፡ |
فَإِذَا هُم بِالسَّاهِرَةِ(14) ወዲያውኑም እነርሱ እንቅልፍ በሌለባት (ምድር) ላይ ይኾናሉ፡፡ |
هَلْ أَتَاكَ حَدِيثُ مُوسَىٰ(15) የሙሳ ወሬ መጣልህን? |
إِذْ نَادَاهُ رَبُّهُ بِالْوَادِ الْمُقَدَّسِ طُوًى(16) ጌታው በተቀደሰው ሸለቆ በጡዋ በጠራው ጊዜ፤ |
اذْهَبْ إِلَىٰ فِرْعَوْنَ إِنَّهُ طَغَىٰ(17) ወደ ፈርዖን ኺድ፡፡ እርሱ ወሰን አልፏልና፡፡ |
فَقُلْ هَل لَّكَ إِلَىٰ أَن تَزَكَّىٰ(18) በለውም፡- «ወደ መጥራራትህ ላንተ (መንገድ) አለህን?» |
وَأَهْدِيَكَ إِلَىٰ رَبِّكَ فَتَخْشَىٰ(19) «ወደ ጌታህም ልመራህ ትፈራውም ዘንድ፤ (መንገድ አለህን?)» አለው፡፡ |
فَأَرَاهُ الْآيَةَ الْكُبْرَىٰ(20) ታላቂቱንም ተዓምር አሳየው፡፡ |
فَكَذَّبَ وَعَصَىٰ(21) አስተባበለም፤ አመጸም፡፡ |
ثُمَّ أَدْبَرَ يَسْعَىٰ(22) ከዚያም (ለማጥፋት) የሚተጋ ኾኖ ዞረ፡፡ |
فَحَشَرَ فَنَادَىٰ(23) (ሰራዊቶቹን) ሰበሰበም፤ ተጣራም፡፡ |
فَقَالَ أَنَا رَبُّكُمُ الْأَعْلَىٰ(24) አለም፡- «እኔ ታላቁ ጌታችሁ ነኝ፡፡» |
فَأَخَذَهُ اللَّهُ نَكَالَ الْآخِرَةِ وَالْأُولَىٰ(25) አላህም በኋለኛይቱና በፊተኛይቱ (ቃል) ቅጣት ያዘው፡፡ |
إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَعِبْرَةً لِّمَن يَخْشَىٰ(26) በዚህ ውስጥ ለሚፈራ ሰው በእርግጥ መገምገሚያ አለበት፡፡ |
أَأَنتُمْ أَشَدُّ خَلْقًا أَمِ السَّمَاءُ ۚ بَنَاهَا(27) ባፈጣጠር እናንተ ይበልጥ የበረታችሁ ናችሁን? ወይንስ ሰማይ? (አላህ) ገነባት፡፡ |
رَفَعَ سَمْكَهَا فَسَوَّاهَا(28) ከፍታዋን አጓነ፤ አስተካከላትም፡፡ |
وَأَغْطَشَ لَيْلَهَا وَأَخْرَجَ ضُحَاهَا(29) ሌሊቷንም አጨለመ፡፡ ቀንዋንም ገለጸ፡፡ |
وَالْأَرْضَ بَعْدَ ذَٰلِكَ دَحَاهَا(30) ምድርንም ከዚህ በኋላ ዘረጋት፡፡ |
أَخْرَجَ مِنْهَا مَاءَهَا وَمَرْعَاهَا(31) ውሃዋንና ግጦሿን ከእርሷ አወጣ፡፡ |
وَالْجِبَالَ أَرْسَاهَا(32) ጋራዎችንም አደላደላቸው፡፡ |
مَتَاعًا لَّكُمْ وَلِأَنْعَامِكُمْ(33) ለእናንተና ለእንስሶቻችሁ መጣቀሚያ ይኾን ዘንድ (ይህን አደረገ)፡፡ |
فَإِذَا جَاءَتِ الطَّامَّةُ الْكُبْرَىٰ(34) ታላቂቱም መዐት በመጣች ጊዜ፣ |
يَوْمَ يَتَذَكَّرُ الْإِنسَانُ مَا سَعَىٰ(35) ሰው ሁሉ የሠራውን በሚያስታውስበት ቀን፣ |
وَبُرِّزَتِ الْجَحِيمُ لِمَن يَرَىٰ(36) ገሀነምም ለሚያይ ሰው በተገለጠች ጊዜ፣ |
فَأَمَّا مَن طَغَىٰ(37) የካደ ሰውማ፣ |
وَآثَرَ الْحَيَاةَ الدُّنْيَا(38) ቅርቢቱንም ሕይወት የመረጠ፣ |
فَإِنَّ الْجَحِيمَ هِيَ الْمَأْوَىٰ(39) ገሀነም እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት፡፡ |
وَأَمَّا مَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِ وَنَهَى النَّفْسَ عَنِ الْهَوَىٰ(40) በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ |
فَإِنَّ الْجَنَّةَ هِيَ الْمَأْوَىٰ(41) ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት፡፡ |
يَسْأَلُونَكَ عَنِ السَّاعَةِ أَيَّانَ مُرْسَاهَا(42) «ከሰዓቲቱ መቼ ነው መኾኛዋ?» ሲሉ ይጠይቁሃል፡፡ |
فِيمَ أَنتَ مِن ذِكْرَاهَا(43) አንተ እርሷን ከማስታወስ በምን ውስጥ ነህ? |
إِلَىٰ رَبِّكَ مُنتَهَاهَا(44) (የዕውቀት) መጨረሻዋ ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡ |
إِنَّمَا أَنتَ مُنذِرُ مَن يَخْشَاهَا(45) አንተ የሚፈራትን ሰው አስፈራሪ ብቻ ነህ፡፡ |
كَأَنَّهُمْ يَوْمَ يَرَوْنَهَا لَمْ يَلْبَثُوا إِلَّا عَشِيَّةً أَوْ ضُحَاهَا(46) እነርሱ በሚያዩዋት ቀን ያንዲት ቀን ምሽትን ወይም ረፏዷን እንጅ ያልቆዩ ይመስላሉ፡፡ |
Plus de sourates en Amharique :
Téléchargez la sourate avec la voix des récitants du Coran les plus célèbres :
Téléchargez le fichier mp3 de la sourate An-Naziat : choisissez le récitateur pour écouter et télécharger la sourate An-Naziat complète en haute qualité.















Donnez-nous une invitation valide