PDF —
21 አንቀጽ Meccan PDF
Built right in your browser — download starts automatically

ሱረቱ አል-ሌል pdf — አውርድ (አማርኛ)

ሱረቱ አል-ሌል pdf አማርኛ — አውርድ ሱረቱ አል-ሌል ትርጉም. ሱረቱ አል-ሌል (Meccan) 21 አንቀጽ.

← አሽ-ሸምስሱረቱ አል-ሌል አድ-ዱሓ →


21 አንቀጽ · Meccan · አማርኛ
bismillah
ﮡﮢﮣﮤ
92:1 በሌሊቱ እምላለሁ (በጨለማው) በሚሸፍን ጊዜ፡፡
ﮥﮦﮧﮨ
92:2 በቀኑም፤ በተገለጸ ጊዜ፡፡
ﮩﮪﮫﮬﮭ
92:3 ወንድንና ሴትን በፈጠረውም (አምላክ እምላለሁ)፡፡
ﮮﮯﮰﮱ
92:4 ሥራችሁ በእርግጥ የተለያየ ነው፡፡
ﯓﯔﯕﯖﯗ
92:5 የሰጠ ሰውማ ጌታውን የፈራም፡፡
ﯘﯙﯚ
92:6 በመልካሚቱም (እምነት) ያረጋገጠ፤
ﯛﯜﯝ
92:7 ለገሪቱ ሥራ እናዘጋጀዋለን፡፡
ﯞﯟﯠﯡﯢ
92:8 የሰሰተ ሰውማ የተብቃቃም፤ (በራሱ የተመካ)፤
ﯣﯤﯥ
92:9 በመልካሚቱ (እምነት) ያሰተባበለም፤
ﭑﭒﭓ
92:10 ለክፉይቱ ሥራ እናዘጋጀዋለን፡፡
ﭔﭕﭖﭗﭘﭙﭚ
92:11 በወደቀም ጊዜ ገንዘቡ ከእርሱ ምንም አይጠቅመውም፡፡
ﭛﭜﭝﭞ
92:12 ቅኑን መንገድ መግለጽ በእኛ ላይ አለብን፡፡
ﭟﭠﭡﭢﭣ
92:13 መጨረሻይቱም መጀመሪያይቱም ዓለም የእኛ ናቸው፡፡
ﭤﭥﭦﭧ
92:14 የምትንቀለቀልንም እሳት አስጠነቀቅኳችሁ (በላቸው)፡፡
ﭨﭩﭪﭫﭬ
92:15 ከጠማማ በቀር ሌላ የማይገባት የኾነችን፡፡
ﭭﭮﭯﭰ
92:16 ያ ያስተባበለና ከትዕዛዝ የሸሸው፡፡
ﭱﭲﭳ
92:17 አላህን በጣም ፈሪውም በእርግጥ ይርቃታል፡፡
ﭴﭵﭶﭷﭸ
92:18 ያ የሚጥራራ ኾኖ ገንዘቡን (ለድኾች) የሚሰጠው፡፡
ﭹﭺﭻﭼﭽﭾﭿ
92:19 ለአንድም ሰው እርሱ ዘንድ የምትመለስ ውለታ የለችም፡፡
ﮀﮁﮂﮃﮄﮅ
92:20 ግን የታላቅ ጌታውን ውዴታ ለመፈለግ (ይህንን ሠራ)፡፡
ﮆﮇﮈ
92:21 ወደፊትም በእርግጥ ይደሰታል፡፡

ቅዱስ ቁርኣን


Wednesday, September 9, 2026

Don't forget us in your sincere prayers