PDF —
40 አንቀጽ Meccan PDF
Built right in your browser — download starts automatically

ሱረቱ አል-ቂያማ pdf — አውርድ (አማርኛ)

ሱረቱ አል-ቂያማ pdf አማርኛ — አውርድ ሱረቱ አል-ቂያማ ትርጉም. ሱረቱ አል-ቂያማ (Meccan) 40 አንቀጽ.



40 አንቀጽ · Meccan · አማርኛ
bismillah
ﮊﮋﮌﮍﮎ
75:1 (ነገሩ ከሓዲዎች እንደሚሉት) አይደለም፡፡ በትንሣኤ ቀን እምላለሁ፡፡
ﮏﮐﮑﮒﮓ
75:2 (ራሷን) ወቃሽ በኾነች ነፍስም እምላለሁ፡፡ (በእርግጥ ትቀሰቀሳላችሁ)፡፡
ﮔﮕﮖﮗﮘﮙ
75:3 ሰው አጥንቶቹን አለመሰብሰባችንን ያስባልን?
ﮚﮛﮜﮝﮞﮟﮠ
75:4 አይደለም ጣቶቹን (ፊት እንደ ነበሩ) በማስተካከል ላይ ቻዮች ስንኾን (እንሰበስባቸዋለን)፡፡
ﮡﮢﮣﮤﮥﮦ
75:5 ይልቁንም ሰው በፊቱ ባለው ነገር (በትንሣኤ) ሊያስተባብል ይፈልጋል፡፡
ﮧﮨﮩﮪﮫ
75:6 «የትንሣኤው ቀን መቼ ነው?» ሲል ይጠይቃል፡፡
ﮬﮭﮮﮯ
75:7 ዓይንም በዋለለ ጊዜ፡፡
ﮰﮱﯓ
75:8 ጨረቃም በጨለመ ጊዜ፡፡
ﯔﯕﯖﯗ
75:9 ፀሐይና ጨረቃም በተሰበሰቡ ጊዜ፡፡
ﯘﯙﯚﯛﯜﯝ
75:10 «ሰው በዚያ ቀን መሸሻው የት ነው?» ይላል፡፡
ﯞﯟﯠﯡ
75:11 ይከልከል፤ ምንም መጠጊያ የለም፡፡
ﯢﯣﯤﯥﯦ
75:12 በዚያ ቀን መርጊያው ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡
ﯧﯨﯩﯪﯫﯬﯭ
75:13 ሰው በዚያ ቀን ባስቀደመውና ባስቆየው ሁሉ ይነገራል፡፡
ﯮﯯﯰﯱﯲﯳ
75:14 በእርግጥም ሰው በነፍሱ ላይ አስረጅ ነው፡፡ (አካሎቹ ይመሰክሩበታል)፡፡
ﯴﯵﯶﯷ
75:15 ምክንያቶቹን ሁሉ ቢያመጣም እንኳ (አይሰማም)፡፡
ﯸﯹﯺﯻﯼﯽﯾ
75:16 በእርሱ (በቁርኣን ንባብ) ልትቸኩል ምላስህን በእርሱ አታላውስ፡፡
ﯿﰀﰁﰂﰃ
75:17 (በልብህ ውስጥ) መሰብሰቡና ማንበቡ በእኛ ላይ ነውና፡፡
ﰄﰅﰆﰇﰈ
75:18 ባነበብነውም ጊዜ (ካለቀ በኋላ) ንባቡን ተከተል፡፡
ﰉﰊﰋﰌﰍ
75:19 ከዚያም ማብራራቱ በእኛ ላይ ነው፡፡
ﭑﭒﭓﭔﭕ
75:20 (ከመጣደፍ) ተከልከል፡፡ ይልቁንም (ሰዎች) ፈጣኒቱን (ዓለም) ትወዳላችሁ፡፡
ﭖﭗﭘ
75:21 መጨረሻይቱንም (ዓለም) ትተዋላችሁ፡፡ (አትዘጋጁላትም)፡፡
ﭙﭚﭛﭜ
75:22 ፊቶች በዚያ ቀን አብሪዎች ናቸው፡፡
ﭝﭞﭟﭠ
75:23 ወደ ጌታቸው ተመልካቾች ናቸው፡፡
ﭡﭢﭣﭤ
75:24 ፊቶችም በዚያ ቀን ጨፍጋጊዎች ናቸው፡፡
ﭥﭦﭧﭨﭩﭪ
75:25 በርሳቸውም ዐደጋ እንደሚሠራባቸው ያረጋግጣሉ፡፡
ﭫﭬﭭﭮﭯ
75:26 ንቁ (ነፍስ) ብሪዎችን በደረሰች ጊዜ፤
ﭰﭱﭲﭳﭴ
75:27 «አሻሪው ማነው?» በተባለም ጊዜ፡፡
ﭵﭶﭷﭸ
75:28 (ሕመምተኛው) እርሱ (የሰፈረበት ነገር ከዚህ ዓለም) መልለየት መኾኑን ባረጋገጠም ጊዜ፡፡
ﭹﭺﭻﭼ
75:29 ባትም በባት በተጣበቀች ጊዜ፡፡
ﭽﭾﭿﮀﮁ
75:30 በዚያ ቀን መነዳቱ ወደ ጌታህ (ፍርድ) ነው፡፡
ﮂﮃﮄﮅﮆ
75:31 አላመነምም አልሰገደምም፡፡
ﮇﮈﮉﮊ
75:32 ግን አስተባበለ፤ (ከእምነት) ዞረም፡፡
ﮋﮌﮍﮎﮏﮐ
75:33 ከዚያም እየተንጎባለለ ወደ ቤተሰቡ ኼደ፡፡
ﮑﮒﮓﮔ
75:34 የምትጠላውን ነገር (አላህ) ያስከትልህ፡፡ ለአንተ ተገቢህም ነው፡፡
ﮕﮖﮗﮘﮙ
75:35 ከዚያም ጥፋት ይጠጋህ ለአንተ የተገባህም ነው፡፡
ﮚﮛﮜﮝﮞﮟ
75:36 ሰው ስድ ኾኖ መትተውን ይጠረጥራልን?
ﮠﮡﮢﮣﮤﮥﮦ
75:37 የሚፈሰስ ከኾነ የፍትወት ጠብታ አልነበረምን?
ﮧﮨﮩﮪﮫﮬ
75:38 ከዚያም የረጋ ደም ኾነ (አላህ ሰው አድርጎ) ፈጠረውም፡፡ አስተካከለውም፡፡
ﮭﮮﮯﮰﮱﯓ
75:39 ከእርሱም ሁለት ዓይነቶችን ወንድና ሴትን አደረገ፡፡
ﯔﯕﯖﯗﯘﯙﯚﯛ
75:40 ይህ (ጌታ) ሙታንን ሕያው በማድረግ ላይ ቻይ አይደለምን?

ቅዱስ ቁርኣን


Wednesday, September 9, 2026

Don't forget us in your sincere prayers