አን-ኑር · 41/64
ትርጉም ፊደሎች — አን-ኑር
أَلَمْ تَرَ أَنَّ اللَّهَ يُسَبِّحُ لَهُ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَالطَّيْرُ صَافَّاتٍ ۖ كُلٌّ قَدْ عَلِمَ صَلَاتَهُ وَتَسْبِيحَهُ ۗ وَاللَّهُ عَلِيمٌ بِمَا يَفْعَلُونَ ۝٤١
Alam tara annal laaha yusabbihu lahoo man fissamaawaati wal ardi wat tairu saaaffaatim kullun qad `alima Salaatahoo wa tasbeehah; wallaahu `aleemum bimaa yaf`aloon
📖 በአማርኛ
አላህ በሰማያትና በምድር ያለ ሁሉ በራሪዎችም ክንፎቻቸውን (በአየር ላይ) ያንሳፈፉ ኾነው ለእርሱ የሚያጠሩ (የሚያወድሱ) መኾናቸውን አላወቅህምን ሁሉም ስግደቱንና ማጥራቱን በእርግጥ ዐወቀ፡፡ አላህም የሚሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡
🎧 ስሙ

📜 አንቀጽ 39-43 — አን-ኑር

39وَالَّذِينَ كَفَرُوا أَعْمَالُهُمْ كَسَرَابٍ بِقِيعَةٍ يَحْسَبُهُ الظَّمْآنُ مَاءً حَتَّىٰ إِذَا جَاءَهُ لَمْ يَجِدْهُ شَيْئًا وَوَجَدَ اللَّهَ عِندَهُ فَوَفَّاهُ حِسَابَهُ ۗ وَاللَّهُ سَرِيعُ الْحِسَابِ
እነዚያም የካዱት ሰዎች ሥራዎቻቸው (መልካሞቹ) በበረሃ ሜዳ እንዳለ ሲሪብዱ የጠማው ሰው ውሃ ነው ብሎ እንደሚያስበው በመጣውም ጊዜ ምንም ነገር ኾኖ እንደማያገኘው ነው፡፡ (ከሓዲው) አላህንም እሠራው ዘንድ ያገኘዋል፡፡ ምርመራውንም (ቅጣቱን) ይሞላለታል፡፡ አላህም ምርመራው ፈጣን ነው፡፡
40أَوْ كَظُلُمَاتٍ فِي بَحْرٍ لُّجِّيٍّ يَغْشَاهُ مَوْجٌ مِّن فَوْقِهِ مَوْجٌ مِّن فَوْقِهِ سَحَابٌ ۚ ظُلُمَاتٌ بَعْضُهَا فَوْقَ بَعْضٍ إِذَا أَخْرَجَ يَدَهُ لَمْ يَكَدْ يَرَاهَا ۗ وَمَن لَّمْ يَجْعَلِ اللَّهُ لَهُ نُورًا فَمَا لَهُ مِن نُّورٍ
ወይም (መጥፎ ሥራዎቻቸውን) ከበላዩ ደመና ያለበት ማዕበል በሚሸፈነው ጥልቅ ባህር ውስጥ እንዳሉ ጨለማዎች ነው፡፡ (እነዚያ) ከፊላቸው ከከፊሉ በላይ ድርብርብ የኾኑ ጨለማዎች ናቸው፡፡ (በዚህች) የተሞከረ (ሰው) እጁን ባወጣ ጊዜ ሊያያት አይቀርብም፡፡ አላህም ለእርሱ ብርሃንን ያላደረገለት ሰው ለእርሱ ምንም ብርሃን የለውም፡፡
41أَلَمْ تَرَ أَنَّ اللَّهَ يُسَبِّحُ لَهُ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَالطَّيْرُ صَافَّاتٍ ۖ كُلٌّ قَدْ عَلِمَ صَلَاتَهُ وَتَسْبِيحَهُ ۗ وَاللَّهُ عَلِيمٌ بِمَا يَفْعَلُونَ
አላህ በሰማያትና በምድር ያለ ሁሉ በራሪዎችም ክንፎቻቸውን (በአየር ላይ) ያንሳፈፉ ኾነው ለእርሱ የሚያጠሩ (የሚያወድሱ) መኾናቸውን አላወቅህምን ሁሉም ስግደቱንና ማጥራቱን በእርግጥ ዐወቀ፡፡ አላህም የሚሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡
42وَلِلَّهِ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ وَإِلَى اللَّهِ الْمَصِيرُ
የሰማያትና የምድርም ግዛት የአላህ ነው፡፡ መመለሻም ወደ አላህ ነው፡፡
43أَلَمْ تَرَ أَنَّ اللَّهَ يُزْجِي سَحَابًا ثُمَّ يُؤَلِّفُ بَيْنَهُ ثُمَّ يَجْعَلُهُ رُكَامًا فَتَرَى الْوَدْقَ يَخْرُجُ مِنْ خِلَالِهِ وَيُنَزِّلُ مِنَ السَّمَاءِ مِن جِبَالٍ فِيهَا مِن بَرَدٍ فَيُصِيبُ بِهِ مَن يَشَاءُ وَيَصْرِفُهُ عَن مَّن يَشَاءُ ۖ يَكَادُ سَنَا بَرْقِهِ يَذْهَبُ بِالْأَبْصَارِ
አላህ ደመናን የሚነዳ መኾኑን አላየህምን ከዚያም ከፊሉን ከከፊሉ ያገናኛል፡፡ ከዚያም የተደራረበ ያደርገዋል፡፡ ዝናቡንም ከመካከሉ የሚወጣ ኾኖ ታየዋለህ፡፡ ከሰማይም (ከደመና) በውስጧ ካሉት ጋራዎች በረዶን ያወርዳል፡፡ በእርሱም የሚሻውን ሰው (በጉዳት) ይነካል፡፡ ከሚሻውም ሰው ላይ ይመልሰዋል፡፡ የብልጭታው ብርሃን ዓይኖችን ሊወስድ ይቀርባል፡፡
አን-ኑርቁርአን ማውጫ
64አንቀጽ
MedinanRevelation
41አንቀጽ

ትርጉም — አን-ኑር 41

ሱረቱ አን-ኑር አንቀጽ 41 - ማንበብ, ስሙ, ትርጉም, አማርኛ : አላህ በሰማያትና በምድር ያለ ሁሉ በራሪዎችም ክንፎቻቸውን (በአየር ላይ) ያንሳፈፉ…

ሱረቱ አንቀጽ 41/64 — አን-ኑር النور (Medinan). ማንበብ ስሙ ትርጉም (አማርኛ). ስሙ: አን-ኑር ስሙ, አን-ኑር ትርጉም, አን-ኑር mp3, አን-ኑር pdf. አንቀጽ 39–43. በአማርኛ: العربية.




ቅዱስ ቁርኣን


Tuesday, August 18, 2026

Don't forget us in your sincere prayers