PDF —
31 አንቀጽ Medinan PDF
Built right in your browser — download starts automatically

ሱረቱ አል-ኢንሳን pdf — አውርድ (አማርኛ)

ሱረቱ አል-ኢንሳን pdf አማርኛ — አውርድ ሱረቱ አል-ኢንሳን ትርጉም. ሱረቱ አል-ኢንሳን (Medinan) 31 አንቀጽ.

← አል-ቂያማሱረቱ አል-ኢንሳን አል-ሙርሳላት →


31 አንቀጽ · Medinan · አማርኛ
bismillah
ﯜﯝﯞﯟﯠﯡﯢﯣﯤﯥﯦﯧ
76:1 በሰው ላይ የሚታወስ ነገር ሳይኾን ከዘመናት የተወሰነ ጊዜ በእርግጥ አልፎበታል፡፡
ﯨﯩﯪﯫﯬﯭﯮﯯﯰﯱﯲ
76:2 እኛ ሰውን (በሕግ ግዳጅ) የምንሞከረው ስንኾን ቅልቅሎች ከኾኑ የፍትወት ጠብታ ፈጠርነው፡፡ ሰሚ ተመልካችም አደረግነው፡፡
ﯳﯴﯵﯶﯷﯸﯹﯺ
76:3 እኛ ወይ አመስጋኝ ወይም ከሓዲ ሲኾን መንገዱን መራነው፤ (ገለጽንለት)፡፡
ﯻﯼﯽﯾﯿﰀﰁ
76:4 እኛ ለከሓዲዎች ሰንሰሎቶችንና እንዛዝላዎችን፣ እሳትንም አዘጋጅተናል፡፡
ﰂﰃﰄﰅﰆﰇﰈﰉﰊ
76:5 በጎ አድራጊዎች መበረዣዋ ካፉር ከኾነች ጠጅ ይጠጣሉ፡፡
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖﭗﭘ
76:6 ከእርሷ የአላህ ባሮች የሚጠጡላት (ወደፈለጉበት) ማንቧቧትን የሚያንቧቧት ከኾነች ምንጭ (ይጠጣሉ)፡፡
ﭙﭚﭛﭜﭝﭞﭟﭠ
76:7 (ዛሬ) በስለታቸው ይሞላሉ፡፡ መከራው ተሰራጪ የኾነንም ቀን ይፈራሉ፡፡
ﭡﭢﭣﭤﭥﭦﭧﭨ
76:8 ምግብንም ከመውደዳቸው ጋር ለድኻ፣ ለየቲምም፣ ለምርኮኛም ለእስረኛም ያበላሉ፡፡
ﭩﭪﭫﭬﭭﭮﭯﭰﭱﭲﭳ
76:9 «የምናበላችሁ ለአላህ ውዴታ ብቻ ነው፡፡ ከእናንተ ዋጋንም ማመስገንንም አንፈልግም፡፡
ﭴﭵﭶﭷﭸﭹﭺﭻ
76:10 «እኛ (ፊትን) የሚያጨፈግግን ብርቱ ቀን ከጌታችን እንፈራለንና፤» (ይላሉ)፡፡
ﭼﭽﭾﭿﮀﮁﮂﮃﮄ
76:11 አላህም የዚያን ቀን ክፋት ጠበቃቸው፡፡ (ፊታቸው) ማማርንና መደሰትንም ገጠማቸው፡፡
ﮅﮆﮇﮈﮉﮊ
76:12 በመታገሣቸውም ገነትንና የሐር ልብስን መነዳቸው፡፡
ﮋﮌﮍﮎﮏﮐﮑﮒﮓﮔﮕﮖ
76:13 በውስጧ በባለ አጎበር አልጋዎች ላይ ተደጋፊዎች በውስጧ ፀሐይንም ጨረቃንም የማያዩ ሲኾኑ፡፡
ﮗﮘﮙﮚﮛﮜﮝ
76:14 ዛፎችዋም በእነርሱ ላይ የቀረበች፣ ፍሬዎችዋም (ለለቃሚዎች) መግገራትን የተገራች ስትኾን (ገነትን መነዳቸው)፡፡
ﮞﮟﮠﮡﮢﮣﮤﮥﮦ
76:15 በእነርሱም ላይ ከብር በኾኑ ዕቃዎች (ሰሐኖች) የብርጭቆዎች በኾኑ ኩባያዎችም ይዝዞርባቸዋል፡፡
ﮧﮨﮩﮪﮫﮬ
76:16 መለካትን የለኳቸው በኾኑ የብር ብርጭቆዎች (ይዝዞርባቸዋል)፡፡
ﮭﮮﮯﮰﮱﯓﯔ
76:17 በእርሷም መበረዣዋ ዘንጀቢል የኾነችን ጠጅ ይጠጣሉ፡፡
ﯕﯖﯗﯘﯙ
76:18 በውስጧ ያለችውን ሰልሰቢል ተብላ የምትጠራውን ምንጭ፡፡
ﯚﯛﯜﯝﯞﯟﯠﯡﯢﯣﯤ
76:19 በእነርሱም ላይ (ባሉበት ኹነታ) የሚዘወትሩ ወጣት ልጆች ይዘዋወራሉ፡፡ ባየሃቸው ጊዜ የተበተነ ሉል ናቸው ብለህ ታስባቸዋለህ፡፡
ﯥﯦﯧﯨﯩﯪﯫﯬ
76:20 እዚያም በተመለከትክ ጊዜ ጸጋንና ታላቅ ንግሥናን ታያለህ፡፡
ﯭﯮﯯﯰﯱﯲﯳﯴﯵﯶﯷﯸﯹﯺﯻ
76:21 አረንጓዴዎች የኾኑ የቀጭን ሐር ልብሶችና ወፍራም ሐርም በላያቸው ላይ አልለ፡፡ ከብር የኾኑ አንባሮችንም ይሸለማሉ፡፡ ጌታቸውም አጥሪ የኾነን መጠጥ ያጠጣቸዋል፡፡
ﯼﯽﯾﯿﰀﰁﰂﰃﰄ
76:22 «ይህ በእርግጥ ለእናንተ ዋጋ ኾነ፡፡ ሥራችሁም ምስጉን ኾነ፤» (ይባላሉ)፡፡
ﰅﰆﰇﰈﰉﰊﰋ
76:23 እኛ ቁርኣንን ባንተ ላይ ማውረድን እኛው አወረድነው፡፡
ﰌﰍﰎﰏﰐﰑﰒﰓﰔﰕ
76:24 ለጌታህ ፍርድም ታገሥ፡፡ ከእነርሱም ኀጢአተኛን ወይም ከሓዲን አትታዘዝ፡፡
ﰖﰗﰘﰙﰚﰛ
76:25 የጌታህንም ስም በጧትና ከቀትር በላይ አውሳ፡፡
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖﭗﭘ
76:26 ከሌሊቱም ለእርሱ ስገድ፡፡ በረዢም ሌሊትም አወድሰው፡፡
ﭙﭚﭛﭜﭝﭞﭟﭠﭡ
76:27 እነዚያ ፈጣኒቱን ዓለም ይወዳሉ፡፡ ከባድን ቀንም በስተፊታቸው ኾኖ ይተዋሉ፡፡
ﭢﭣﭤﭥﭦﭧﭨﭩﭪﭫﭬ
76:28 እኛ ፈጠርናቸው፡፡ መለያልያቸውንም አጠነከርን፡፡ በሻንም ጊዜ መሰሎቻቸውን መለወጥን እንለውጣለን፡፡
ﭭﭮﭯﭰﭱﭲﭳﭴﭵﭶﭷ
76:29 ይህቺ መገሠጫ ናት፡፡ የሻም ሰው ወደ ጌታው መንገድን ይይዛል፡፡
ﭸﭹﭺﭻﭼﭽﭾﭿﮀﮁﮂﮃﮄ
76:30 አላህም ካልሻ በስተቀር አትሹም፡፡ አላህ ዐዋቂ ጥበበኛ ነውና፡፡
ﮅﮆﮇﮈﮉﮊﮋﮌﮍﮎﮏﮐ
76:31 የሚሻውን ሰው በእዝነቱ ውስጥ ያገባዋል፡፡ በዳዮቹንም (ዝቶባቸዋል)፡፡ ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣትን አዘጋጅቶላቸዋል፡፡

ቅዱስ ቁርኣን


Wednesday, September 9, 2026

Don't forget us in your sincere prayers