PDF —
22 አንቀጽ Meccan PDF
Built right in your browser — download starts automatically

ሱረቱ አል-ቡሩጅ pdf — አውርድ (አማርኛ)

ሱረቱ አል-ቡሩጅ pdf አማርኛ — አውርድ ሱረቱ አል-ቡሩጅ ትርጉም. ሱረቱ አል-ቡሩጅ (Meccan) 22 አንቀጽ.



22 አንቀጽ · Meccan · አማርኛ
bismillah
ﭛﭜﭝﭞ
85:1 የቡርጆች ባለቤት በኾነችው ሰማይ እምላለሁ፡፡
ﭟﭠﭡ
85:2 በተቀጠረው ቀንም፤
ﭢﭣﭤ
85:3 በተጣጅና በሚጣዱትም፤ (እምላለሁ)፡፡
ﭥﭦﭧﭨ
85:4 የጉድቡ ባለቤቶች ተረገሙ፡፡
ﭩﭪﭫﭬ
85:5 የማገዶ ባለቤት የኾነቺው እሳት (ባለቤቶች)፡፡
ﭭﭮﭯﭰﭱ
85:6 እነርሱ በርሷ (አፋፍ) ላይ ተቀማጮች በኾኑ ጊዜ፤ (ተረገሙ)፡፡
ﭲﭳﭴﭵﭶﭷﭸ
85:7 እነርሱም በምእምናኖቹ በሚሠሩት (ማሰቃየት) ላይ መስካሪዎች ናቸው፡፡
ﭹﭺﭻﭼﭽﭾﭿﮀﮁﮂ
85:8 ከእነርሱም በአላህ አሸናፊው፣ ምስጉኑ በኾነው (ጌታ) ማመናቸውን እንጅ ሌላ ምንም አልጠሉም፡፡
ﮃﮄﮅﮆﮇﮈﮉﮊﮋﮌﮍﮎ
85:9 በእዚያ የሰማያትና የምድር ንግሥና ለእርሱ ብቻ በኾነው (አላህ ማመናቸውን)፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ መስካሪ ነው፡፡
ﮏﮐﮑﮒﮓﮔﮕﮖﮗﮘﮙﮚﮛﮜﮝ
85:10 እነዚያ ምእምንንና ምእምናትን ያሰቃዩ፣ ከዚያም ያልተጸጸቱ ለእነርሱ የገሀነም ቅጣት አልላቸው፡፡ ለእነርሱም የመቃጠሉ ስቃይ አልላቸው፡፡
ﮞﮟﮠﮡﮢﮣﮤﮥﮦﮧﮨﮩﮪﮫﮬﮭ
85:11 እነዚያ ያመኑና መልካም ሥራዎችንም የሠሩ ለእነርሱ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች አሏቸው፡፡ ይህ ታላቅ ማግኘት ነው፡፡
ﮮﮯﮰﮱﯓ
85:12 የጌታህ በኀይል መያዝ ብርቱ ነው፡፡
ﯔﯕﯖﯗﯘ
85:13 እነሆ እርሱ መፍጠርን ይጀምራል፤ ይመልሳልም፡፡
ﯙﯚﯛﯜ
85:14 እርሱም ምሕረተ ብዙ ወዳድ ነው፡፡
ﯝﯞﯟﯠ
85:15 የዙፋኑ ባለቤት የላቀው ነው፡፡
ﯡﯢﯣﯤ
85:16 የሚሻውን ሁሉ ሠሪ ነው፡፡
ﯥﯦﯧﯨﯩ
85:17 የሰራዊቶቹ ወሬ መጣልህን?
ﯪﯫﯬ
85:18 የፈርዖንና የሰሙድ፤ (ወሬ)፡፡
ﯭﯮﯯﯰﯱﯲ
85:19 በእውነቱ እነዚያ የካዱት በማስተባበል ውስጥ ናቸው፡፡
ﯳﯴﯵﯶﯷ
85:20 አላህም በዙሪያቸው (በዕውቀቱ) ከባቢ ነው፡፡
ﯸﯹﯺﯻﯼ
85:21 ይልቁንም እርሱ የከበረ ቁርኣን ነው፡፡
ﯽﯾﯿﰀ
85:22 የተጠበቀ በኾነ ሰሌዳ ውስጥ ነው፡፡

ቅዱስ ቁርኣን


Wednesday, September 9, 2026

Don't forget us in your sincere prayers