ሱረቱ አት-ጣሪቅ ዐረቢ እና አማርኛ

ሱረቱ አት-ጣሪቅን ሙሉ አማርኛ ትርጉምና የድምፅ ቅኔ ጋር አንብቡ። ከአንቀጽ ወደ አንቀጽ ትርጉም። (17 አንቀጽ — مكية). አት-ጣሪቅ ስሙ, አት-ጣሪቅ ትርጉም, አት-ጣሪቅ mp3, አት-ጣሪቅ pdf.

ሱረቱ አት-ጣሪቅን አንብቡ እና ስሙ

🎧 አንቀጽ
M Mishary Rashid Alafasy ✓
M Mahmoud Khalil Al-Husary ✓
A Abdurrahman As-Sudais ✓
M Mohamed Siddiq Al-Minshawi ✓
A Abdul Basit Abdul Samad ✓
A Ali Al-Hudhaify ✓
A Ahmed ibn Ali al-Ajamy ✓
A Abu Bakr Ash-Shaatree ✓
M Muhammad Ayyoub ✓
A Abdullah Basfar ✓
A Abdullah Al-Juhani ✓
M Maher Al Muaiqly ✓
—
x1
bismillah
وَالسَّمَاءِ وَالطَّارِقِ ۝١
📖 ትርጉም አንቀጽ 1
በሰማዩ በሌሊት መጪውም እምላለሁ፡፡
وَمَا أَدْرَاكَ مَا الطَّارِقُ ۝٢
📖 ትርጉም አንቀጽ 2
የሌሊት መጪውም ምን እንደ ኾነ ምን አሳወቀህ?
النَّجْمُ الثَّاقِبُ ۝٣
📖 ትርጉም አንቀጽ 3
ጨለማን ቀዳጁ ኮከብ ነው፡፡
إِن كُلُّ نَفْسٍ لَّمَّا عَلَيْهَا حَافِظٌ ۝٤
📖 ትርጉም አንቀጽ 4
ነፍስ ሁሉ በእርሷ ላይ ጠባቂ ያለባት እንጅ ሌላ አይደለችም፡፡
فَلْيَنظُرِ الْإِنسَانُ مِمَّ خُلِقَ ۝٥
📖 ትርጉም አንቀጽ 5
ሰውም ከምን እንደተፈጠረ ይመልከት፡፡
خُلِقَ مِن مَّاءٍ دَافِقٍ ۝٦
📖 ትርጉም አንቀጽ 6
ከተስፈንጣሪ ውሃ ተፈጠረ፡፡
يَخْرُجُ مِن بَيْنِ الصُّلْبِ وَالتَّرَائِبِ ۝٧
📖 ትርጉም አንቀጽ 7
ከጀርባና ከእርግብግብቶች መካከል የሚወጣ ከኾነ (ውሃ)፡፡
إِنَّهُ عَلَىٰ رَجْعِهِ لَقَادِرٌ ۝٨
📖 ትርጉም አንቀጽ 8
እርሱ (አላህ) በመመለሱ ላይ በእርግጥ ቻይ ነው፡፡
يَوْمَ تُبْلَى السَّرَائِرُ ۝٩
📖 ትርጉም አንቀጽ 9
ምስጢሮች በሚገለጡበት ቀን፡፡
فَمَا لَهُ مِن قُوَّةٍ وَلَا نَاصِرٍ ۝١٠
📖 ትርጉም አንቀጽ 10
ለእርሱም (ለሰው) ኀይልና ረዳት ምንም የለውም፡፡
وَالسَّمَاءِ ذَاتِ الرَّجْعِ ۝١١
📖 ትርጉም አንቀጽ 11
የመመለስ ባለቤት በኾነችው ሰማይም እምላለሁ፡፡
وَالْأَرْضِ ذَاتِ الصَّدْعِ ۝١٢
📖 ትርጉም አንቀጽ 12
(በበቃይ) የመሰንጠቅ ባለቤት በኾነችው ምድርም፤
إِنَّهُ لَقَوْلٌ فَصْلٌ ۝١٣
📖 ትርጉም አንቀጽ 13
እርሱ (እውነትን ከውሸት) የሚለይ ቃል ነው፡፡
وَمَا هُوَ بِالْهَزْلِ ۝١٤
📖 ትርጉም አንቀጽ 14
እርሱም ቀልድ አይደለም፡፡
إِنَّهُمْ يَكِيدُونَ كَيْدًا ۝١٥
📖 ትርጉም አንቀጽ 15
እነርሱ በእርግጥ ተንኮልን ይሠራሉ፡፡
وَأَكِيدُ كَيْدًا ۝١٦
📖 ትርጉም አንቀጽ 16
(እኔ) ተንኮልንም እመልሳለሁ፡፡
فَمَهِّلِ الْكَافِرِينَ أَمْهِلْهُمْ رُوَيْدًا ۝١٧
📖 ትርጉም አንቀጽ 17
ከሓዲዎችንም ቀን ስጣቸው፡፡ ጥቂትን ጊዜ አቆያቸው፡፡
← 85 አት-ጣሪቅ (86/114) 87 →
ማንበብ ሱረቱ አት-ጣሪቅ አማርኛ ትርጉም – ንባብ እና ድምፅ

86الطارق At-Tariq 📚 17 አንቀጽ مكية



ቅዱስ ቁርኣን


Monday, September 28, 2026

Don't forget us in your sincere prayers