PDF —
40 አንቀጽ Meccan PDF
Built right in your browser — download starts automatically

ሱረቱ አን-ነበእ pdf — አውርድ (አማርኛ)

ሱረቱ አን-ነበእ pdf አማርኛ — አውርድ ሱረቱ አን-ነበእ ትርጉም. ሱረቱ አን-ነበእ (Meccan) 40 አንቀጽ.



40 አንቀጽ · Meccan · አማርኛ
bismillah
ﭑﭒﭓ
78:1 ከምን ነገር ይጠያየቃሉ?
ﭔﭕﭖﭗ
78:2 ከታላቁ ዜና (ከቁርኣን ይጠያየቃሉ)፡፡
ﭘﭙﭚﭛﭜ
78:3 ከዚያ እነርሱ በእርሱ የተለያዩበት ከኾነው፡፡
ﭝﭞﭟ
78:4 ይከልከሉ፤ ወደፊት (የሚደርስበቸውን) በእርግጥ ያውቃሉ፡፡
ﭠﭡﭢﭣ
78:5 ከዚያም ይከልከሉ፤ ወደፊት ያውቃሉ፡፡
ﭤﭥﭦﭧﭨ
78:6 ምድርን ምንጣፍ አላደረግንምን?
ﭩﭪﭫ
78:7 ጋራዎችንም ችካሎች አላደረግንምን?
ﭬﭭﭮ
78:8 ብዙ ዓይነቶችም አድርገን ፈጠርናችሁ፡፡
ﭯﭰﭱﭲ
78:9 እንቅልፋችሁንም ዕረፍት አደረግን፡፡
ﭳﭴﭵﭶ
78:10 ሌሊቱንም ልባስ አደረግን፡፡
ﭷﭸﭹﭺ
78:11 ቀኑንም (ለኑሮ) መስሪያ አደረግን፡፡
ﭻﭼﭽﭾﭿ
78:12 ከበላያችሁም ሰባትን ብርቱዎች (ሰማያት) ገነባን፡፡
ﮀﮁﮂﮃ
78:13 አንጸባራቂ ብርሃንንም አደረግን፡፡
ﮄﮅﮆﮇﮈﮉ
78:14 ከአረገዙት ደመናዎችም ተንቧቢ ውሃን አወረድን፡፡
ﮊﮋﮌﮍﮎ
78:15 በእርሱ እኽልንና ቅጠላ ቅጠልን እናወጣ ዘንድ (አወረድን)፡፡
ﮏﮐﮑ
78:16 የተቆላለፉ አትክልቶችንም፡፡
ﮒﮓﮔﮕﮖﮗ
78:17 የመለያው ቀን የተወሰነ ጊዜ ነው፡፡
ﮘﮙﮚﮛﮜﮝﮞ
78:18 በቀንዱ በሚነፋና የተለያዩ ጭፍሮች ኾናችሁ በምትመጡ ቀን ነው፡፡
ﮟﮠﮡﮢﮣ
78:19 ሰማይም በምትከፈትና (ባለ) ደጃፎችም በምትኾንበት፡፡
ﮤﮥﮦﮧﮨ
78:20 ጋራዎችም በሚነዱበት (እንደ) ሲሪብዱም በሚኾኑበት (ቀን) ነው፡፡
ﮩﮪﮫﮬﮭ
78:21 ገሀነም መጠባበቂያ (ስፍራ) ናት፡፡
ﮮﮯﮰ
78:22 ለሕግ ተላላፊዎች መመለሻ ስትኾን፡፡
ﮱﯓﯔﯕ
78:23 በውስጧ ብዙን ዘመናት ነዋሪዎች ሲኾኑ፤
ﯖﯗﯘﯙﯚﯛﯜ
78:24 በውስጧ ቅዝቃዜንም መጠጥንም አይቀምሱም፡፡
ﯝﯞﯟﯠ
78:25 ግን ሙቅ ውሃንና እዥን (ይቀምሳሉ)፡፡
ﯡﯢﯣ
78:26 ተስማሚን ምንዳ ይምመነዳሉ፡፡
ﯤﯥﯦﯧﯨﯩ
78:27 እነርሱ ምርመራን የማይፈሩ ነበሩና፡፡
ﯪﯫﯬﯭ
78:28 በአንቀጾቻችንም ማስተባበልን አስተባበሉና፡፡
ﯮﯯﯰﯱﯲ
78:29 ነገሩንም ሁሉ የተጻፈ ሲኾን አጠቃለልነው፡፡
ﯳﯴﯵﯶﯷﯸ
78:30 ቅመሱም ቅጣትንም እንጅ (ሌላን) አንጨምራችሁም (ይባላሉ)፡፡
ﭑﭒﭓﭔ
78:31 ለጥንቁቆቹ መዳኛ ስፍራ አልላቸው፡፡
ﭕﭖﭗ
78:32 አትክልቶችና ወይኖችም፡፡
ﭘﭙﭚ
78:33 እኩያዎች የኾኑ ጡተ ጉቻማዎችም፡፡
ﭛﭜﭝ
78:34 የተሞሉ ብርጭቆዎችም፡፡
ﭞﭟﭠﭡﭢﭣﭤ
78:35 በውስጧ ትርፍ ቃልንም ማስዋሸትንም አይሰሙም፡፡
ﭥﭦﭧﭨﭩﭪ
78:36 ከጌታህ የኾነን ምንዳ በቂ ስጦታን (ተሰጡ)፡፡
ﭫﭬﭭﭮﭯﭰﭱﭲﭳﭴﭵﭶ
78:37 የሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ያለው ሁሉ ጌታ በጣም አዛኝ ከኾነው (ተመነዱ)፡፡ ከእርሱ ጋር መነጋገርን አይችሉም፡፡
ﭷﭸﭹﭺﭻﭼﭽﭾﭿﮀﮁﮂﮃﮄﮅﮆ
78:38 መንፈሱ (ጂብሪል) መላእክቶቹም የተሰለፉ ኾነው በሚቆሙ ቀን አል-ረሕማን ለእርሱ የፈቀደለትና ትክክለኛን ቃል ያለ ሰው ቢኾን እንጅ (መነጋገርን አይችሉም)፡፡
ﮇﮈﮉﮊﮋﮌﮍﮎﮏﮐﮑ
78:39 ይህ የተረጋገጠው ቀን ነው፡፡ የሻም ሰው ወደ ጌታው መመለስን ይይዛል፡፡
ﮒﮓﮔﮕﮖﮗﮘﮙﮚﮛﮜﮝﮞﮟﮠﮡ
78:40 እኛ ሰው ሁሉ እጆቹ ያስቀደሙትን በሚያይበትና ከሓዲውም ዋ ምኞቴ! ምንነው ዐፈር በኾንኩ በሚልበት ቀን ቅርብ የኾነን ቅጣት አስጠነቀቅናችሁ፡፡

ቅዱስ ቁርኣን


Wednesday, September 9, 2026

Don't forget us in your sincere prayers