PDF —
ሱረቱ አድ-ዱሓ pdf — አውርድ (አማርኛ)
ሱረቱ አድ-ዱሓ pdf አማርኛ — አውርድ ሱረቱ አድ-ዱሓ ትርጉም. ሱረቱ አድ-ዱሓ (Meccan) 11 አንቀጽ.
More ሱረቱ PDF
ሱረቱ አድ-ዱሓ

ﮉﮊ
93:1
በረፋዱ እምላለሁ፡፡
ﮋﮌﮍﮎ
93:2
በሌሊቱም ጸጥ ባለ ጊዜ፤
ﮏﮐﮑﮒﮓﮔ
93:3
ጌታህ አላሰናበተህም፤ አልጠላህምም፡፡
ﮕﮖﮗﮘﮙﮚ
93:4
መጨረሻይቱም (ዓለም) ከመጀመሪያይቱ ይልቅ ላንተ በላጭ ናት፡፡
ﮛﮜﮝﮞﮟ
93:5
ጌታህም ወደ ፊት (ብዙን ስጦታ) በእርግጥ ይሰጥሃል፡፡ ትደሰታለህም፡፡
ﮠﮡﮢﮣﮤ
93:6
የቲም ኾነህ አላገኘህምና አላስጠጋህምን? (አስጠግቶሃል)፡፡
ﮥﮦﮧﮨ
93:7
የሳትክም ኾነህ አገኘህ መራህም፡፡
ﮩﮪﮫﮬ
93:8
ድኻም ኾነህ አገኘህ፤ አከበረህም፡፡
ﮭﮮﮯﮰﮱ
93:9
የቲምንማ አትጨቁን፡፡
ﯓﯔﯕﯖﯗ
93:10
ለማኝንም አትገላምጥ፡፡
ﯘﯙﯚﯛﯜ
93:11
በጌታህም ጸጋ አውራ፤ (ግለጻት)፡፡
ቅዱስ ቁርኣን
Tuesday, September 29, 2026
Don't forget us in your sincere prayers







