La sourate Al-Mursalat en Amharique
وَالْمُرْسَلَاتِ عُرْفًا(1) ተከታታይ ኾነው በተላኩት፣ |
فَالْعَاصِفَاتِ عَصْفًا(2) በኀይል መንፈስን ነፋሾች በኾኑትም፣ |
وَالنَّاشِرَاتِ نَشْرًا(3) መበተንን በታኞች በኾኑትም፤ (ነፋሶች)፣ |
فَالْفَارِقَاتِ فَرْقًا(4) መለየትን ለይዎች በኾኑትም፣ |
فَالْمُلْقِيَاتِ ذِكْرًا(5) መገሠጫን (ወደ ነቢያት) ጣይዎች በኾኑትም፣ |
عُذْرًا أَوْ نُذْرًا(6) ምክንያትን ለማስወገድ ወይም ለማስፈራራት (ጣይዎች በኾኑት መላእክት) እምላለሁ፡፡ |
إِنَّمَا تُوعَدُونَ لَوَاقِعٌ(7) ያ የምትስፈራሩበት (ትንሣኤ) በእርግጥ ኋኝ ነው፡፡ |
فَإِذَا النُّجُومُ طُمِسَتْ(8) ከዋክብትም (ብርሃንዋ) በታበሰች ጊዜ፡፡ |
وَإِذَا السَّمَاءُ فُرِجَتْ(9) ሰማይም በተከፈተች ጊዜ፡፡ |
وَإِذَا الْجِبَالُ نُسِفَتْ(10) ጋራዎችም በተንኮተኮቱ ጊዜ፡፡ |
وَإِذَا الرُّسُلُ أُقِّتَتْ(11) መልክተኞቹም ወቅት በተደረገላቸው ጊዜ፡፡ |
لِأَيِّ يَوْمٍ أُجِّلَتْ(12) ለየትኛው ቀን ተቀጠሩ (የሚባል ሲኾን)፤ |
لِيَوْمِ الْفَصْلِ(13) ለመለያው ቀን (በተባለ ጊዜ፤ በፍጡሮች መካከል ይፈረዳል)፡፡ |
وَمَا أَدْرَاكَ مَا يَوْمُ الْفَصْلِ(14) የመለያውም ቀን ምን እንደኾነ ምን አሳወቀህ? |
وَيْلٌ يَوْمَئِذٍ لِّلْمُكَذِّبِينَ(15) ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡ |
أَلَمْ نُهْلِكِ الْأَوَّلِينَ(16) የፊተኞቹን (ሕዝቦች) አላጠፋንምን? |
ثُمَّ نُتْبِعُهُمُ الْآخِرِينَ(17) ከዚያም የኋለኞቹን እናስከትላቸዋለን፡፡ |
كَذَٰلِكَ نَفْعَلُ بِالْمُجْرِمِينَ(18) በአመጸኞች ሁሉ እንደዚሁ እንሠራለን፡፡ |
وَيْلٌ يَوْمَئِذٍ لِّلْمُكَذِّبِينَ(19) ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡ |
أَلَمْ نَخْلُقكُّم مِّن مَّاءٍ مَّهِينٍ(20) ከደካማ ውሃ አልፈጠርናችሁምን? |
فَجَعَلْنَاهُ فِي قَرَارٍ مَّكِينٍ(21) በተጠበቀ መርጊያ ውስጥም (በማሕፀን) አደረግነው፡፡ |
إِلَىٰ قَدَرٍ مَّعْلُومٍ(22) እስከ ታወቀ ልክ ድረስ፡፡ መጠንነውም፤ ምን ያማርንም |
فَقَدَرْنَا فَنِعْمَ الْقَادِرُونَ(23) መጣኞች ነን! |
وَيْلٌ يَوْمَئِذٍ لِّلْمُكَذِّبِينَ(24) ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡ |
أَلَمْ نَجْعَلِ الْأَرْضَ كِفَاتًا(25) ምድርን ሰብሳቢ አላደረግናትምን? |
أَحْيَاءً وَأَمْوَاتًا(26) ሕያዋን ኾናችሁ ሙታንም ኾናችሁ፡፡ |
وَجَعَلْنَا فِيهَا رَوَاسِيَ شَامِخَاتٍ وَأَسْقَيْنَاكُم مَّاءً فُرَاتًا(27) በውስጧም ከፍተኛዎችን ተራራዎች አደረግን፡፡ ጣፋጭ ውሃንም አጠጣናችሁ፡፡ |
وَيْلٌ يَوْمَئِذٍ لِّلْمُكَذِّبِينَ(28) ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡ |
انطَلِقُوا إِلَىٰ مَا كُنتُم بِهِ تُكَذِّبُونَ(29) «ወደዚያ በእርሱ ታስተባብሉ ወደ ነበራችሁት (ቅጣት) አዝግሙ፡፡ |
انطَلِقُوا إِلَىٰ ظِلٍّ ذِي ثَلَاثِ شُعَبٍ(30) «ባለ ሦስት ቅርንጫፎች ወደ ኾነው ጥላ አዝግሙ፤» (ይባላሉ)፡፡ |
لَّا ظَلِيلٍ وَلَا يُغْنِي مِنَ اللَّهَبِ(31) አጠላይ ያልኾነ ከእሳቱም ላንቃ የማያድን ወደ ኾነው (አዝግሙ)፡፡ |
إِنَّهَا تَرْمِي بِشَرَرٍ كَالْقَصْرِ(32) እርሷ እንደ ታላላቅ ሕንጻ የኾኑን ቃንቄዎች ትወረውራለች፡፡ |
كَأَنَّهُ جِمَالَتٌ صُفْرٌ(33) (ቃንቄውም) ልክ ዳለቻዎች ግመሎችን ይመስላል፡፡ |
وَيْلٌ يَوْمَئِذٍ لِّلْمُكَذِّبِينَ(34) ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡ |
هَٰذَا يَوْمُ لَا يَنطِقُونَ(35) ይህ የማይናገሩበት ቀን ነው፡፡ |
وَلَا يُؤْذَنُ لَهُمْ فَيَعْتَذِرُونَ(36) ይቅርታም ይጠይቁ ዘንድ፤ ለእነርሱ አይፈቀድላቸውም፡፡ |
وَيْلٌ يَوْمَئِذٍ لِّلْمُكَذِّبِينَ(37) ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡ |
هَٰذَا يَوْمُ الْفَصْلِ ۖ جَمَعْنَاكُمْ وَالْأَوَّلِينَ(38) ይህ መለያው ቀን ነው፡፡ እናንተንም የፊተኞቹንም ሰብሰብናችሁ፡፡ |
فَإِن كَانَ لَكُمْ كَيْدٌ فَكِيدُونِ(39) ለናንተም (ለማምለጥ) ብልሃት እንዳላችሁ ተተናኮሉኝ፡፡ |
وَيْلٌ يَوْمَئِذٍ لِّلْمُكَذِّبِينَ(40) ላስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡ |
إِنَّ الْمُتَّقِينَ فِي ظِلَالٍ وَعُيُونٍ(41) ጥንቁቆቹ በጥላዎችና በምንጮች ውስጥ ናቸው፡፡ |
وَفَوَاكِهَ مِمَّا يَشْتَهُونَ(42) ከሚከጅሉትም ሁሉ በፍራፍሬዎች ውስጥ ናቸው፡፡ |
كُلُوا وَاشْرَبُوا هَنِيئًا بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ(43) «ትሠሩት በነበራችሁት ዋጋ የምትደሰቱ ኾናችሁ ብሉ፣ ጠጡም፤» (ይባላሉ)፡፡ |
إِنَّا كَذَٰلِكَ نَجْزِي الْمُحْسِنِينَ(44) እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን ሁሉ እንመነዳለን፡፡ |
وَيْلٌ يَوْمَئِذٍ لِّلْمُكَذِّبِينَ(45) ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡ |
كُلُوا وَتَمَتَّعُوا قَلِيلًا إِنَّكُم مُّجْرِمُونَ(46) ብሉ፤ ጥቂትንም (ጊዜ) ተጠቀሙ፡፡ እናንተ አመጸኞች ናችሁና፡፡ |
وَيْلٌ يَوْمَئِذٍ لِّلْمُكَذِّبِينَ(47) ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡ |
وَإِذَا قِيلَ لَهُمُ ارْكَعُوا لَا يَرْكَعُونَ(48) «ለእነርሱ ስገዱም» በተባሉ ጊዜ አይሰግዱም፡፡ |
وَيْلٌ يَوْمَئِذٍ لِّلْمُكَذِّبِينَ(49) ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው፡፡ |
فَبِأَيِّ حَدِيثٍ بَعْدَهُ يُؤْمِنُونَ(50) ከእርሱም ሌላ በየትኛው ንግግር ያምናሉ? |
Plus de sourates en Amharique :
Téléchargez la sourate avec la voix des récitants du Coran les plus célèbres :
Téléchargez le fichier mp3 de la sourate Al-Mursalat : choisissez le récitateur pour écouter et télécharger la sourate Al-Mursalat complète en haute qualité.















Donnez-nous une invitation valide