La sourate Al-Maarij en Amharique
سَأَلَ سَائِلٌ بِعَذَابٍ وَاقِعٍ(1) ወዳቂ ከኾነው ቅጣት ጠያቂ ጠየቀ፡፡ |
لِّلْكَافِرِينَ لَيْسَ لَهُ دَافِعٌ(2) በከሓዲዎች ላይ (ወዳቂ ከኾነው) ለእርሱ መላሽ የለውም፡፡ |
مِّنَ اللَّهِ ذِي الْمَعَارِجِ(3) የ(ሰማያት) መሰላሎች ባለቤት ከኾነው አላህ (መላሽ የለውም)፡፡ |
تَعْرُجُ الْمَلَائِكَةُ وَالرُّوحُ إِلَيْهِ فِي يَوْمٍ كَانَ مِقْدَارُهُ خَمْسِينَ أَلْفَ سَنَةٍ(4) መላእክቱና መንፈሱም ልኩ አምሳ ሺሕ ዓመት በኾነ ቀን ውስጥ ወደእርሱ ያርጋሉ፤ (ይወጣሉ)፡፡ |
فَاصْبِرْ صَبْرًا جَمِيلًا(5) መልካምንም ትዕግስት ታገሥ፡፡ |
إِنَّهُمْ يَرَوْنَهُ بَعِيدًا(6) እነርሱ (ያንን ቀን) ሩቅ አድርገው ያዩታል፡፡ |
وَنَرَاهُ قَرِيبًا(7) እኛም ቅርብ ኾኖ እናየዋለን፡፡ |
يَوْمَ تَكُونُ السَّمَاءُ كَالْمُهْلِ(8) ሰማይ እንደ ዘይት አተላ በምትኾንበት ቀን፡፡ |
وَتَكُونُ الْجِبَالُ كَالْعِهْنِ(9) ጋራዎችም በተለያዩ ቀለማት እንደ ተነከረ ሱፍ (ነፋስ እንደሚያበረው) በሚኾኑበት ቀን፡፡ |
وَلَا يَسْأَلُ حَمِيمٌ حَمِيمًا(10) ዘመድም ዘመድን በማይጠይቅበት ቀን፤ (መላሽ የለውም)፡፡ |
يُبَصَّرُونَهُمْ ۚ يَوَدُّ الْمُجْرِمُ لَوْ يَفْتَدِي مِنْ عَذَابِ يَوْمِئِذٍ بِبَنِيهِ(11) (ዘመዶቻቸውን) ያዩዋቸዋል፡፡ አመጸኛው ከዚያ ቀን ስቃይ (ነፍሱን) በልጆቹ ሊበዥ ይመኛል፡፡ |
وَصَاحِبَتِهِ وَأَخِيهِ(12) በሚስቱም በወንድሙም፡፡ |
وَفَصِيلَتِهِ الَّتِي تُؤْوِيهِ(13) በዚያችም በምታስጠጋው ጎሳው፡፡ |
وَمَن فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا ثُمَّ يُنجِيهِ(14) በምድርም ላይ ባለው ሁሉ (ሊበዥ) ከዚያም ሊያድነው (ይመኛል)፡፡ |
كَلَّا ۖ إِنَّهَا لَظَىٰ(15) ይተው! እርሷ (እሳቲቱ) ለዟ ናት፡፡ |
نَزَّاعَةً لِّلشَّوَىٰ(16) የራስን ቅል ቆዳ የምትሞሽልቅ ስትኾን፡፡ |
تَدْعُو مَنْ أَدْبَرَ وَتَوَلَّىٰ(17) (ከእምነት) የዞረንና የሸሸን ሰው (ወደእርሷ) ትጠራለች፡፡ |
وَجَمَعَ فَأَوْعَىٰ(18) ገንዘብን የሰበሰበንና (ዘካውን ሳይሰጥ) የቆጠረንም፤ (ትጠራለች)፡፡ |
۞ إِنَّ الْإِنسَانَ خُلِقَ هَلُوعًا(19) ሰው ቅጠ ቢስ ኾኖ ተፈጠረ፡፡ |
إِذَا مَسَّهُ الشَّرُّ جَزُوعًا(20) ክፉ ነገር ባገኘው ጊዜ ብስጪተኛ፡፡ |
وَإِذَا مَسَّهُ الْخَيْرُ مَنُوعًا(21) መልካምም ነገር (ድሎት) ባገኘ ጊዜ ከልካይ (ኾኖ ተፈጠረ)፡፡ |
إِلَّا الْمُصَلِّينَ(22) ሰጋጆቹ ብቻ ሲቀሩ፡፡ |
الَّذِينَ هُمْ عَلَىٰ صَلَاتِهِمْ دَائِمُونَ(23) እነዚያ እነርሱ በስግደታቸው ላይ ዘውታሪዎች የኾኑት፡፡ |
وَالَّذِينَ فِي أَمْوَالِهِمْ حَقٌّ مَّعْلُومٌ(24) እነዚያም በገንዘቦቻቸው ላይ የታወቀ መብት ያለባቸው የኾኑት፡፡ |
لِّلسَّائِلِ وَالْمَحْرُومِ(25) ለለማኝ ከልመና ለሚከለከልም (መብት ያለባቸው የኾኑት)፡፡ |
وَالَّذِينَ يُصَدِّقُونَ بِيَوْمِ الدِّينِ(26) እነዚያም በፍርዱ ቀን እውነት የሚሉት (የሚያረጋግጡት)፡፡ |
وَالَّذِينَ هُم مِّنْ عَذَابِ رَبِّهِم مُّشْفِقُونَ(27) እነዚያም እነርሱ ከጌታቸው ቅጣት ፈሪዎች የኾኑት፡፡ |
إِنَّ عَذَابَ رَبِّهِمْ غَيْرُ مَأْمُونٍ(28) የጌታቸው ቅጣት (መምጣቱ) የማያስተማምን ነውና፡፡ |
وَالَّذِينَ هُمْ لِفُرُوجِهِمْ حَافِظُونَ(29) እነዚያም እነርሱ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች የኾኑት፡፡ |
إِلَّا عَلَىٰ أَزْوَاجِهِمْ أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُهُمْ فَإِنَّهُمْ غَيْرُ مَلُومِينَ(30) በሚስቶቻቸው ወይም እጆቻቸው በያዙዋቸው (ባሪያዎች) ላይ ሲቀር፡፡ እነርሱ (በእነዚህ) የማይወቀሱ ናቸውና፡፡ |
فَمَنِ ابْتَغَىٰ وَرَاءَ ذَٰلِكَ فَأُولَٰئِكَ هُمُ الْعَادُونَ(31) ከዚያም ወዲያ የፈለገ ሰው እነዚያ እነሱ ድንበር አላፊዎች ናቸው፡፡ |
وَالَّذِينَ هُمْ لِأَمَانَاتِهِمْ وَعَهْدِهِمْ رَاعُونَ(32) እነዚያም እነርሱ አደራዎቻቸውንና ቃል ኪዳናቸውን ጠባቂዎች የኾኑት፡፡ |
وَالَّذِينَ هُم بِشَهَادَاتِهِمْ قَائِمُونَ(33) እነዚያም እነርሱ በምስክርነታቸው ትክክለኞች የኾኑት፡፡ |
وَالَّذِينَ هُمْ عَلَىٰ صَلَاتِهِمْ يُحَافِظُونَ(34) እነዚያም እነርሱ በሶላቶቻቸው ላይ የሚጠባበቁት፡፡ |
أُولَٰئِكَ فِي جَنَّاتٍ مُّكْرَمُونَ(35) እነዚህ (ከዚህ በላይ የተወሱት ሁሉ) በገነቶች ውስጥ የሚከበሩ ናቸው፡፡ |
فَمَالِ الَّذِينَ كَفَرُوا قِبَلَكَ مُهْطِعِينَ(36) ለእነዚያም ለካዱት ወደ አንተ በኩል አንገቶቻቸውን መዝዘው የሚያተኩሩት ምን አላቸው? |
عَنِ الْيَمِينِ وَعَنِ الشِّمَالِ عِزِينَ(37) ከቀኝና ከግራ ክፍልፍል ጭፍሮች ሲኾኑ፡፡ |
أَيَطْمَعُ كُلُّ امْرِئٍ مِّنْهُمْ أَن يُدْخَلَ جَنَّةَ نَعِيمٍ(38) ከእነርሱ እያንዳንዱ ሰው የጸጋይቱን ገነት መግባትን ይከጅላልን? |
كَلَّا ۖ إِنَّا خَلَقْنَاهُم مِّمَّا يَعْلَمُونَ(39) ይከልከል፤ እኛ ከሚያውቁት ነገር (ከፍቶት ጠብታ) ፈጠርናቸው፡፡ |
فَلَا أُقْسِمُ بِرَبِّ الْمَشَارِقِ وَالْمَغَارِبِ إِنَّا لَقَادِرُونَ(40) በምሥራቆችና በምዕራቦችም ጌታ እምላለሁ፡፡ እኛ በእርግጥ ቻዮች ነን፡፡ |
عَلَىٰ أَن نُّبَدِّلَ خَيْرًا مِّنْهُمْ وَمَا نَحْنُ بِمَسْبُوقِينَ(41) ከእነርሱ የተሻለን በመለወጥ ላይ፡፡ እኛም ተሸናፊዎች አይደለንም፡፡ |
فَذَرْهُمْ يَخُوضُوا وَيَلْعَبُوا حَتَّىٰ يُلَاقُوا يَوْمَهُمُ الَّذِي يُوعَدُونَ(42) ያንንም የሚስፈራሩበትን ቀናቸውን እስከሚገናኙ ድረስ ተዋቸው፡፡ ይዋኙ ይጫወቱም፡፡ |
يَوْمَ يَخْرُجُونَ مِنَ الْأَجْدَاثِ سِرَاعًا كَأَنَّهُمْ إِلَىٰ نُصُبٍ يُوفِضُونَ(43) ወደ ጣዖቶች እንደሚሽቀዳደሙ ኾነው ከመቃብሮቻቸው ፈጥነው የሚወጡበትን ቀን (እስከሚገናኙ ድረስ ተዋቸው)፡፡ |
خَاشِعَةً أَبْصَارُهُمْ تَرْهَقُهُمْ ذِلَّةٌ ۚ ذَٰلِكَ الْيَوْمُ الَّذِي كَانُوا يُوعَدُونَ(44) ዓይኖቻቸው ያፈሩ ኾነው ውርደት ትሸፍናቸዋለች፡፡ ይህ ቀን ያ ይስፈራሩበት የነበሩት ነው፡፡ |
Plus de sourates en Amharique :
Téléchargez la sourate avec la voix des récitants du Coran les plus célèbres :
Téléchargez le fichier mp3 de la sourate Al-Maarij : choisissez le récitateur pour écouter et télécharger la sourate Al-Maarij complète en haute qualité.















Donnez-nous une invitation valide