ፉሲላት · 36/54
ትርጉም ፊደሎች — ሱረቱ ፉሲላት
وَإِمَّا يَنزَغَنَّكَ مِنَ الشَّيْطَانِ نَزْغٌ فَاسْتَعِذْ بِاللَّهِ ۖ إِنَّهُ هُوَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ ۝٣٦
Wa immaa yanzaghannaka minash Shaitaani nazghun fasta`iz billaahi innahoo Huwas Samee`ul `Aleem
📖 በአማርኛ
ከሰይጣንም ጉትጎታ ቢያገኝህ (ከመልካም ጠባይም ቢመልስህ) በአላህ ተጠበቅ፡፡ እነሆ እርሱ ሰሚው ዐዋቂው ነውና፡፡

🎧 ስሙ


📜 አንቀጽ 34-38 — ሱረቱ ፉሲላት

34وَلَا تَسْتَوِي الْحَسَنَةُ وَلَا السَّيِّئَةُ ۚ ادْفَعْ بِالَّتِي هِيَ أَحْسَنُ فَإِذَا الَّذِي بَيْنَكَ وَبَيْنَهُ عَدَاوَةٌ كَأَنَّهُ وَلِيٌّ حَمِيمٌ
መልካሚቱና ክፉይቱም (ጸባይ) አይተካከሉም፡፡ በዚያች እርሷ መልካም በኾነችው ጸባይ (መጥፎይቱን) ገፍትር፡፡ ያን ጊዜ ያ ባንተና በእርሱ መካከል ጠብ ያለው ሰው እርሱ ልክ እንደ አዛኝ ዘመድ ይኾናል፡፡
35وَمَا يُلَقَّاهَا إِلَّا الَّذِينَ صَبَرُوا وَمَا يُلَقَّاهَا إِلَّا ذُو حَظٍّ عَظِيمٍ
(ይህችንም ጠባይ) እነዚያ የታገሱት እንጅ ሌላው አያገኛትም፡፡ የትልቅም ዕድል ባለቤት እንጅ ማንም አይገጠማትም፡፡
36وَإِمَّا يَنزَغَنَّكَ مِنَ الشَّيْطَانِ نَزْغٌ فَاسْتَعِذْ بِاللَّهِ ۖ إِنَّهُ هُوَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ
ከሰይጣንም ጉትጎታ ቢያገኝህ (ከመልካም ጠባይም ቢመልስህ) በአላህ ተጠበቅ፡፡ እነሆ እርሱ ሰሚው ዐዋቂው ነውና፡፡
37وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ ۚ لَا تَسْجُدُوا لِلشَّمْسِ وَلَا لِلْقَمَرِ وَاسْجُدُوا لِلَّهِ الَّذِي خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُونَ
ሌሊትና ቀንም ፀሐይና ጨረቃም ከምልክቶቹ ናቸው፡፡ ለፀሐይና ለጨረቃ አትስገዱ፡፡ ለእዚያም ለፈጠራቸው አላህ ስገዱ፡፡ እርሱን ብቻ የምትግገዙ እንደ ኾናችሁ (ለሌላ አትስገዱ)፡፡
38فَإِنِ اسْتَكْبَرُوا فَالَّذِينَ عِندَ رَبِّكَ يُسَبِّحُونَ لَهُ بِاللَّيْلِ وَالنَّهَارِ وَهُمْ لَا يَسْأَمُونَ ۩
ቢኮሩም እነዚያ በጌታህ ዘንድ ያሉት (መላእክት) በቀንም በሌሊትም ለእርሱ ያወድሳሉ፡፡ እነርሱም አይሰለቹም፡፡
ፉሲላትቁርአን ማውጫ
54አንቀጽ
MeccanRevelation
36አንቀጽ

ትርጉም — ፉሲላት 36

ሱረቱ ፉሲላት አንቀጽ 36 - ማንበብ, ስሙ, ትርጉም, አማርኛ : ከሰይጣንም ጉትጎታ ቢያገኝህ (ከመልካም ጠባይም ቢመልስህ) በአላህ ተጠበቅ፡፡ እነሆ እርሱ…

ሱረቱ አንቀጽ 36/54 — ሱረቱ ፉሲላት فصلت (Meccan). ማንበብ ስሙ ትርጉም (አማርኛ). ስሙ: ሱረቱ ፉሲላት ስሙ, ሱረቱ ፉሲላት ትርጉም, ሱረቱ ፉሲላት mp3, ሱረቱ ፉሲላት pdf. አንቀጽ 34–38. በአማርኛ: العربية.




ቅዱስ ቁርኣን


Monday, September 7, 2026

Don't forget us in your sincere prayers