PDF —
11 አንቀጽ Meccan PDF
Built right in your browser — download starts automatically

ሱረቱ አል-ቃሪዐ pdf — አውርድ (አማርኛ)

ሱረቱ አል-ቃሪዐ pdf አማርኛ — አውርድ ሱረቱ አል-ቃሪዐ ትርጉም. ሱረቱ አል-ቃሪዐ (Meccan) 11 አንቀጽ.



11 አንቀጽ · Meccan · አማርኛ
bismillah
ﭴﭵ
101:1 ቆርቋሪይቱ (ጩኸት)፤
ﭶﭷﭸ
101:2 ምን አስደናቂ ቆርቋሪ ናት!
ﭹﭺﭻﭼﭽ
101:3 ቆርቋሪይቱም ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ?
ﭾﭿﮀﮁﮂﮃ
101:4 ሰዎች እንደ ተበታተነ ቢራቢሮ (ወይም ኩብኩባ) በሚኾኑበት ቀን፤
ﮄﮅﮆﮇﮈ
101:5 ጋራዎችም እንደ ተነደፈ ሱፍ በሚኾኑበት (ቀን ልቦችን በድንጋጤ ትቆረቁራለች፡፡)
ﮉﮊﮋﮌﮍ
101:6 ሚዛኖቹ የከበዱለት ሰውማ፤
ﮎﮏﮐﮑﮒ
101:7 እርሱ በምትወደድ ኑሮ ውስጥ ይኾናል፡፡
ﮓﮔﮕﮖﮗ
101:8 ሚዛኖቹም የቀለሉበት ሰውማ፤
ﮘﮙﮚ
101:9 መኖሪያው ሃዊያህ ናት
ﮛﮜﮝﮞﮟ
101:10 እርሷም ምን እንደ ኾነች ምን አሳወቀህ?
ﮠﮡﮢ
101:11 (እርሷ) በጣም ተኳሳ እሳት ናት፡፡

ቅዱስ ቁርኣን


Wednesday, September 9, 2026

Don't forget us in your sincere prayers