ሱረቱ አት-ተካሱር pdf — አውርድ (አማርኛ)
ሱረቱ አት-ተካሱር pdf አማርኛ — አውርድ ሱረቱ አት-ተካሱር ትርጉም. ሱረቱ አት-ተካሱር (Meccan) 8 አንቀጽ.
Related
More ሱረቱ PDF
ሱረቱ አት-ተካሱር

ﮣﮤﮥ
102:1
በብዛት መፎካከር (ጌታችሁን ከመገዛት) አዘነጋችሁ፡፡
ﮦﮧﮨﮩ
102:2
መቃብሮችን እስከ ጎበኛችሁ ድረስ፡፡
ﮪﮫﮬﮭ
102:3
ተከልከሉ፤ ወደፊት (ውጤቱን) ታውቃላችሁ፡፡
ﮮﮯﮰﮱﯓ
102:4
ከዚያም ተከልከሉ፤ ወደ ፊት ታውቃላችሁ፡፡
ﯔﯕﯖﯗﯘﯙ
102:5
በእውነቱ (የሚጠብቃችሁን) እርግጠኛ ዕውቀትን ብታውቁ ኖሮ፤ (ባልዘናጋችሁ ነበር)፡፡
ﯚﯛﯜ
102:6
ገሀነምን በእርግጥ ታያላችሁ፡፡
ﯝﯞﯟﯠﯡ
102:7
ከዚያም እርግጠኛን ማየት ታዩዋታላችሁ፡፡
ﯢﯣﯤﯥﯦﯧ
102:8
ከዚያም ከድሎታችሁ ሁሉ በዚያ ቀን ትጠየቃላችሁ፡፡
ቅዱስ ቁርኣን
Wednesday, September 9, 2026
Don't forget us in your sincere prayers







