PDF —
46 አንቀጽ Meccan PDF
Built right in your browser — download starts automatically

ሱረቱ አን-ናዚዓት pdf — አውርድ (አማርኛ)

ሱረቱ አን-ናዚዓት pdf አማርኛ — አውርድ ሱረቱ አን-ናዚዓት ትርጉም. ሱረቱ አን-ናዚዓት (Meccan) 46 አንቀጽ.

← አን-ነበእሱረቱ አን-ናዚዓት ዐበሰ →


46 አንቀጽ · Meccan · አማርኛ
bismillah
ﮢﮣﮤ
79:1 በኃይል አውጪዎች በኾኑት፤
ﮥﮦﮧ
79:2 በቀስታ መምዘዝንም መዘዦች በኾኑት፤
ﮨﮩﮪ
79:3 መዋኘትም ዋኚዎች በኾኑት፤
ﮫﮬﮭ
79:4 መቅደምንም ቀዳሚዎች በኾኑት፤
ﮮﮯﮰ
79:5 ነገርንም አስተናባሪዎች በኾኑት (መላእክት) እምላለሁ፡፡ (በእርግጥ ትቀሰቀሳላችሁ)፡፡
ﮱﯓﯔﯕ
79:6 ተርገፍጋፊይቱ (ምድር) በምትርገፈገፍበት ቀን፤
ﯖﯗﯘ
79:7 ለጣቂይቱ የምትከተላት ስትኾን (ትቀሰቀሳላችሁ)፡፡
ﯙﯚﯛﯜ
79:8 በዚያ ቀን ልቦች ተሸባሪዎች ናቸው፡፡
ﯝﯞﯟ
79:9 ዓይኖቻቸው ተዋራጆች (አቀርቃሪዎች) ናቸው፡፡
ﯠﯡﯢﯣﯤﯥ
79:10 «እኛ ወደ መጀመሪያይቱ ኹነታ ተመላሾች ነን?» ይላሉ፡፡
ﯦﯧﯨﯩﯪ
79:11 «የበሰበሱ አጥንቶች በኾን ጊዜ (እንቀሰቀሳለን?)»
ﯫﯬﯭﯮﯯﯰ
79:12 «ይህቺ ያን ጊዜ ባለ ከሳራ መመለስ ናት» ይላሉ፡፡
ﯱﯲﯳﯴﯵ
79:13 እርሷም አንዲት ጩኸት ብቻ ናት፡፡
ﯶﯷﯸﯹ
79:14 ወዲያውኑም እነርሱ እንቅልፍ በሌለባት (ምድር) ላይ ይኾናሉ፡፡
ﯺﯻﯼﯽﯾ
79:15 የሙሳ ወሬ መጣልህን?
ﯿﰀﰁﰂﰃﰄﰅ
79:16 ጌታው በተቀደሰው ሸለቆ በጡዋ በጠራው ጊዜ፤
ﭑﭒﭓﭔﭕﭖ
79:17 ወደ ፈርዖን ኺድ፡፡ እርሱ ወሰን አልፏልና፡፡
ﭗﭘﭙﭚﭛﭜﭝ
79:18 በለውም፡- «ወደ መጥራራትህ ላንተ (መንገድ) አለህን?»
ﭞﭟﭠﭡﭢ
79:19 «ወደ ጌታህም ልመራህ ትፈራውም ዘንድ፤ (መንገድ አለህን?)» አለው፡፡
ﭣﭤﭥﭦ
79:20 ታላቂቱንም ተዓምር አሳየው፡፡
ﭧﭨﭩ
79:21 አስተባበለም፤ አመጸም፡፡
ﭪﭫﭬﭭ
79:22 ከዚያም (ለማጥፋት) የሚተጋ ኾኖ ዞረ፡፡
ﭮﭯﭰ
79:23 (ሰራዊቶቹን) ሰበሰበም፤ ተጣራም፡፡
ﭱﭲﭳﭴﭵ
79:24 አለም፡- «እኔ ታላቁ ጌታችሁ ነኝ፡፡»
ﭶﭷﭸﭹﭺﭻ
79:25 አላህም በኋለኛይቱና በፊተኛይቱ (ቃል) ቅጣት ያዘው፡፡
ﭼﭽﭾﭿﮀﮁﮂ
79:26 በዚህ ውስጥ ለሚፈራ ሰው በእርግጥ መገምገሚያ አለበት፡፡
ﮃﮄﮅﮆﮇﮈﮉﮊ
79:27 ባፈጣጠር እናንተ ይበልጥ የበረታችሁ ናችሁን? ወይንስ ሰማይ? (አላህ) ገነባት፡፡
ﮋﮌﮍﮎ
79:28 ከፍታዋን አጓነ፤ አስተካከላትም፡፡
ﮏﮐﮑﮒﮓ
79:29 ሌሊቷንም አጨለመ፡፡ ቀንዋንም ገለጸ፡፡
ﮔﮕﮖﮗﮘ
79:30 ምድርንም ከዚህ በኋላ ዘረጋት፡፡
ﮙﮚﮛﮜﮝ
79:31 ውሃዋንና ግጦሿን ከእርሷ አወጣ፡፡
ﮞﮟﮠ
79:32 ጋራዎችንም አደላደላቸው፡፡
ﮡﮢﮣﮤ
79:33 ለእናንተና ለእንስሶቻችሁ መጣቀሚያ ይኾን ዘንድ (ይህን አደረገ)፡፡
ﮥﮦﮧﮨﮩ
79:34 ታላቂቱም መዐት በመጣች ጊዜ፣
ﮪﮫﮬﮭﮮﮯ
79:35 ሰው ሁሉ የሠራውን በሚያስታውስበት ቀን፣
ﮰﮱﯓﯔﯕ
79:36 ገሀነምም ለሚያይ ሰው በተገለጠች ጊዜ፣
ﯖﯗﯘﯙ
79:37 የካደ ሰውማ፣
ﯚﯛﯜﯝ
79:38 ቅርቢቱንም ሕይወት የመረጠ፣
ﯞﯟﯠﯡﯢ
79:39 ገሀነም እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት፡፡
ﯣﯤﯥﯦﯧﯨﯩﯪﯫﯬ
79:40 በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ
ﯭﯮﯯﯰﯱ
79:41 ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት፡፡
ﯲﯳﯴﯵﯶﯷ
79:42 «ከሰዓቲቱ መቼ ነው መኾኛዋ?» ሲሉ ይጠይቁሃል፡፡
ﯸﯹﯺﯻﯼ
79:43 አንተ እርሷን ከማስታወስ በምን ውስጥ ነህ?
ﯽﯾﯿﰀ
79:44 (የዕውቀት) መጨረሻዋ ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡
ﰁﰂﰃﰄﰅﰆ
79:45 አንተ የሚፈራትን ሰው አስፈራሪ ብቻ ነህ፡፡
ﰇﰈﰉﰊﰋﰌﰍﰎﰏﰐ
79:46 እነርሱ በሚያዩዋት ቀን ያንዲት ቀን ምሽትን ወይም ረፏዷን እንጅ ያልቆዩ ይመስላሉ፡፡

ቅዱስ ቁርኣን


Wednesday, September 9, 2026

Don't forget us in your sincere prayers