PDF —
17 አንቀጽ Meccan PDF
Built right in your browser — download starts automatically

ሱረቱ አት-ጣሪቅ pdf — አውርድ (አማርኛ)

ሱረቱ አት-ጣሪቅ pdf አማርኛ — አውርድ ሱረቱ አት-ጣሪቅ ትርጉም. ሱረቱ አት-ጣሪቅ (Meccan) 17 አንቀጽ.

← አል-ቡሩጅሱረቱ አት-ጣሪቅ አል-አዕላ →


17 አንቀጽ · Meccan · አማርኛ
bismillah
ﭑﭒﭓ
86:1 በሰማዩ በሌሊት መጪውም እምላለሁ፡፡
ﭔﭕﭖﭗﭘ
86:2 የሌሊት መጪውም ምን እንደ ኾነ ምን አሳወቀህ?
ﭙﭚﭛ
86:3 ጨለማን ቀዳጁ ኮከብ ነው፡፡
ﭜﭝﭞﭟﭠﭡﭢ
86:4 ነፍስ ሁሉ በእርሷ ላይ ጠባቂ ያለባት እንጅ ሌላ አይደለችም፡፡
ﭣﭤﭥﭦﭧ
86:5 ሰውም ከምን እንደተፈጠረ ይመልከት፡፡
ﭨﭩﭪﭫﭬ
86:6 ከተስፈንጣሪ ውሃ ተፈጠረ፡፡
ﭭﭮﭯﭰﭱﭲ
86:7 ከጀርባና ከእርግብግብቶች መካከል የሚወጣ ከኾነ (ውሃ)፡፡
ﭳﭴﭵﭶﭷ
86:8 እርሱ (አላህ) በመመለሱ ላይ በእርግጥ ቻይ ነው፡፡
ﭸﭹﭺﭻ
86:9 ምስጢሮች በሚገለጡበት ቀን፡፡
ﭼﭽﭾﭿﮀﮁﮂ
86:10 ለእርሱም (ለሰው) ኀይልና ረዳት ምንም የለውም፡፡
ﮃﮄﮅﮆ
86:11 የመመለስ ባለቤት በኾነችው ሰማይም እምላለሁ፡፡
ﮇﮈﮉﮊ
86:12 (በበቃይ) የመሰንጠቅ ባለቤት በኾነችው ምድርም፤
ﮋﮌﮍﮎ
86:13 እርሱ (እውነትን ከውሸት) የሚለይ ቃል ነው፡፡
ﮏﮐﮑﮒ
86:14 እርሱም ቀልድ አይደለም፡፡
ﮓﮔﮕﮖ
86:15 እነርሱ በእርግጥ ተንኮልን ይሠራሉ፡፡
ﮗﮘﮙ
86:16 (እኔ) ተንኮልንም እመልሳለሁ፡፡
ﮚﮛﮜﮝﮞ
86:17 ከሓዲዎችንም ቀን ስጣቸው፡፡ ጥቂትን ጊዜ አቆያቸው፡፡

ቅዱስ ቁርኣን


Wednesday, September 9, 2026

Don't forget us in your sincere prayers