PDF —
11 አንቀጽ Meccan PDF
Built right in your browser — download starts automatically

ሱረቱ አል-ዐዲያት pdf — አውርድ (አማርኛ)

ሱረቱ አል-ዐዲያት pdf አማርኛ — አውርድ ሱረቱ አል-ዐዲያት ትርጉም. ሱረቱ አል-ዐዲያት (Meccan) 11 አንቀጽ.

← አዝ-ዘልዘላሱረቱ አል-ዐዲያት አል-ቃሪዐ →


11 አንቀጽ · Meccan · አማርኛ
bismillah
ﮱﯓﯔ
100:1 እያለከለኩ ሩዋጮች በኾኑት (ፈረሶች) እምላለሁ፡፡
ﯕﯖﯗ
100:2 (በሰኮናቸው) እያጋጩ እሳትን አውጪዎች በኾኑትም፤
ﯘﯙﯚ
100:3 በማለዳ ወራሪዎች በኾኑትም፤
ﯛﯜﯝﯞ
100:4 በእርሱ አቧራን በቀሰቀሱትም፤
ﯟﯠﯡﯢ
100:5 በ(ጠላት) ክቢ መካከል በእርሱ (በጧት) በተጋፈጡትም እምላለሁ፡፡
ﭑﭒﭓﭔﭕ
100:6 ሰው ለጌታው ብርቱ ከሓዲ ነው፡፡
ﭖﭗﭘﭙﭚ
100:7 እርሱም በዚህ ላይ መስካሪ ነው፡፡
ﭛﭜﭝﭞﭟ
100:8 እርሱም ገንዘብን ለመውደድ በጣም ብርቱ ነው፡፡
ﭠﭡﭢﭣﭤﭥﭦﭧﭨ
100:9 (ሰው) አያውቅምን? በመቃብሮች ያሉት (ሙታን) በተቀሰቀሱ ጊዜ፤
ﭩﭪﭫﭬﭭ
100:10 በልቦች ውስጥ ያለውም ሁሉ በተገለጸ ጊዜ (እንዴት እንደሚኾን)፡፡
ﭮﭯﭰﭱﭲﭳ
100:11 ጌታቸው በዚያ ቀን በእነርሱ (ነገር) በእርግጥ ውስጠ አዋቂ ነው፡፡

ቅዱስ ቁርኣን


Wednesday, September 9, 2026

Don't forget us in your sincere prayers