PDF —
29 አንቀጽ Meccan PDF
Built right in your browser — download starts automatically

ሱረቱ አት-ተክዊር pdf — አውርድ (አማርኛ)

ሱረቱ አት-ተክዊር pdf አማርኛ — አውርድ ሱረቱ አት-ተክዊር ትርጉም. ሱረቱ አት-ተክዊር (Meccan) 29 አንቀጽ.

← ዐበሰሱረቱ አት-ተክዊር አል-ኢንፊጣር →


29 አንቀጽ · Meccan · አማርኛ
bismillah
ﭙﭚﭛﭜ
81:1 ፀሐይ በተጠቀለለች ጊዜ፤
ﭝﭞﭟﭠ
81:2 ከዋክብትም በረገፉ ጊዜ፤
ﭡﭢﭣﭤ
81:3 ተራራዎችም በተነዱ ጊዜ፤
ﭥﭦﭧﭨ
81:4 የዐሥር ወር እርጉዞች ግመሎችም (ያለጠባቂ) በተተዉ ጊዜ፤
ﭩﭪﭫﭬ
81:5 እንስሳትም ሁሉ በተሰበሰቡ ጊዜ፤
ﭭﭮﭯﭰ
81:6 ባሕሮችም በተቃጠሉ ጊዜ፤
ﭱﭲﭳﭴ
81:7 ነፍሶችም (በየአካሎቻቸው) በተቆራኙ ጊዜ፤
ﭵﭶﭷﭸ
81:8 በሕይወቷ የተቀበረችውም ሴት ልጅ በተጠየቀች ጊዜ፤
ﭹﭺﭻﭼ
81:9 በምን ወንጀል እንደ ተገደለች፤
ﭽﭾﭿﮀ
81:10 ጽሑፎችም በተዘረጉ ጊዜ፤
ﮁﮂﮃﮄ
81:11 ሰማይም በተገሸለጠች ጊዜ፤
ﮅﮆﮇﮈ
81:12 ገሀነምም በተነደደች ጊዜ፤
ﮉﮊﮋﮌ
81:13 ገነትም በተቀረበች ጊዜ፤
ﮍﮎﮏﮐﮑ
81:14 ነፍስ ሁሉ (ከሥራ) ያቀረበችውን ታውቃለች፤
ﮒﮓﮔﮕ
81:15 ተመላሾችም በኾኑት (ዐዋድያት) እምላለሁ፡፡
ﮖﮗﮘ
81:16 ኺያጆች ገቢዎች በኾኑት (ከዋክብት)፡፡
ﮙﮚﮛﮜ
81:17 በሌሊቱም (ጨለማውን) በጠነሰሰ ጊዜ፤
ﮝﮞﮟﮠ
81:18 በንጋቱም (በብርሃን) በተነፈሰ ጊዜ፤ (እምላለሁ)፡፡
ﮡﮢﮣﮤﮥ
81:19 እርሱ (ቁርኣን) የክቡር መልክተኛ ቃል ነው፡፡
ﮦﮧﮨﮩﮪﮫﮬ
81:20 የኀይል ባለቤት በዙፋኑ ባለ ቤት ዘንድ ባለሟል የኾነ፡፡
ﮭﮮﮯﮰ
81:21 በዚያ ስፍራ ትእዛዙ ተሰሚ፤ ታማኝ የኾነ (መልክተኛ ቃል) ነው፡፡
ﮱﯓﯔﯕ
81:22 ነቢያችሁም በፍጹም ዕብድ አይደለም፡፡
ﯖﯗﯘﯙﯚ
81:23 በግልጹ አድማስም በእርግጥ አይቶታል፡፡
ﯛﯜﯝﯞﯟﯠ
81:24 እርሱም በሩቁ ወሬ ላይ ሰሳች (ንፉግ) አይደለም፡፡
ﯡﯢﯣﯤﯥﯦ
81:25 እርሱም (ቁርኣን) የእርጉም ሰይጣን ቃል አይደለም፡፡
ﯧﯨﯩ
81:26 ታዲያ ወዴት ትኼዳላችሁ?
ﯪﯫﯬﯭﯮﯯ
81:27 እርሱ የዓለማት መገሠጫ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡
ﯰﯱﯲﯳﯴﯵ
81:28 ከናንተ ቀጥተኛ መኾንን ለሻ ሰው (መገሰጫ ነው)፡፡
ﯶﯷﯸﯹﯺﯻﯼﯽﯾ
81:29 የዓለማት ጌታ አላህ ካልሻም አትሹም፡፡

ቅዱስ ቁርኣን


Wednesday, September 9, 2026

Don't forget us in your sincere prayers