La sourate Abasa en Amharique
عَبَسَ وَتَوَلَّىٰ(1) ፊቱን አጨፈገገ፤ ዞረም፡፡ |
أَن جَاءَهُ الْأَعْمَىٰ(2) ዕውሩ ስለ መጣው፡፡ |
وَمَا يُدْرِيكَ لَعَلَّهُ يَزَّكَّىٰ(3) ምን ያሳውቅሃል? (ከኀጢአቶቹ) ሊጥራራ ይከጀላል፡፡ |
أَوْ يَذَّكَّرُ فَتَنفَعَهُ الذِّكْرَىٰ(4) ወይም ሊገሠጽ ግሠጼይቱም ልትጠቅመው (ይከጀላል)፡፡ |
أَمَّا مَنِ اسْتَغْنَىٰ(5) የተብቃቃው ሰውማ፤ |
فَأَنتَ لَهُ تَصَدَّىٰ(6) አንተ ለእርሱ (ለእምነቱ በመጓጓት) በፈገግታ ትቀበለዋለህ፡፡ |
وَمَا عَلَيْكَ أَلَّا يَزَّكَّىٰ(7) ባይጥራራ (ባያምን) ባንተ ላይ ምንም የሌለብህ ስትኾን፡፡ |
وَأَمَّا مَن جَاءَكَ يَسْعَىٰ(8) እየገሰገሰ የመጣህ ሰውማ፤ |
وَهُوَ يَخْشَىٰ(9) እርሱ (አላህን) የሚፈራ ሲኾን፤ |
فَأَنتَ عَنْهُ تَلَهَّىٰ(10) አንተ ከእርሱ ትዝዘናጋለህ፡፡ |
كَلَّا إِنَّهَا تَذْكِرَةٌ(11) ተከልከል፡፡ እርሷ ማስገንዘቢያ ናት፡፡ |
فَمَن شَاءَ ذَكَرَهُ(12) የሻም ሰው (ቁርኣኑን) ያስታውሰዋል፡፡ |
فِي صُحُفٍ مُّكَرَّمَةٍ(13) በተከበሩ ጽሑፎች ውስጥ ነው፡፡ |
مَّرْفُوعَةٍ مُّطَهَّرَةٍ(14) ከፍ በተደረገች ንጹሕ በተደረገች (ጽሑፍ ውስጥ ነው)፡፡ |
بِأَيْدِي سَفَرَةٍ(15) በጸሐፊዎቹ (መላእክት) እጆች (ንጹሕ የተደረገች)፡፡ |
كِرَامٍ بَرَرَةٍ(16) የተከበሩና ታዛዦች በኾኑት (ጸሐፊዎች እጆች)፡፡ |
قُتِلَ الْإِنسَانُ مَا أَكْفَرَهُ(17) ሰው ተረገመ፤ ምን ከሓዲ አደረገው? |
مِنْ أَيِّ شَيْءٍ خَلَقَهُ(18) (ጌታው) በምን ነገር ፈጠረው? (አያስብምን?) |
مِن نُّطْفَةٍ خَلَقَهُ فَقَدَّرَهُ(19) ከፍትወት ጠብታ ፈጠረው፤ መጠነውም፡፡ |
ثُمَّ السَّبِيلَ يَسَّرَهُ(20) ከዚያም (መውጫ) መንገዱን አገራው፡፡ |
ثُمَّ أَمَاتَهُ فَأَقْبَرَهُ(21) ከዚያም ገደለው፤ እንዲቀበርም አደረገው፡፡ |
ثُمَّ إِذَا شَاءَ أَنشَرَهُ(22) ከዚያም (ማንሳቱን) በሻ ጊዜ ያስነሳዋል፡፡ |
كَلَّا لَمَّا يَقْضِ مَا أَمَرَهُ(23) በእውነት ያንን (ጌታው) ያዘዘውን ገና አልፈጸመም፡፡ |
فَلْيَنظُرِ الْإِنسَانُ إِلَىٰ طَعَامِهِ(24) ሰውም ወደ ምግቡ ይመልከት፡፡ |
أَنَّا صَبَبْنَا الْمَاءَ صَبًّا(25) እኛ ውሃን ማንቧቧትን ያንቧቧን መኾናችንን፡፡ |
ثُمَّ شَقَقْنَا الْأَرْضَ شَقًّا(26) ከዚያም ምድርን (በደካማ ቡቃያ) መሰንጠቅን የሰነጠቅን፤ |
فَأَنبَتْنَا فِيهَا حَبًّا(27) በውስጧም እኽልን ያበቀልን፤ |
وَعِنَبًا وَقَضْبًا(28) ወይንንም፤ እርጥብ ያበቀልን፤ |
وَزَيْتُونًا وَنَخْلًا(29) የዘይት ወይራንም ዘንባባንም፤ |
وَحَدَائِقَ غُلْبًا(30) ጭፍቆች አትክልቶችንም፤ |
وَفَاكِهَةً وَأَبًّا(31) ፍራፍሬንም ገለባንም፤ (ያበቀልን መኾናችንን ይመልከት)፡፡ |
مَّتَاعًا لَّكُمْ وَلِأَنْعَامِكُمْ(32) ለእናንተም ለእንስሶቻችሁም መጠቀሚያ ይኾን ዘንድ (ይህን ሠራን)፡፡ |
فَإِذَا جَاءَتِ الصَّاخَّةُ(33) አደንቋሪይቱም (መከራ) በመጣች ጊዜ፤ |
يَوْمَ يَفِرُّ الْمَرْءُ مِنْ أَخِيهِ(34) ሰው ከወንድሙ በሚሸሽበት ቀን፤ |
وَأُمِّهِ وَأَبِيهِ(35) ከናቱም ካባቱም፤ |
وَصَاحِبَتِهِ وَبَنِيهِ(36) ከሚስቱም ከልጁም፤ |
لِكُلِّ امْرِئٍ مِّنْهُمْ يَوْمَئِذٍ شَأْنٌ يُغْنِيهِ(37) ከእነርሱ ለየሰው ሁሉ በዚያ ቀን (ከሌላው) የሚያብቃቃው ኹነታ አልለው፡፡ |
وُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ مُّسْفِرَةٌ(38) ፊቶች በዚያ ቀን አብሪዎች ናቸው፤ |
ضَاحِكَةٌ مُّسْتَبْشِرَةٌ(39) ሳቂዎችም ተደሳቾችም ናቸው፡፡ |
وَوُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ عَلَيْهَا غَبَرَةٌ(40) ፊቶችም በዚያ ቀን በላያቸው ላይ ትቢያ አልለባቸው፤ |
تَرْهَقُهَا قَتَرَةٌ(41) ጥቁረት ትሸፍናቸዋለች፤ |
أُولَٰئِكَ هُمُ الْكَفَرَةُ الْفَجَرَةُ(42) እነዚያ እነሱ ከሓዲዎቹ አመጸኞቹ ናቸው፡፡ |
Plus de sourates en Amharique :
Téléchargez la sourate avec la voix des récitants du Coran les plus célèbres :
Téléchargez le fichier mp3 de la sourate Abasa : choisissez le récitateur pour écouter et télécharger la sourate Abasa complète en haute qualité.















Donnez-nous une invitation valide