PDF —
42 አንቀጽ Meccan PDF
Built right in your browser — download starts automatically

ሱረቱ ዐበሰ pdf — አውርድ (አማርኛ)

ሱረቱ ዐበሰ pdf አማርኛ — አውርድ ሱረቱ ዐበሰ ትርጉም. ሱረቱ ዐበሰ (Meccan) 42 አንቀጽ.



42 አንቀጽ · Meccan · አማርኛ
bismillah
ﭑﭒﭓ
80:1 ፊቱን አጨፈገገ፤ ዞረም፡፡
ﭔﭕﭖﭗ
80:2 ዕውሩ ስለ መጣው፡፡
ﭘﭙﭚﭛﭜ
80:3 ምን ያሳውቅሃል? (ከኀጢአቶቹ) ሊጥራራ ይከጀላል፡፡
ﭝﭞﭟﭠﭡ
80:4 ወይም ሊገሠጽ ግሠጼይቱም ልትጠቅመው (ይከጀላል)፡፡
ﭢﭣﭤﭥ
80:5 የተብቃቃው ሰውማ፤
ﭦﭧﭨﭩ
80:6 አንተ ለእርሱ (ለእምነቱ በመጓጓት) በፈገግታ ትቀበለዋለህ፡፡
ﭪﭫﭬﭭﭮ
80:7 ባይጥራራ (ባያምን) ባንተ ላይ ምንም የሌለብህ ስትኾን፡፡
ﭯﭰﭱﭲﭳ
80:8 እየገሰገሰ የመጣህ ሰውማ፤
ﭴﭵﭶ
80:9 እርሱ (አላህን) የሚፈራ ሲኾን፤
ﭷﭸﭹﭺ
80:10 አንተ ከእርሱ ትዝዘናጋለህ፡፡
ﭻﭼﭽﭾ
80:11 ተከልከል፡፡ እርሷ ማስገንዘቢያ ናት፡፡
ﭿﮀﮁﮂ
80:12 የሻም ሰው (ቁርኣኑን) ያስታውሰዋል፡፡
ﮃﮄﮅﮆ
80:13 በተከበሩ ጽሑፎች ውስጥ ነው፡፡
ﮇﮈﮉ
80:14 ከፍ በተደረገች ንጹሕ በተደረገች (ጽሑፍ ውስጥ ነው)፡፡
ﮊﮋﮌ
80:15 በጸሐፊዎቹ (መላእክት) እጆች (ንጹሕ የተደረገች)፡፡
ﮍﮎﮏ
80:16 የተከበሩና ታዛዦች በኾኑት (ጸሐፊዎች እጆች)፡፡
ﮐﮑﮒﮓﮔ
80:17 ሰው ተረገመ፤ ምን ከሓዲ አደረገው?
ﮕﮖﮗﮘﮙ
80:18 (ጌታው) በምን ነገር ፈጠረው? (አያስብምን?)
ﮚﮛﮜﮝﮞ
80:19 ከፍትወት ጠብታ ፈጠረው፤ መጠነውም፡፡
ﮟﮠﮡﮢ
80:20 ከዚያም (መውጫ) መንገዱን አገራው፡፡
ﮣﮤﮥﮦ
80:21 ከዚያም ገደለው፤ እንዲቀበርም አደረገው፡፡
ﮧﮨﮩﮪﮫ
80:22 ከዚያም (ማንሳቱን) በሻ ጊዜ ያስነሳዋል፡፡
ﮬﮭﮮﮯﮰﮱ
80:23 በእውነት ያንን (ጌታው) ያዘዘውን ገና አልፈጸመም፡፡
ﯓﯔﯕﯖﯗ
80:24 ሰውም ወደ ምግቡ ይመልከት፡፡
ﯘﯙﯚﯛﯜ
80:25 እኛ ውሃን ማንቧቧትን ያንቧቧን መኾናችንን፡፡
ﯝﯞﯟﯠﯡ
80:26 ከዚያም ምድርን (በደካማ ቡቃያ) መሰንጠቅን የሰነጠቅን፤
ﯢﯣﯤﯥ
80:27 በውስጧም እኽልን ያበቀልን፤
ﯦﯧﯨ
80:28 ወይንንም፤ እርጥብ ያበቀልን፤
ﯩﯪﯫ
80:29 የዘይት ወይራንም ዘንባባንም፤
ﯬﯭﯮ
80:30 ጭፍቆች አትክልቶችንም፤
ﯯﯰﯱ
80:31 ፍራፍሬንም ገለባንም፤ (ያበቀልን መኾናችንን ይመልከት)፡፡
ﯲﯳﯴﯵ
80:32 ለእናንተም ለእንስሶቻችሁም መጠቀሚያ ይኾን ዘንድ (ይህን ሠራን)፡፡
ﯶﯷﯸﯹ
80:33 አደንቋሪይቱም (መከራ) በመጣች ጊዜ፤
ﯺﯻﯼﯽﯾﯿ
80:34 ሰው ከወንድሙ በሚሸሽበት ቀን፤
ﰀﰁﰂ
80:35 ከናቱም ካባቱም፤
ﰃﰄﰅ
80:36 ከሚስቱም ከልጁም፤
ﰆﰇﰈﰉﰊﰋﰌ
80:37 ከእነርሱ ለየሰው ሁሉ በዚያ ቀን (ከሌላው) የሚያብቃቃው ኹነታ አልለው፡፡
ﰍﰎﰏﰐ
80:38 ፊቶች በዚያ ቀን አብሪዎች ናቸው፤
ﰑﰒﰓ
80:39 ሳቂዎችም ተደሳቾችም ናቸው፡፡
ﰔﰕﰖﰗﰘ
80:40 ፊቶችም በዚያ ቀን በላያቸው ላይ ትቢያ አልለባቸው፤
ﭑﭒﭓ
80:41 ጥቁረት ትሸፍናቸዋለች፤
ﭔﭕﭖﭗﭘ
80:42 እነዚያ እነሱ ከሓዲዎቹ አመጸኞቹ ናቸው፡፡

ቅዱስ ቁርኣን


Wednesday, September 9, 2026

Don't forget us in your sincere prayers